Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Orthodox Tewahedo’

ዓርብ ስቅለት በደብረ ቤቴል አበ ብዙሃን-አብርሃም ገዳም | የማይረሳ መንፈሳዊ ዕለት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2023

✞✞✞ ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) –የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት✞✞✞

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡

ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?” ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡

“ክፉ የሠራ ባይኾንስ ወደ አንተ ባላመጣነውም ነበር” በሚል የሸፍጥ ቃል ሲያጕረመርሙ ጲላጦስ መልሶ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተ ወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት፤” አላቸው፡፡ አይሁድም ኦሪት “ኢትቅትል ብእሴ ጻድቀ ወኀጥአ ኢታኅዩ፤ጻድቅን ሰ ውአትግደል፤ኀጥኡንም ከፍርድ አታድን፤” ትላለችና “እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፤” ብለዋል (ዮሐ. ፲፰፥፳፰-፴፩)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ “በሕጋችን ጻድቀ ባሕርይ ክርስቶስን መግደልአ ይገባንም ሙሉ በሙሉ ጥፋተኞች ነን፤” ሲያሰኛቸው ነው፡፡ በኋላም እርሱ ሞቶ ዓለም ይድን ዘንድዳ ምድር መጥቷልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጥፋቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ ስለዚህም ገርፈው ሰቀሉት፡፡

ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን

ልክ አሁን የሕማማተ መስቀልን ፀሎት አንብቤ እንደጨረስኩ፤ ከጎረቤቴ ሕንጻ ጣራ ላይ ፲፫ ርግቦች ተነስተው በዙሪያዬ አንድ ጊዜና በአንድ ላይ ጅው ብለው በመብረር የተነሱበት ጣራ ላይ ተመልሰው አረፉ። ተገርሜ በመመሰጥ፤ “ምን የሚሉኝ ነገር ሊኖር ይችላል?” የሚለውን ጥያቄ ጠየቅኩ። ፲፫/13ቱ ሕማማተ መስቀል?

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ “የድኅነት ቀን” ይባላል፡

✞ ፲፫ቱ ሕማማተ መስቀል

  • ፩ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
  • ፪ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
  • ፫ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)
  • ፬ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
  • ፭ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
  • ፮ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
  • ፯ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
  • ፰ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
  • ፱ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
  • ፲ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
  • ፲፩ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
  • ፲፪ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
  • ፲፫ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)

✞ ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

  • ፩. ፀሐይ ጨለመ፤
  • ፪. ጨረቃ ደም ኾነ፤
  • ፫. ከዋክብት ረገፉ፤
  • ፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤
  • ፭. አለቶች ተፈረካከሱ፤
  • ፮. መቃብራት ተከፈቱ፤
  • ፯. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩-፶፬)፡፡

✞ ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

  • ፩. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)”፤
  • ፪. “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ”፤
  • ፫. “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው”፤
  • ፬. እመቤታችንን “ሴትዮሆይ፣እነሆ ልጅሽ” ደቀ መዝሙሩንም “እናትህ እነኋት” በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤
  • ፭. “አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ”
  • ፮. “ተጠማሁ”፤
  • ፯. “ዅሉ ተፈጸመ” (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡

ከሰድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ሁኖአል፡፡ ወፍናሠር ክይበርህ ብርሃነ ፀሐይእንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡

ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም “ንሴብሖ ለእግዚአብሔርእየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ምንጭ

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ረቡዕ የምክር ቀን፤ ይሑዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠ | የዘመኑ ይሑዳዎችም ጌታቸውን፣ ሀይማኖታቸውንና ሃገራቸውን ለገንዘብና ለስጋዊ ጥቅም ብለው እየሸጡ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 12, 2023

❖❖❖ የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ስያሜዎች ❖❖❖

  • ሰኞ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ፤ አንጽሖተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ሰኞ።
  • ማግሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን።
  • ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን።
  • ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ።
  • ዐርብ፤ የስቅለት ዐርብ።
  • ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ፡፡

🗣 ለምን የምክር ቀን ተባለ?

ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሑዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ [ማቴ. ፳፮፤፩፡፲፬፣ ማር. ፲፬፤፩፡፪፣ ቁ ፲፤፲፩፣ ሉቃ. ፳፪፤፩፡፮]

💐 የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል

ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ “ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ” ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ነው ረቡዕ የመዓዛ ቀን የተባለው፡፡

😢 የእንባ ቀንም ይባላል

ይህም ይህቸው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ [ማቴ.፳፮፤፮፡፲፫፣ ማር.፲፬፤፫፡፱፣ ዮሐ.፲፪፤፩፡፰] ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡

ይሑዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠ

የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር

ይሑዳ ጌታችንን ለ፴ ዲናር ብሎ መሽጠቱ እንዳለ ሆኖ የዘመኑ ይሑዳዎችም እንዲሁ ጌታቸውን፣ ሀይማኖታቸውን፣ እምነታቸውን፣ ሃገራቸውን፣ መንፈሳዊ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን ለገንዘብና ለስጋዊ ጥቅም ብለው እየሸጡት ነው፦

ቅዱስ መጽሐፉ፦

ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ #ከሃይማኖት_ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ። አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ #ከዚህ_ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል። መልካሙን የእምነት ገድል #ተጋደል፥ [[[[መልካሙን ገድል #ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ #ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም። ፪ጢሞ᎐፬፥፯]]] የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት #ያዝ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን #ጠብቅ። (፩ጢሞ᎐፮፥፲፩፲፪(፲፬))እንግዲህ እኔ ወደዚህች ዓለም የመጣሁት ራቁቴን ነውና እንዲሁም የምሄደውም ራቁቴን ነውና ጌታዬን በብር አልለውጠውም! እናቴ ማርያምን ለገንዘብ አልከዳትም! በዚህች ምድር ላይ ምንም ምን አያስፈልገኝምና እኔ ክርስቶስ አለልኝ።

ድንኳን የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና። በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና፥ ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም።” [፪ቆሮ᎐፭፥፩]

ለብርሃነ ትንሣኤው አምላካችን በሰላም ያድርሰን።

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Jerusalem Mount of Olives: Ethiopian Christians Celebrate the 5th Sunday of the Great Lent | ደብረ ዘይት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 19, 2023

❖❖❖

የዐቢይ ጾም ፭ተኛ ሳምንት ደብረ ዘይት

የክርስቶስ ዳግም ምጽአት መቼ ነው የሚሆነው?

እንኳን ለደብረዘይት በዓል አደረሰን!

ደብረ ዘይት በግዕዝ ልሣን ደብረዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት ነው። ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:-ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሰረት ነገረ ምጽአቱን (የመምጣቱን ነገር) እንድናስታዉስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነዉ።

በዚያ ልማድ መሠረት ጌታችን ዓለምን ለማሳለፍ ደግሞ የሚመጣበትን ምልክትና ጠቋሚ ነገር ምን ምን እንደሆነ፣ እርሱ ከመምጣቱ በፊት በዓለም ላይ ምን፥ ምን እንደሚደረግና ምን እንደሚታይ ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ነው። (ማቴ. ፳፬፥፩፡፶፩) ስለ ዓለም ሁሉ ቤዛ ለመሆን በሚሰቀልበት ቀን ዋዜማ ማለት በትልቁ ሐሙስ (ጸሎተ ሐሙስ) በለበሰው ሥጋ የጸለየው ከደብረ ዘይት ጋር ተያይዞ በሚገኘው ቦታ በጌተሴማኒ ነበር። (ማቴ. ፳፮፥፴፮) በኃላ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላም ለደቀመዛሙርቱ እንዲነግሩ ሲልካቸው፥ “ሂዱና ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፥ በዚያም ታዩኛላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው፥” ብሎ የላካቸው በደብረ ዘይት ገሊላ ተብላ ትጠራ ወደ ነበረችው ቦታ ነው። (ማቴ. ፳፰፥፱) ገሊላውያን ወደ ኤየሩሳሌም ሲመጡ በደብረ ዘይት ያርፍ ነበርና እነሱ ሲያርፉባት የነበረችው ቦታ ገሊላ እየተባለች ትጠራ ነበር። መድኃኔዓለም ክርስቶስ የድኅነት ሥራ ፈጽሞ ወደ ሰማይ ያረገው ከዚህ ተራራ ተነሥቶ ነው። (ሐዋ. ፩፥፲፪) ቀደም ብሎም የሆሳእናው የመድኃኔዓለም አስደናቂ ጉዞ የተጀመረው ከደብረ ዘይት ሥር ነበር። (ማቴ. ፳፩፥፩፡፲፮)

ደብረዘይት ምሳሌነቱ ይህች ቤተክርስቲያን ናት፣ ደብረዘይት የኦርቶዶክሳውያን ተራራ፣ የእግዚአብሔር ቃል የሚነገርባት፣ መሠረታዊ ሐይማኖት የምንማርባት፣ ካሕናት የሚሠፍሩባት፣ ምዕመናን የሚገናኙባት፣ እግዚአብሔርን የምንወድ ሁሉ የምንሰባሰብባት አማናዊት ደብረ ዘይት ቤተክርስቲያን ናት።

ትልቁ መሠረተ ልማት የሰው ልጅ ነው፤ ቁሳቁሱን፣ ድንጋይና ድንጋይ፣ አሸዋና ሲሚንቶ ማቀላቀል አይደለም”

ሰውን ከእግዚአብሔር ከሚለየው አጉል ሰላም ይልቅ ከእግዚአብሔር የማይለየው ጦርነት ይሻላል፤ ስሜታዊ ከሆነና ለቤተ ክርስቲያን ዘለቄታዊ ጉዳት ከሚኖረው ስምምነትና አንድነት ይልቅ ስለ ሐይማኖት መጠበቅ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ የሚኖረውና ለዚህ ሲባል የሚሆን አለመስማማት ይሻላል፡፡” ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

🔥 ኢትዮጵያዊቷን የ ‘ደብረዘይት’ ከተማን ‘ቢሸፍቱ’ በማለት እራሳቸውን ከ ፍዬል ሕዝብ 🐐 የመደቡት ከሃዲዎቹና የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ጋላሮሞዎች የትንቢት መፈጸሚያ ይሆናሉ

Debre Zeit (ደብረ ዘይት): the Ge’ez phrase for Mount of Olives is one of the nine minor feast days of the Lord observed halfway in the fifth week of the great lent. The Ethiopian Orthodox Church celebrates the feast with special consideration based upon the second coming of Christ, which was announced by our Lord on the Mount of Olives. Biblical verses and the hymn of St.Yared pertinent to our Lord’s second coming are read and sung on this day.

The signs of the end times spoken by our Lord will culminate in final judgment and resurrection of the living and dead, believers and unbelievers, righteous and sinners. It is in the knowledge of this truth of the second coming of Christ that all people must repent, believe and baptize in preparation for the arrival of God’ Kingdom.

The church advises us to be spiritually prepared for judgment at any moment and to put our trust in God that He will make everything right in the end. The final phase of the process of redemption began with the first coming of Jesus and will culminate in the events surrounding His Second Coming. There will be a final judgment of all people, living and dead. There will be a final defeat and destruction of all evil — Satan, sin, suffering and death. The kingdom of God will come to its fulfillment at last.

Signs of the end

Jesus, Himself, said no one would be able to predict exactly the end of the time but He informs that many events will occur before the Second Coming and which will be signs that the end is near. There will be wars, famines, earthquakes, false prophets, persecutions and an increase in wickedness, rebellion against God, worship of demons, idolatry, murders, sorceries, sexual immorality, and thefts. (Matthew 24:3-14; Rev. 9: 20). The Gospel of the kingdom must be preached to all nations for a witness to all the nations, and then the end shall come. (Matthew 24:14-28).

Resurrection and Final Judgment

Everyone who has ever lived will be brought back to life in some form to face the final judgment along with those still living. When the end time comes, all who are in the graves will hear His voice and come forth and can be in front of two different Judgment Seats (righteous in the right hand of Jesus and sinners in the left) — those who have done good will be granted eternal life; and those who have done evil, will be condemned to eternal punishment. (Matthew 5:29-30, 25:31-46, Mark 9:43-48 ; John 5:25-29)

While we are still living, or until Jesus comes again, we have every opportunity to repent. We can change our ways from evil to good. But in the end we will all be judged. No one knows about that day or hour, not even the angels in heaven, nor the Son, but only the Father. You do not know when that time will come. The event, when it happens, will be swift and unexpected. So you also must be ready, because the Son of Man will come at an hour when you do not expect Him. (Mark 13:32-33; Matthew 24:43-44)

Be alert! Be Prepared!

The Mount of Olive (Debre Zeit) የደብረ ዘይት ተራራ(ኢየሩሳሌም)

The Mount of Olive is the highest mountain in the suburbs of Jerusalem, 730 metres over the surface of the Mediterranean, comprising of a mountain range with three peaks; The South peak of the Ascension of Christ, around which all the Christian Shrines of the Mount of Olives are gathered. The North peak (Mount Scopus), on which the Hebrew University of Jerusalem is built. The middle peak with the Augusta Victoria Hospital dedicated to the wife of the German Emperor Wilhelm II. In Hebrew it is called Har-Hazeitim, the Mount of Olives. From the 4th century onwards, the Mount of Olives attracted many Christian pilgrims and monks, resulting to the building of houses of prayer, churches and monasteries on it. A Christian travelling book of the 6th century numbers 24 churches and shrines on the Mount.

During the apostasy era, Lord and Savior Jesus Christ taught the disciples about judgment day on the mount of olive. In scripted as in the Holy Bible on (Gospel of Matthew 24:1-44) “Then Jesus went out and departed from the temple, and His disciples came up to show Him the buildings of the temple. And Jesus said to them, “Do you not see all these things? Assuredly, I say to you, not one stone shall be left here upon another, that shall not be thrown down.”

The Signs of the Times and the End of the Age

Now as He sat on the Mount of Olives, the disciples came to Him privately, saying, “Tell us, when will these things be? And what will be the sign of Your coming, and of the end of the age?” And Jesus answered and said to them: “Take heed that no one deceives you. For many will come in My name, saying, ‘I am the Christ,’ and will deceive many. And you will hear of wars and rumors of wars. See that you are not troubled; for all these things must come to pass, but the end is not yet. For nation will rise against nation, and kingdom against kingdom. And there will be famines, pestilences, and earthquakes in various places. All these are the beginning of sorrows.

“Then they will deliver you up to tribulation and kill you, and you will be hated by all nations for My name’s sake. And then many will be offended, will betray one another, and will hate one another. Then many false prophets will rise up and deceive many. And because lawlessness will abound, the love of many will grow cold. But he who endures to the end shall be saved. And this gospel of the kingdom will be preached in all the world as a witness to all the nations, and then the end will come.

The Great Tribulation

“Therefore when you see the ‘abomination of desolation,’ spoken of by Daniel the prophet, standing in the holy place” (whoever reads, let him understand), “then let those who are in Judea flee to the mountains. Let him who is on the housetop not go down to take anything out of his house. And let him who is in the field not go back to get his clothes. But woe to those who are pregnant and to those who are nursing babies in those days! And pray that your flight may not be in winter or on the Sabbath. For then there will be great tribulation, such as has not been since the beginning of the world until this time, no, nor ever shall be. And unless those days were shortened, no flesh would be saved; but for the [c]elect’s sake those days will be shortened.

“Then if anyone says to you, ‘Look, here is the Christ!’ or ‘There!’ do not believe it. For false Christ’s and false prophets will rise and show great signs and wonders to deceive, if possible, even the elect. See, I have told you beforehand. “Therefore if they say to you, ‘Look, He is in the desert!’ do not go out; or ‘Look, He is in the inner rooms!’ do not believe it. For as the lightning comes from the east and flashes to the west, so also will the coming of the Son of Man be. For wherever the carcass is, there the eagles will be gathered together.

The Coming of the Holy Son

“Immediately after the tribulation of those days the sun will be darkened, and the moon will not give its light; the stars will fall from heaven, and the powers of the heavens will be shaken. Then the sign of the Son of Man will appear in heaven, and then all the tribes of the earth will mourn, and they will see the Son of Man coming on the clouds of heaven with power and great glory. And He will send His angels with a great sound of a trumpet, and they will gather together His [d]elect from the four winds, from one end of heaven to the other.

The Parable of the Fig Tree

“Now learn this parable from the fig tree: When its branch has already become tender and puts forth leaves, you know that summer is near. So you also, when you see all these things, know that it is near—at the doors! Assuredly, I say to you, this generation will by no means pass away till all these things take place. Heaven and earth will pass away, but My words will by no means pass away.

No One Knows the Day or Hour

“But of that day and hour no one knows, not even the angels of heaven, but My Father only. But as the days of Noah were, so also will the coming of the Son of Man be. For as in the days before the flood, they were eating and drinking, marrying and giving in marriage, until the day that Noah entered the ark, and did not know until the flood came and took them all away, so also will the coming of the Son of Man be. Then two men will be in the field: one will be taken and the other left. Two women will be grinding at the mill: one will be taken and the other left. Watch therefore, for you do not know what hour your Lord is coming. But know this, that if the master of the house had known what hour the thief would come, he would have watched and not allowed his house to be broken into. Therefore you also be ready, for the Son of Man is coming at an hour you do not expect.

So dear brethren! Just as it is foretold by our Lord Himself about the anonymity of His second coming, it is always better to be ready by repentance and avoid any harmful act for we might not have time to cleanse our sin and face our Lord for judgment because He will say to us, “Depart from Me, you cursed, into the everlasting fire prepared for the devil and his angels: for I was hungry and you gave Me no food; I was thirsty and you gave Me no drink; I was a stranger and you did not take Me in, naked and you did not clothe Me, sick and in prison and you did not visit Me.’”

But it shall always be our desire to be called His children and be said, “Come, you blessed of My Father, inherit the kingdom prepared for you from the foundation of the world: for I was hungry and you gave Me food; I was thirsty and you gave Me drink; I was a stranger and you took Me in; I was naked and you clothed Me; I was sick and you visited Me; I was in prison and you came to Me.’

May God’s mercy be upon us, Amen!

👉 Source: Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ትክክለኛ ተዋሕዷውያን ለተዋሕዶ ልጆች በተለየ መልክ መልካም ያደርጋሉ | እነ ጋንኤል ክስረት ግን በጽዮናውያን ላይ ቦምብ ያስጥላሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 6, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 😇 መድኃኔ ዓለም

✞ “ፍትሕ” እና “አብሮነት” ✞

❖❖❖[፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ ፭፥፰]❖❖❖

ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።”

❖❖❖[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፫፥፲፮]❖❖❖

እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።

✞✞✞ መድኃኔ ዓለም ✞✞✞

✞ እንኳን ለፈጣሪያችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!✞

አዎ! መምህር ወንድማችን ያሉት ትክክል ነው፤ ብዙ ትሕትና፣ ፍቅር እና ይሉኝታ ተገቢ አይደለም፤ አደገኛም ነው። ጽዮናውያን ትሕትናን በማብዛታቸው ነው በሃይማኖት ወንድሞቻቸውና እኅቶቻቸው የሆኑትን ጨምሮ በሁሉም አካላት ዘንድ ይህን ያህል ክህደት፣ በደልና ስቃይ እየተፈጸመባቸው ያለው። በጣም የበዛ ትሕትና እና ፍቅር፤ ቅናትን፣ ምቀኝነትና ጥላቻን ያፈራል። ለሁሉም ነገር እኮ ጊዜ አለው እኮ፤ ሰይጣንን፤ “ባክህ ሂድ! ጥፋ !” ብሎ መቆጣት ተገቢ ነው፤ ጭፍሮቹን ወይ ከእርሱ ነፃ ማውጣት አሊያ ደግሞ አጥብቆ መምታት ተገቢ ነው።

ብዙዎች በሃይማኖት ከሚመሳሰሏቸው ጋር በማበርና አንድ ከመሆን ይልቅ ለጠላቶቻቸው ሲቆሙና ድጋፍ ሲሰጡ ይታያሉ። ይህ ትልቅ ስህተት ነው! የተዋሕዶ ልጅ ከሌሎች ማስቀደም ያለበት እንደርሱ ተዋሕዶ የሆኑትን ወገኖቹን ብሎም በተለየ መልክ መልካም አያያዝ ሊያደርግ የሚገባው ለመድኃኔ ዓለም ልጆች መሆን አለበት ፤ በተለይ በዚህ ከማይመስሉን ሁሉ መራቅ በሚገባን ዘመን። ማንነታቸውን ባለማወቅ ወይም እራሳቸውን በመጥላት፣ ወይም በምዕራቡ ለብ ለብ ለዘብተኝነት ስልተወሰዱና መሃል-ስፋሪያዊ ማንነት በመያዛቸው “ሁሉን አቃፊ” ለመሆን ሲወራጩ ይታያሉ። “ገለልተኝነት”፣ “ሚዛናዊነት” እና “ሁሉን አቃፊነት” ከላይ ቆንጆ የሚመስሉ ነገር ግን ውስጣቸው ከንቱ የሆኑና በዓላማ-የለሽኝነት ላይ የተመረኮዙና በስንፍና ቅመም የተከለሱ የለዘብተኛነት መገለጫ ከኮሮና የከፉ በሽታዎች ናቸው። አንድ ዜጋ ወይ ኢትዮጵያዊ ነው ወይም አይደለም ፥ ወይ ከተዋሕዶ ነው ወይም አይደለም ፥ ወይ ጥሩ ወይም መጥፎ ፥ ወይ በስትግራ ፣ ወይም በስተቀኝ ፥ ወይ በራድ ወይም ትኩስ ፣ ወይ ከእውነት ጋር ወይም ከሐስት ጋር ፥ ወይ ከበጉ ጋር ወይም ከፍየሎች ጋር ፥ ወይ ከመድኃኔ ዓለም ጋር ወይም ከዋቄዮ-አላህ/አዱኛ ፈይሳ ጋር።

አህዛብ የዋቄዮ-አላህ ልጆች ምንም እንኳን ፍቅረ-ቢሶችና ብቻቸውንም ሲቀሩ እርስበርስ የሚነካከሱ ግብዞች ቢሆኑም ቅሉ ለጋራ ግባቸው ሲሉ ግን እርስበርስ ሲተባበሩ ይታያሉ፤ ነገራቸው ሁሉ በጥላቻ ላይ የተመረኮዘ ቢሆንም ግን ለዓላማቸው ሲሉ በአንድነት ይቆማሉ። ዓላማቸው ኢትዮጵያን፣ ተዋሕዶ ባሕሏን፣ ቁንቋዋን እና ሃይማኖቷን ለማጥፋት ስለሆነ ኢትዮጵያና አምላኳ እስካሉ ድረስ ከዚህ ዓላማቸው ፎቀቅ አይሉም። ልክ እንደ ነቀርሳ፤ የሚመገበው ጤናማ ሕዋሳት እስካሉ ድረስ እነርሱን እይተመገበ ይስፋፋል፤ ጤናማው ህዋሳት ሲያልቅ ነቀርሳው እራሱን በልቶ ይጠፋል። አዎ! በእነርሱ ያለውን ማንነትና ምንነት ነው ገለባብጠው በማንጸባርቅና በጽዮናውያን ላይ በመለጠፍ (Projecting) ሲጨፈጭፏቸው የምናየው። ይህ ደግሞ ቀንደኛ የዋቄዮ-አላህ ባሪያዎች ባሕርይ ነው።

ጋላ-ኦሮሞዎች፤ “ኢትዮጵያ የመቶ ሰላሳ ዓመት ታሪክ ነው ያላት!” ሲሉን፤ “ጋላ-ኦሮሞዎች የፈጠሯት ደካማዋ፣ በዓለም ዘንድ የተዋረደችዋና ጋላ-ኦሮሞዎቹ እነ ምንሊክ የፈጠሯት ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ ከተመሠረተች መቶ ሃምሳ ዓመቷ ነው!” ማለታቸው ነው እንጂ ሊያጠፏት የመጡትን ታሪካዊቷን አጋዚአዊቷን ኢትዮጵያን ማለታቸው አይደለም።

የዘመናችን ተዋሕዷውያን ተገቢ በሆነ መልክ እርስበርስ እንዳይተባበሩና የራሳቸው የሆነውን ነገር ሁሉ እንዳያስቀድሙ እንቅፋት የሆኑባቸው ነገሮች፦ ማንነታቸውን በሚገባ አለመገንዘባቸው፣ መድኃኔ ዓለም የሰጣቸውን ፀጋና በረከት ዋጋ ባለማወቃቸው፣ ሃገራቸውና ሃይማኖታቸው ያሰቀመጧቸውን ተልዕኮዎችና ዓላማዎች ባለመከተላቸው እንዲሁም የአምላካቸውንና የራሳቸውን ጠላት በብልጠት እንዲያውቁ ባለመፍቀዳቸው ብሎም ለመዋጋት ቁርጠኝነት ባለማሳየታቸው ነው።

እስኪ ይታየን፤ የዋቄዮ-አላህ ልጆች ፍቅር-አልባ በሆነ የጥላቻ መንፈስ ተነሳስተው ዲያብሎሳዊ አላማዎቻቸውን ሁሉ ለጊዜውም ቢሆን አንድ ባንድ በማሳካት ላይ ናቸው ፥ በሌላ በኩል፡ በፍቅር የተሞሉት የመድኃኔ ዓለም ልጆች ኃያሉን አምላካቸውን አጥብቀው በመያዝና ቅዱሳን ሠራዊቱንም ከጎናቸው በማሰለፍ እርስበርስ እየተሳሰቡና እየተደጋገፉ በአንድ ዓላማ ቢኖሩ ምን ያህል መሬት አንቀጥቅጥ ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ። እስኪ እናስበው! አዎ! የመድኃኔ ዓለም ጠላት የሆኑት የዋቄዮ-አላህ ልጆች ፻፶/150 ዓመት አይደለም አንድ ቀን እንኳን አይቆዩም ነበር።

ላለፉት ጥቂት ዓመታት አንድ የታዘብኩት በጣም አስሳቢ ነገር፤ ቤተክርስቲያን + ቤተክህነት + አገልጋዮች በጎቻቸው የሆኑትን ምዕመናናቸውን ለፍትህና(Justice) አብሮነት (Solidarity) በአግባቡ፣ ተገቢና ስልታዊ በሆነ መልክ አለማስተማራቸውና አለማዘጋጀታቸው ነው። በግብጽ ኮፕት ክርስቲያን ወገኖቻችን በመሀመዳውያኑ ያኔ ሲሰቃዩ ቆራጥ የሆን አብሮነትን አሳይተናቸው ቢሆን ኖሮ ዛሬ አህዛብ ባልደፈሩንና ባልቀለዱብን ነበር። የቀደሙት አክሱማውያን ነገሥታት አባቶቻችን እኮ ለግብጽ ካሊፎች፤ “ዋ! ክርስቲያን ወንድሞቻችንና እኅቶቻችንን ትነኩ እና፤ እዚህ በእጃችን ያሉትን መሀመዳውያን ዱቄት ነው የምናደርጋቸው፤ የግዮንን ወንዝ ፍሰት እንገድበዋለን/እናዞረዋለን!” ብለው በመዛት የእስላማዊት ግብጽ መሪዎችን ያንበረክኩ ነበር።

❖ የአንድ ተዋሕዶ ክርስቲያን ጽዮናዊ መርሕ፤

“እስላምንና ጋላ-ኦሮሞን ወይ በእግርህ ሥር ረግጠህ በፍትህ ልትገዛቸው ይገባሃል ፥ አሊያ ግን ራስህ ላይ ወጥተው አንገትህን ይቆርጡሃል”

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ስውር ጽዮናውያን አባቶች አዲስ አበባ እንደገቡ ብዙ ተዓምራት በየጸበሉ ይታዩ ነበር | መድኃኔ ዓለም ፀበል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 7, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ ❖ መድኃኔ ዓለም

ይህን አስደናቂ ክስተት እኔ እራሴ በዓይኔ እና በጆሮየ ታዝቤው ነበር። ልክ አረመኔው ግራኝ ሥልጣን ላይ እንደወጣ ለኢትዮጵያ እና ለሕዝቦቿ ተግተው የሚጸልዩ ብዙ ጽዮናውያን አባቶችና እናቶች በስውር ወደ አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ መግባት ጀምረው ነበር፣ ብዙ ተዓምራትም በመታየት ላይ ነበሩ፤ ከሁለት ዓመታት በፊት ለመስከረም ፬፣ ፳፻፲፪ቱ ሰልፍ አስፈላጊውን ድጋፍ ሲያደርጉ ነበሩ፣ በኮሮና ሰበብ የስቅለት እና ትን ሣኤ በዓላት በየአድባራቱ ይከበሩ ዘንድ የማርያም መቀነትን በየቦታው ለምልክትነት እስከ ማሳየት ድረስ የደረሱ ብቁ አባቶች ነበሩ። ሰው ግን ብዙዎቹን ምልክቶች አይቶ እንኳን ባግባቡ የቤት ሥራውን አልሠራም። እንዲያውም ይባስ ብሎ የዋቄዮ-አላህን የሞት እና ባርነት መንፈስን ለመቀበለ እራሱን ማዘጋጀት ጀምሮ ነበር።

አዎ፤ ይህን ያወቀው ኦሮሞ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ባፋጣኝ ያደረገው እነዚህን ተዓምር የታየባቸውን ቦታዎች “በልማት” ስም መውረስ፣ የዋቄዮአላህአቴቴ ቃልቻዎችን እና ሴቶችን ወደየ አድባራቱ እና ገዳማቱ መላክ፣ ቤተ ክህነትን በእነ ኢሬቻ በላይ እና አቡነ ናትናኤል መበከል፣ ከዚያም ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑ ጽዮናውያን አባቶችን እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ማገት፣ ማባረርና መግደል ነው። ለፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝና ለእባብ ገንዳ ቃልቻዎቹ ዋቄዮአላህ የሚነግስባትን እስላማዊቷን ኦሮሚያ ኤሚራትን ለመመስረት ባላቸው ሕልም ኃይለኛ መንፈሳዊ ተፎካካሪዎች የሆኑባቸው ጽዮናውያን ብቻ መሆናቸውን በደንብ ደርሰውበታል፤ አማኝ የሆነው አማራ መልፈስፈሱን እና መውደቁን አይተውታል፤ ስለዚህ እስከ ዛሬ ድረስ ምሰሶና የጀርባ አጥንት የሆኗቸውን ጽዮናውያንን ከአዲስ አበባ፣ ናዝሬት፣ ደብረዘይት ወይንም ጂማ ብቻ ሳይሆን ትግራይን ጨምሮ ከምድረ ገጽ ማጥፋት የሚፈልጉት ለዚህ ነው። ግን ፻/100% ሆኜ መናገር እችላለሁ በጭራሽ አይሳካላቸውም፤ እንዲያውም በዚህ ዲያብሎሳዊ ዘመቻ ላይ የተሳተፉት የዋቄዮአላህ ጭፍሮች ሁሉ ከምድረ ኢትዮጵያ በእሳት ተጠራርገው ይጠፋሉ። አብዛኛው ይህ ትውልድ ኢትዮጵያም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያንም አይደለምና በሃገረ ኢትዮጵያ ይኖር ዘንድ አይፈቀድለትም።

💭 ቪዲዮው ላይ የሚታየው የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ለUAE ኤሚራቶች የሰጣቸው ተዓምረኛው የመድኃኔ ዓለም ፍልውሃ የጸበል ቦታነው። ካዛንቺስ በፍልውሃ አካባቢ (አቴቴ ጣይቱ ብጡል ‘ፊንፊኔ’ ብላ በሰየመችው ቦታ ላይ) ሸረተን ሆቴልን የሠራው በከሃዲ ባለሥልጣናት የተመራው ወስላታው ሸህ አላሙዲንም፤ “ከግራኝ አህመድ ቀዳማዊ የተደበቁ ቅዱሳት ጽላቶች ተደብቀውባቸዋል” ተብሎ ነበር ይህንና ሌሎችም መንፈሳዊ ኃይል ያላቸውን ቦታዎች ለመውረስ አጥብቆ ይፈልጋቸው ነበር። በጊዜው እነ መለስ ዜናዊ ነበር ፈቃዱን የነፈጉት። ይህ አላሙዲንና አብዮት አህመድ አሊ መለስን ከገደሉበት አንዱ ምክኒያት ነው።

✞✞✞የሊቢያን ሰማዕታት ረሳናቸው፤ አይደል?! አዎ! ይህ ማፈሪያ ትውልድ ፈላጭ ቆራጭ የሆነባት የዛሬዋ “ኢትዮጵያ” ሊቢያ ሆናለች! የሞትና ባርነት መንፈስ ወደ ኢትዮጵያም እንዳይገባ በወቅቱ ሳንታክት አስስጠነቅቅንም ነበር፤ የቤት ሥራችንን ብዙ መስዋዕት ከፍለን ሠርተናልና አንጸጸትም✞✞✞

በሊቢያ በረሃ በሙስሊሞች የታረዱት ፲፪/12ቱ የቂርቆስ ሠፈር ሰማዕታት ፡ በሁለት ህገወጥ መስጊዶች መካከል የፈለቀውን እጹብ ድንቅ ጸበል አፍልቀውት ይሆን?

💭 ከቪዲዮው የተወሰደ | ስለ ጸበሉ ጥሩ እውቀት ያላቸው ወንድሞች ያካፈሉኝ አስገራሚ መረጃ በከፊል እነሆ፦

✞ ግንቦት ፴፡ ፪ሺ፱ ዓ.ም አዲስ የመድኃኔ ዓለም ፍልውሃ ጸበል ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ፈለቀ።

✞ እስካሁን ግማሽ ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ በጸበሉ ተጠምቋል።

✞ የኪዳነ ምህረት፣ የአርሴማና የዮሐንስ ጸበሎች በተጨማሪ እንደሚፈልቁ ተጠማቂዎች መስክረዋል።

✞ አራቱም ጽላቶች በዚህ ቦታ ላይ እንደሚገኙ፡ አባቶች በ፲፱፻፸፮/1976 ዓ.ም ጠቁመው ነበር።

✞ በሊብያ በረሃ ከሁልት ዓመታት በፊት በሙስሊሞች ታርደው ሰማዕትነት ከተቀበሉት ኢትዮጵያውያን መካከል ፲፪/12ቱ የቂርቆስ አካባቢ ነዋሪዎች ነበሩ።

✞ በጸበሉ መፍለቅ የሚያነገራግሩት ሙስሊሞች “ዘምዘም”ነው ብለው ወደ ሳዑዲ ነፍስ አባቶቻቸው ይመላለሳሉ።

✞ ብዙ “የጠፉ በጎች” ሙስሊሞች በጸበሉ ሲጠመቁና ሲድኑ የኢየሱስ ክርስቶስን መድኃኔ ዓለምነት በቦታው ይመሰክራሉ፤ „ኧረ መድኃኔ ዓለም ተው!ኧረ መድኃኔ ዓለም ተው! ይህ ለኛ ለሙስሊሞች ውርደት ነው!”በማለት ይጮሃሉ።

✞ በጸበሉ ተዓምራዊነት አጋንንቱ እራሳቸው መስካሪዎች ናቸው።

✞ የጴንጤ መንፈስ አለብን ብለው የሚጮሁና አላህ ስይጣን ነው፣ ክርስቶስ አዳኝ አምላክ ነው የሚሉ ብዙ ናቸው።

✞ እስልምና ከጥንቆላ ብዙ የከፋ ጣዖታዊ አምልኮት መሆኑን እና ቅዱስነትንም ፈጽሞ እንደማያውቅ አጋንንቱ ይመሰክራሉ።

✞ እንደዚህ ቀሚስ ለባሽ የአረብ ወኪሎች እየተቅነዘነዙና ጋኔናዊ የአረብኛ ቃላትን እየለፈለፉ፤ ለመጠመቅ የሚጎርፉትን ኢትዮጵያውያን በየጊዜው ያውካሉ።

✞ ዓለማውያኑ “የጠፉት በጎች“፤

(”ሸገር ራዲዮ”፣“ኢቢሲ”፣”ሙስሊም ፖሊሶች”)በቦታው ተገኝተው፤ “ውሃው በኬሚካል የተበከለ

ነው”በማለት የሃሰት ምስክርነት መስጠታቸውንና በሚፈወሱት ሰዎች ብዛት አፍረዋል።

✞ ተተኩሶ የወጣው ፍልውሃ ጸበል ያቃጠለው ዛፍ ጉድጓዱን ሲቆፍር የነበረው ቻይናዊ መሀንዲስ

በፍልውሃው አንድ ዓይኑ ጠፋ፤ በኋላም ራእይ ታይቶት በጸበሉ ተፈውሶ ዓይኑ በርቷል።

✞ ዛሬ ከ ለገሃር እስከ መድኃኔ ዓለም ጸበል ድረስ ያለውን ቦታ፡ ኢትዮጵያን አንድ ባንድ በመሸጥ ላይ ያለው የአክሱም ጽዮን ጨፍጫፊ አረመኔው አብዮት አህመድ ለተባበሩት አረብ ኤሚራቶች አበርክቶላቸዋል። የትግራይን ሕዝብ ለጨፈጨፉት የኤሚራቶች ድሮኖቹ ቀብድ መሆኑ ነበር።

✞✞✞ሰማዕታቱን ሁሉ በማስብ በደማቸው ያጸኑትን የእምነት በረከት ተካፋዮች ለመሆን መድኃኔ ዓለም ያብቃን✞✞✞

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቀዳም ሥዑር | የቅዱስ እሳት ተአምር በኢየሩሳሌም | The Miracle of the Holy Fire in Jerusalem

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2021

✞✞✞ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ።✞✞✞

የማያቃጥለው እና የክርስቲያኖችን ነፍስ የሚያስደስተው ይህ ድንቅ ሥነ-ስርዓት በኢየሩሳሌም በሚገኘው የትንሳኤ ቤተክርስቲያን ውስጥ በቅዱስ ቅዳሜ ይካሄዳል።

ፋሲካ የሚውልበት ቀን በየዓመቱ እንደ አዲስ ይወሰናል፡፡ የቀን እና የሌሊት ርዝመት እኩል በሚሆንበት የፀደይ እኩልነት እና ከአይሁድ ፋሲካ በኋላ የመጀመሪያ እሁድ መሆን አለበት። ስለዚህ ብዙ ጊዜ የተለያዩ መስፈርቶችን በመጠቀም ከሚወስነው የካቶሊክና ፕሮቴስታንት ፋሲካ ቀን ይለያል።፡ የቅዱስ እሳት በዓለም ምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ በጣም የታወቀ ተዓምር ነው፡፡ ለዘመናት በየአመቱ በተመሳሳይ ቦታ፣ በተመሳሳይ ጊዜና በተመሳሳይ ሁኔታ ይካሄዳል። ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደዚህ በመደበኛነት እና ያለማቋረጥ የሚከሰት ሌላ ተዓምር አይታወቅም። የሚከናወነው በኢየሩሳሌም በሚገኘው የትንሳኤ/ የቅዱስ ጎለጎታ ቤተ ክርስቲያንን ውስጥ ነው ፣ በምድር በጣም በተቀደሰው ስፍራ ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታሰረበት፣ በተሰቀለበት እና በመጨረሻም ከሞት በተነሳበት፡፡

The ceremony, which awes the souls of Christians, takes place in the Church of the Resurrection in Jerusalem. The date for Pascha is determined anew for every year. It must be a first Sunday after the spring equinox and Jewish Passover. Therefore, most of the time it differs from the date of Papal Protestant and Protestant Easter, which is determined using different criteria. The Holy Fire is the most renowned miracle in the world of Eastern Orthodoxy. It has taken place at the same time, in the same manner, every single year for centuries. No other miracle is known to occur so regularly and so steadily over time. No other miracle is known to occur so regularly and so steadily over time. It happens in the Church of the Holy Sepulchre in Jerusalem, the holiest place on earth, where Christ was crucified, entombed, and where He finally rose from the dead.

Breaking News from #Jerusalem the Resurrection Church :blood is leaking from the stone Jesus body was laid before his burial . You can hear the Israeli police closed the area.

___________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የጌታችን ስቅለት በዓል የአዲስ አበባ አድባራት በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው በነበሩበት ዘመን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2021

ዛሬስ? ዛሬማ የአርዮስ ኢሬቻ በላይና አጋንንት መንጋው መፈንጫዎች ሆነዋል።

✞✞✞ዓርብ ስቅለት በደብረ ቤቴል አበ ብዙሃን-አብርሃም ገዳም✞✞✞

✞✞✞ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን✞✞✞

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ የድኅነት ቀንይባላል፡

👉 ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

፩. ፀሐይ ጨለመ፤

. ጨረቃ ደም ኾነ፤

. ከዋክብት ረገፉ፤

. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤

. አለቶች ተፈረካከሱ፤

. መቃብራት ተከፈቱ፤

. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩፶፬)፡፡

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የጌታችን ስቅለት ከ፸፫/73 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅዱስ ኡራኤል ዕለት ዋለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2021

✞✞✞ዓርብ ስቅለት ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ነው✞✞✞

ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡ ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?” ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡

“ክፉ የሠራ ባይኾንስ ወደ አንተ ባላመጣነውም ነበር በሚል የሸፍጥ ቃል ሲያጕረመርሙ ጲላጦስ መልሶ እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተ ወስዳችሁ እንደሕጋችሁ ፍረዱበት፤ አላቸው፡፡ አይሁድም ኦሪት ኢትቅትል ብእሴጻድቀወኀ ጥአ ኢታኅዩ፤ ጻድቅን ሰው አትግደል፤ ኀጥኡንም ከፍርድ አታድን፤ ትላለችና እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፤ብለዋል (ዮሐ. ፲፰፥፳፰-፴፩)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ በሕጋችን ጻድቀ ባሕርይ ክርስቶስን መግደል አይገባንም ሙሉ በሙሉ ጥፋተኞች ነን፤ሲያሰኛቸው ነው፡፡ በኋላም እርሱ ሞቶ ዓለም ይድን ዘንድዳ ምድር መጥቷልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጥፋቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ ስለዚህም ገርፈው ሰቀሉት፡፡

ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ የድኅነት ቀንይባላል፡

👉 ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

፩. ፀሐይ ጨለመ፤

. ጨረቃ ደም ኾነ፤

. ከዋክብት ረገፉ፤

. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤

. አለቶች ተፈረካከሱ፤

. መቃብራት ተከፈቱ፤

. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩፶፬)፡፡

👉 ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)”

. “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ

. “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው

፬. እመቤታችንን “ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ”፤ ደቀ መዝሙሩንም “እናትህ እነኋት” በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤

፭. “አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ”

. ተጠማሁ

፯. “ዅሉ ተፈጸመ (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡

ከሰድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ሁኖአል፡፡ “ወፍና ሠርክ ይበርህ ብርሃነፀሐይእንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡

ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም “ንሴብሖለእግዚአብሔር እየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

በዕለተ ሥቅለት በደመ ወልድ ዓለምን ለመቀደስ ከሁሉ ይልቅ የተሰየመው ቅዱስ ኡራኤል ነው።

ቅዱስ ኡራኤል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በፍጹም መጠበቅን ጠብቆ ለዚህ ያደረሰን አምላካችን ክብርና ምስጋን አምልኮትና ውዳሴ ይድረሰውና ይህን ታላቅ መልአክ በችሎታችን መጠን እንድናመሰግን እግዚአብሔር ይርዳን፤ አምላክ ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን፤ ምስጢሩን ይግለጥልን አሜን፡፡

ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡” [/ዕዝ. ሱቱ. ]

በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።

በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ

በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውለሁ። ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ። መዝ. [/፺፩/፥፲፩፡፲፮]

አፈቅሮ ፈድፋደ፡ዑራኤል ሆይ፣ ከመልኮች ሁሉ ይልቅ ያንተን መልክአ ጸሎት እወዳለሁ፡፡ የመልክህ ስነ ጸዳል በደመ ወልድ እግዚአብሔር የታተመ ነውና፡፡

ዑራኤል ሆይ፣ እግዚአብሔር ሀይሉን የሚገልጽብን መልአከ ብርሃናት አንተ ነህ፡፡ በዕለተ ሥቅለት በደመ ወልድ ዓለምን ለመቀደስ ከሁሉ ይልቅ አንተ ተሰይመሃልና፡፡ ስለክብርህ የሰማይ መላእክት አደነቁ፡፡

ለተፈጥሮትከ፡

ዑራኤል ሆይ፡ያለ መናገር በጥንት አርምሞ ከነፋስና ከእሳት ለተፈጠረ ተፈጥሮህ ሰላም እላለሁ፡፡ ዑራኤል ሆይ የተፈጥሮና የይቅርታና የቸርነት ክቡር መልአክ ነህና ስለኛ ስለሰው ልጆች ወደ ልዑል እግዚአብሔር ማልድ አማላጅነትህ ዘወትር ከጥፋት ያድናልና፡፡

ለዝክረ ስምከ፡

ዑራኤል ሆይ፡ከማርና ከወተት ይልቅ ለሚጥመው ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡

ዑራኤል ሆይ፡ክፍልህ /ክንፍህ/ በደመ ወልድ እግዚአብሔር የተከበረ /የታለለ/ ነውና፡፡ ለዓለሙ ሁሉ መድሃኒት ትሆን ዘንድ ግሩም የሚሆን የእግዚአብሔር ሥልጣን በክብር ከፍ ከፍ አደረገ፡፡ (መልክአ ዑራኤል)

የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” [መዝ.፴፫/፴፬/፥፯]የሊቀ መልአኩ የክዱስ ዑራኤል ረድኤቱ በረከቱ ፍጹም አማላጅነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡

በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡ ሌሊትና ቀን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑና ሳይሰለቹ የሚጠብቁን ሊቀነ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሩፋኤል ቅዱስ ዑራኤል ቅዱስ ራጉኤል ቅዱስ ፋኑኤል እልፍ አእላፋት የሆኑ ጠባቂ መላእክት ሳመሰግን በደስታ ነው፡፡

በጸሎታቸው ያልተለዩኝን ጻድቃን አባቶቼን አቡነ ተክለሃይማኖትን አቡነ ገብረምንፈስ ቅዱስን አቡነ ሀብተማርያምን አቡነ አረጋዊን አቡነ ኪሮስንና ሌሎች ቅዱሳን አባቶቼን እንዲሁም እናቶቼን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራን ቅድስት አርሴማን ብዙ ያልጠቀስኳቸው ቅዱሳንን ለማመስገን ቃላት የለኝም፡፡

በሰማኝትነታቸው የጥንካሬ ምሳሌ የሆኑልኝ በጸሎታቸው የረዱኝን ቅዱሳን ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ቅዱስ እስጢፋኖን መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስንና ሌሎችን ቅዱሳን ሰማዕታትን ሁሉ በእጅጉ አመሰግናለሁ ለዘላለሙ አሜን፡፡

የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

___________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ግራኝ ለ UAE ኤሚራቶች የሰጣቸው ተዓምረኛው የመድኃኔ ዓለም ፍልውሃ የጸበል ቦታ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 5, 2021

✞✞✞የሊቢያን ሰማዕታት ረሳናቸው፤ አይደል?! ማፈሪያ ትውልድ!✞✞✞

በሊቢያ በረሃ በሙስሊሞች የታረዱት ፲፪/12ቱ የቂርቆስ ሠፈር ሰማዕታት ፡ በሁለት ህገወጥ መስጊዶች መካከል የፈለቀውን እጹብ ድንቅ ጸበል አፍልቀውት ይሆን?

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

👉 ከቪዲዮው የተወሰደ | ስለ ጸበሉ ጥሩ እውቀት ያላቸው ወንድሞች ያካፈሉኝ አስገራሚ መረጃ በከፊል እነሆ፦

✞ ግንቦት ፴፡ ፪ሺ፱ ዓ.ም አዲስ የመድኃኔ ዓለም ፍልውሃ ጸበል ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ፈለቀ።

✞ እስካሁን ግማሽ ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ በጸበሉ ተጠምቋል።

✞ የኪዳነ ምህረት፣ የአርሴማና የዮሐንስ ጸበሎች በተጨማሪ እንደሚፈልቁ ተጠማቂዎች መስክረዋል።

✞ አራቱም ጽላቶች በዚህ ቦታ ላይ እንደሚገኙ፡ አባቶች በ፲፱፻፸፮/1976 ዓ.ም ጠቁመው ነበር።

✞ በሊብያ በረሃ ከሁልት ዓመታት በፊት በሙስሊሞች ታርደው ሰማዕትነት ከተቀበሉት ኢትዮጵያውያን መካከል ፲፪/12ቱ የቂርቆስ አካባቢ ነዋሪዎች ነበሩ።

✞ በጸበሉ መፍለቅ የሚያነገራግሩት ሙስሊሞች “ዘምዘም”ነው ብለው ወደ ሳዑዲ ነፍስ አባቶቻቸው ይመላለሳሉ።

✞ ብዙ “የጠፉ በጎች” ሙስሊሞች በጸበሉ ሲጠመቁና ሲድኑ የኢየሱስ ክርስቶስን መድኃኔ ዓለምነት በቦታው ይመሰክራሉ፤ „ኧረ መድኃኔ ዓለም ተው!ኧረ መድኃኔ ዓለም ተው! ይህ ለኛ ለሙስሊሞች ውርደት ነው!”በማለት ይጮሃሉ።

✞ በጸበሉ ተዓምራዊነት አጋንንቱ እራሳቸው መስካሪዎች ናቸው።

✞ የጴንጤ መንፈስ አለብን ብለው የሚጮሁና አላህ ስይጣን ነው፣ ክርስቶስ አዳኝ አምላክ ነው የሚሉ ብዙ ናቸው።

✞ እስልምና ከጥንቆላ ብዙ የከፋ ጣዖታዊ አምልኮት መሆኑን እና ቅዱስነትንም ፈጽሞ እንደማያውቅ አጋንንቱ ይመሰክራሉ።

✞ እንደዚህ ቀሚስ ለባሽ የአረብ ወኪሎች እየተቅነዘነዙና ጋኔናዊ የአረብኛ ቃላትን እየለፈለፉ፤ ለመጠመቅ የሚጎርፉትን ኢትዮጵያውያን በየጊዜው ያውካሉ።

✞ ዓለማውያኑ “የጠፉት በጎች“፤

(”ሸገር ራዲዮ”፣“ኢቢሲ”፣”ሙስሊም ፖሊሶች”)በቦታው ተገኝተው፤ “ውሃው በኬሚካል የተበከለ

ነው”በማለት የሃሰት ምስክርነት መስጠታቸውንና በሚፈወሱት ሰዎች ብዛት አፍረዋል።

✞ ተተኩሶ የወጣው ፍልውሃ ጸበል ያቃጠለው ዛፍ ጉድጓዱን ሲቆፍር የነበረው ቻይናዊ መሀንዲስ

በፍልውሃው አንድ ዓይኑ ጠፋ፤ በኋላም ራእይ ታይቶት በጸበሉ ተፈውሶ ዓይኑ በርቷል።

✞ ዛሬ ከ ለገሃር እስከ መድኃኔ ዓለም ጸበል ድረስ ያለውን ቦታ፡ ኢትዮጵያን አንድ ባንድ በመሸጥ ላይ ያለው የአክሱም ጽዮን ጨፍጫፊ አረመኔው አብዮት አህመድ ለተባበሩት አረብ ኤሚራቶች አበርክቶላቸዋል። የትግራይን ሕዝብ ለጨፈጨፉት የኤሚራቶች ድሮኖቹ ቀብድ መሆኑ ነበር።

✞✞✞ሰማዕታቱን በማስብ በደማቸው ያጸኑትን የእምነት በረከት ተካፋዮች ለመሆን መድኃኔ ዓለም ያብቃን✞✞✞

_____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 7, 2021

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፮]

፩ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

፪ ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።

፫ ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።

፬ እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።

፭ በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።

፮ እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ።

፯ አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ። ማረኝና አድምጠኝ።

፰ አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ። አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።

፱ ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ።

፲ አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ።

፲፩ አቤቱ፥ መንገድህን አስተምረኝ፥ ስለ ጠላቶቼም በቀና መንገድ ምራኝ።

፲፪ የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፈቃድ አትስጠኝ።

፲፫ የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ።

፲፬ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: