Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2024
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ተዋሕዶ’

የቅድስት ልደታ ለማርያም ክብረ በዓል ከ ሰባት ዓመታት በፊት | Lideta Le Maryam Wereb

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 8, 2024

❖❖❖ ልደታ ለማርያም፡ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ ይህች ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀባት ዕለት ናት | ምስጋና ❖❖❖

❖❖❖በሰንበት ተማሪዎች የቀረበ ወረብ ፥ የቅድስት ልደታ ለማርያም ክብረ በዓል ፩ ግንቦት ፪ሺ፱ ዓ.ም ❖❖❖

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም “የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት” ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ “ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች” [ኢሳ ፯፡፲፬] ብሎ ትንቢት የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡ ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ” የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።” [መዝ ፵፬፡፱] ብሎ የተናገረላት ንግሥት የተገኘችባት ዕለት ናት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ “ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት።”[ራዕ ፲፪፡፩] ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡ የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ ነው፡፡

የድንግል ማርያም ልደት በነቢያት አንደበት

መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡ መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፡፡ [መዝ ፹፮፥፩፡፯]

እግዚአብሔር የዝማሬና የትንቢት ጸጋን ያበዛለት ክቡር ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥርወ ልደት አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት ተገልጾለት “መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን /መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው/” በማለት ትንቢት ተናግሯል፡፡ “የተቀደሱ ተራሮች” ያለውም የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ከሆኑት ከተቀደሱት ከኢያቄምና ከሐና የመሆኑን ነገር ሲያመለክት ነው፡፡ ይህንን ትንቢትና እውነተኛውን የእመቤታችንን የትውልድ ሀረግ አስማምታ ቤተክርስቲያን “የእመቤታችን ማርያም ትውልዷ ባባቷ በኩል ከንጉሡ ከዳዊት ወገን ነው፤ በናቷም በኩል ከካህኑ ከአሮን ወገን ነው፤ የአባቷ ስም ኢያቄም ነው፤ የእናቷም ስም ሐና ነው፡፡” ብላ ታስተምራለች፡፡

ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ፡ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል፡፡ [ኢሳ. ፲፩፡፩]

ቁጥሩ ከዐበይት ነቢያት ወገን የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስም ጥበብንና እውቀትን በሚገልጽ ስለሚመጣውም ነገር ትንቢትን በሚያናግር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ከነገደ ዕሴይ እንደሚሆንና እርሷም ጽጌ (አበባ) የተባለ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በሕቱም ድንግልና እንደምትወልድ ተገልጾለት “ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ /ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል/” በማለት ታላቅ ትንቢትን ተናግሮ ነበር፡፡ ይህች በትርም ከእሴይ ዘር የተገኘችው በዚህች ዕለት ነውና ልደቷን በታላቅ ድምቀት እናከብራለን፡፡ ይህንን መሰረት በማድረግ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም “መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ከእሴይ ሥር የተገኘሽ መዓዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ” በማለት በውዳሴ አመስግኗታል፡፡ “በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ” [መዝ.፻፴፩፡፲፫]” የተባለልን የአባቶቻችን ልጆች እኛም እንዲሁ እያልን እናመሰግናታለን፡፡

ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ፡ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፡፡ [መኃ ፬፡፰]

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት መሰረት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡ በሊባኖስ ስለመሆኑ አስቀድሞ ጠቢቡ ሰሎሞን “ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት /ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች/” በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ የዚህ ትንቢት ምስጢርም የእመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸው የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ትንቢቱም ሲፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት ፩ ቀን በ፲፭ ዓ.ዓ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡

ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ የተባለው የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እመቤታችን በሊባኖስ እንደምትወለድ አስቀድሞ ሰሎሞን የተናገረው ቃልም መፈጸሙን ሲገልጽ “….የአናብስት ልጅ አልኩሽ፡፡ ሰሎሞን እንዲህ ሲል እንደተናገረ፡- ሙሽራዪት ሆይ ከሊባኖስ ተራራ ነዪ፤ ከአንበሶች ጒድጓድ ወጥተሽ ነዪ፤ ከምርጥ ነገድነት የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ዜና እጅግ ግሩም ነው፡፡” በማለት አመስጥሮታል፡፡ እመቤታችንም በሊባኖስ ተራራ እንድትወለድ ምክንያት የሆነው በማሕፀን ሳለች የአርሳባንን ልጅ ዓይን በማብራቷና ሳሚናስ የሚባለውን የጦሊቅን ልጅ ከሞት በማስነሳቷ አይሁድ በቅናት ተነሳስተውባቸው ስለነበር ሐናና ኢያቄም ወደ ሊባኖስ ተራራ እንዲሄዱ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ስለነገራቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡

የድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌ

ከትንቢቱ በተጨማሪም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌም አስቀድሞ የተገለጸ ነበር፡፡ ከእነዚህም መካከል ከእርሷ ሰባት ትውልድ አስቀድሞ ለነበሩት ደጋግ ሰዎች እንዲሁም ለእናትና ለአባቷ የተገለጹት ምሳሌዎች በቅዱሳት መጻሕፍት በሰፊው ሰፍረው ይገኛሉ፡፡

ሰባተኛዪቱ እንቦሳ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየሁ (ቴክታ)

በቅድስና የሚኖሩ ነገር ግን መካን የነበሩት ቴክታና ጴጥርቃ ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ ፤ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ስትደርስ ፤ ስድስተኛዪቱ ጨረቃን ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አይተው በሀገራቸው መፈክረ ሕልም (ሕልም ፈች ሊቅ) አለና ሂደው ነገሩት፡፡ ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ፤ ጨረቃይቱ ከፍጡራን በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ፡፡ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም፤ እንደ ነቢይ እንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል አላቸው፡፡ እነርሱም ጊዜ ይተርጉመው ብለውት ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላ ልጅ ወለዱ፡፡ ስሟንም “ረከብኩ ስእለትዬ፤ ረከብኩ ተምኔትዬ” /የተሳልኩትን አገኘሁ፤ የተመኘሁትን አገኘሁ/ ሲሉ “ሄኤሜን”አሏት፡፡ ሄኤሜን ዴርዴን፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡ ሐና ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሑዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ ከኢያቄምና ከሐናም በጨረቃ የተመሰለች ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡

ፀዓዳ ርግብ ሰባቱ ሰማያትን ሰንጥቃ መጥታ በማሕፀኔ ስታድር አየሁ (ቅድስት ሐና)

ኢያቄምና ሐና መካን ስለነበሩ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ጸልየው፤ ሲሰጣቸውም መልሰው ለእርሱ እንደሚሰጡ ስዕለትን ተስለው ነበር፡፡ ጸሎታቸው ሲደርስ ለሐና በሕልም ተገልጾላት ለባለቤቷ ለኢያቄም “ብእሴሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ /ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብቶ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ፡፡” ብላዋለች፡፡ የዚህ ራእይ ምስጢርም ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትሆን፤ ፀዓዳ (ነጭ) መሆኗ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ” ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መሆኗን ሲያጠይቅ ነው::

ከሰባተኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ (ቅዱስ ኢያቄም)

በተመሳሳይ ኢያቄምም በሕልሙ ያየውን ለባለቤቱ ለሐና “እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ /ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” ብሎ በሕልሙ የተገለጸለትን ነግሯታል፡፡ የዚህም ራዕይ ምስጢር ዖፍ የተባለው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፡፡ ኢያቄም “ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ የሚያጠይቅ ሲሆን ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ባህርይው፣ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው።

የድንግል ማርያም ልደት በሐዲስ ኪዳን ሊቃውንት

የሐዲስ ኪዳን ሊቃውንትም ትንቢተ ነቢያትንና ወንጌልን በማጣጣም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት አመስጥረው አስተምረዋል፤ አመስግነዋል፤ ተቃኝተዋልም፡፡ የእርሷን ልደት እጅግ ብዙ ሊቃውንት በስፋትና በጥልቀት ያመሰጠሩት ሲሆን ለምሳሌ ያህል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡

ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች (ቅዱስ ያሬድ)

ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለእመቤታችን ልደት “ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ/ ማርያምስ (ማርያም ግን) ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች፡፡” በማለት እርሷ በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና፣ በቅድስናና በድንግልና ስታበራ እንደነበርና ኋላም የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷን አመስጥሮ ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም ስለ ሥርወ ልደቷ “እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ…ሐረገ ወይን/ ሥሮቿ በምድር ጫፎቿም በሰማይ ያሉ…የወይን ሐረግ” በማለት የተወለደችው በምድር ከነበሩት ኢያቄምና ሐና መሆኑን የወለደችው ግን ሰማያዊውን ንጉሥ እንደሆነ በማመስጠር ዘምሯል፡፡ በዚህም ሰውና እግዚአብሔርን ያገናኘች መሰላል መሆኗል ገልጾ አስተምሯል፡፡

ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ (አባ ሕርያቆስ)

የብህንሳው ሊቀ ጳጳስ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም “ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ/ ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ” በማለት የድንግል ማርያም ጽንሰትና ልደት እንዴት እንደነበር በድርሰቱ አስፍሮታል፡፡ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚላት የሁላችን እናት ድንግል ማርያም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ነሐሴ ፯ ቀን ተፀንሳ ከዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በኋላ ግንቦት ፩ ቀን ተወልዳለች፡፡ እርስዋም ስትፀነስ ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከጥንተ አብሶ (original Sin) ጠብቋታል፤ አበሳው አልነካትም፡፡ ይህንንም ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በኃጢአት በተከበበ፣ መርገም በሞላበት ዓለም ውስጥ ከኃጢአት ከበደል ርቃ (ተለይታ) እንደ ጌዲዮን ጸምር በንጽህና የጠገኘች ንጽህት ዘር መሆኗን ሲያስረዳ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር፡፡”[ኢሳ.፩፡፲፱]በማለት ተናግሯል፡፡ እንዲሁም ጠቢቡ ሰሎሞን ንጽህናዋን በትንቢት መነጽር አይቶ “ወዳጄ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፣ ምንም ነውር የለብሽም፡፡ ሙሽሪት ሆይ ከሊባኖስ ነዪ፡፡”[መሓልይ ፬፡፯፡፲፮] በማለት በንጽህና በቅድስና ያጌጠች፣ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያልነካት፣ የድህነታችን ምክንያት፣ የንጽህናችን መሰረት የሰው ባህርይ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲዋሀድ ምክንያት የሆነች ንጽሕት የሰርግ ቤት ድንግል ማርያም በሊባኖስ የመወለዷን ነገር አስቀድሞ ነግሮናል፡፡

ይህች ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀባት ዕለት ናት (ቅዱስ እንድርያስ)

የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ የከበረ ስለሆነው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ታላቅነት “ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል፤ የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ ዕለት (ጌታ) መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” በማለት ገልጾታል፡፡ በእውነት የእርሷ ልደት የልዑል ማደሪያው መቅደስ የተሰራበት ዕለት ነውና ሁላችን እናከብረዋለን፡፡ በዚህም ዕለት “ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም/ እነሆ ዛሬ በእመቤታችን ልደት ደስታ ሆነ” እያልን እንዘምራለን። ይህችን የልዑል ማደሪያ እናቷ ሐናና አባቷ ኢያቄምም በእጅጉ ተደስተው በተወለደች በስምንተኛ ቀኗ ስሟን “ማርያም” ብለው ሰይመዋታል፡፡

የእመቤታችን የልደት በዓል አከባበር

አባታችን አዳም በኃጢአት ከወደቀ በኋላ፣ ንስሃ በገባ ጊዜ አምላካችን ጌታ እግዚአብሔር የድህነት ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ቃል ኪዳኑም “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚል ነበር፡፡ ስለሆነም አዳም ፶፻፭፻/5500 ዘመን የሕይወት ምክንያት የሆነች የልጅ ልጁ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአብራኩ ከተከፈሉ ቅዱሳን ልጆቹ የምትወለድበትን ቀን ተስፋ እያደረገ ኖረ፡፡ የእመቤታችንን የድንግል ማርያምን የመወለዷን ዜና ተስፋ በማድረግ “ሴት” ይላት የነበረውን ሚስቱን ሔዋንን በእመቤታችን ምሳሌነት “ሔዋን”፣ የሕያዋን ሁሉ እናት ብሎ ሰየማት፡፡ [ዘፍ.፫፡፳] ዳግማዊ አዳም የተባለ ክርስቶስም የአዳምን ተስፋ በመስቀል ላይ በፈጸመ ጊዜ እውነተኛዋን ሔዋን (ዳግሚት፣ አማናዊት ሔዋንን) ድንግል ማርያምን በዮሐንስ ወንጌላዊ በኩል ለሕያዋን ምዕመናን ሁሉ እናት አድርጎ ሰጠ፡፡ [ዮሐ. ፲፱፡፳፮] ይህን የከበረ ምስጢር የማይረዳ “ክርስቲያን” እንዴት ያሳዝናል!? እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን የቀዳማዊ አባታችንን የአዳምን፣ እንዲሁም በዳግም ተፈጥሮ ያከበረንን ዳግማዊ አዳም የተባለ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ተቀብለን “የሕያዋን ሁሉ እናት” ድንግል ማርያምን ልደቷን በፍፁም ደስታ እናከብራለን፣ ከተወደደ ልጇ ምሕረትን ትለምንልን ዘንድም ወደ እርሷ እናንጋጥጣለን፡፡

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለን ምዕመናን ከጌታችን ልደት ቀጥሎ በታላቅ ድምቀት የምናከብረው የልደት በዓል የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ቀን ነው፡፡ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ “በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።”[ሉቃ ፩፡፲፬] ከተባለ የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ የሚያስደስት ይሆን?! የነቢያቱ ትንቢት የተፈፀመበት፣ የታየው ራዕይም በገሀድ የተከናወነበት፣ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጆች ሁሉ (ለሕያዋን ሁሉ) ታላቅ የደስታ ቀን ነው፡፡ ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም በንጽህናዋ በቅድስናዋ ተደንቀው “እህትነ ነያ/እህታችን እነኋት” ብለው ያመሰግኗታል፡፡ በዘመናችን ያሉ የሰዎች ልደት በድምቀት የሚከበር ከሆነ ለሰው ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ምንኛ ሊከበር ይገባው ይሆን?! ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ከዚህ ታላቅ በዓል በረከት ረድኤትን እንድናገኝበት ነው፡፡ የሕይወት ክርስቶስ እናት ዛሬ ተወልዳለችና፡፡

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ፡፡ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ “ንፍሮና ጥራጥሬ” ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ነገር ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡ በዚህ ዕለት አንዳንዶች ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ በድፍረት “ለአድባር አዉጋር ነዉ፤ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ” እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡ እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን፤ በምሕረቱ የጎበኘንን አምላካችንን ብቻ እያመለክን፤ የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምንም እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ አሜን፡፡

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ከፍኖተ መስቀሉ ከህያው ቅዱስ ቃሉ በረከት ይክፈለን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 3, 2024

❖ ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ “የድኅነት ቀን” ይባላል። ❖

✞ ፲፫ቱ ሕማማተ መስቀል

  • ፩ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
  • ፪ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
  • ፫ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)
  • ፬ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
  • ፭ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
  • ፮ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
  • ፯ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
  • ፰ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
  • ፱ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
  • ፲ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
  • ፲፩ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
  • ፲፪ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይ መሰቀል)
  • ፲፫ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)

✞ ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

  • ፩. ፀሐይ ጨለመ፤
  • ፪. ጨረቃ ደም ኾነ፤
  • ፫. ከዋክብት ረገፉ፤
  • ፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤
  • ፭. አለቶች ተፈረካከሱ፤
  • ፮. መቃብራት ተከፈቱ፤
  • ፯. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩-፶፬)፡፡

✞ ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

  • ፩. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)”፤
  • ፪. “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ”፤
  • ፫. “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው”፤
  • ፬. እመቤታችንን “ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ”፤ ደቀ መዝሙሩንም “እናትህ እነኋት” በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤
  • ፭. “አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ”
  • ፮. ተጠማሁ”፤
  • ፯. ዅሉ ተፈጸመ (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡

ከሰድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ሁኖአል፡፡ “ወፍና ሠርክ ይበርህ ብርሃነ ፀሐይእንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡

ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም “ንሴብሖ ለ እግዚአብሔር እየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ረቡዕ የምክር ቀን፤ ይሑዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠ | የዘመኑ ይሑዳዎች ዛሬም ጌታቸውን፣ ሀይማኖታቸውን፣ ሕዝባቸውን እና ሃገራቸውን ለገንዘብና ለስጋዊ ጥቅም ብለው እየሸጡ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2024

ሰሙነ ሕማማት – ረቡዕ ፤ የይሁዳ ክህደት፥ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን

ለምን የምክር ቀን ተባለ?

ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ [ማቴ. ፳፮፥፩፡፲፬ ፣ ማር. ፲፬፥፩፡፪ ቁ ፲.፲፩፣ ሉቃ. ፳፪፥ ፩፡፮]

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል

ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ “ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ” ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ነው ረቡዕ የመዓዛ ቀን የተባለው፡፡

የእንባ ቀንም ይባላል

ይህም ይህቸው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ [ማቴ.፳፮፥፮፡፲፫ ፣ ማር.፲፬፥፫፡፱፣ ዮሐ.፲፪፥፩፡፰] ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው። ምህሩንና ጌታውን ክዶ፣ ስሞ ለግርፋት እና ለመስቀል ሞት ተስማማ። ይህንን የጌታን ሕማማት፣ ስቅላት፣ ሞትና ትንሣኤ በምናስብበት በአሁኑ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ለሕማም፣ ለስቅላት እና ለሞት አሳልፎ ተስጥቷል። ይሁዳ ለ፴/30 ዲናር ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው፤ ከዚያም ዲናሩን መልሶ እራሱን አጠፋ። የዘመናችን ሰቃልያን የሆኑት ኦሮማራዎቹ የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮች ደግሞ “አክሱም ጽዮን ለብዙ ሺህ ዓመታት ያፈራችውን እውቀት፣ ስልጣኔና ሀብት በሙሉ ለመዝረፍ፣ አሳልፎ ለመስጠትና ለማውደም ጊዜው አሁን ነው” ብለው የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ከሆኑት አህዛብ፣ መናፍቃንና ግብረ-ሰዶማውያን ጋር ተባበሩ። በዚህም በዚያም ትልቅ ክህደት እና ስቅለት። በተለይ ተዋሕዶ ክርስትናን የተቀብሉትና ማሕተብ ያጠለቁት አማራ ወገኖች ክህደት ታሪክ የማይረሳው ነው፤ ብዙ ዋጋም የሚያስከፍላቸውና ከሌሎቹ ሁሉ የከፋው ክህደት ነው። ከይሁዳ ይልቅ የጴጥሮስ ዓይነት ክህደት ያድርግላቸው።

😈 የአስቆሮቱ ይሁዳ ክህደት + የቃኤል ቅናት = ሞት 💀

አወቁትም አላወቁትም፤ ዛሬ በአማራዎችና ኦሮሞዎች ህብረት በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለው ጂሃዳዊ የጭፍጨፋ ዘመቻ የመጨረሻው ግብ፤ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ትግራዋያንን ከአኩም ጽዮን አጽድቶ የሕይወት ዛፍ እና ጽላተ ሙሴ የሚገኙበትን ቅድስት ምድር ለተለከፉት ባዕዳውያኑ ውሾች ማስረከብ ነው። አዎ! ኢትዮጵያን/አክሱም ጽዮንን ለባዕዳውያኑ ሉሲፈራውያን ለማስረከብ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነት ከፈቱ። እስኪ እናስበው! ዋው!

በሰባዎቹ ዓመታት ሉሲፈራውያኑ ድርቅና ረሃብ ፈጥረው በዚህ አካባቢ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሃገራት፤ በተለይ ብሪታኒያ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ ሰራዊቶቻቸውን በእርዳታ ስም አስፍረው እንደነበር እናስታውስ። ከዚያ በሰማኒያዎቹ እና በባድሜው ጦርነት የተባበሩት መንግስታት “ሰላም አስከባሪዎች” እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ዛሬም ዓለም የተራቡ የትግራይን ሕፃናት ምስሎች በበቂ እንድታይ ከተደረገች በኋላና የተረፉትንም ትግራይ ወገኖቼንም በስደት የተቀደሰችውን ምድር እየለቀቁ እንዲወጡ (የአውሮፓን እና አሜሪካን ድንበሮች ይከፍቱላቸዋል፤ ከጥቂት ከፍተኛ ቦታ ላይ ከሚገኙት የዓለማችን ቦታዎች በቀር አውሮፓና አሜሪካ ሌሎችም አኅጉራት ይጠፋሉ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል) ከተደረጉ በኋላ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሠራዊቶች በትግራይ ይሰፍራሉ።

ገና ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት “ኔቶ በአፍጋኒስታን የሚገኘው ለኢትዮጵያ ለመለማመድ ነው፤ ተመሳሳይ የመልከዓ ምድር አቀማመጥ ስላላቸው…” በማለጥ ጽፌ ነበር። ምዕራባውያኑ እዚያ መስፈር ከጀመሩ በኋላ ቀስ በቀስ ዜጎቻቸውን ማስገባት ይጀምሩና በመጨረሻም “ኢትዮጵያውያኑም ተዋሕዶ ክርስቲያኖቹም እኛ ነን” በማለት እያታለሉና ደማቸውን እያፈሰሱ ለብዙ ሺህ ዓመታት ጠብቀውት የነበረውን ብኩርናቸውን በምስር ወጥ እንዲሸጡ ብሎም የመንፈስ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን እየተነጠቁ “ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን” ቀስበቀስ እንዲከዱ ይደረጓቸውን “የቀድሞ ኢትዮጵያውያን” “አናስገባም!” ብለው ከኢትዮጵያ ድንብር ይመልሷቸዋል። ይህ ትንቢት ሳይሆን የሉሲፈራውያኑ ግልጽ የሆነ ተልዕኮ ነው። እግዚአብሔር ይህን ተልዕኳቸውን እንደሚያጨናግፈው አልጠራጠረም፤ ነገር ግን በኢትዮጵያውያኑ ደንቆሮነት፣ ስንፍና እና እንደ ግራኝ ያሉትን የውስጥ ጠላታቸውን በሰዓቱ ለማስወገድ ባለመድፈራቸው ብሎም አክሱም ጽዮንን ለመከላከል ባለመሻታቸው ብዙ መስዋዕት ይከፍሉ ዘንድ ግድ ይሆናል። በተለይ ከሃዲዎቹ ኦሮማራዎች!

የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰሙነ ሕማማት (ዘሰሉስ) | እንደዛሬዎቹ ፈሪሳውያን ጌታችንን የጠየቁት የካህናትና የሕዝብ አለቆች ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2024

✞ በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡

ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠው ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡

ጥያቄውም አይሁድ ጌታችንን “ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያኝ ካህናት አይደለህ፤ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” የሚል ነበር፡፡ እርሱም ሲመልስ እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ፣ ከሰማይን? ወይስ በሰው ፈቃድ?” አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን፡፡ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅምብለው መለሱለት፤ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም፡፡አላቸው፡፡ ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፤ ልቦናቸው በክፋትና ጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡[ማቴ ፳፩፥፳፫፡፳፯]

ዳግመኛም ይህ ዕለት ጌታችን ስለዳግም ምጽአቱ ሰፊ ትምህርት የሰጠበት ዕለት ነው፡፡ [ማቴ ፳፬ እና ፳፭ እንዲሁም ማር ፲፪ እና ፲፫፣ ሉቃ ፳ እና ፳፩] ላይ የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሠንበቱ መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡

ዛሬም ቢሆን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊሆን እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን ዐሳባችን ከዓለም ዘንድ የተገላቢጦሽ ነገር እንደ ሚጠብቀን “ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው” የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ ይህ በመሆኑ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልን ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡፡

? ከሦስት ዓመታት በፊት ልክ በዚህ በሑዳዴ ጾም ነበር ከሺህ በላይ የሚቆጠሩት የዋልድባ ገዳም አባቶቻችን ለዘመናት ለመላዋ ኢትዮጵያ ፀሎት እያደረሱ ሲኖሩባት ከነበረችው ከታሪካዊቷ ገዳም በዳግማዊ ግራኝና ጭፍሮቹ እንዲባረሩ የተደረጉት። ኢትዮጵያዊ ነኝ! ክርስቲያን ነኝ! ” እያለ የሚኩራራው ግብዝ ግን እስካሁን ዝም ጭጭ በማለት የጠላቶቹን ኤዶማውያንን፣ እስማኤላውያንን፣ ጋላኦሮሞዎችን፣ ሻዕቢያንና ሕወሓትን ምኞት ተከትሎ ይጓዛል። ያኔ፤ አማራ ተው ወደ ትግራይ እንዳትዘምት፤ ተዋጊዎችም ሆነ ድጋፍ ለፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ በጭራሽ አትስጥ፤ ዋ!” ስንል ነበር። አስታውሳለሁ፤ ይህን በአንድ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በተሳተፉበት የቀጥታ ሥርጭት ወቅት ስናገር፤ ሻለቃው ያሽሟጥጡ ነበር፤ አማራ እርሱትን ማስመለስ አለበት!” ሲሉ ነበር። እኝህ ሰው በደርግ ጊዜ በትግራይና ኤርትራ በብዙ ሺህ ወገኖቻችን ለረሃብና ስደት እንዲጋለጡ ካደረጓቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ናቸው።

አሁንም የአማራ ኃይሎች የተባሉት፤ ግን ምናልባት የጋላኦሮሞ ሊሆኑ የሚችሉት፤ ኃይሎች ባፋጣኝ ከወልቃይት እና ራያ እንዲወጡ የአማራ ዕጣ ፈንታ የሚያሳስበው ወገን ሁሉ ዛሬውኑ ይወትውት፤ ዋ! ! ! እንላለን።

በሉሲፈራውያኑ ምዕራባውያን እጅ ውስጥ የገቡት ሻዕቢያ፣ ሕወሓትና ኦነግ/ኦህዴድ/ብልጽግና ፈጠነም ዘገየም አስገድደው እንዲያወጧችሁ ከመደረጋችሁ በፊት እራሳችሁ አስቀድማችሁ ብትወጡ ለራሳችሁም ትልቅ ድልና ክብር በሆነ ነበር። ብዙ ንጹሐን ለማዳን በቻላችሁ ነበር። አሁን ግን ኦሮማራ ልሂቆቻችሁ ሕዝባችሁን በድሮን ታስጨፈጭፉ ዘንድ በድጋሚ “ግፋ በለው፣ ወጥር! እርስትህን ትተህ የትም እንዳትሄድ! ቅብርጥሴ” በማለት ላይ ናቸው። እንግዲህ ቆሻሻው ዳግማዊ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ሆን ብሎ በእነዚህ ቅዱስ የሕማማት ቀናት ይህን አረሜኒያዊ አጀንዳ ይዞ የመጣው። የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ምዕራባውያኑ አማካሪዎቹ የሰጡትን ስክሪፕት ነው ተከትሎ የሚሄደው። ልሂቆቻችሁ፣ ፈሪሳውያን ካህናቶቻችሁ፣ መሪዎቻችሁና ሜዲያዎቻችሁ ሁሉ እኮ አማርኛ ተናጋሪ በሆኑ በጋላኦሮሞ እባቦች ቁጥጥር ሥር ናቸው። ተቃውሞ ሰልፎችንም የሚመሩት እነርሱው ናቸው፤ ምንም ውጤት እንዳያመጡ ተደርገው የተዘጋጁትን አሰልቺ መፈክሮችንም እነርሱ ናቸው በማሰማት ላይ ያሉት። መንጋው ግን እነርሱን ተከትሎ ይወጣል፣ የእነርሱን መፈክር እያሰማ ለድሮኖችን አደንዛዥና አድካሚ ጨረሮች እራሱን ያጋልጣል። የእነ አሜሪካና አረቦች ሳተላይቶችም በዚህ ወቅት ነው የማደንዘዣ ጨረሮቻቸውን የሚያፈነቅጡት። የተቃውሞ ሰልፍና አመጽ መካሄድ ያለበት በአዲስ አበባ ነው። በምዕራባውያኑ አረቦቹ የሚረዱት፣ የሚመከሩትና የሚረዱትና የሚመሩት እባቦቹ ጋላኦሮሞዎች ይህን ስለሚያውቁ ነው አማራውን ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ ያደረጉት።

ከአምስት ዓመታት በፊት የጋላኦሮሞን ተንኮል፣ ከሃዲነትና አረመኔነት በቅጡ ያልተረዳው አማራ፤ “የኦሮሞ ደም ደሜ ነው!” እያለ ላንቃው እስኪበጠስ ቅስቀሳዎችን በማድረግና ለተቃውሞ ሰልፎች በኢትዮጵያም በመላው ዓለምም በመውጣት ብዙ ደከመ፣ ልጆቹንም አስገበረ፤ አረመኔውን ጋላኦሮሞን ለማንገስ። ታዲያ ዛሬ ጋላኦሮሞ፤ “የአማራ ደም ደሜ ነው!” ብሎ ከአማራው ጎን ለመሰለፍ ፈቃደኝነቱንና ዝግጁነቱን ለማሳያት ይችላልን? በጭራሽ! የስጋ ማንነቱና ምንነቱ ፈጽሞ አይፈቅድለትምና።

አማራው ያኔ ከሁለት ዓመታት በፊት ከዳግማዊ ግራኝ ጎን በመሰለፍ ፈንታ፤ “የትግሬ ደም ደሜ ነው” ብሎ ከአክሱም ጽዮናውያን ጎን ቢሰለፍ ኖሮ የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ገና በእንጭጩ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተጠራርጎ በተወገደ ነበር። ግን ከመንፈሳዊ ማንነቱና ምንነቱ የስጋዊ ማንነቱና ምንነቱ በለጠበት። ይህ እስከሆነ ድረስ ባርነቱ፣ ስቃዩና ሞቱ ይቀጥላል።

የኢትዮጵያና ተዋሕዶ እምነቷ ቍ.፩ ታሪካዊ ጠላት ፳፯ ጥንታውያን የኢትዮጵያን ነገዶችን ከምድረ ገጽ ያጠፋቸው ጋላኦሮሞ ቢሆንም፤ የኦሮሞን ክህደት፣ ተንኮልና አረመኔነት ዛሬም ያልተረዳው አሻንጉሊት አማራ ግን ቍ.፩ የኢትዮጵያና ተዋሕዶ አፍራሽ ነው! ቶሎ ካልተመለሱ እንግዲህ ጉዳዩ መለኮታዊ ነው፤ ሁለቱም በሕዝብ ደረጃ ከእግዚአብሔር መንፈስ የራቁ አህዛብ ናቸውና ማንም ምንም የሚያድናቸው አይኖረም፤ እሳት ከሰማይ ይወርድባቸዋል!

የሚታየኝ ነገር አለ፤ ይህን አስቀድሜ ለማሳወቅ የበኩሌን ብዙ ደክሜአለሁ፤ አሁን ግን እጅግ በጣም አዝናለሁ!

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፭፥፵፩፡፵፫]

“በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል። እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።”

❖❖❖[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፭፥ ፴፩፡፴፬]❖❖❖

የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።”

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Orthodox Christians in Ethiopia celebrate Palm Sunday

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 29, 2024

🌴 ሆሣዕና በአርያም፤ በርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን 🌴

♱ Ethiopian Orthodox Christians celebrated Palm Sunday with prayers and a ceremony at the ornate Entoto Maryam Church outside Addis Ababa.

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሕማማተ እግዚእ ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 29, 2024

❖ ሕማማተ እግዚእ ክፍል ፩ | የቀናቱ ስም እና ትርጓሜ፣ ጸሎቱ፣ ግብረ ሕማማት ❖

የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ስያሜዎች ❖

  • ሰኞ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ፤ አንጽሖተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ሰኞ።
  • ማክሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን።
  • ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን።
  • ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ።
  • ዐርብ፤ የስቅለት ዐርብ።
  • ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ፡፡

❖❖❖[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩፥፲፱] ❖❖❖

“በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና። ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።”

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Russell Brand Announces Baptism: Many Returning To Christianity As World Crumbles

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 28, 2024

✞ ራስል ብራንድ ጥምቀትን አስታወቀ፡ ብዙዎች ወደ ክርስትና እንደ ዓለም ፍርፋሪ ይመለሳሉ

ታዋቂው የብሪታኒያ ተዋናይ እና ኮሜዲያን ራስል ብራንድ ለወራት ከዘለቀው መንፈሳዊ ጉዞ በኋላ በዛሬው የሆሣዕና እሑድ ዕለት እንደሚጠመቅ አስታወቀ

ዓለም እየፈራረስች ባለችበት በዚህ ወቅት ብዙዎች ወደ ክርስትና እየተመለሱ መሆናቸውን ራሰል የአርባ ስምንት/48 አመቱ ብራንድ በ X ላይ በለጠፈው ቪዲዮ ላይ ይናገራል።

ተዋናይ እና ኮሜዲያን ራስል ብራንድ በዚህ ቅዳሜና እሁድ እንደሚጠመቅ አሳውቋል ይህም ከክርስትና እምነት አስተምህሮ ጋር ለወራት በዘለቀ ተጋድሎ ካደረገ በኋላ ነው።

ብራንድ ጥምቀት ሲገለጽለት እንደሰማው እንዲህ ሲል ተናግሯል፤ “ለመሞት እና ለመወለድ እድል፤ ያለፈውን ትተን በገላትያ ውስጥ እንደተገለጸው በክርስቶስ ስም እንደገና ለመወለድ – እንደ ብሩህ እና የነቃ ሰው መኖር ትችላለህ፤ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና”።

✞ Russell Brand announces baptism after months-long spiritual journey: ‘Taking the plunge’

Brand says many returning to Christianity as world crumbles

Actor and comedian Russell Brand announced Friday that he is going to be baptized this weekend, the culmination of his months-long public wrestling with the tenets of Christianity.

“This Sunday, I’m taking the plunge,” Brand, 48, said in a video he posted to X. “I’m getting baptized.”

Brand said he had heard baptism explained to him as “an opportunity to die and be reborn; an opportunity to leave the past behind and be reborn in Christ’s name like it says in Galatians — that you can live as an enlightened and awakened person.”

He also referenced what he suggested were non-Christian reflections on the same theme of embracing death for the sake of life, quoting Stoic philosopher and Roman emperor Marcus Aurelius and the Buddha.

“All of these things seem so inviting and beautiful,” he said.

Brand also suggested that increasing numbers are turning back to Christianity as the empty value system of modernity disintegrates and leaves them wanting more.

“I know a lot of people are sort of cynical about the increasing interest in Christianity and the return to God, but to me, it’s obvious,” he said. “As meaning deteriorates in the modern world, as our value systems and institutions crumble, all of us become increasingly aware that there is this eerily familiar awakening and beckoning figure that we’ve all known all of our lives, within us and around us. And for me, it’s very exciting.”

Brand added that he intends to get baptized in the heavily polluted River Thames, joking that he might be also getting baptized in toxoplasmosis and E. coli.

“I may be leaving behind the sins, but I might be picking up some pretty serious viruses,” he said.

Brand’s baptism comes after other videos he has been making in recent months about his spiritual journey to the Christian faith.

In December, he told followers he was reading the Bible and The Problem of Pain, a 1940 book by C.S. Lewis that explores the role of suffering in the Christian life.

In January, he noted that he was reading Rick Warren’s The Purpose-Driven Life, and that he desired a “personal relationship with God” as he found Jesus Christ increasingly important as he grows older, despite once seeing many churches as either too “old-fashioned” or too modernized.

“The reason I wear a cross is because Christianity and, in particular, the figure of Christ, are, it seems to me, inevitably becoming more important as I become more familiar with suffering, purpose, self, and not-self,” he said at the time.

In March, he posted a video explaining that he had been visiting churches of various denominations with the intention of possibly getting baptized, and asked his followers their opinions on the sacrament.

During an interview with Tucker Carlson last year, Brand said, “Like many desperate people, I need spirituality. I need God, or I cannot cope in this world. I need to believe in the best in people.”

Acknowledging he “didn’t have enough self-discipline to resist the allure of stardom,” he said he “fell face-first into the glitter, and I’m only just pulling myself out now.”

Brand faces multiple allegations of sexual misconduct going back years, including one report that claims he assaulted a 16-year-old girl after pulling her into an “emotionally and sexually abusive” relationship.

Brand has denied the “very serious criminal allegations” and maintained that while he was “very, very promiscuous” in the past, all of his sexual relationships were “always consensual.”

Source

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሆሣዕና በአርያም፤ ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ እና አህዛብ አጋሮቻቸው በሰቀሏት የኢትዮጵያ ዘ-ነፍስ እናት በአክሱም ጽዮን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 28, 2024

🌴 ሰውን ከወደቀበት የበደል ጉድጓድ ያወጣው ዘንድ እግዚአብሔር ክንዱን ወደ ዓለም ላከ፡፡ ሰው ሆኖ የተገለጠው የእግዚአብሔር ክንድ በጉድጓድ ተጥሎ የነበረን በዚያም በሥጋ በነፍስ፤ በውስጥ በአፍአ ቆስሎ የነበረ አዳምን በትህትና ሁለተኛ አዳም ሆኖ በሥጋ የቆሰለውን በለበሰው ሥጋ ቆስሎ;በነፍስ የታመመውን በትምህርት አዳነ፡፡ ከእርሱ አስቀድሞ ሰውን ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከባርነት ወደ ነፃነት የሚያመጣ ባለመኖሩ እርሱ ሁሉን የፈጠረ ሁሉን የሚያኖር እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ለሰው መድኃኒት ሆነ፡፡ በሞቱም መድኃኒትነትን አሣየ፡፡ በነቢይ መድኃኒተ ፈነወ እግዚአብሔር ለሕዝቡ፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ መድኃኒትን ሰደደ፡፡ (መዝ.፻፲፥፱) ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፡፡

ክርስቶስ ባለ መድኃኒት ሆኖ በኃጢአት ለታመሙ ደቂቀ አዳም ሁሉ ሕይወትን ይሰጥ ዘንድ ወደዚህኛው ዓለም መጣ፡፡ በምድራዊ ሥርዓት እንደምናየው መድኃኒትና ባለ መድኃኒት እንደሚለያዩ አይደለም፡፡ ሁለቱንም እርሱ በመምጣቱ (ሰው በመሆኑ) ፈጸመ እንጂ፡፡ መድኃኒት አድርጎ ሥጋውን ደሙን የሰጠ እርሱ ነው፡፡ በካህናት አድሮ ሰው በንስሐ ሲመለስ መድኃኒት ወደሆነው ወደ ራሱ የሚመራ እርሱ ነው፡፡

ክርስቶስ መድኃኒት መሆኑ በሕማሙ እና በሞቱ ነው፡፡ በእመቤታችን ማኅፀን የተጀመረው የእርሱ መድኃኒትነት እና ፍቅሩ ፍፃሜውን ያገኘው በሕማሙ እና በሞቱ ነው፡፡ መሐሪ ንጉሥ እርሱ መሆኑን ይገልጥ ዘንድ በፈቃዱ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡ ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም ከመግባቱ አስቀድሞ ከኢየሩሳሌም ፲፮ ያህል ምዕራፍ በምትርቀው በቤተፋጌ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ነበር፡፡

ከደቀ መዛሙርቱም ሁለቱን (ማለትም ጴጥሮስን እና ዮሐንስን) በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ ወዲያውም ወደ እርሷ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበትን ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ፡፡ (ማር ፲፩፡፪) በማለት አዘዛቸው፡፡ ዳግመኛም ሰው ወዳልገባባት የተዘጋች የምሥራቅ ደጅ ወደ ምትባል ወደ ድንግል መጥቶ ዘጠኝ ወር ማኅፀኗን ከተማ አድርጎ እንደኖረ፤ ማኅየዊት ከምትሆን ሕማሙ በኋላም ሰው ባልተቀበረበት መቃብር እንደተቀበረ፤ አሁንም ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባት ማንም ሰው ያልተቀመጠባቸውን በሌላ መንደር የሚገኙ አህያንና ውርንጫን እንዲያመጡ ደቀመዛሙርቱን አዘዘ፡፡

የፍጥረት ሁሉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በልደቱ እስትንፋሷን የገበረችለትን አህያ አሁን ደግሞ በፈቃዱ ስለ ሰው ሁሉ ሊሞት ሲል ንጉሥነቱን ሊያስመሰክርባት ወደደ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ካለው ፲፮ ምዕራፍ አሥራ አራቱን በአህያ ላይ ሳይቀመጥ በእግሩ ሄደ፡፡ ከዚያም ሁለቱን ምዕራፍ በአህያ ላይ በመቀመጥ ከተጓዘ በኋላ የኢየሩሳሌምን መቅደስ ሦስት ጊዜ በውርጫዋ ላይ በመሆን ዞረ፡፡ በዚህም ለሰው ሁሉ ያለው ቸርነቱ፣ ሕግ የተሰጣቸው አይሁድ እና ሕግ ያልተሰጣቸው አሕዛብ ላይ እኩል ቀንበርን መጫን እንዳይገባ አጠየቀ፡፡

ወደ ኢየሩሳሌምም ሲሄድ ብዙ ሰዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፣ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቆረጡ ያነጥፉ ነበር፡፡ (ማር. ፲፩፡፰)፡፡ ከዚያም ሰዎች ሆሣዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው (ማር. ፲፩፡፱) በማለት አመሰገኑ፡፡ ይህም ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን እኛ ክርስቲያኖች ቡሩክ ስሙ ለእግዚብሔር ወቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር፤ የእግዚአብሔር ስሙ ምስጉን ነው፡፡ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ ክርስቶስም ምስጉን ነው በማለት የአብ እና የወልድን መስተካከልን ገልጸን ጌታን እናመሰግናለን፡፡ ጌታን የሚከተሉት ሰዎች ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር (ማር.11፲፩፡፲) ይኸውም በልዕልና፣ በሰማይ ያለ መድኃኒት፣ ከሰማይ የመጣ መድኃኒት ማለት ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅር እና መሓሪ መሆን በክርስቶስ ሕማም እና ሞት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተገልጧል፡፡ ክርስቶስ የተቀበለው ሕማም እና ሞት የእርሱን አምላክነት እና ንጉሥነት አልሸሸገውም፡፡ እንደውም ዙፋኑን መስቀል በማድረግ ንጉሥነቱን በመድኃኒትነቱ ገልጿል እንጂ፡፡ በነቢይ እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር፣ እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፤ በምድር መካከልም መድኃኒትን አደረገ መዝ. ፸፫፤፲፪ ተብሎ የተነገረው እግዚአሔብር ድኅነትን በፈጸመበት ማዕከለ ምድር ሲሰቀል በመድኀኒትነቱ ንጉሥነቱን መግለጡን ያመለክታል፡፡ ዳግመኛም አንሰ ተሰየምኩ ንጉሠ በላዕሌሆሙ በጽዮን በደብረ መቅደሱ፤ እኔ ንጉሥ ሆኜ ተሸምኩ በተቀደሰው ተራራ ላይ(መዝ.፪፡፮) ተብሎ የተነገረው ኦርቶዶክሳውያን አበው እነርሱ (አይሁድ) ሰቅለነው ገድለነው ኋላ ፈርሶ በስብሶ ይቀራል ይሉኛል እንጂ እኔ ደብረ መቅደስ በምትባል በመስቀል ላይ ነግሻለሁ በማለት ይተረጉሙታል፡፡

ጌታ ንግሥናው ክብሩ የተገለጠበት ሆነ እንጂ መታመሙ እና መሞቱ ውርደት ክብሩንም የሚሸሽግ አይደለም፡፡ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ይትባረክ እግዚአብሔር ዘሰመየ ሕማማት ወልዱ ክብረ ወስብሐት፣ የልጁን ሕማማት ክብርና ምስጋና አድርጎ የሰየመ እግዚአብሔር ይመስገን አለ፡፡ እኛን ያከበረበት በመሆኑ ሕማሙ ክብር እንደተባለ እናስተውል፡፡ በመስቀል ላይ ሆኖም በቀኝ የተሠቀለው ወንበዴ አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ (ሉቃ ፳፬ )በማለት ንጉሥነቱ መስክሮለታል፡፡ ለዚህ ነው ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም በምስጋና መግባቱ መድኃኒትነቱን እና ንጉሥነቱን ያሳያል ያልነው፡፡ ዳግመኛም ሁሉን የያዘ ጌታ በአህያ ላይ መቀመጡ ትህትናው ያስረዳል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል ዲባ ዕዋለ አድግ ነበረ፡፡ በማለት ሰማያዊ ልዑል አምላክ ትሑት ሆኖ እንደተገለጠ ተናገረ፡፡

ጌታ ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ድንቅ የሆኑ እና ተአምራትን ለሰዎች አሳየ (ገለጠ)፡፡ እም ሆሳዕናሁ አርአያ ተአምረ ወመንክረ (ቅዳ. ጎርጎ.ዘኑሲስ) እንዲል፡፡ ይኸውም በአህያ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አእምሮ ጠባይዕ ያልቀናላቸው ሕፃናት ዕውቀት ተገልጾላቸው ሆሳዕና በአርያም እያሉ ጌታ በማመስገናቸው ነው፡፡ ዳግመኛም በከሃሊነቱ መናገር ለማይችሉ ዕውቀት ለሌላቸው ድንጋዮች ዕውቀት ተሰጥቷቸው መናገር ችለው ጌታን አመስግነዋል፡፡ እርሱ የባሕርይ አምላክ መሆኑ በሰውነቱም ቀድሞ በበደል ምክንያት ለሰው ከመገዛት ውጪ የሆኑ ፍጥረታት ዳግመኛ በሥጋዌ ለሰው እንደተገዙ ከዚህ ሁሉ ማስተዋል ይገባል፡፡

ጌታ ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ልጅነት እና ተአምራት ማድረግን ገለጸ፡፡ እም ሆሳዕናሁ አርአያ ጸጋ ወኅይለ እንዲል (ቅዳሴ ጎርጎ. ዘኑሲስ)፡፡ የእርሱ ማዳን ከሰው ተወስዶበት የነበረ የጸጋ ልጅነት እንዲመለስለት አድርጋ በልጅነት ላይ ገቢረ ተአምራት (ተአምራትን ማድረግ) ገልጿል፡፡ ይኸውም እርሱ በረድኤት አድሮባቸው ድንቅ ተአምራትን ለሚያደርጉ ቅዱሳን መሠረት ነው፡፡ በተጨማሪም ልጅነትን ካገኙ በኋላ በበደል ሲገኙ ለንስሓ የሚሆን እንባን ሠጠ፡፡ እምሆሳዕናሁ ወሀበ ፈልፈለ አንብዕ ለኅጥአን እንዲል (ቅዳሴ ጎርጎ. ዘኑሲስ) ይኸውም የበደሉትን ያከብራቸው ዘንድ፣ ኀጥአንን ከኃጢአታቸው ያነጻቸው ዘንድ እንዲሁም የሳቱትን በንስሐ ይመልሳቸው ዘንድ ነው፡፡

ዳግመኛም ጌታ መድኀኒት ከመሆኑ የተነሣ ለዕውራን ዳግመኛ ብርሃንን ሰጠ፡፡ ይኸውም ለጊዜው በተፈጥሮ ዐይን ተሰጥቷቸው የታወሩትን ፈውሶ በሥጋ ብርሃን መስጠቱ ሲሆን፤ ፍጻሜው ግን በነፍስ ዕውቀትን ከማጣት የተነሣ ዕውራን የነበሩትን ትምህርትን; ዕውቀትን ገለጸላቸው፡፡ ይኸውም የእርሱ ገንዘቡ ስለሚሆን አንድነት ሦስትነት፣ አምላክነቱን መድኃኒት መሆኑን ገለጠላቸው ማለት ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት) ፍጹም ፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 21, 2024

  • ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው። ዮሐንስ ፫፥፩
  • ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው። ዮሐንስ ፫፥፩
  • ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው። ዮሐንስ ፫፥፲
  • ኒቆዲሞስ ምሑረ ኦሪት ነው። ዮሐንስ ፯፥፶፩

ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል፡: ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል። (ዮሐ ፩–፪)

በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ እግዚአብሔርነት ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር ”አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሳ መርምርና እይ“ አሉት እንጂ አልተቀበሉትም። ዮሐ ፯፥፵፰–፶፪። ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ”ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ። ዮሐ ፲፱፥፴፱። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል።

የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ­ የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ ዮሐንስ ፫፤፪

ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው በሌሊት ወደ ጌታ እየሄደ ይማር ነበር ኒቆዲሞስ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ ?

/ ኒቆዲሞስ መምህር ስለነበር ስማር ሰዎች ቢያዩኝ ውዳሴ ከንቱ መምህር መባል ይቀርብኛል ብሎ ነው እኛስ ዛሬ የዘላለም ህይወት የሚሰጠንን ቅዱስ ቃል በትህትና መማር ሲገባን ለምድራዊ ክብር ብለን በቀን ጊዜያችን መማር ያልቻልን ስንቶቻችን ነን ስለዚህ ቀን ጊዜአችንን በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።

ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችና › ዮሐንስ ፱፤፬

/ .ኒቆዲሞስ የአይሁድ መምህር ስለነበር እንዳያዩት ፈርቶ ሌሊት እየመጣ ይማር ነበር እኛስ ዛሬ ልባችን የተረዳውን እውነት በግልጥ እንዳንፈጽም በፍራቻ በይሉኝታ የምንሰውር ስንቶቻችን ነን

ፍጹም ፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና› ፩ ዮሐንስ ፬፤፲፰ ፍርሃትን አስወግደን ለእውነት ልንቆም ይገባል።

/ ኒቆዲሞስ ከቀን ልብ ይልቅ የሌሊት ልብ የተካተተ ስለሆነ በሙሉ ልቡ በማስተዋል ለመማር ስለፈለገ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የማታውን መረጠ ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል ከልብ ሆነን የምንማር የሰማነው ቅዱስ ቃል በህይወታችን ፍሬ እንዲያፈራ ቅዱስ ቃሉን ከልብ ሆነን በማስተዋል ልንሰማ ይገባናል ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ልብ መልካም መሬት ተብⶀል

በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው› ማቴ ፲፫፡፳፫

አንዳንዶቻችን ጸሎት እያደረግን እንኳን አንደበታችን የእግዚአብሄርን ቃል ይነዳል ልባችን ሌላ ቦታ ይንጎዳጎዳል በማህበር ጸሎትም አብረን እየጸልይን በመሃል ሳይን አውት አርገን ልክ ሲፈጸም አለቀ እንዴ ብለን ሳይን ኢን የምናደርግ አንጠፋም።

/ ሌሊት ጨለማ ነው ብርሃን የለም ይህም የኃጢአት ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስ በሌሊት መምጣቱ በኃጢአት እንዳለ ንስሃ እንደሚፈግ ያስረዳናል ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን ስንሰማ በተአምኖ ኃጢአት በንስሃ ውስጥ ሆነን የምንሰማ ያለንስሃ የምንሰማው ቃል በህይወታችን ፍሬ የማፍራት እድሉ ጠባብ ነው ምክንያቱም በንስሃ ከልባችን ያልጸዱት ክፉ ምኞቶች እንደ እሾህ ሆነው ያንቁታልና

ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ እሾህም ወጣና አነቀው› ማቴ ፲፫፤፰ ተብሎ የተጻፈው ለዚህ ነው።

/ ሌሊት የቆየው ኪዳን ወይም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስም እኔ ምሁረ ኦሪት እንጂ ምሁረ ወንጌል አይደለሁም ወንጌልን ካንተ እማር ዘንድ ያስፈልገኛል ሲል በሌሊት ይመጣ ነበር ብሉያት ከሓዲሳት ጋር ተዋህደው ሲተረጎሙ ሰሙና ወርቁ ተጣምሮ የሕይወት ትምህርት ያስገኛል አንዳንዶች ዛሬ ብሉያት ጭራሽ አያስፈልጉም ሲሉ ይደመጣሉ ነገር ግን እንደ ኒቆዲሞስ ሁለቱን ኪዳናት አዋህዶ መጓዝ ትክክለኛው መንገድ ነው ለዚህም ነው ጌታ ሲያስተምር‹እውነት እላችኋለው ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከህግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ አታልፍም› ማቴ ፭፤፲፰ በማለት አበክሮ የተናገረው ኒቆዲሞስ ምንም እንኳን የቀኑ ክፍለ ጊዜ ባይመቸውም በሌሊቱ ሰአት ለመማር ችⶀል እኛም ከሱ ተምረን ከልብ ካለቀሱ እንባ አይጠፋምና ምንም ስራ ቢበዛብን ለቅዱስ ቃሉ ጊዜ አይጠፋምና ህይወት ለሚገኝበት ትምህርት ጊዜ ልንሰት ይገባል።

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Jerusalem Mount of Olives: Ethiopian Christians Celebrate the 5th Sunday of the Great Lent | ደብረ ዘይት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 7, 2024

የዐቢይ ጾም ፭ተኛ ሳምንት ደብረ ዘይት

የክርስቶስ ዳግም ምጽአት መቼ ነው የሚሆነው?

እንኳን ለደብረዘይት በዓል አደረሰን!

😮 በነገው ዕለት በተለይ በአሜሪካ በሚከሰተው/ በሚጠበቀው የፀሐይ ግርዶሽ ክስተት ዋዜማ፤ ደብረ ዘይት? ዋው! ሌላ አስገራሚ ክስተት አለ፤ ጊዜ ስላጠረኝ እና ‘ነገሮች’ ኮፒውተሬን እየዘጉ ብዙ ስለተፈታተኑኝ በነገው ዕለት አቀርበዋለሁ

ደብረ ዘይት በግዕዝ ልሣን ደብረዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት ነው። ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:-ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሰረት ነገረ ምጽአቱን (የመምጣቱን ነገር) እንድናስታዉስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነዉ።

በዚያ ልማድ መሠረት ጌታችን ዓለምን ለማሳለፍ ደግሞ የሚመጣበትን ምልክትና ጠቋሚ ነገር ምን ምን እንደሆነ፣ እርሱ ከመምጣቱ በፊት በዓለም ላይ ምን፥ ምን እንደሚደረግና ምን እንደሚታይ ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ነው። (ማቴ. ፳፬፥፩፡፶፩) ስለ ዓለም ሁሉ ቤዛ ለመሆን በሚሰቀልበት ቀን ዋዜማ ማለት በትልቁ ሐሙስ (ጸሎተ ሐሙስ) በለበሰው ሥጋ የጸለየው ከደብረ ዘይት ጋር ተያይዞ በሚገኘው ቦታ በጌተሴማኒ ነበር። (ማቴ. ፳፮፥፴፮) በኃላ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላም ለደቀመዛሙርቱ እንዲነግሩ ሲልካቸው፥ “ሂዱና ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፥ በዚያም ታዩኛላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው፥” ብሎ የላካቸው በደብረ ዘይት ገሊላ ተብላ ትጠራ ወደ ነበረችው ቦታ ነው። (ማቴ. ፳፰፥፱) ገሊላውያን ወደ ኤየሩሳሌም ሲመጡ በደብረ ዘይት ያርፍ ነበርና እነሱ ሲያርፉባት የነበረችው ቦታ ገሊላ እየተባለች ትጠራ ነበር። መድኃኔዓለም ክርስቶስ የድኅነት ሥራ ፈጽሞ ወደ ሰማይ ያረገው ከዚህ ተራራ ተነሥቶ ነው። (ሐዋ. ፩፥፲፪) ቀደም ብሎም የሆሳእናው የመድኃኔዓለም አስደናቂ ጉዞ የተጀመረው ከደብረ ዘይት ሥር ነበር። (ማቴ. ፳፩፥፩፡፲፮)

ደብረዘይት ምሳሌነቱ ይህች ቤተክርስቲያን ናት፣ ደብረዘይት የኦርቶዶክሳውያን ተራራ፣ የእግዚአብሔር ቃል የሚነገርባት፣ መሠረታዊ ሐይማኖት የምንማርባት፣ ካሕናት የሚሠፍሩባት፣ ምዕመናን የሚገናኙባት፣ እግዚአብሔርን የምንወድ ሁሉ የምንሰባሰብባት አማናዊት ደብረ ዘይት ቤተክርስቲያን ናት።

ትልቁ መሠረተ ልማት የሰው ልጅ ነው፤ ቁሳቁሱን፣ ድንጋይና ድንጋይ፣ አሸዋና ሲሚንቶ ማቀላቀል አይደለም”

ሰውን ከእግዚአብሔር ከሚለየው አጉል ሰላም ይልቅ ከእግዚአብሔር የማይለየው ጦርነት ይሻላል፤ ስሜታዊ ከሆነና ለቤተ ክርስቲያን ዘለቄታዊ ጉዳት ከሚኖረው ስምምነትና አንድነት ይልቅ ስለ ሐይማኖት መጠበቅ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ የሚኖረውና ለዚህ ሲባል የሚሆን አለመስማማት ይሻላል፡፡” ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

🔥 ኢትዮጵያዊቷን የ ደብረዘይትከተማን ቢሸፍቱበማለት እራሳቸውን ከ ፍዬል ሕዝብ 🐐 የመደቡት ከሃዲዎቹና የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ጋላ-ኦሮሞዎች የትንቢት መፈጸሚያ ይሆናሉ

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »