Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Baptism’

በጥምቀት ዕለት ወንዝ ውስጥ ልትጠመቅ ስትል የተሠወረችው ሩሲያዊቷ እናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 23, 2022

💭 አንዲት የአርባ ዓመት ጠበቃ ሴት ሁለት ልጆቿ ፊት ስትጠመቅ ሳታውቀው የወንዝ ጅረት ያለበት ጉድጓድ ውስጥ ገብታ ተሰወረች። 😢😢😢

ይህ የሆነው ባለፈው የጌታችን የጥምቀት በዓል ዕለት ጥር ፲፩/፳፻፳፪ ዓ.ም ነበር በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ አቅራቢያ ክልል ውስጥ በቪራ መንደር አቅራቢያ በሚገኘው በጣም ቀዝቃዛ የሆነ ወንዝ ላይ ነው።

ከሥፍራው የተገኘው ይህ ቪዲዮ በመገናኛ ብዙኃን በሰፊው ተሰራጭቷል። ቀረጻው እንደሚያሳየው ሴትየዋ ወደ ጉድጓዱ ውስጥ እንዴት እንደዘለለች ነው። ከዚያም ወደ ውሃ ውስጥ ይጠፋል.

በኃይለኛ ጅረት ከበረዶው በታች ተጎትታለች ተብሎ ይጠበቃል። የፍለጋ ሥራ በጠላቂ ዋናተኞች አማካኝነት እስከ ምሽት ድረስ ጠላቂዎች ጋር በጥምረት ተከናውኗል። ምንም በጎ ውጤት ግን አላማጣም።

በጥምቀት ዕለት በቀዝቃዛ በረዷማ ውሃ መጠመቅ በሩሲያውያኑ ኦርቶዶክሶች ዘንድ በጣም ተወዳጅ ነው፤ ፕሬዚደንት ፑቲን በየዓመቱ በዚህ መልክ ይጠመቃሉ።

👉 ይህ በጣም ብዙ መልሶች የተሰጡት የደይሊ ሜል ዘገባ ነው፤

💭 Distressing moment Russian lawyer, 40, is swept away by a frozen river after jumping through ice to mark Orthodox Epiphany as her children scream in horror

**WARNING UPSETTING CONTENT**

❖ A mother-of-two, 40, was swept away in a frozen river in front of her children

❖ The St Petersburg lawyer plunged into the river to mark Orthodox Epiphany

❖ Footage shows a strong current pull her away in the Oredezh River, Russia

________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የእስስቱ ግራኝ ፓስተር፤ “በፍል ውሃ አጥምቁኝ ምንም አልሆንም!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 19, 2022

የፍል ውሃ ፓስተር

________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ብዙዎቻችን ኢትዮጵያን አናውቃትም ዓለም ግን ሊወራትና ሊበላት ተነስቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 19, 2022

💥 የሚሰማው ብዙ ሆኖ የሚያስተውለው ግን ትንሽ ነው!💥

💭“የኢትዮጵያ ትንሣኤ የተዋሕዶ ክርስትና ትንሣኤ ነው፤ እግዚአብሔርን የሚያመልክ መሪ ሲመጣ ዛሬ የተደበላለቀችው/የደፈረሰችው ኢትዮጵያ ትጠራለች፤ እጇን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ መንፈሳዊነቷን ትቀበላለች፤ ዛሬ ሁላችንም በረሃብ፣ በሥጋ፣ በጥላቻና በእርስበርስዕልቂት ደዌ ተይዘናልና ከዚህ ሁሉ ደዌ ይፈውሰን።

ቆሻሻው የኢትዮጵያ ዘስጋ መሪ አብዮት አህመድ አሊ እርስበርስ እያባላን ነው፤ ኦርቶዶክሳውያንን በመላዋ ኢትዮጵያ እየጨረሰን ነው፣ ሁሉም ኦርቶዶክስን ማጥፋት ነው የሚሻው። እስስቱ አብዮት አህመድ የራሱን እስኪያዘጋጅና እስኪያመቻች ድረስ እያታለለ/እያጭበረበረ ይሳለቅብናል ያለው፤ ግን ጊዜው አጭር ነው እሱም ነገ ይበላል፤ እግዚአብሔር እስከተወሰነ ጊዜ እንዲያጸዳ ስለሚፈልገው ነው እንጂ እሱም አሟሟቱ የከፋ ነው፤”

ዲያቆን ቢንያም ፍሬው

እንኳን አብሮ አደረሰን! አይዞን!✞

_________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አንድ ጌታ፣ አንድ ሐይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት | ምሥጢረ ጥምቀት – ጥምቀት አንዲት ናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 19, 2022

ጥምቀት የማትደገም፣ የማትከለስ አንዲት ናት፡፡ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ልጅነትን የምናገኝባት ጥምቀት የማትደገምና የማትከለስ አንዲት ብቻ መሆንዋን ሲያስተምር ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት…አለ›› ብሏል (ኤፌ.4÷5)፡፡

ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ሊቃውንትም ‹‹ኃጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡›› ብለው አስተምረዋል፡፡ በዚህ የተነሣ ኣርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድ ጊዜ ያጠመቀችውን ድጋሚ አታጠምቅም፡፡ ነገር ግን አማናዊቷን ጥምቀት ቀድሞም አልፈጸሙምና ከቤተ ክርስቲያናችን ውጪ በሌላ በማናቸውም ሁኔታ ‹‹ተጠምቀን ነበር›› የሚሉትን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ሲቀርቡ በሥርዓቷ መሠረት አስተምራ አሳምና ታጠምቃቸዋለች፡፡

በሌላ መልኩ ደግሞ ቀድሞ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ተጠምቆ ኋላ ግን ወደ ሌላ እምነት ቢገባ ተናዞ (ንስሐ ገብቶ) በማየ ጸሎት (መጽሐፈ ቄደር ተደግሞለት) ይረጫል እንጂ ድጋሚ አይጠመቅም፡፡ ቄደር የንስሐ እጽበት ነው፡፡ ያደፈ ልብስ እንደሚታጠብ ሁሉ ይህም ሰው ንጽሕት እምነቱን አሳድፏልና ከኃጢአቱ ለመታጠቡ ምልክት ይሆን ዘንድ በማየ ጸሎት ይታጠባል፡፡

ጥምቀት የማይደገምበት ምክንያት

ሀ. ጥምቀት ከእግዚአብሔር ዳግም የምንወለድበት ምሥጢር ነው፡፡

የሥጋን ልደት ስንመለከት ሰው ከእናቱ ማኀፀን የሚወጣው (የሚወለደው) አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔርም በእውነት አንድ ጊዜ ወልዶናል፡፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ ብቻ እንጠመቃለን፡፡

ለ. ጥምቀት ከጌታ ሞትና ትንሣኤ ተሳታፊ የምንሆንበት ምሥጢር ነው፡፡

‹‹በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ በጥምቀትም ደግሞ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ›› (ቈላ.2÷12)፡፡ ጌታ የሞተውና የተነሣው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም እኛ ከእርሱ ጋር የምንቀበረውና የምነሣው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ለምን በውኃ እንጠመቃለን

  • ፩. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በውኃ ነው እኛም እርሱን አብነት በማድረግ በውኃ ልንጠመቅ ይገባናል (ማቴ.3÷13-16)፡፡
  • ፪. ጌታችን ለኒቆዲሞስ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም›› ስላለ እኛም የጌታን ትእዛዝ ለመፈጸም በውኃ እንጠመቃለን (ዮሐ.3÷5)፡፡
  • ፫. ሐዋርያት ከጌታ በተማሩት መሠረት ያጠመቁት በውኃ ነው፡፡ ጴጥሮስም መልሶ ‹‹እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውኃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው? አለ›› (የሐዋ.10÷46ና 47)፡፡ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ አጠመቃቸውም (የሐዋ.8÷28)፡፡
  • ፬. ውኃ የሰውነትን እድፍ እንደሚያጠራ ሁሉ እንዲሁም ጥምቀት የነፍስን እድፍ ያስወግዳል ያነጻል፡፡
  • ፭. ውኃ መልክን ያሳያል እኛም በውኃ በመጠመቅ የሥላሴን ምሥጢር በዓይነ ኅሊናችን እናያለን፡፡
  • ፮. በጥንተ ፍጥረት መንፈስ እግዚአብሔር በውኃ ላይ ረብቦ እንደነብር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ይገልጻል፡- ‹‹የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር›› (ዘፍ.1÷2)፡፡ እንዲሁም በውኃ፣ በሕይወትና በመንፈስ ያለውን ግንኚነት ማስተዋል ይገባል፡፡ ልዑለ ባሕርይ ጌታ በነቢዩ በኤርምያስ አንደበት እንዲህ ሲል ተናግራል ‹‹ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች አድርገዋልና እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል…›› (ኤር.7÷13)፡፡
  • ፯. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ትምህርቱ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ አስተምሯል (ዮሐ.7÷39)፡፡ ለሳምራዊቷ ሴትም ‹‹እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፡፡ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት›› (ዮሐ.4÷14)፡፡
  • ፰. ከላይ በተገለጸው መሠረት ውኃ የሕይወት ምልክት ነው፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደምናነበው ውኃ ለሰማያዊው መንግሥት፣ ለዘላለም ሕይወት ምሳሌ ሆኖ ተገልጿል፡፡ ‹‹እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር አንደተተከለች ፍሬዋን በየጊዜው እንደምትሰጥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል›› (መዝ. 1÷3) እና የመሳሰሉትን ሁሉ እናገኛለን (ራእይ.2÷16፣ 22÷1፣ 22÷17)፡፡
  • ፱. እንግዲህ ውኃ ከክፉ ኀሊና ለመንጻታችንና ለመቀደሳችን ማረጋገጫ መሆኑን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል አስተምሯል፡- ‹‹ከክፉ ሕሊና ለመነጻት ልባችንን ተረጭተን፣ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን፣ በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ›› (ዕብ.10÷22)፡፡
  • ፲. ለንጊኖስ የተባለው ሐራዊ (ወታደር) የጌታን ቀኝ ጎን በጦር በወጋው ጊዜ ትኩስ ደምና ውኃ ባንድነት ፈሷል (ዮሐ. 19÷34)፡፡
  • ፲፩. ደሙ ለመጠጣችን፣ ውኃው ለጥምቀታችን መሆኑን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ይህንንም ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ገልጾታል ‹‹በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው፡፡ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በውኃና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም፡፡… የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም፡፡… የሚመሰክሩተ መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፡፡ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ›› (1ዮሐ.5÷6-8)፡፡
  • ፲፪. ውኃ በሁሉም ቤት ይገኛል፡፡ በሀብታሙም በድኃውም ጥምቀትም ላመነ ሁሉ የተፈቀደ መሆኑን ለማጠየቅ በውኃ ሆኗል፡፡ ስለዚህም በውኃ ብቻ እንጠመቃለን፡፡ ሥርዓተ ጥምቀቱን የሚፈጽመው ካህን አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ሲባርከው ውኃው ተለውጦ በዕለተ ዓርብ ከጌታችን ቀኝ ጐን የፈሰሰውን ውኃ ይሆናል፡፡

ኣከባብራ በዓል ጥምቀት ኣብ ዓብይ አዲ ❖

💭 “ምስጢራዊቷ የዓብይ አዲ ከተማ | ጂኒው ከመስጊዱ ፈለቀ ፥ ግራኝ በአላሙዲን ተመለመለ | የሉሲፈር ኮከብ”

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

✞✞✞ረቡዕ ፥ ሚያዝያ ፲፱/19 ፪ሺ፫ /2003 .(ቅዱስ ገብርኤል ፥ ትንሣኤ ማግስት)✞✞✞

👉 ልክ እንደ ዛሬው ያኔም ቅዱስ ገብርኤል በረቡዕ ዕለት ነበር የዋለው፤ ዋው!

ዘንድሮ ሁለት መቶ ክርስቲያን የጽዮን ልጆች በሉሲፈራውያኑ ወኪል በግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ተጨፍጭፈው የሰማዕትነት አክሊል በተቀዳጁባት በ ዓብይ አዲ ከተማ ከ ፲/10 ዓመታት በፊት ብዙ ምስጢራዊ ነገሮች ተከስተዋል። ይህ ተሽከርካሪ ነፋስ ጋኔን (አቧራ) ከዚህ መስጊድ ከተላከ በኋላ ልክ በዓመቱ ግራኝ አብዮት አህመድ + የግብጹ ሙርሲ + ሸህ መሀመድ አላሙዲን + ፕሬዚደንት ባራክ ሁሴን ኦባማ ብጹእ አቡነ ጳውሎስን እና ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ገደሏቸው።

💭 በሁለተኛው ክፍል ስለ ኮከቡ እና ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚ ሃገር ስለ ቱርክ የቀረበውን መረጃ በጥሞና እንከታተለው። በጣም ጠቃሚ ነውና!

👉 ሉሲፈር የዋቄዮአላህ ባሪያውን ሙስሊሙን አብዮት አህመድ አሊን በዚህ ከአብይ አዲ መስጊድ በወጣው ጋኔን ቀብቶታልን?

😈 ከቀናት በፊት ግራኝ ለቱርኩ ኤርዶጋን የሚከተለውን መናዘዙን የማውቃቸው ቱርኮች አውስተውኛል፤

እኔ ሙስሊም ነኝ፣ ለእስልምና ጉዳይ የቆምኩ አህመድነኝ፣ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ሙስሊሞቹ ቱርኮችንና ግብጾችን ወንድሞቻችንን ያዋረዷቸውን ተዋሕዶ ትግራዋይንና አማራዎችን እርስበርስ እያባላሁ በመጨረስ ኢትዮጵያን አፈራርሰን ልክ እንደ አፍጋኒስታን ታሊባኖች የእስላማዊቷን ኦሮሚያ ኤሚራት ለመመስረት ቆርጬ ተንስቻለሁ፤ ታሪካዊዎቹን ቦታዎችን በማውደም ላይ ነኝ፣ ታሪካዊ የሆኑት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችንም በማዘጋትና በምትካቸውም የእስላማዊቷን ኦሮሚያ ኤሚራት ኤምባሲዎች ለመተካት አቅደናል፤ ይህ እድል እንዳያመልጠን የግራኝ ቀዳማዊን መሸነፍና ሞት አብረን እንበቀል፣ ድሮንህን ስጠኝ፣ ገንዘብ ካስፈለገም ከሸህ አላሙዲን ይገኛል‘” በማለት የኢትዮጵያ ቀንደኛ ታሪካዊ ጠላት የሆነችውን የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክን ከአምስት መቶ ዓመታት በኋላ ፀረክርስቲያን ጂሃዷን እንድትደግመው በር ከፍቶላታል።

ጂኒው አብይ ከመስጊዱ በወጣው ጋኔን ልክ በቅዱስ ገብርኤል ዕለት ተጠመቀ ፥ በዓመቱም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን እና ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ከእነ አላሙዲን እና ኦባማ ጋር ሆኖ በመግደል እራሱን በሉሲፈራውያኑ አስመረጠ። የተቀባው በዓብይ አዲ ጋኔን ነውን?

____________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አምኖ ያልተጠመቀ አይድንም | በአክሱም ጽዮን ላይ የዘመተ ሁሉ እንደ አህዛብ አልዳንም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 18, 2022

💭 አንድ ጌታ፣ አንድ ሐይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት | ኢትዮጵያ ላይ የሚኖረው የተጠመቀ ብቻ ነው

✞✞✞[ኤፌ. ፬ ፥ ፭]✞✞✞

በጥምቀት-ያልተጠመቀ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስምና

[፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ ፭፥፰]

ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።”

💭 በእነዚህ ቀናት ቀንደኛው የኢትዮጵያ፣ የተዋሕዶ ክርስትናዋ እና የጥምቀቱ ጠላት ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ጥምቀቱን ከኢትዮጵያዊው ለማራቅና ለመንጠቅ ብዙ ዲያብሎሳዊ ተንኮሎችን በመሥራት ላይ ይገኛል። እንደተለመደው በመቀበጣጠር፣ “ጽዮናዊውን የአጼ ዮሐንስን ቀይ፣ ቢጫና አረንጓዴ ሰንደቅ መያዝ ክልክል ነው! ወዘተ” በማለት፤ እንዲሁም የአሜሪካ ልዑካንን ወደ አዲስ አበባ በመጋበዝ።

ልብ እንበል፤ ባለፈው የጌታችን ልደት ዕለት አሰቃቂ የድሮን ጭፍጨፋዎችን በትግራይ ያካሄደው የአሜሪካ ልዑካን ከአዲስ አበባ በተመለሱ እና ግራኝ ከፕሬዚደንት ባይድን ጋር በስልክ በተነጋገረበት ማግስት ነው? አሁንስ ጽዮናውያንን በኢትዮጵያዊነታቸው ተስፋ ቆርጠው እንዲገነጠሉና የኦሮሚያ እስላማዊት ካሊፋት ምስረታ ሕልሙን ለማሳካት በወገኖቼ ላይ የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ድሮኖችን በመጠቀምን ጭፍጨፋውን ይቀጥልበት ይሆን?

እንኳን ለጥምቀቱ አደረሰን!

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጥምቀት በታንዛኒያ | 200 ሙስሊሞች በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተጠመቁ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 2, 2020

እስኪ ተመልከቱት፦ በአፍሪቃ አፍሪቃውያን የኦሮቶዶክስ ክርስትና እምነትን መቀበል ያልማሉ (ምን ያህል ፍላጎት እንዳላቸው እኔ በግሌ ያየሁት ነው) ኦሮሞ ነንየሚሉት ከሃዲዎች ግን ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን ያግታሉ፣ ይገድላሉ፣ ቤተ ክርስቲያናቸውን ያቃጥላሉ፣ ታቦታቸው ላይ ድንጋይ ይወረውራሉ፣ ሰንድቃቸውን ይቀዳሉ፣ ባሕልና ቋንቋንቋቸውን ለማጥፋት ይታገላሉ። ወደ ታንዛኒያ መላክ ይኖርባቸዋል፤ ለነገሩማ የፈለሱትም ከዚያው አካባቢ አይደል።

በመላው አፍሪቃ ወንጌልን የመስበክና አፍሪቃውያንንም የማጥመቅ ኃላፊነት መውሰድ የነበረባትማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነበረች።

230 Africans, Many Former Muslims, Baptized In Tanzania

Another mass Baptism was celebrated in Africa, this time in the eastern Tanzanian city of Morogoro, with 230 indigenous souls being united to Christ in the washing of regeneration (Tit. 3:5).

The service was celebrated by Metropolitan Dimitrios of Irinopolis on Sunday, January 26 at the Church of Sts. Arsenios and Paisios, which, built in 2005, was the first church in the world dedicated to St. Paisios the Athonite, reports Romfea.

Among the newly-illumined were many former Muslims.

Before receiving the Sacraments of Baptism and Chrismation, the faithful Africans underwent systematic catechization with Monk Thaddeus from the Monastery of Tharri in Rhodes and approached the font and the chalice with great joy and reverence.

Source

________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

የፀረ-ክርስቶሱ ዓለም፡ “ሥርዓተ ጥምቀቱን” ለመንጠቅ፡ የግሪክ ኦርቶዶክስ አባቶችን በማንቋሸሽ ላይ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 14, 2018

በቆጵሮስ ደሴት፡ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ተከታዮች፡ ልጆቻቸውን በጠበቀ መንፈሳዊ ሥነስርዓት ያጠምቃሉ። በዚህ መልክ ለሁለት ሺህ ዓመታት ያህል ያጠመቋቸው ህፃናት ያው ስንቱን መከራና ስቃይ አልፈው የዛሬው ዘመን ላይ ደርሰዋል።

የጥምቀትን ጥቅም ያውቃሉ፤ ጥምቀት የማትደገም፣ የማትከለስ አንዲት ናትና። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ልጅነትን የምናገኝባት ጥምቀት የማትደገምና የማትከለስ አንዲት ብቻ መሆንዋን ሲያስተምር ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት…አለ›› ብሏል (ኤፌ.÷)። ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ሊቃውንትም ‹‹ኃጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡››ብለው አስተምረዋል።

አሁን በሜዲያና በማህበረሰባዊ ድኽረ ገጾች ላይ፡ ሥርዓተ ጥምቀቱን በማጥላላት፡ “ተመለከቱ! ኦርቶዶክሶች ሕፃናትን በሚረብሽ መልክ ያጠምቃሉ” እያሉ የአውሬው ደቀመዛምርት በመለፈፍ ላይ ይገኛሉ። በዚህ ዘመን የምንጠብቀውና፡ ከፀረክርስቶሱ ወታደሮች ጋር የመፋለሚያ መስኮቹ ከሆኑት አንዱ አንዱ ሥርዓተ ጥምቀት ነው። በአንድ በኩል ለሰው ልጅ አሳቢዎችና ተቆርቋሪዎች ሆነው ለመታየት ይሻሉ፤ በሌላ በኩል ግን ለልጆቻቸው ሥርዓተ ጥምቀትን በመንፈግ፣ ብሎም ጥሩውን ከመጥፎ ሳይለዩ ያለ እመንት እንዲያድጉ በማድረግ የሚሠሩት ተወዳዳሪ የሌለው ኃጢአትና ግፍ በጭራሽ አይታያቸውም። እንዲያውም ቀዳዳ እየፈለጉ ክርስትናን ማጥቃት ይመርጣሉ።

በተለይ የእንግሊዙ DailyMail ጋዜጣ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሌታም የሆነ ጽሑፍ ይዞ ወጥቷል፤ እጅግ በጣም ብዙ አንባቢዎችም ዘግበዋል፤ 95 % የሚሆነው ከአውሬው አፍ የወጣ ነው። (https://addisabram.wordpress.com/ )

የሚገርመው፡ የእንግሊዟ ንግሥት ኤልሳቤጥ ባለቤት፡ ልዑል ፊሊፕ በግሪክ ተወልደው አድገዋል፤ በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን የተጠመቁና አጥባቂ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እንደሆኑም ይነገርላቸዋል።

DailyMail

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የምሥራች! የምሥራች | ቅዱስ ፊሊጶስ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ/ በጅሮንድን ያጠመቀበት ገንዳ ተገኘ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 2, 2018

ይህ እጅግ በጣም ትልቅ ግኝት ነው፤ እልልል! እንበል ወገኖች፤ በጥምቀት ማግስት ይህን መሰል ዜና!!!

በባይዛንታይን ዘመን የተሠሩ መጠመቂያ ገንዳዎች እና ፏፏቴ በእስራኤል ውስጥ ተገኝተዋል

ሚስጥራዊ አርኪኦሎጂስቶች የ 1,500 አመት እድሜ ያላቸው የውኃ ማጠራቀሚያዎች እና በጥንታዊው የክርስትና ቦታ ምስሎች ያጌጡ ድንቅየፏፏቴ ኮረብታዎች አግኝተዋል።

በኢየሩሳሌም የሚገኙ አርኪኦሎጂስቶች የክርስትና እምነት እጅግ ታዋቂ ከሆኑት ባሕረ ጥምቀቶች መካከል አንዱ የሆነውን የ 1,500 ዓመታት የውኃ ገንዳ እና የፏፏቴ ውኃ አግኝተዋል

የውኃ ማጠራቀሚያው በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተገለጸ ቁልፍ ታሪክ ሆኖ ያገለግል የነበረ ሲሆን ሐዋርያው ፊሊፖስ ኢትዮጵያዊን ጃንደረባ/ በጅሮንድን ያጠመቀበት ገንዳ ነው።

ቦራውና ቅርጻ ቅርጾ የሚገኙት በኢየሩሳሌም ኢንያን ሐና አውራጃ ነው፣ ይህም በይሁዳ ኮረብታዎች ሁለተኛውን ደረጃ የያዘ ነው።

ኢንያን ሐና አካባቢ በአይሁድ ባህል አቅራቢያ በአይሁድ መሐንዲሶች ተገኝተዋል.

ውሃው ገንዳ ለመስኖ ለእጥበት ለመሬት ገጽታ ወይም ምናልባትም ጥምቀት ሥነ ሥርዓቶች ያገለግል ነበር።

አርኪኦሎጂስቶች በ 2012 . እስከ 2016 . ድረስ ቦታውን በቁፋሮ ያገኙት ሲሆን፤ ግን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ላይ ነው ለሕዝብ ይፋ ሊሆን የበቃው።

አዳዲሶቹ ገንዳዎች ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከ4ኛው እስከ 6ኛው ክፍለ ዘመን ባሉት ጊዚያት የተገነቡ ናቸው።

ይህ በባይዛንታይን ዘመን የተገነባው ገንዳ በተለያዩ ምስሎች ሸበረቀ ድንቅፏፏቴ ወደ ማጠራቀሚያ ጣቢያዎች ይጓታል::

የውኃ ማጠራቀሚያ በኢየሩሳሌም ውስጥ ውስጥ የመጀመሪያው እንደሆነ የሳይንስ ሊቃውን ይናገራሉ

ሳይንቲስቶቹ እንደገለጹት, ይህ ገንዳ 3000 ዓመታት በፊት፣ በመጀመሪያው የቤተ መቅደ ዘመን የተገነባ የንጉሳዊ ቤተሰብ ንብረት ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ።

ሳይንቲስቶች እንደገለጹት ኢንያን ሐና በሚገኘው ፏፏቴ ውስጥ የኒምፍ ምስሎች የተቀረጹ ሲሆን በኢየሩሳሌም ውስጥ የመጀመሪያው ዓይነትመሆኑ ነው።

የእስራኤላውያን ቅርሶች ባለሥልጣን በኢንያን ሐና አካባቢ በይሁዳ ቅጥር ግቢ ውስጥ አንድ ምንጭ እና ጥንታዊ ኩሬዎችን አግኝቷል ከኢየሩሳሌም ብዙ የማይርቀው የረፋይም ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ አካል ነው

በቦታው ላይ የተገኘ የ 2,400 ዓመታት እድሜ ያለው ዓምድ ግቢው የንጉሣዊ ንብረት እንደነበር ያመለክታል

ገንዳው በአንድ ወቅት ሰፊ በነበረው ግቢ ውስጥ የነበረውን አንድ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጥምቀተ ባሕር ያገለግል ነበር።

ባለሙያዎቹ ቦታውን እንደገና ወደ ቀድሞ ሁኔታው እንዲመለሱ ለማድረግ በመቻላቸው ፏፏቴው በሥራ ላይ ነው

ገንዳው ወይም ጥምቀተ ባሕሩ በጣም አስገራሚ የሆነ ግኝት ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።

ኢንያን ሐና ቅዱስ ፊሊፖስ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ/ በጅሮንድን ያጠመቀበት ቦታ ነው ተብሎ በሰፊው ይታመናልይህም የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ጅማሬ ያመለክታል

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ/ በጅሮንድ መጠመቂያ ገንዳ መሆኑ ከተረጋገጠ ይህ ቦታ ክርስትናን በማሰራጨቱ ረገድ ዘንድ ቁልፍ ሚና ከተጫወቱት ድርጊቶች መካከል አንዱ ይሆናል

የኢየሩሳሌም አውራጃ አርኪዎሎጂ ባለሞያ የሆኑት ዩቫርስ ባሮክ እንደገለጹት የተገኙበትን ቦታ ለይቶ ማወቅ በርካታ ትውልዶችን መስዋዕት የጠየቀና፡ በክርስቲያናዊ ሥነ ጥበብ በኩልም የተለመደ ነገር ለመሆን መብቃቱንም ተናግረዋል ።

ከኩሬው እና ከፏፏቴው በተጨማሪ የሳይንስ ሊቃውንት በቦታው ላይ የተለያዩ እንቁራሪቶችን አግኝተዋል የሸክላ የብርጭቆ የጣራ ግድግዳዎችን፣ ሳንቲሞችን እና በርካታ ቀለም ያላቸው ቅርፊቶች አግኝተዋል። በበርካታ ቀለማት የተሰሩ ጥንታዊ ቅርጻ ቅርጾችን ጨምሮ ያልተለመዱ ትናንሽ መጫወቻዎችንም አግኝተዋል።

የሳይንስ ሊቃውን ግሪክ ገንዘብ ድራክማዎችንም አግኝተዋል።

እነዚህ ነገሮች ቦታው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 4 ኛው እና 6 ኛ ክፍለ ዘመን በደንብ ይንቀሳቀስ እንደነበር የሳይንስ ሊቃውንቱ አውስተዋል።

[የኢንያን ሐና] አሁንም ድረስ ክርስቲያኖችን ያገለግላል፤ በተለይ የአርሜኒያ እና የኢትዮጵያ ዓብያተ ክርስቲያናት የሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችን በዚህ ቦታ ማከናወናቸው ያለምክኒያት አለመሆኑን እስራኤላዊው ዩቫል ባሮክ በተጨማሪ ጠቁመዋል።

ምንጭ

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፰፥፳፮፡፵

፳፮ የጌታም መልአክ ፊልጶስን። ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ አለው።

፳፯ ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤

፳፰ ሲመለስም በሰረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር።

፳፱ መንፈስም ፊልጶስን። ወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ አለው።

ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና። በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን? አለው።

፴፩ እርሱም። የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል? አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው።

፴፪ ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፥ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

፴፫ በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና ትውልዱንስ ማን ይናገራል?

፴፬ ጃንደረባውም ለፊልጶስ መልሶ። እባክህ፥ ነቢዩ ይህን ስለ ማን ይናገራል? ስለ ራሱ ነውን ወይስ ስለ ሌላ? አለው።

፴፭ ፊልጶስም አፉን ከፈተ፥ ከዚህም መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌልን ሰበከለት።

፴፮ በመንገድም ሲሄዱ ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም። እነሆ ውኃ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድር ነው? አለው።

፴፯ ፊልጶስም። በፍጹም ልብህ ብታምን፥ ተፈቅዶአል አለው። መልሶም። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ አለ።

፴፰ ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፥ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ፥ አጠመቀውም።

፴፱ ከውኃውም ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ነጠቀው፤ ጃንደረባውም ሁለተኛ አላየውም፥ ደስ ብሎት መንገዱን ይሄድ ነበርና።

ፊልጶስ ግን በአዛጦን ተገኘ፥ ወደ ቂሣርያም እስኪመጣ ድረስ እየዞረ በከተማዎች ሁሉ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ምሥጢረ ጥምቀት – ጥምቀት አንዲት ናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 18, 2018

ጥምቀት የማትደገም፣ የማትከለስ አንዲት ናት፡፡ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ልጅነትን የምናገኝባት ጥምቀት የማትደገምና የማትከለስ አንዲት ብቻ መሆንዋን ሲያስተምር ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት…አለ›› ብሏል (ኤፌ.4÷5)፡፡ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ሊቃውንትም ‹‹ኃጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡››

ብለው አስተምረዋል፡፡ በዚህ የተነሣ ኣርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድ ጊዜ ያጠመቀችውን ድጋሚ አታጠምቅም፡፡ ነገር ግን አማናዊቷን ጥምቀት ቀድሞም አልፈጸሙምና ከቤተ ክርስቲያናችን ውጪ በሌላ በማናቸውም ሁኔታ ‹‹ተጠምቀን ነበር›› የሚሉትን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ሲቀርቡ በሥርዓቷ መሠረት አስተምራ አሳምና ታጠምቃቸዋለች፡፡

በሌላ መልኩ ደግሞ ቀድሞ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ተጠምቆ ኋላ ግን ወደ ሌላ እምነት ቢገባ ተናዞ (ንስሐ ገብቶ) በማየ ጸሎት (መጽሐፈ ቄደር ተደግሞለት) ይረጫል እንጂ ድጋሚ አይጠመቅም፡፡ ቄደር የንስሐ እጽበት ነው፡፡ ያደፈ ልብስ እንደሚታጠብ ሁሉ ይህም ሰው ንጽሕት እምነቱን አሳድፏልና ከኃጢአቱ ለመታጠቡ ምልክት ይሆን ዘንድ በማየ ጸሎት ይታጠባል፡፡

ጥምቀት የማይደገምበት ምክንያት

. ጥምቀት ከእግዚአብሔር ዳግም የምንወለድበት ምሥጢር ነው፡፡

የሥጋን ልደት ስንመለከት ሰው ከእናቱ ማኀፀን የሚወጣው (የሚወለደው) አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔርም በእውነት አንድ ጊዜ ወልዶናል፡፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ ብቻ እንጠመቃለን፡፡

. ጥምቀት ከጌታ ሞትና ትንሣኤ ተሳታፊ የምንሆንበት ምሥጢር ነው፡፡

‹‹በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ በጥምቀትም ደግሞ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ›› (ቈላ.2÷12)፡፡ ጌታ የሞተውና የተነሣው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም እኛ ከእርሱ ጋር የምንቀበረውና የምነሣው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ለምን በውኃ እንጠመቃለን

  1. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በውኃ ነው እኛም እርሱን አብነት በማድረግ በውኃ ልንጠመቅ ይገባናል (ማቴ.3÷13-16)፡፡
  2. ጌታችን ለኒቆዲሞስ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም›› ስላለ እኛም የጌታን ትእዛዝ ለመፈጸም በውኃ እንጠመቃለን (ዮሐ.3÷5)፡፡
  3. ሐዋርያት ከጌታ በተማሩት መሠረት ያጠመቁት በውኃ ነው፡፡ ጴጥሮስም መልሶ ‹‹እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውኃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው? አለ›› (የሐዋ.10÷4647)፡፡ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ አጠመቃቸውም (የሐዋ.8÷28)፡፡
  4. ውኃ የሰውነትን እድፍ እንደሚያጠራ ሁሉ እንዲሁም ጥምቀት የነፍስን እድፍ ያስወግዳል ያነጻል፡፡
  5. ውኃ መልክን ያሳያል እኛም በውኃ በመጠመቅ የሥላሴን ምሥጢር በዓይነ ኅሊናችን እናያለን፡፡
  6. በጥንተ ፍጥረት መንፈስ እግዚአብሔር በውኃ ላይ ረብቦ እንደነብር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ይገልጻል፡– ‹‹የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር›› (ዘፍ.1÷2)፡፡ እንዲሁም በውኃ፣ በሕይወትና በመንፈስ ያለውን ግንኚነት ማስተዋል ይገባል፡፡ ልዑለ ባሕርይ ጌታ በነቢዩ በኤርምያስ አንደበት እንዲህ ሲል ተናግራል ‹‹ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች አድርገዋልና እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል…›› (ኤር.7÷13)፡፡

    ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ትምህርቱ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ አስተምሯል (ዮሐ.7÷39)፡፡ ለሳምራዊቷ ሴትም ‹‹እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፡፡ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት›› (ዮሐ.4÷14)፡፡

    ከላይ በተገለጸው መሠረት ውኃ የሕይወት ምልክት ነው፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደምናነበው ውኃ ለሰማያዊው መንግሥት፣ ለዘላለም ሕይወት ምሳሌ ሆኖ ተገልጿል፡፡ ‹‹እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር አንደተተከለች ፍሬዋን በየጊዜው እንደምትሰጥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል›› (መዝ. 1÷3) እና የመሳሰሉትን ሁሉ እናገኛለን (ራእይ.2÷1622÷122÷17)፡፡እንግዲህ ውኃ ከክፉ ኀሊና ለመንጻታችንና ለመቀደሳችን ማረጋገጫ መሆኑን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል አስተምሯል፡– ‹‹ከክፉ ሕሊና ለመነጻት ልባችንን ተረጭተን፣ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን፣ በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ›› (ዕብ.10÷22)፡፡

  7. ለንጊኖስ የተባለው ሐራዊ (ወታደር) የጌታን ቀኝ ጎን በጦር በወጋው ጊዜ ትኩስ ደምና ውኃ ባንድነት ፈሷል (ዮሐ. 19÷34)፡፡ ደሙ ለመጠጣችን፣ ውኃው ለጥምቀታችን መሆኑን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ይህንንም ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ገልጾታል ‹‹በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው፡፡ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በውኃና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም፡፡… የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም፡፡… የሚመሰክሩተ መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፡፡ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ›› (1ዮሐ.5÷6-8)፡፡
  8. ውኃ በሁሉም ቤት ይገኛል፡፡ በሀብታሙም በድኃውም ጥምቀትም ላመነ ሁሉ የተፈቀደ መሆኑን ለማጠየቅ በውኃ ሆኗል፡፡ ስለዚህም በውኃ ብቻ እንጠመቃለን፡፡ ሥርዓተ ጥምቀቱን የሚፈጽመው ካህን አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ሲባርከው ውኃው ተለውጦ በዕለተ ዓርብ ከጌታችን ቀኝ ጐን የፈሰሰውን ውኃ ይሆናል፡፡

ምንጭ

+++እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን!+++

______

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Timket Festival 2016

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 20, 2016

Where: Addis Ababa, Gondar, Lalibela Ethiopia

Timket is a religious festival celebrated with much zeal in Addis Ababa, Gondar, and Lalibela in Ethiopia. It is also spelled as Timkat or Timqat. The festival is the Ethiopian Orthodox celebration of Epiphany and venerates Christ’s baptism in the River Jordan. Although the festival is observed by orthodox Christians all over the world, in Ethiopia it takes on a special significance as it is the most colourful event of the year in the country. The most relevant symbol of the festival is colourful embroidered umbrellas that protect the sacred Tabot and the priests carrying the Tabot.

Timket Festival Celebrations

Timket festival is celebrated to commemorate the divine ritual of the baptism of Christ in the Jordan River. The celebrations start from the eve of the festival which is on 18th January at 2 pm local time with traditional horns that herald the celebrations with colourful processions and ceremonies. The main ceremony commences with the priest solemnly carrying the Tabot which is a model of the Ark of the Covenant, reverently wrapped in rich silk cloth to the nearby stream at around 2am on 19th January. The Tabot is a representation of Jesus as the Messiah when he came to the Jordan River for baptism. The Holy Ark is immersed in the water by one priest whilst the other chants some prayers. Once the Ark is baptised, the priest then blesses the water body and sprinkles some of the blessed water on the devotees. Thereafter the Holy Ark is carried back to its church amidst lots of chanting, music, and dancing.

Tips for Timket Festival

Travellers can enjoy the festivities of Timket Festival at Addis Ababa, Gondar, or Lalibela.

Although the festival is celebrated at Addis Ababa, Lalibela, and Gondar in Ethiopia and each one has its own charm, the festivities at Addis Ababa are tourist friendly as Addis Ababa offers variety of facilities to tourists.

Pilgrims need to be careful of touts and pickpockets and not carry any valuable items with them while attending the festivities.

If you are attending the festivities in Gondar do make sure to visit the Church of Debre Berhan Selassie renowned for its finest art in Ethiopia.

Downtown Gondar with its Italian-inspired architecture, shops, and eating joints, is another interesting place you can explore once the festivities are over.

If you happen to be in Addis Ababa then you can shop for traditional crafts or catch some art shows or visit various museums in the city.

Since it is cold in January it is advisable to bring some woollens along with you.

Source

The Sacrament of Baptism in the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

EthiopiaTimket

A baby boy is baptized 40 days after he is born. A baby girl is baptized 80 days after birth. If a baby is sick and may die baptism takes place immediately.

Babies are anointed with oil to “undo the works of devils and their magic,and so become an anointing for faith in Christ.”

Babies are baptized naked because, “undressing the child reminds us of the nakedness of Adam and Eve when they obeyed satan and disobeyed the commandment of God, so they were put to shame before Him and hid from Him when they realized their nakedness. Such is what sin and satan do to human beings, they strip them from all virtues and the protection of grace, and hence put them to shame before others.”

Continue reading

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: