Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2024
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘እምነት’

ከፍኖተ መስቀሉ ከህያው ቅዱስ ቃሉ በረከት ይክፈለን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 3, 2024

❖ ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ “የድኅነት ቀን” ይባላል። ❖

✞ ፲፫ቱ ሕማማተ መስቀል

  • ፩ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
  • ፪ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
  • ፫ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)
  • ፬ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
  • ፭ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
  • ፮ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
  • ፯ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
  • ፰ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
  • ፱ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
  • ፲ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
  • ፲፩ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
  • ፲፪ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይ መሰቀል)
  • ፲፫ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)

✞ ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

  • ፩. ፀሐይ ጨለመ፤
  • ፪. ጨረቃ ደም ኾነ፤
  • ፫. ከዋክብት ረገፉ፤
  • ፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤
  • ፭. አለቶች ተፈረካከሱ፤
  • ፮. መቃብራት ተከፈቱ፤
  • ፯. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩-፶፬)፡፡

✞ ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

  • ፩. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)”፤
  • ፪. “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ”፤
  • ፫. “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው”፤
  • ፬. እመቤታችንን “ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ”፤ ደቀ መዝሙሩንም “እናትህ እነኋት” በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤
  • ፭. “አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ”
  • ፮. ተጠማሁ”፤
  • ፯. ዅሉ ተፈጸመ (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡

ከሰድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ሁኖአል፡፡ “ወፍና ሠርክ ይበርህ ብርሃነ ፀሐይእንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡

ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም “ንሴብሖ ለ እግዚአብሔር እየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ረቡዕ የምክር ቀን፤ ይሑዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠ | የዘመኑ ይሑዳዎች ዛሬም ጌታቸውን፣ ሀይማኖታቸውን፣ ሕዝባቸውን እና ሃገራቸውን ለገንዘብና ለስጋዊ ጥቅም ብለው እየሸጡ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2024

ሰሙነ ሕማማት – ረቡዕ ፤ የይሁዳ ክህደት፥ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን

ለምን የምክር ቀን ተባለ?

ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ [ማቴ. ፳፮፥፩፡፲፬ ፣ ማር. ፲፬፥፩፡፪ ቁ ፲.፲፩፣ ሉቃ. ፳፪፥ ፩፡፮]

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል

ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ “ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ” ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ነው ረቡዕ የመዓዛ ቀን የተባለው፡፡

የእንባ ቀንም ይባላል

ይህም ይህቸው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ [ማቴ.፳፮፥፮፡፲፫ ፣ ማር.፲፬፥፫፡፱፣ ዮሐ.፲፪፥፩፡፰] ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው። ምህሩንና ጌታውን ክዶ፣ ስሞ ለግርፋት እና ለመስቀል ሞት ተስማማ። ይህንን የጌታን ሕማማት፣ ስቅላት፣ ሞትና ትንሣኤ በምናስብበት በአሁኑ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ለሕማም፣ ለስቅላት እና ለሞት አሳልፎ ተስጥቷል። ይሁዳ ለ፴/30 ዲናር ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው፤ ከዚያም ዲናሩን መልሶ እራሱን አጠፋ። የዘመናችን ሰቃልያን የሆኑት ኦሮማራዎቹ የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮች ደግሞ “አክሱም ጽዮን ለብዙ ሺህ ዓመታት ያፈራችውን እውቀት፣ ስልጣኔና ሀብት በሙሉ ለመዝረፍ፣ አሳልፎ ለመስጠትና ለማውደም ጊዜው አሁን ነው” ብለው የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ከሆኑት አህዛብ፣ መናፍቃንና ግብረ-ሰዶማውያን ጋር ተባበሩ። በዚህም በዚያም ትልቅ ክህደት እና ስቅለት። በተለይ ተዋሕዶ ክርስትናን የተቀብሉትና ማሕተብ ያጠለቁት አማራ ወገኖች ክህደት ታሪክ የማይረሳው ነው፤ ብዙ ዋጋም የሚያስከፍላቸውና ከሌሎቹ ሁሉ የከፋው ክህደት ነው። ከይሁዳ ይልቅ የጴጥሮስ ዓይነት ክህደት ያድርግላቸው።

😈 የአስቆሮቱ ይሁዳ ክህደት + የቃኤል ቅናት = ሞት 💀

አወቁትም አላወቁትም፤ ዛሬ በአማራዎችና ኦሮሞዎች ህብረት በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለው ጂሃዳዊ የጭፍጨፋ ዘመቻ የመጨረሻው ግብ፤ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ትግራዋያንን ከአኩም ጽዮን አጽድቶ የሕይወት ዛፍ እና ጽላተ ሙሴ የሚገኙበትን ቅድስት ምድር ለተለከፉት ባዕዳውያኑ ውሾች ማስረከብ ነው። አዎ! ኢትዮጵያን/አክሱም ጽዮንን ለባዕዳውያኑ ሉሲፈራውያን ለማስረከብ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነት ከፈቱ። እስኪ እናስበው! ዋው!

በሰባዎቹ ዓመታት ሉሲፈራውያኑ ድርቅና ረሃብ ፈጥረው በዚህ አካባቢ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሃገራት፤ በተለይ ብሪታኒያ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ ሰራዊቶቻቸውን በእርዳታ ስም አስፍረው እንደነበር እናስታውስ። ከዚያ በሰማኒያዎቹ እና በባድሜው ጦርነት የተባበሩት መንግስታት “ሰላም አስከባሪዎች” እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ዛሬም ዓለም የተራቡ የትግራይን ሕፃናት ምስሎች በበቂ እንድታይ ከተደረገች በኋላና የተረፉትንም ትግራይ ወገኖቼንም በስደት የተቀደሰችውን ምድር እየለቀቁ እንዲወጡ (የአውሮፓን እና አሜሪካን ድንበሮች ይከፍቱላቸዋል፤ ከጥቂት ከፍተኛ ቦታ ላይ ከሚገኙት የዓለማችን ቦታዎች በቀር አውሮፓና አሜሪካ ሌሎችም አኅጉራት ይጠፋሉ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል) ከተደረጉ በኋላ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሠራዊቶች በትግራይ ይሰፍራሉ።

ገና ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት “ኔቶ በአፍጋኒስታን የሚገኘው ለኢትዮጵያ ለመለማመድ ነው፤ ተመሳሳይ የመልከዓ ምድር አቀማመጥ ስላላቸው…” በማለጥ ጽፌ ነበር። ምዕራባውያኑ እዚያ መስፈር ከጀመሩ በኋላ ቀስ በቀስ ዜጎቻቸውን ማስገባት ይጀምሩና በመጨረሻም “ኢትዮጵያውያኑም ተዋሕዶ ክርስቲያኖቹም እኛ ነን” በማለት እያታለሉና ደማቸውን እያፈሰሱ ለብዙ ሺህ ዓመታት ጠብቀውት የነበረውን ብኩርናቸውን በምስር ወጥ እንዲሸጡ ብሎም የመንፈስ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን እየተነጠቁ “ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን” ቀስበቀስ እንዲከዱ ይደረጓቸውን “የቀድሞ ኢትዮጵያውያን” “አናስገባም!” ብለው ከኢትዮጵያ ድንብር ይመልሷቸዋል። ይህ ትንቢት ሳይሆን የሉሲፈራውያኑ ግልጽ የሆነ ተልዕኮ ነው። እግዚአብሔር ይህን ተልዕኳቸውን እንደሚያጨናግፈው አልጠራጠረም፤ ነገር ግን በኢትዮጵያውያኑ ደንቆሮነት፣ ስንፍና እና እንደ ግራኝ ያሉትን የውስጥ ጠላታቸውን በሰዓቱ ለማስወገድ ባለመድፈራቸው ብሎም አክሱም ጽዮንን ለመከላከል ባለመሻታቸው ብዙ መስዋዕት ይከፍሉ ዘንድ ግድ ይሆናል። በተለይ ከሃዲዎቹ ኦሮማራዎች!

የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Orthodox Christians in Ethiopia celebrate Palm Sunday

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 29, 2024

🌴 ሆሣዕና በአርያም፤ በርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን 🌴

♱ Ethiopian Orthodox Christians celebrated Palm Sunday with prayers and a ceremony at the ornate Entoto Maryam Church outside Addis Ababa.

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Russell Brand Announces Baptism: Many Returning To Christianity As World Crumbles

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 28, 2024

✞ ራስል ብራንድ ጥምቀትን አስታወቀ፡ ብዙዎች ወደ ክርስትና እንደ ዓለም ፍርፋሪ ይመለሳሉ

ታዋቂው የብሪታኒያ ተዋናይ እና ኮሜዲያን ራስል ብራንድ ለወራት ከዘለቀው መንፈሳዊ ጉዞ በኋላ በዛሬው የሆሣዕና እሑድ ዕለት እንደሚጠመቅ አስታወቀ

ዓለም እየፈራረስች ባለችበት በዚህ ወቅት ብዙዎች ወደ ክርስትና እየተመለሱ መሆናቸውን ራሰል የአርባ ስምንት/48 አመቱ ብራንድ በ X ላይ በለጠፈው ቪዲዮ ላይ ይናገራል።

ተዋናይ እና ኮሜዲያን ራስል ብራንድ በዚህ ቅዳሜና እሁድ እንደሚጠመቅ አሳውቋል ይህም ከክርስትና እምነት አስተምህሮ ጋር ለወራት በዘለቀ ተጋድሎ ካደረገ በኋላ ነው።

ብራንድ ጥምቀት ሲገለጽለት እንደሰማው እንዲህ ሲል ተናግሯል፤ “ለመሞት እና ለመወለድ እድል፤ ያለፈውን ትተን በገላትያ ውስጥ እንደተገለጸው በክርስቶስ ስም እንደገና ለመወለድ – እንደ ብሩህ እና የነቃ ሰው መኖር ትችላለህ፤ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና”።

✞ Russell Brand announces baptism after months-long spiritual journey: ‘Taking the plunge’

Brand says many returning to Christianity as world crumbles

Actor and comedian Russell Brand announced Friday that he is going to be baptized this weekend, the culmination of his months-long public wrestling with the tenets of Christianity.

“This Sunday, I’m taking the plunge,” Brand, 48, said in a video he posted to X. “I’m getting baptized.”

Brand said he had heard baptism explained to him as “an opportunity to die and be reborn; an opportunity to leave the past behind and be reborn in Christ’s name like it says in Galatians — that you can live as an enlightened and awakened person.”

He also referenced what he suggested were non-Christian reflections on the same theme of embracing death for the sake of life, quoting Stoic philosopher and Roman emperor Marcus Aurelius and the Buddha.

“All of these things seem so inviting and beautiful,” he said.

Brand also suggested that increasing numbers are turning back to Christianity as the empty value system of modernity disintegrates and leaves them wanting more.

“I know a lot of people are sort of cynical about the increasing interest in Christianity and the return to God, but to me, it’s obvious,” he said. “As meaning deteriorates in the modern world, as our value systems and institutions crumble, all of us become increasingly aware that there is this eerily familiar awakening and beckoning figure that we’ve all known all of our lives, within us and around us. And for me, it’s very exciting.”

Brand added that he intends to get baptized in the heavily polluted River Thames, joking that he might be also getting baptized in toxoplasmosis and E. coli.

“I may be leaving behind the sins, but I might be picking up some pretty serious viruses,” he said.

Brand’s baptism comes after other videos he has been making in recent months about his spiritual journey to the Christian faith.

In December, he told followers he was reading the Bible and The Problem of Pain, a 1940 book by C.S. Lewis that explores the role of suffering in the Christian life.

In January, he noted that he was reading Rick Warren’s The Purpose-Driven Life, and that he desired a “personal relationship with God” as he found Jesus Christ increasingly important as he grows older, despite once seeing many churches as either too “old-fashioned” or too modernized.

“The reason I wear a cross is because Christianity and, in particular, the figure of Christ, are, it seems to me, inevitably becoming more important as I become more familiar with suffering, purpose, self, and not-self,” he said at the time.

In March, he posted a video explaining that he had been visiting churches of various denominations with the intention of possibly getting baptized, and asked his followers their opinions on the sacrament.

During an interview with Tucker Carlson last year, Brand said, “Like many desperate people, I need spirituality. I need God, or I cannot cope in this world. I need to believe in the best in people.”

Acknowledging he “didn’t have enough self-discipline to resist the allure of stardom,” he said he “fell face-first into the glitter, and I’m only just pulling myself out now.”

Brand faces multiple allegations of sexual misconduct going back years, including one report that claims he assaulted a 16-year-old girl after pulling her into an “emotionally and sexually abusive” relationship.

Brand has denied the “very serious criminal allegations” and maintained that while he was “very, very promiscuous” in the past, all of his sexual relationships were “always consensual.”

Source

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሆሣዕና በአርያም፤ ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ እና አህዛብ አጋሮቻቸው በሰቀሏት የኢትዮጵያ ዘ-ነፍስ እናት በአክሱም ጽዮን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 28, 2024

🌴 ሰውን ከወደቀበት የበደል ጉድጓድ ያወጣው ዘንድ እግዚአብሔር ክንዱን ወደ ዓለም ላከ፡፡ ሰው ሆኖ የተገለጠው የእግዚአብሔር ክንድ በጉድጓድ ተጥሎ የነበረን በዚያም በሥጋ በነፍስ፤ በውስጥ በአፍአ ቆስሎ የነበረ አዳምን በትህትና ሁለተኛ አዳም ሆኖ በሥጋ የቆሰለውን በለበሰው ሥጋ ቆስሎ;በነፍስ የታመመውን በትምህርት አዳነ፡፡ ከእርሱ አስቀድሞ ሰውን ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከባርነት ወደ ነፃነት የሚያመጣ ባለመኖሩ እርሱ ሁሉን የፈጠረ ሁሉን የሚያኖር እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ለሰው መድኃኒት ሆነ፡፡ በሞቱም መድኃኒትነትን አሣየ፡፡ በነቢይ መድኃኒተ ፈነወ እግዚአብሔር ለሕዝቡ፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ መድኃኒትን ሰደደ፡፡ (መዝ.፻፲፥፱) ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፡፡

ክርስቶስ ባለ መድኃኒት ሆኖ በኃጢአት ለታመሙ ደቂቀ አዳም ሁሉ ሕይወትን ይሰጥ ዘንድ ወደዚህኛው ዓለም መጣ፡፡ በምድራዊ ሥርዓት እንደምናየው መድኃኒትና ባለ መድኃኒት እንደሚለያዩ አይደለም፡፡ ሁለቱንም እርሱ በመምጣቱ (ሰው በመሆኑ) ፈጸመ እንጂ፡፡ መድኃኒት አድርጎ ሥጋውን ደሙን የሰጠ እርሱ ነው፡፡ በካህናት አድሮ ሰው በንስሐ ሲመለስ መድኃኒት ወደሆነው ወደ ራሱ የሚመራ እርሱ ነው፡፡

ክርስቶስ መድኃኒት መሆኑ በሕማሙ እና በሞቱ ነው፡፡ በእመቤታችን ማኅፀን የተጀመረው የእርሱ መድኃኒትነት እና ፍቅሩ ፍፃሜውን ያገኘው በሕማሙ እና በሞቱ ነው፡፡ መሐሪ ንጉሥ እርሱ መሆኑን ይገልጥ ዘንድ በፈቃዱ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡ ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም ከመግባቱ አስቀድሞ ከኢየሩሳሌም ፲፮ ያህል ምዕራፍ በምትርቀው በቤተፋጌ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ነበር፡፡

ከደቀ መዛሙርቱም ሁለቱን (ማለትም ጴጥሮስን እና ዮሐንስን) በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ ወዲያውም ወደ እርሷ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበትን ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ፡፡ (ማር ፲፩፡፪) በማለት አዘዛቸው፡፡ ዳግመኛም ሰው ወዳልገባባት የተዘጋች የምሥራቅ ደጅ ወደ ምትባል ወደ ድንግል መጥቶ ዘጠኝ ወር ማኅፀኗን ከተማ አድርጎ እንደኖረ፤ ማኅየዊት ከምትሆን ሕማሙ በኋላም ሰው ባልተቀበረበት መቃብር እንደተቀበረ፤ አሁንም ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባት ማንም ሰው ያልተቀመጠባቸውን በሌላ መንደር የሚገኙ አህያንና ውርንጫን እንዲያመጡ ደቀመዛሙርቱን አዘዘ፡፡

የፍጥረት ሁሉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በልደቱ እስትንፋሷን የገበረችለትን አህያ አሁን ደግሞ በፈቃዱ ስለ ሰው ሁሉ ሊሞት ሲል ንጉሥነቱን ሊያስመሰክርባት ወደደ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ካለው ፲፮ ምዕራፍ አሥራ አራቱን በአህያ ላይ ሳይቀመጥ በእግሩ ሄደ፡፡ ከዚያም ሁለቱን ምዕራፍ በአህያ ላይ በመቀመጥ ከተጓዘ በኋላ የኢየሩሳሌምን መቅደስ ሦስት ጊዜ በውርጫዋ ላይ በመሆን ዞረ፡፡ በዚህም ለሰው ሁሉ ያለው ቸርነቱ፣ ሕግ የተሰጣቸው አይሁድ እና ሕግ ያልተሰጣቸው አሕዛብ ላይ እኩል ቀንበርን መጫን እንዳይገባ አጠየቀ፡፡

ወደ ኢየሩሳሌምም ሲሄድ ብዙ ሰዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፣ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቆረጡ ያነጥፉ ነበር፡፡ (ማር. ፲፩፡፰)፡፡ ከዚያም ሰዎች ሆሣዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው (ማር. ፲፩፡፱) በማለት አመሰገኑ፡፡ ይህም ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን እኛ ክርስቲያኖች ቡሩክ ስሙ ለእግዚብሔር ወቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር፤ የእግዚአብሔር ስሙ ምስጉን ነው፡፡ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ ክርስቶስም ምስጉን ነው በማለት የአብ እና የወልድን መስተካከልን ገልጸን ጌታን እናመሰግናለን፡፡ ጌታን የሚከተሉት ሰዎች ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር (ማር.11፲፩፡፲) ይኸውም በልዕልና፣ በሰማይ ያለ መድኃኒት፣ ከሰማይ የመጣ መድኃኒት ማለት ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅር እና መሓሪ መሆን በክርስቶስ ሕማም እና ሞት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተገልጧል፡፡ ክርስቶስ የተቀበለው ሕማም እና ሞት የእርሱን አምላክነት እና ንጉሥነት አልሸሸገውም፡፡ እንደውም ዙፋኑን መስቀል በማድረግ ንጉሥነቱን በመድኃኒትነቱ ገልጿል እንጂ፡፡ በነቢይ እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር፣ እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፤ በምድር መካከልም መድኃኒትን አደረገ መዝ. ፸፫፤፲፪ ተብሎ የተነገረው እግዚአሔብር ድኅነትን በፈጸመበት ማዕከለ ምድር ሲሰቀል በመድኀኒትነቱ ንጉሥነቱን መግለጡን ያመለክታል፡፡ ዳግመኛም አንሰ ተሰየምኩ ንጉሠ በላዕሌሆሙ በጽዮን በደብረ መቅደሱ፤ እኔ ንጉሥ ሆኜ ተሸምኩ በተቀደሰው ተራራ ላይ(መዝ.፪፡፮) ተብሎ የተነገረው ኦርቶዶክሳውያን አበው እነርሱ (አይሁድ) ሰቅለነው ገድለነው ኋላ ፈርሶ በስብሶ ይቀራል ይሉኛል እንጂ እኔ ደብረ መቅደስ በምትባል በመስቀል ላይ ነግሻለሁ በማለት ይተረጉሙታል፡፡

ጌታ ንግሥናው ክብሩ የተገለጠበት ሆነ እንጂ መታመሙ እና መሞቱ ውርደት ክብሩንም የሚሸሽግ አይደለም፡፡ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ይትባረክ እግዚአብሔር ዘሰመየ ሕማማት ወልዱ ክብረ ወስብሐት፣ የልጁን ሕማማት ክብርና ምስጋና አድርጎ የሰየመ እግዚአብሔር ይመስገን አለ፡፡ እኛን ያከበረበት በመሆኑ ሕማሙ ክብር እንደተባለ እናስተውል፡፡ በመስቀል ላይ ሆኖም በቀኝ የተሠቀለው ወንበዴ አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ (ሉቃ ፳፬ )በማለት ንጉሥነቱ መስክሮለታል፡፡ ለዚህ ነው ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም በምስጋና መግባቱ መድኃኒትነቱን እና ንጉሥነቱን ያሳያል ያልነው፡፡ ዳግመኛም ሁሉን የያዘ ጌታ በአህያ ላይ መቀመጡ ትህትናው ያስረዳል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል ዲባ ዕዋለ አድግ ነበረ፡፡ በማለት ሰማያዊ ልዑል አምላክ ትሑት ሆኖ እንደተገለጠ ተናገረ፡፡

ጌታ ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ድንቅ የሆኑ እና ተአምራትን ለሰዎች አሳየ (ገለጠ)፡፡ እም ሆሳዕናሁ አርአያ ተአምረ ወመንክረ (ቅዳ. ጎርጎ.ዘኑሲስ) እንዲል፡፡ ይኸውም በአህያ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አእምሮ ጠባይዕ ያልቀናላቸው ሕፃናት ዕውቀት ተገልጾላቸው ሆሳዕና በአርያም እያሉ ጌታ በማመስገናቸው ነው፡፡ ዳግመኛም በከሃሊነቱ መናገር ለማይችሉ ዕውቀት ለሌላቸው ድንጋዮች ዕውቀት ተሰጥቷቸው መናገር ችለው ጌታን አመስግነዋል፡፡ እርሱ የባሕርይ አምላክ መሆኑ በሰውነቱም ቀድሞ በበደል ምክንያት ለሰው ከመገዛት ውጪ የሆኑ ፍጥረታት ዳግመኛ በሥጋዌ ለሰው እንደተገዙ ከዚህ ሁሉ ማስተዋል ይገባል፡፡

ጌታ ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ልጅነት እና ተአምራት ማድረግን ገለጸ፡፡ እም ሆሳዕናሁ አርአያ ጸጋ ወኅይለ እንዲል (ቅዳሴ ጎርጎ. ዘኑሲስ)፡፡ የእርሱ ማዳን ከሰው ተወስዶበት የነበረ የጸጋ ልጅነት እንዲመለስለት አድርጋ በልጅነት ላይ ገቢረ ተአምራት (ተአምራትን ማድረግ) ገልጿል፡፡ ይኸውም እርሱ በረድኤት አድሮባቸው ድንቅ ተአምራትን ለሚያደርጉ ቅዱሳን መሠረት ነው፡፡ በተጨማሪም ልጅነትን ካገኙ በኋላ በበደል ሲገኙ ለንስሓ የሚሆን እንባን ሠጠ፡፡ እምሆሳዕናሁ ወሀበ ፈልፈለ አንብዕ ለኅጥአን እንዲል (ቅዳሴ ጎርጎ. ዘኑሲስ) ይኸውም የበደሉትን ያከብራቸው ዘንድ፣ ኀጥአንን ከኃጢአታቸው ያነጻቸው ዘንድ እንዲሁም የሳቱትን በንስሐ ይመልሳቸው ዘንድ ነው፡፡

ዳግመኛም ጌታ መድኀኒት ከመሆኑ የተነሣ ለዕውራን ዳግመኛ ብርሃንን ሰጠ፡፡ ይኸውም ለጊዜው በተፈጥሮ ዐይን ተሰጥቷቸው የታወሩትን ፈውሶ በሥጋ ብርሃን መስጠቱ ሲሆን፤ ፍጻሜው ግን በነፍስ ዕውቀትን ከማጣት የተነሣ ዕውራን የነበሩትን ትምህርትን; ዕውቀትን ገለጸላቸው፡፡ ይኸውም የእርሱ ገንዘቡ ስለሚሆን አንድነት ሦስትነት፣ አምላክነቱን መድኃኒት መሆኑን ገለጠላቸው ማለት ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት) ፍጹም ፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 21, 2024

  • ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው። ዮሐንስ ፫፥፩
  • ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው። ዮሐንስ ፫፥፩
  • ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው። ዮሐንስ ፫፥፲
  • ኒቆዲሞስ ምሑረ ኦሪት ነው። ዮሐንስ ፯፥፶፩

ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል፡: ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል። (ዮሐ ፩–፪)

በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ እግዚአብሔርነት ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር ”አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሳ መርምርና እይ“ አሉት እንጂ አልተቀበሉትም። ዮሐ ፯፥፵፰–፶፪። ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ”ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ። ዮሐ ፲፱፥፴፱። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል።

የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ­ የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ ዮሐንስ ፫፤፪

ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው በሌሊት ወደ ጌታ እየሄደ ይማር ነበር ኒቆዲሞስ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ ?

/ ኒቆዲሞስ መምህር ስለነበር ስማር ሰዎች ቢያዩኝ ውዳሴ ከንቱ መምህር መባል ይቀርብኛል ብሎ ነው እኛስ ዛሬ የዘላለም ህይወት የሚሰጠንን ቅዱስ ቃል በትህትና መማር ሲገባን ለምድራዊ ክብር ብለን በቀን ጊዜያችን መማር ያልቻልን ስንቶቻችን ነን ስለዚህ ቀን ጊዜአችንን በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።

ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችና › ዮሐንስ ፱፤፬

/ .ኒቆዲሞስ የአይሁድ መምህር ስለነበር እንዳያዩት ፈርቶ ሌሊት እየመጣ ይማር ነበር እኛስ ዛሬ ልባችን የተረዳውን እውነት በግልጥ እንዳንፈጽም በፍራቻ በይሉኝታ የምንሰውር ስንቶቻችን ነን

ፍጹም ፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና› ፩ ዮሐንስ ፬፤፲፰ ፍርሃትን አስወግደን ለእውነት ልንቆም ይገባል።

/ ኒቆዲሞስ ከቀን ልብ ይልቅ የሌሊት ልብ የተካተተ ስለሆነ በሙሉ ልቡ በማስተዋል ለመማር ስለፈለገ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የማታውን መረጠ ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል ከልብ ሆነን የምንማር የሰማነው ቅዱስ ቃል በህይወታችን ፍሬ እንዲያፈራ ቅዱስ ቃሉን ከልብ ሆነን በማስተዋል ልንሰማ ይገባናል ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ልብ መልካም መሬት ተብⶀል

በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው› ማቴ ፲፫፡፳፫

አንዳንዶቻችን ጸሎት እያደረግን እንኳን አንደበታችን የእግዚአብሄርን ቃል ይነዳል ልባችን ሌላ ቦታ ይንጎዳጎዳል በማህበር ጸሎትም አብረን እየጸልይን በመሃል ሳይን አውት አርገን ልክ ሲፈጸም አለቀ እንዴ ብለን ሳይን ኢን የምናደርግ አንጠፋም።

/ ሌሊት ጨለማ ነው ብርሃን የለም ይህም የኃጢአት ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስ በሌሊት መምጣቱ በኃጢአት እንዳለ ንስሃ እንደሚፈግ ያስረዳናል ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን ስንሰማ በተአምኖ ኃጢአት በንስሃ ውስጥ ሆነን የምንሰማ ያለንስሃ የምንሰማው ቃል በህይወታችን ፍሬ የማፍራት እድሉ ጠባብ ነው ምክንያቱም በንስሃ ከልባችን ያልጸዱት ክፉ ምኞቶች እንደ እሾህ ሆነው ያንቁታልና

ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ እሾህም ወጣና አነቀው› ማቴ ፲፫፤፰ ተብሎ የተጻፈው ለዚህ ነው።

/ ሌሊት የቆየው ኪዳን ወይም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስም እኔ ምሁረ ኦሪት እንጂ ምሁረ ወንጌል አይደለሁም ወንጌልን ካንተ እማር ዘንድ ያስፈልገኛል ሲል በሌሊት ይመጣ ነበር ብሉያት ከሓዲሳት ጋር ተዋህደው ሲተረጎሙ ሰሙና ወርቁ ተጣምሮ የሕይወት ትምህርት ያስገኛል አንዳንዶች ዛሬ ብሉያት ጭራሽ አያስፈልጉም ሲሉ ይደመጣሉ ነገር ግን እንደ ኒቆዲሞስ ሁለቱን ኪዳናት አዋህዶ መጓዝ ትክክለኛው መንገድ ነው ለዚህም ነው ጌታ ሲያስተምር‹እውነት እላችኋለው ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከህግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ አታልፍም› ማቴ ፭፤፲፰ በማለት አበክሮ የተናገረው ኒቆዲሞስ ምንም እንኳን የቀኑ ክፍለ ጊዜ ባይመቸውም በሌሊቱ ሰአት ለመማር ችⶀል እኛም ከሱ ተምረን ከልብ ካለቀሱ እንባ አይጠፋምና ምንም ስራ ቢበዛብን ለቅዱስ ቃሉ ጊዜ አይጠፋምና ህይወት ለሚገኝበት ትምህርት ጊዜ ልንሰት ይገባል።

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Jerusalem Mount of Olives: Ethiopian Christians Celebrate the 5th Sunday of the Great Lent | ደብረ ዘይት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 7, 2024

የዐቢይ ጾም ፭ተኛ ሳምንት ደብረ ዘይት

የክርስቶስ ዳግም ምጽአት መቼ ነው የሚሆነው?

እንኳን ለደብረዘይት በዓል አደረሰን!

😮 በነገው ዕለት በተለይ በአሜሪካ በሚከሰተው/ በሚጠበቀው የፀሐይ ግርዶሽ ክስተት ዋዜማ፤ ደብረ ዘይት? ዋው! ሌላ አስገራሚ ክስተት አለ፤ ጊዜ ስላጠረኝ እና ‘ነገሮች’ ኮፒውተሬን እየዘጉ ብዙ ስለተፈታተኑኝ በነገው ዕለት አቀርበዋለሁ

ደብረ ዘይት በግዕዝ ልሣን ደብረዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት ነው። ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:-ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሰረት ነገረ ምጽአቱን (የመምጣቱን ነገር) እንድናስታዉስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነዉ።

በዚያ ልማድ መሠረት ጌታችን ዓለምን ለማሳለፍ ደግሞ የሚመጣበትን ምልክትና ጠቋሚ ነገር ምን ምን እንደሆነ፣ እርሱ ከመምጣቱ በፊት በዓለም ላይ ምን፥ ምን እንደሚደረግና ምን እንደሚታይ ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ነው። (ማቴ. ፳፬፥፩፡፶፩) ስለ ዓለም ሁሉ ቤዛ ለመሆን በሚሰቀልበት ቀን ዋዜማ ማለት በትልቁ ሐሙስ (ጸሎተ ሐሙስ) በለበሰው ሥጋ የጸለየው ከደብረ ዘይት ጋር ተያይዞ በሚገኘው ቦታ በጌተሴማኒ ነበር። (ማቴ. ፳፮፥፴፮) በኃላ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላም ለደቀመዛሙርቱ እንዲነግሩ ሲልካቸው፥ “ሂዱና ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፥ በዚያም ታዩኛላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው፥” ብሎ የላካቸው በደብረ ዘይት ገሊላ ተብላ ትጠራ ወደ ነበረችው ቦታ ነው። (ማቴ. ፳፰፥፱) ገሊላውያን ወደ ኤየሩሳሌም ሲመጡ በደብረ ዘይት ያርፍ ነበርና እነሱ ሲያርፉባት የነበረችው ቦታ ገሊላ እየተባለች ትጠራ ነበር። መድኃኔዓለም ክርስቶስ የድኅነት ሥራ ፈጽሞ ወደ ሰማይ ያረገው ከዚህ ተራራ ተነሥቶ ነው። (ሐዋ. ፩፥፲፪) ቀደም ብሎም የሆሳእናው የመድኃኔዓለም አስደናቂ ጉዞ የተጀመረው ከደብረ ዘይት ሥር ነበር። (ማቴ. ፳፩፥፩፡፲፮)

ደብረዘይት ምሳሌነቱ ይህች ቤተክርስቲያን ናት፣ ደብረዘይት የኦርቶዶክሳውያን ተራራ፣ የእግዚአብሔር ቃል የሚነገርባት፣ መሠረታዊ ሐይማኖት የምንማርባት፣ ካሕናት የሚሠፍሩባት፣ ምዕመናን የሚገናኙባት፣ እግዚአብሔርን የምንወድ ሁሉ የምንሰባሰብባት አማናዊት ደብረ ዘይት ቤተክርስቲያን ናት።

ትልቁ መሠረተ ልማት የሰው ልጅ ነው፤ ቁሳቁሱን፣ ድንጋይና ድንጋይ፣ አሸዋና ሲሚንቶ ማቀላቀል አይደለም”

ሰውን ከእግዚአብሔር ከሚለየው አጉል ሰላም ይልቅ ከእግዚአብሔር የማይለየው ጦርነት ይሻላል፤ ስሜታዊ ከሆነና ለቤተ ክርስቲያን ዘለቄታዊ ጉዳት ከሚኖረው ስምምነትና አንድነት ይልቅ ስለ ሐይማኖት መጠበቅ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ የሚኖረውና ለዚህ ሲባል የሚሆን አለመስማማት ይሻላል፡፡” ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

🔥 ኢትዮጵያዊቷን የ ደብረዘይትከተማን ቢሸፍቱበማለት እራሳቸውን ከ ፍዬል ሕዝብ 🐐 የመደቡት ከሃዲዎቹና የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ጋላ-ኦሮሞዎች የትንቢት መፈጸሚያ ይሆናሉ

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቤቱ፥ የሚጠሉህን እኔ የጠላሁ አይደለሁምን? ስለ ጠላቶችህም አልተሰቀቅሁምን? ፍጹም ጥል ጠላኋቸው፥ ጠላቶችም ሆኑኝ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 24, 2024

♱ ከ፫ ዓመታት በፊት በፋሺስቱ ጋላ-ኦሮሞ ሰአራዊት እና አጋሮቹ የተጨፈጨፈው የእንዳ ቅዱስ ጨርቆስ ቤተክርስቲያን ፍረዳሽም (ወረዳ ጉሎመኸዳ)

+ በተጨማሪም፤

  • ❖ አባቶች ተገደሉ
  • ❖ በውስጡ የነበሩ ጥንታዊ የብራና መጽሐፍት ከአቧራ ጋር ተደባለቁ!

👹 የደም ሰዎች የሆኑትን ጋላ-ኦሮሞዎችን (የስጋ ማንነታቸውን እና ምንነታቸውን) ጠላኋቸው

😠😠😠 ዋይ! ዋይ! ዋይ! 😢😢😢

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አስባቸው፤ በእቅፍህ አስቀምጣቸው!

😇 በእውነት እግዚአብሔር ይጠላልን?

ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ

❖[ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ ፱፥፮፡፲፫]❖

ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም። እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤ የአብርሃምም ዘር ስለሆኑ ሁላቸው ልጆች አይደሉም፥ ነገር ግን። በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል ተባለ። ይህም፥ የተስፋ ቃል ልጆች ዘር ሆነው ይቆጠራሉ እንጂ እነዚህ የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም ማለት ነው። ይህ። በዚህ ጊዜ እመጣለሁ ለሳራም ልጅ ይሆንላታል የሚል የተስፋ ቃል ነውና። ይህ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ርብቃ ደግሞ ከአንዱ ከአባታችን ከይስሐቅ በፀነሰች ጊዜ፥ ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፥ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ፥ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ፥ ለእርስዋ። ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ተባለላት። ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።”

❖[ትንቢተ ሚልክያ ምዕራፍ ፩፥፩፡፬]❖

በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተ ግን። በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ፤ ተራሮቹንም በረሃ አደረግኋቸው፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች አሳልፌ ሰጠኋቸው። ኤዶምያስ። እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ በሰዎችም ዘንድ። የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።”

‘ፍቅር የሆነ አምላክ ሊጠላ ይችላል’ የሚለው ጉዳይ ተቃርኖ ሊመስል ይችላል። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ነው የሚለው ይህ ነው፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነው (፩ኛ ዮሐንስ ፬፥፰) እና እግዚአብሔር ይጠላል (ሆሴዕ ፱፥፲፭)። የእግዚአብሔር ተፈጥሮ ፍቅር ነው ፥ ሁልጊዜም ለሌሎች የሚበጀውን ነገር ያደርጋል ፥ እናም ከተፈጥሮው ጋር የሚቃረንን ይጠላል፤ ፍቅርን የሚጻረርን ይጠላል።

አምላክ አንዳንድ ነገሮችን እንደሚጠላ ማንንም ሊያስደነቅ አይገባም። እርሱ የፈጠረን ነውና የመውደድም የመጥላትም አቅም አለው፣ እናም ጥላቻ አንዳንዴ ትክክል እንደሆነ እንገነዘባለን ፥ በተፈጥሮ የምንወደውን የሚያበላሹ ነገሮችን እንጠላለን። ይህ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠርንበት አካል ነው። ሁላችንም በኃጢአት መበከላችን ፍቅራችንና ጥላቻችን አንዳንድ ጊዜ የተሳሳተ ቦታ ይሆናል ማለት ነው። ነገር ግን የኃጢአት ተፈጥሮ መኖር እግዚአብሔር የሰጠንን የመውደድና የመጥላት ችሎታን አያጠፋውም። የሰው ልጅ መውደድና መጥላት መቻሉ አይቃረንም፤ የእግዚአብሔር መውደድና መጥላትም ተቃራኒ አይደለም።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ጥላቻ ሲናገር የሚጠላው ኃጢአትና ክፋት ነው። እግዚአብሔር ከሚጠላቸው ነገሮች መካከል ጣዖትን ማምለክ (ዘዳግም ፲፪፥፴፩፤ ፲፮፥፳፪)፣ የሕጻናት መሥዋዕትን፣ የፆታ ብልግናን (ዘሌዋውያን ፳፥፩፡፳፫) እና ክፉ የሚያደርጉትን (መዝ. ፭፥፬፡፮ ፤ ፲፩፥፭) ይገኙበታል። ምሳሌ ፮፥፲፮፡፲፱) እግዚአብሔር የሚጠላቸው ሰባት ነገሮችን ይዘረዝራል፤ ትዕቢትን፣ ውሸትን፣ ግድያን፣ ክፉ ሴራን፣ ክፉን የሚወዱ፣ ሐሰተኛ ምስክሮች እና አስጨናቂዎች፣ በወንድማማች መካከል ፀብን የሚዘራውን ። ይህ ክፍል እግዚአብሔር የሚጠላቸውን ነገሮች ብቻ እንደማያካትት እናስተውል፤ ሰዎችንም ያጠቃልላል። ምክንያቱ ቀላል ነው፡ ኃጢአት በክርስቶስ ብቻ ካለው ይቅርታ በቀር ከኃጢአተኛው ሊለይ አይችልም። ክርስቶስ ደግሞ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ተሰውቶልናል። አምላክ ውሸትን ይጠላል፣ አዎ፣ ምንጊዜም ውሸትን የሚመርጥ ሰው ውሸታም ነው። እግዚአብሔር በሐሰተኛው ላይ ሳይፈርድ በውሸት ሊፈርድ አይችልም።

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር የዓለምን ሰዎች እንደሚወድ በግልጽ ያስተምራል (ዮሐንስ ፫፡፲፮)። እግዚአብሔር ክፉዋን ነነዌን ወደ ንስሐ አመጣት (ዮናስ ፫)። እግዚአብሔር በክፉዎች ሞት ደስ አይለውም (ሕዝ ፲፰፥፴፪)። እስከ ጽንፍ ይታገሣል፣ “ሁሉም ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ አይወድም” (፪ኛ ጴጥሮስ ፫፥፱)። ይህ ሁሉ የፍቅር ማረጋገጫ ነው ፥ እግዚአብሔር ለፍጥረታቱ የሚበጀውን ይፈልጋል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ (መዝሙረ ዳዊት ፭፥፭) ስለ እግዚአብሔር ሲናገር “ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ትጠላለህ”። (መዝሙር ፲፩፥፭) “እግዚአብሔር ጻድቅንና ኅጥእን ይመረምራል፤ ዓመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቶአል።” የሚለው ደግሞ የበለጠ ከባድ ነው።

አንድ ሰው ንስሐ ከመግባቱ እና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ከማመኑ በፊት የእግዚአብሔር ጠላት ነው (ቆላስይስ ፩፥፳፩)። ሆኖም፣ ከመዳኑ በፊት እንኳን፣ በእግዚአብሔር የተወደደ ነው (ሮሜ ፭፥፰)፥ ማለትም፣ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ስለ እርሱ ሠዋ። ጥያቄው እንግዲህ የእግዚአብሔርን ፍቅር የናቀ፣ ንስሐ ለመግባት ፈቃደኛ ያልሆነ እና በኃጢአቱ ላይ ግትር የሆነ ሰው ምን ይሆናል? መልስ፡ እግዚአብሔር ይፈርድበታል። ምክንያቱም እግዚአብሔር ኃጢአትን መፍረድ አለበትና ነው፤ ይህም ማለት በኃጢአተኛው ላይ መፍረድ ማለት ነው። እነዚህ እግዚአብሔር የሚጠላቸው “ክፉዎች” ናቸው ፥ በክርስቶስ ያለውን የእግዚአብሔርን ጸጋና ምሕረት እንኳ ሳይቀር ንቀው በኃጢአታቸውና በአመፃቸው ጸንተው የሚኖሩ ክፉዎች ናቸው።

ጋላ-ኦሮሞዎቹን እኮ ላለፉት አምስት መቶ ዓመታት / በተለይ በያዝናቸው አምስት ዓመታት በዓይናችን አየናቸው። ሩኽሩሆቹ ኢትዮጵያውያን እና ቅድስት ሃገረ ኢትዮጵያ ብዙ ታገሳቸውን ሰጥታቸው ነበር። እግዚአብሔር አምላክ፣ የመዳኛ እድሉን ሁሉ በነጻ አበርክቶላቸው ነበር፤ ነገር ግን እነርሱ አሻፈረን ብለው ስጋዊውን የዋቄዮ-አላህ-ባፎሜት-ሉሲፈር መንገድን በመምረጣቸው በግራኝ አህመድ ቀዳማዊ ዘመን + በዳግማዊ ምንሊክ ዘመን + በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን + በመንግስቱ ኃይለ ማርያም ዘመን እንዲሁም ዛሬ በዳግማዊ ግራኝ አህመድ ዘመን ደም ማፍሰሱን፣ ሕዝበ ክርስቲያኑን ማስራቡንና ማሳደዱን፣ ብሎም ዘረፋውን ቀጥለውበታል።

ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ሲል ጽፏል:- “አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፤ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም።” (መዝሙረ ዳዊት ፭፥፬) በአንጻሩ፣ በእግዚአብሔር የሚታመኑት ሁሉ “ደስ ይላቸዋል” እና “ለዘላለም በደስታ ይዘምራሉ” (ቁጥር ፲፩)። እንዲያውም መዝሙር ፭ እና መዝሙር ፲፩ በጻድቃን (በእግዚአብሔር የሚታመኑት) እና በክፉዎች (በእግዚአብሔር ላይ በሚያምፁት) መካከል ትልቅ ልዩነት እንዳአላቸው ይነግሩናል። ጻድቃን እና ክፉዎች የተለያዩ ምርጫዎችን ያደርጋሉ እና የተለያዩ እጣ ፈንታዎች ነው ያሏቸው ፥ አንድኞቹ የእግዚአብሔርን ፍቅር የመጨረሻውን መግለጫ ያያሉ ፥ ሌላኛዎቹ ደግሞ የመጨረሻውን የእግዚአብሔርን የጥላቻ መግለጫ ያውቁ ዘንድ ግድ ነው።

በፍፁም ፍቅር መውደድ አንችልም፣ በፍጹም ጥላቻም መጥላት አንችልም። እግዚአብሔር ግን ፍጹም መውደድም ሆነ መጥላት ይችላል ምክንያቱም እርሱ እግዚአብሔር ነውና ነው። እግዚአብሔር ያለ ኃጢያት ሃሳብ መጥላት ይችላል። ኃጢአተኛውን ፍጹም በሆነ ቅዱስ መንገድ ሊጠላ እና አሁንም ኃጢአተኛውን በፍቅር በንስሐ እና በእምነት ጊዜ ይቅር ማለት ይችላል (ሚልክያስ ፩፥፫ ፤ ራእይ ፪፥፮ ፤ ፪ ጴጥሮስ ፫፥፱)።

እግዚአብሔር ለሁሉም ባለው ፍቅር መድኃኔ ዓለም ልጁን አዳኝ እንዲሆን ልኮታል። ኃጢአተኞች፣ አሁንም ይቅር የማይባሉት፣ እግዚአብሔር “ስለ ኃጢአታቸው ብዛት፣ ዐምፀዋልና” (መዝሙረ ዳዊት ፭፥፲) ይጠላቸዋል። ነገር ግን ፥ ይህ ለመረዳት አስፈላጊ ነው ፥ እግዚአብሔር የሚፈልገው ክፉዎች ለኃጢአታቸው ንስሐ እንዲገቡ እና በክርስቶስ መጠጊያ እንዲያገኙ ነው። እምነት በሚድንበት ጊዜ፣ ኃጢአተኛው ከጨለማው መንግሥት ተወግዶ ወደ ፍቅር መንግሥት ተላልፏል(ቆላስይስ ፩፥፲፫፡፲፬)ይመልከቱ)። ጥል ሁሉ ፈርሷል፣ ኃጢአት ሁሉ ተወግዷል፣ እና ሁሉም ነገር አዲስ ሆኗል (፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፥፲፯)፤

“ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፴፰]❖❖❖

  • ፩ አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም።
  • ፪ አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፤ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ።
  • ፫ ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ፤ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥
  • ፬ የዓመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ።
  • ፭ አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቅህ፤ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ።
  • ፮ እውቀትህ ከእኔ ይልቅ ተደነቀች፤ በረታች፥ ወደ እርስዋም ለመድረስ አልችልም።
  • ፯ ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?
  • ፰ ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ። ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።
  • ፱ እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥
  • ፲ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።
  • ፲፩ በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፥ ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች፤
  • ፲፪ ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና፥ ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና፤ እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው።
  • ፲፫ አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል።
  • ፲፬ ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።
  • ፲፭ እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም።
  • ፲፮ ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።
  • ፲፯ አቤቱ፥ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው! ቍጥራቸውም እንደ ምን በዛ!
  • ፲፰ ብቈጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ፤ ተነሣሁም፥ እኔም ገና ከአንተ ጋር ነኝ።
  • ፲፱ አቤቱ፥ አንተ ኃጢአተኞችን የምትገድል ከሆንህስ፥ የደም ሰዎች ሆይ፥ ከእኔ ፈቀቅ በሉ።
  • ፳ በክፋት ይናገሩብሃልና፤ ጠላቶችህም በከንቱ ያምፁብሃል።
  • ፳፩ አቤቱ፥ የሚጠሉህን እኔ የጠላሁ አይደለሁምን? ስለ ጠላቶችህም አልተሰቀቅሁምን?
  • ፳፪ ፍጹም ጥል ጠላኋቸው፥ ጠላቶችም ሆኑኝ።
  • ፳፫ አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ፤ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ፤
  • ፳፬ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፤ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ።

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

The Islamic Devil / Shaitan Has Entered One of The Most Sacred Orthodox Monasteries of Ethiopia

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 14, 2024

👹 እስላማዊው ዲያብሎስ/ሰይጣን በኢትዮጵያ ከሚገኙት የተቀደሱ የኦርቶዶክስ ገዳማት መካከል አንዱ ወደ ሆነው ወደ አቡነ የማታ ጎህ ገዳም ገብቷል።

😢😢😢 ዋይ! ዋይ! ዋይ! 😠😠😠

♱ የሑዳዴ ጾም ነው! ♱

ሙስሊሙ ግን ወደ ገዳም እንዲገባ ተፈቅዶለታል። ይህ ትልቅ ስድብ ነው! አስቡት አንድ ክርስቲያን በመካ ታላቁ መስጊድ (መስጂድ አል ሀራም) ወንጌልን እንዲህ ለመስበክ ቢሞክር። የማይታሰብ ነው!

😈 የዚህ ከሁለት ሰአታት በፊት ዩቲዩብ ላይ የተለጠፈው የስድብ ቪዲዮ ርዕስ፡- “ዳዋህ 600 ጫማ ከፍታ ባለው ቤተክርስቲያን ውስጥ በኢትዮጵያ ገደል ውስጥ!” የሚለው ነው።

አጋንንታዊ ዳዋ ከጥንታዊ የኢትዮጵያ ገዳማት አንዱ በሆነው አቡነ የመታ ጎህ ፥ ያውም በዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ቀን?! እናም በገንዘብ፣ በወታደራዊና በዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ በሙስሊም አረቦች፣ በቱርኮች፣ በኢራንና በምዕራባውያን አገሮች የሚደገፈው የፋሽስቱ ጋላ-ኦሮሞ አገዛዝ ባለፉት ሦስት ዓመታት እስከ ሁለት ሚሊዮን የሚደርሱ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በጅምላ ከጨፈጨፈ፣ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን እና ገዳማትን ካወደመ በኋላ ይህ መከሰቱ እጅግ በጣም ያስቆጣል።

☪ ጂሃድ፣ በችግር – ምላሽ – መፍትሄ

ክርስቲያኖችን እየጨፈጨፉ በረሃብ ገድለው ሴቶቻቸውን ይደፍራሉ – ከዚያም መፍትሔውን ይዘው ይመጣሉ።

👉 ወደዚህ የተቀደሰ ገዳም እንዲገቡ ማን ፈቀደላቸው? (ልብ እንበል ብዙ የውጭ ሃገራት ቱሪስቶችን ወደዚህ ብርቅዬ ገዳም እያስገቧቸው ነው። ፈቃዱንም የሚሰጧቸው በርግጥ ፋሽስቱ የጋላ-ኦሮሞ አገዛዝ እና አጋር የሆነው ኢ-አማኒው የሕወሓት ስብስብ ናቸው።

ከሺህ አራት መቶ ዓመታት በፊትም ምስራቅ ሮማውያን እና የመካከለኛው ምስራቅ ኃይሎች የሃሰተኛው ነቢይ መሀመድ ተከታዮችን ወደዚሁ የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ግዛት ሲልኩ በጥንታውያኑ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ዘንድ ‘ዳዋህ’ ለማድረግ፤ ማለትም አጋንንታቸውን ያራግፉ ዘንድ ነበር። አዎ! ታሪክ እራሷን እየደገመች ነው፤ ዛሬ የራሳችን ወደ ሆኑት የተቀደሱ ዓብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት እንዳንገባ እያደረጉ፣ ኢ-አማኒያኑን እና የክርስቶስን ልጅነት፣ አምላክነት፣ መሰቀልና መነሳት የሚክዱትን ተቃዋሚዎቹን መሀመዳውያንን ግን ገዳማቱን ያረክሷቸው ዘንድ በዚህ መልክ በስልት እያስገቧቸው ነው። ያውም ሁለት ሚሊየን ክርስቲያኖችን ከጨፈጨፉ በኋላ። ጊዜውማ ከዚህ ሁሉ ዕልቂትና ሰማዕትነት በኋላ በተለይ ሙሉ ትግራይ ክፍለ ሃገርን ከኢ-አማኒያን፣ ከመናፍቃን እና ከመሀመዳውያን ንጹሕ ማድረግ የሚጠይቅ ጊዜ ነበር።

😇 ቅዱሳን አባቶቻችን እነ፤

  • ❖ ንጉሥ ኢዛና
  • ❖ ነገሥታት አብርሃ ወ አጽብሃ
  • ❖ አፄ ካሌብ
  • ❖ አቡነ የማታ ጎህ
  • ❖ ቅዱስ ያሬድ
  • ❖ አቡነ አረጋዊ
  • ❖ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
  • ❖ አባ ዓቢየ እግዚእ
  • ❖ አፄ ዮሐንስ
  • ❖ እንዲሁም ላለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት የዋቄዮ-አላህ-ባፎሜት-ሉሲፈር ባሪያዎች በሆኑት ጋላ-ኦሮሞዎች እና መሀመዳውያኑ አጋሮቻቸው ጂሃድ የሰማዕትነትን አክሊል የተቀዳጁት መቶ ሚሊየን የሚሆኑ የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ

ይህን የመሀመዳውያኑን ሰይጣናዊ ድፍረት፣ ንቀትና ስላቅ ሲያዩ ምን ይሰማቸው ይሆን? በዚህ ትውልድ እጅግ በጣም እንደሚያዝኑና እንደሚቆጡ ምንም አያጠራጥርም። ታዲያ እስከ መቼ ነው ይህ ትውልድ ለሕዝባችን እርግማን እና መከራ ማምጣቱን የሚያቆመው? እንግዲህ እንደ ታላቁ አፄ ዮሐንስ አራተኛ ክርስቲያን የሆነ መሪ ተነስቶ የተሠሩትን ከባባድ ስህተቶችንና ሃጢዓቶችን እስካላስተካከለ ድረስ መከራና ስቃያችን ይቀጥላል።

አየን/ ሰማን አይደል፤ ቆሻሻው እባብ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ልክ ወደ አቡነ የማታ ጎህ እንደተጓዙት መሀመዳውያን የሑዳዴ ጾም መግቢያውን ዕለት (ሰይጣናዊው ረመዳንም በዚሁ ወቅት ነው የጀመረው) ጠብቆ፤ “በአዲስ አበባ ቱሪስቶች በቤተ ክርስቲያን እና መስጊድ አዛን ጩኸት ተረብሸዋል!” አለ። ይህች የተለመደችው የእነ ሲ.አይ.ኤ ምክር ናት! እንግዲህ የተበዳዩነትን ካርድ ከትክክለኛዎቹ ክርስቲያን ተበዳዮች ለመንጠቅና ክርስቲያኑን ከሙስሊሙ ጋር ለማደባለቅና አንድ ለማድረግ የታሰበ ተንኮል ነው። አዲስ ነገር አይደለም፤ አክሱም ጽዮንን ሲጨፈጭፍ ወዲያው ወደ ውሮ አምርተው የደበደቡት አል ነጃሽየተባለውን የሰይጣን ማምለኪያ መስጊድን ነበር። ትግራይን ለመምታት ሕወሓትን እና ኦላ/ሸኔየተሰኙትን የብልግና/ኦነግ ግራ እጆች እንደሚዘረጉት። ይህ ሁሉ እንግዲህ የትግራይን ክርስቲያን ሕዝብን መጨፍጨፉን ለመቀጠል ያስችለው ዘንድ ነው። ለዚህም ነው መሀመዳውያኑ መስጊዳቸው ሲመታ እስካሁን ድረስ ጸጥ ያሉት።

“ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ነኝ” የሚል ወገን ሁሉ፤ በተለይ ሰሜን ኢትዮጵያዊው በጽኑ የሚፈተንበት ወቅትና፣ ጉዳይ እና ሥራ ይህ ነው። ከሌላው ሁሉ ለዚህ መንፈሳዊ ጉዳይ ሰበባሰበብ ሳይፈልግና ሉሲፈራውያኑ በሰጡት አጀንዳ በከንቱ ሳይጠመድ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠውና በአንፃሩ ሊታገልበት ይገባል።

ዲያቆኑ ከጦር ግንባር | ጦርነቱ ክርስቲያኖችን አጥፍቶ የ666ቱን እስላማዊ ኤሚራትን በኢትዮጵያ የማንገሻ መንገድ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 2, 2021

ዲያቆኑ ከጦር ግንባር | ጦርነቱ ክርስቲያኖችን አጥፍቶ የ666ቱን እስላማዊ ኤሚራትን በኢትዮጵያ የማንገሻ መንገድ ነው

♱ It’s Great Lent! ♱

But a Muslim is inside an Ethiopian Monastery, this is Blasphemy! Imagine if a Christian tries to evangelize at the great mosque (Masjid al-Haram) of Mecca. Inconceivable!

😈 This blasphemous video, which is posted two hours ago on YouTube, is originally titled: “Dawah in a Church 600ft high up in the cliffs of Ethiopia!„

Demonic Dawah inside one of the most ancient ♱ Ethiopian Monasteries, Abuna Yemata Guh – and this during the first day of The Great Lent (“Clean Monday”)?! And this right after the fascist Oromo regime of Ethiopia, which is financially, militarily and diplomatically supported by Muslim Arabs, Turks, Iranians and Western countries have been able to massacre up to two million Orthodox Christians, destroyed several churches and monasteries in the past three years.

Jihad, through Problem – Reaction – Solution

They massacre Christians, starve them to death, and rape their women – and then they come up with the solution.

Who gave them permission to enter this very sacred monastery?

Of course, the fascist Gala-Oromo regime and its ally, the atheist TPLF group.

👉 ከጥቂት ቀናት በፊት እነዚህን ልኪያቸው ነበር / A few days ago a posted these:

😈 Ethiopia: The U.N. and the U.S. Suspended Food Aid to Christian Tigray, for This Satanic Purpose

😈 ለዚህ ሰይጣናዊ አላማ (ለአውሬው የዲጂታል ቁጥጥር ተልዕኮ) የተመዱ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) እና የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (USAID)

እንደምናየውም የኤዶማውያኑ ምዕራባውያን እና የእስማኤላውያኑ ምስራቃውያን ተቋማትና ግለሰቦች፣ ጎብኚዎች አንድ በአንድ ወደ አክሱማዊቷ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ ናቸው። የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ጨፍጫፊዎቻችን እነ ቱርክ እና የአረብ ኤሚራቶች፤ ትምህርት ቤት‘(መድረሳ)፣ የእስላም ባንክ፣ ሰይጣናዊ ሃላል ምግብ ወደ ትግራይ ክፍለሃገር በማስገባት ላይ ይገኛሉ። ጎን ለጎን፤ አይዱሃዊው ፖለቲከኛ በአረጀንቲና ፕሬዚደንት እንዲሆን ካደረጉ በኋላ ከሱ በፊት የነበረው መሪ አስገብቶት የነበረውን የብሪክስ አባልነት ማመልከቻን እንዲሠርዝ ሲያደርጉት ፥ የፋሺስቱ ጋላኦሮሞ አገዛዝን ግን የብርኪስ አባል እንዲሆን አዘዙት። የሚቆጣጠሯቸው ተቃዋሚዎች የሆኑት እነ ፕሬዚደንት ፑቲንም የተጠለፈችውን ኢትዮጵያንከታሪካዊ ጠላቶቻችን ከእነ ግብጽ፣ ሳውዲ እና ኤሚራቶች ጋር ወደ ብሪክስ አስገቧት።

A Warning For Lent? | Tornado Rips Through Antichrist Turkey

  • የሑዳዴ ጾም ማስጠንቀቂያ? | ኃይለኛ ቶርናዶ የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክን አመሳት

ቅዱሱ የሑዳዴ ፆም እና ጣዖታዊው የረመዳን ጾምበአንድ ወቅት በመዋላቸው የትግሉ እና ድሉ መዘጋጀት አለብን። ብዙ አስገራሚ ክስተቶች የሚፈጹማባቸው ቀናትና ሳምንታት ከፊታችን ናቸው። ረመዳን ኤርዶጋንም “ሥልጣኑ በቃኝ” በማለት ላይ ነው!

አስደሳች የመንፈሳዊ ጦርነት ጊዜ። እውነተኛው ውጊያ በሰማያዊው ዓለም ውስጥ በሥራ ላይ ካሉት መንፈሳዊ ኃይሎች እና አለቆች ጋር ነው።

March 11th – May 5th, 2024 is the Ethiopian Orthodox Great Holy Lent Fast lasting 55 days culminating on Easter May 5th, observed by followers of the Ethiopian Orthodox Church.

Interesting, that this year, the Islamic Ramadan ‘Fasting’ which is of Pagan Origin – begins at the same time.

Indeed, an interesting time of spiritual warfare. The real battle is against the spiritual powers and principalities at work in the heavenly realms.

Ethiopia’s Chapel In The Sky: The Reason For The Genocidal War Against Orthodox Christians

  • ❖ በሰማይ ላይ የሚገኝ ፀሎት ቤት፤ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ የዘር ማጥፋት ጂሃድ እንዲካሄድ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል አንዱ ይህ ነው፤ ቅናት፣ ምቀኝነት ጥላቻ!

♱ አቡነ ይምዓታ ጉህ ገዳም ፥ አቤቱ ለደጅህ አብቃን! ♱

ቪዲዮው የሚያሳየው የኢትዮጵያን ውብ የሆነ መልክዓምድራዊ ገጽታን የተላበሰው የ ”ገራልታ ሰንሰለታማ ተራራ” ነው። በውስጡም እንደ “አቡነ ይምዓታ ጎህ ገዳም” የመሳሰሉትን እፁብ ድንቅ የሚባሉ ታሪካዊና ኃይማኖታዊ ቅርሶችን አቅፎ ይዟል፡፡ ገራልታ በትግራይ ክልል ሓውዜን ይገኛል፡፡ ሓውዜን ከውቡ ገራልታ ሰንሰለታማ ተራራ በተጨማሪ በርካታ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት የሚገኙባት፤ የታታሪ ነዋሪዎች መገኛም ነች፡፡

ሁሉም ነገር ድንቅ ነው! ተራራዎቹ፣ ብርሃኑና ቀለማቱ በጣም ያስደንቃሉ።

ይህን የመላው ዓለምን ዓፍ በመገረም የሚያስከፍት ድንቅ ገዳም እንደ ዓይን ብሌናችን ልንከባከብ፣ ልንከላከልና ልንዋደቅለን ሲገባን፤ ይህ ከሃዲ የዳግማዊ ምንሊክ የመጨረሻው ትውልድ ርዝራዥ ግን የፋሺስቱ ጋላ-ኦሮሞ አገዛዝንና መሀመዳውያኑን፣ መናፍቃኑን፣ ኢ-አማኒያኑን እና ባዕዳውያኑን የክርስቶስ ተቃዋሚ አጋሮቹን አስገብቶ ለማስጨፍጨፍ፣ ለማዘረፍ እና ለማርከስ ፈቀደ። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? እጅግ በጣም የሚያሳዝን ክስተት እኮ ነው! ከአምስት መቶ ዓመታት በፊትም ግራኝ ቀዳማዊን በተመሳሳይ ክህደት ከጅጅጋ ተነስቶ እስከ አክሱም ጽዮን ዘልቆ እንዲገባ ፈቅደውለታልን? ለምንድን ነው ያኔስ በሐረር፣ ሸዋ እና ቤተ አምሐራ ያሉ አባቶች ቅድስት አክሱም ጽዮንን ያልተከላከሉላት? ይህ መመርመር የሚገባን ጉዳይ ነው!

እንግዲህ ይህ አሳዛኝ ክስተት የሚጠቁመን “ክርስቲያን እና ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚለውን ወገን ሁሉ ጨምሮ ትውልዱ በዋቄዮ-አላህ-ባፎሜት-ሉሲፈር መንፈስ ሥር መወድቁን ነው። ግድየለሽነት፣ ቅናት፣ ምቀኝነት፣ ተንኮል፣ ጥላቻ እና ግድያ የአህዛብና መናፍቃን መገለጫዎች ናቸው።

😢😢😢 ዋይ! ዋይ! ዋይ! 😠😠😠

♱ At 2,580 metres (8,460 ft) Abuna Yemata Guh: The Most Inaccessible Place Of Worship on Earth Is Located in Northern Ethiopia

The Image: Its entrance is highlighted by a red circle and has to be climbed on foot to reach.

If churches were assessed by their risk factor, Abuna Yemata Guh would be our new Sistine Chapel. Perched 650 feet above a steep cliff in Northern Ethiopia, visitors face a 45-minute climb up the cliff’s vertical face in order to access the precariously positioned church. The first 45 minutes of the climb is mildly challenging, with a couple of tricky sheer sections requiring toehold action; guides carry ropes for the final push. The last two minutes require nerves of steel to make the final scramble and precarious ledge walk over a 200m drop.

🦎 Reptilian Conspiracy Theorists: E.T. Spotted in Old Painting in a Very Old Christian Church In Ethiopia

  • “በጥንታዊው የአቡነ ይምዓታ ገዳም የሚገኘው ሥዕል ከምድር ውጭ ያሉትን የሚሳቡ እንስሳትን ያሳያሉ!“ ይሉናል የሚሳቡ እንስሳትን ሤራ የሚከታተሉ ሰዎች

Posted in Ethiopia, Faith, News/ዜና | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 10, 2024




👉 ማስተካከያ፤ [፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬]❖

❖❖❖[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬]❖❖❖

  • ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።
  • የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥
  • ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።
  • ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።
  • እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ ዓለሙም ይሰማቸዋል።
  • እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ በዚህ እናውቃለን።
  • ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።
  • ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።
  • በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።
  • ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።
  • ፲፩ ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።
  • ፲፪ እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።
  • ፲፫ ከመንፈሱ ስለ ሰጠን፥ በእርሱ እንድንኖር እርሱም በእኛ እንዲኖር በዚህ እናውቃለን።
  • ፲፬ እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።
  • ፲፭ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።
  • ፲፮ እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
  • ፲፯ በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።
  • ፲፰ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።
  • ፲፱ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።
  • ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
  • ፳፩ እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።

እግዚአብሔርም እንዳላቸው አሕዛብን አላጠፉም፤ ከአሕዛብም ጋር ተደባለቁ፥ ሥራቸውንም ተማሩ

አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ፥ አድነን ፣ ከአሕዛብ መካከል ሰብስበን ❖

❖❖❖ መዝሙረ ዳዊት ከ ምዕራፍ ፻፩ እስከ ምዕራፍ ፻፭ ❖❖❖

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፭]❖

  • ሃሌ ሉያ፤ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።
  • የእግዚአብሔርን ኃይል ሥራ ማን ይናገራል? ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ያሰማል?
  • ፍርድን የሚጠብቁ፥ ጽድቅንም ሁልጊዜ የሚያደርጉ ምስጉኖች ናቸው።
  • አቤቱ፥ በሕዝብህ ሞገስ አስበን፥ በመድኃኒትህም ጐብኘን፤
  • የመረጥሃቸውን በጎነት እናይ ዘንድ፥ በሕዝብህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከርስትህም ጋር እንጓደድ ዘንድ።
  • ከአባቶቻችን ጋር ኃጢአትን ሠራን፥ ዐመፅንም፥ በደልንም።
  • አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ ተኣምራትህን አላስተዋሉም፥ የምሕረትህንም ብዛት አላሰቡም፤ በኤርትራ ባሕር ባለፉ ጊዜ ዐመፁብህ።
  • ኃይሉን ግን ለማስታወቅ። ስለ ስሙ አዳናቸው።
  • የኤርትራንም ባሕር ገሠጸ እርሱም ደረቀ፤ እንደ ምድረ በዳ በጥልቅ መራቸው።
  • ከሚጠሉአቸውም እጅ አዳናቸው፥ ከጠላትም እጅ ተቤዣቸው።
  • ፲፩ ያሳደዱአቸውንም ውኃ ደፈናቸው፥ ከእነርሱም አንድ አልቀረም።
  • ፲፪ በዚያን ጊዜ በቃሉ አመኑ፥ ምስጋናውንም ዘመሩ።
  • ፲፫ ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥ በምክሩም አልታገሡም።
  • ፲፬ በምድረ በዳም ምኞትን ተመኙ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።
  • ፲፭ የለመኑትንም ሰጣቸው፤ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።
  • ፲፮ ሙሴንም እግዚአብሔር የቀደሰውንም አሮንን በሰፈር ተመቀኙአቸው።
  • ፲፯ ምድርም ተከፈተች ዳታንንም ዋጠችው፥ የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፤
  • ፲፰ በማኅበራቸውም እሳት ነደደች፥ ነበልባልም ኅጥኣንን አቃጠላቸው።
  • ፲፱ በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።
  • ሣርም በሚበላ በበሬ ምሳሌ ክብራቸውን ለወጡ።
  • ፳፩፳፪ ታላቅ ነገርንም በግብጽ፥ ድንቅንም በካራን ምድር፥ ግሩም ነገርንም በኤርትራ ባሕር ያደረገውን ያዳናቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ።
  • ፳፫ እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።
  • ፳፬ የተወደደችውን ምድር ናቁ፥ በቃሉም አልታመኑም፥
  • ፳፭ በድንኳኖቻቸውም ውስጥ አንጐራጐሩ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።
  • ፳፮፳፯ በምድረ በዳም ይጥላቸው ዘንድ፥ ዘራቸውንም በአሕዛብ መካከል ይጥል ዘንድ፥ በየአገሩም ይበትናቸው ዘንድ፥ እጁን አነሣባቸው።
  • ፳፰ በብዔል ፌጎርም ተባበሩበት፥ የሙታንንም መሥዋዕት በሉ።
  • ፳፱ በሥራቸውም አስመረሩት፥ ቸነፈርም በላያቸው በዛ።
  • ፊንሐስም ተነሥቶ ፈረደባቸው፥ ቸነፈሩም ተወ፤
  • ፴፩ ያም እስከ ዘላለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።
  • ፴፪፴፫ በክርክር ውኃ ዘንድም አስቈጡት፥ መንፈሱን አስመርረዋታልና፤ ስለ እነርሱም ሙሴ ተበሳጨ፤ በከንፈሮቹም በስንፍና ተናገረ።
  • ፴፬ እግዚአብሔርም እንዳላቸው አሕዛብን አላጠፉም፤
  • ፴፭ ከአሕዛብም ጋር ተደባለቁ፥ ሥራቸውንም ተማሩ።
  • ፴፮ ለጣዖቶቻቸውም ተገዙ፥ ወጥመድም ሆኑባቸው።
  • ፴፯ ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠው፤
  • ፴፰ የወንዶች ልጆቻቸውንና የሴቶች ልጆቻቸን ደም፥ ለከነዓን ጣዖቶች የሠውአቸውን ንጹሕ ደም አፈሰሱ፥ ምድርም በደም ረከሰች።
  • ፴፱ በሥራቸው ረከሱ፥ በማድረጋቸውም አመነዘሩ።
  • የእግዚአብሔርም ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፥ ርስቱንም ተጸየፈ።
  • ፵፩ ወደ አሕዛብም እጅ አሳለፋቸው፥ የሚጠሉአቸውም ገዙአቸው።
  • ፵፪ ጠላቶቻቸውም ግፍ አደረጉባቸው፥ ከእጃቸውም በታች ተዋረዱ።
  • ፵፫ ብዙ ጊዜ አዳናቸው፤ ነገር ግን በምክራቸው አስመረሩት፥ በኃጢአታቸውም ተዋረዱ።
  • ፵፬ እርሱ ግን ጩኸታቸውን በሰማ ጊዜ ጭንቃቸውን ተመለከተ፤
  • ፵፭ ለእነርሱም ኪዳኑን አሰበ፥ እንደ ምሕረቱም ብዛት ተጸጸተ።
  • ፵፮ በማረኩአቸውም ሁሉ ፊት ሞገስን ሰጣቸው።
  • ፵፯ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ አድነን፤ ቅዱስ ስምህን እናመሰግን ዘንድ፥ በምስጋናህም እንመካ ዘንድ፥ ከአሕዛብ መካከል ሰብስበን።
  • ፵፰ ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ ሕዝብም ሁሉ አሜን ይበል። ሃሌ ሉያ።

Muslim Fanatics Felt Disillusioned When A Christian Preacher Told Them That There is No Salvation in Islam

አንድ ክርስቲያን ሰባኪ በእስልምና አምልኮ መዳን እንደሌለ ☪ ለሙስሊም አክራሪዎች ሲነገራቸው ተስፋ ቆርጠው ተንጫጩ።

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »