Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Pharisees’

አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2023

😇 በተለይ በዚህ ዘመን አባታችን፣ ካኽናችን፣ ፓትርያርካችን፣ መምህራችንና መሪያችን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።

💭 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው። ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል። ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ። ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም። ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በገበያም ሰላምታና። መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ። እናንተ ግን። መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ። አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም። አባት ብላችሁ አትጥሩ።

❖❖❖[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፫]❖❖❖

፩ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው።

፪ ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።

፫ ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ።

፬ ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም።

፭ ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፥

፮ በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥

፯ በገበያም ሰላምታና። መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።

፰ እናንተ ግን። መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።

፱ አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም። አባት ብላችሁ አትጥሩ።

፲ ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና። ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ።

፲፩ ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል።

፲፪ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።

፲፫ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።

፲፬ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።

፲፭ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ።

፲፮ እናንተ። ማንም በቤተ መቅደስ የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በቤተ መቅደስ ወርቅ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል የምትሉ፥ ዕውሮች መሪዎች፥ ወዮላችሁ።

፲፯ እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ?

፲፰ ደግማችሁም። ማንም በመሠዊያው የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በላዩ ባለው መባ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል ትላላችሁ።

፲፱ እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?

፳ እንግዲህ በመሠዊያው የሚምለው በእርሱና በእርሱ ላይ ባለው ሁሉ ይምላል፤

፳፩ በቤተ መቅደስም የሚምለው በእርሱና በእርሱ በሚኖረው ይምላል፤

፳፪ በሰማይም የሚምለው በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል።

፳፫ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።

፳፬ እናንተ ዕውሮች መሪዎች፥ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ።

፳፭ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ።

፳፮ አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ።

፳፯ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።

፳፰ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ፥ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኝነት ሞልቶባችኋል።

፳፱ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ የጻድቃንንም መቃብር ስለምታስጌጡና።

፴ በአባቶቻችን ዘመን ኖረን በሆነስ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር ስለምትሉ፥ ወዮላችሁ።

፴፩ እንግዲያስ የነቢያት ገዳዮች ልጆች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ ትመሰክራላችሁ።

፴፪ እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ።

፴፫ እናንተ እባቦች፥ የእፉኝት ልጆች፥ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?

፴፬ ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤

፴፭ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።

፴፮ እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል።

፴፯ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።

፴፰ እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።

፴፱ እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።

______________

Posted in Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Church of England Considers Abandoning Christianity | የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን ክርስትናን መተው ታስባለች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 11, 2023

ፖለቲከኞቹና ከሃዲዎቹ ፓርቲዎች ጦርነት ቀስቅሰው ከሚሊየን በላይ ክርስቲያን ወገኖቼን ከጨረሱ በኋላ፤ “ለድርድር ተቀመጥን፣ ታረቅን” ብለው ሕዝቡን ለማታለል እንደሞከሩት የሃይማኖት ተቋማቱም በተመሳሳይ መልክ ቀጣዩን ድራማ ሠርተውና ምናልባት በብዙ ሚሊየን ዜጎች እንዲያልቁ ካደረጉ በኋላ፤ “እንደራደር! አንድ እንሁን፤ ሰላምና እርቅ አመጣን!” እንደሚሉን ለሰከንድ አልጠራጠረም።”

💭 አንድ በአንድ ነው የሚደረገው፦

የቪዲዮው ምስል፤ ከሰባት አመታት በፊት ቆሻሻው አርቲስት ፔት ዶህርቲ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መስሎ የሚያሳይ ምስል በለንደን ጎዳናዎች ላይ እንዲታይ ተደርጎ ነበር። በእርግጥ ይህ ለክርስቲያኖች ትልቅ ስድብ ነው!

💭 It’s done one at a time:

The image thumbnail: Seven years ago, a statue of Pete Doherty posing as Christ on the Cross went on view in London. Surely this is blasphemous! The raucous, wild-living pop star as Jesus, his sufferings in the media equated with the passion of Christ, his naked flesh nailed up as if he were the son of God? Shame of you, leaders of the Church of England! Surely this is too much to take!

🛑 በመምከር ላይ ያሉት የዛሬዋ የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን መሪዎች ተልዕኮ፤

👉 ፩ኛ. የአንግሊካን ቄሶች የተመሳሳይ ጾታ ሠርግ እና የሲቪል ሽርክናዎችን እንዲባርኩ ለማድረግ። ግብረ ሰዶማውያን እና ሌዝቢያን ሰርግ በቤተክርስቲያን ውስጥ ቢከለከሉም በረከቶቹ ግን እንዲሰጡ ይደረጋሉ።

👉 ፪ኛ. ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የቤተክርስቲያና ሲኖድ ስብሰባ ላይ የወጣው ትልቁ የዜና ታሪክ አንዳንድ የእንግሊዝ ቤተክርስትያን ውስጥ የሚገኙ መሪዎች ከፆታገለልተኛ ወይም የሴት አማራጮችን በመጠቀም ለ 2000 ዓመታት የቆዩ ማጣቀሻዎች እግዚአብሔርን እርሱእሱወይም አባትየሚሉትን ቃላት ቤተክርስቲያኗ እንዳትጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።

እግዚኦ! እግዚኦ! እግዚኦ!

🛑 በሃገራችንም ተመሳሳይ ሁኔታ እየታየ ይመስላል፤ ቤተ ክህነት የችግሩ አካል ናት! ወኔያችሁን በመቀስቀስ ተስፋ ይሰጧችሁና በበነገታው በበረዶ ሻወር ኩምሽሽ፣ እራሳችሁን፣ ማንነታችሁን፣ ሃገራችሁንና ቤተክርስቲያናችሁን እንድትጠሉ ያደርጓችኋል። በአክሱም ጽዮን ላይ የተከፈተው የዘር ማጥፋት ዋናው ተልዕኮ ይህ ነው።

👉 ዛሬም፤ “መንግስት ጥሩ ሲሠራ እናመሰግናለን፤ ሲያጠፋ እናወግዘዋለን፤ ይህን ለተከበሩ ጠቅላያችንአሳውቀናቸዋል…” አሉን፤ ፈሪሳዊው አቡነአብርሃም። እግዚኦ!

‘የቤተክርስቲያን አባቶች’ የሚባለው ነገር ያለቀለት የመስከረም ፬/4 ፡ ፳፻፲፪/2012ቱ ሰልፍ ተቃውሞ ሰልፍ እንዲሠረዝ ሲደረግ ነው። ያኔ በዝቅጠኛ ደረጃ ነበር “ሲደራደሩ” የነበሩት፤ አሁን ግን በከፍተኛ ደረጃ ነው። በወቅቱ መስከረም ፬ ተጠርቶ ለነበረው ተቃውሞ ሰልፍ ወደ አዲስ አበባ ደስ እያለኝ አምርቼ ነበር፤ ምንም ሳላመነታ ከቤተሰብ አባላት ጋር ሆኜ በመስቀል አደባባይ ተገኝቼ ነበር፤ ግን ልክ እንደዛሬው፤ “ተስማምተናል፣ ታርቀናልና ሰልፉ ቀርቷል!” ሲባል ምን ያህል እንዳዘንኩና፤ እንደተቆጣሁና “አባቶች” በተባሉት ተስፋ እንደቆረጥኩ ለመናገር ከብዶኝ ነበር። “ባፋጣኝ ወኔ ቀስቃሽ ሰልፍ በአዲስ አበባ ካልተደረገ ጭፍጨፋው ይቀጥላል!” በማለት በወቅቱ አውስቼ ነበር።

የዛሬዋ ቤተክህነት (የትግራይን ጨምሮ) በፈሪሳውያን የተሞላች ናት። ከአንዴም፣ ሁለቴም ሦስቴም አይተነዋል። ምንም አዲስ ነገር የለም! ቤተ ክርስቲያንና ሃገርን የመበታተን፣ ሕዝበ ክርስቲያኑን የማስጨረሱ ሤራ ይቀጥላል።

😇 በዚህ ዘመን አባታችን፣ ካኽናችን፣ ፓትርያርካችና መሪያችን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው

የሩሲያ፣ ቡልጋሪያ እና ሰርቢያ መሪዎች የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርኮቻቸውን ለመማጸን ወደ ሲኖዶሱ ያመራሉ፤ የእኛዎቹ ደግሞ የ፩ ሚሊየን ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን ደም እንደ ከልብ ያፈሰሰውን አረመኔ ለመለመን ወደ ቤተ ፒኮክ ይገባሉ። እግዚኦ!

ከ፩ ሚሊየን በላይ አክሱም ጽዮናውያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን ከጨፈጨፈው አረመኔ ጋር ለስብሰባ መቀመጥስ ተገቢ ነውን? ምን ዓይነት ቅሌት ነው?!

👉አሁን ሁሉም የዛሬውን ዕለት የሜዲያዎች ውጥንቅጥ የሆነና የተመሰቃቀል መገኘት በጥሞና ይከታተል። ካድሬዎቻቸው መጽሐፍ ቅዱስን እየጠቀሱ ሞኙን የተዋሕዶ በግ እያስተኙ ወደገደል ይመሩት ዘንድ በደንብ አዘጋጅተዋቸዋል።

ከሳምንት በፊት ሲናገሩ የነበሩትን ዛሬ የማይደግሙት እንዲያውም የሚቃረኑት ጋላ-ኦሮሞዎቹን እና ኦሮማራዎቹን እነ ዘመድኩን በቀለን፣ ‘መምህር ፋንታሁን ዋቄን፣ ‘ዲያቆን አባይነህ ካሴን፣ እንዲሁም ‘አቡነ’ ናትናኤልን ወጥተው እንዲለፈልፉ ያደርጓቸዋል። በጣም የሚገርም ነው ሜዲያውን ሁሉ የተቆጣጠሩት አማርኛ ተናጋሪ ጋላ-ኦሮሞውችና ኦሮማራዎች ናቸው። ጊዜው ያስገድደናል፣ በጣምም አስፈላጊ ነውና ጎሣዊ ማንነታቸውን እንመርምር! እርስበርስ እንጂ አክሱም ጽዮናውያንን በሁለት ዓመት አንዴ ለማዋረድና ለማቅለል ካልሆነ በጭራሽ አይጋብዟቸውም። ይህን በንደንብ እናስተውል።

ከሳምንት በፊት የወንጀለኛው ‘ኦሮማራ360’ ሜዲያ አባል እባቡ ጋላ-ኦሮሞ ኤርሚያስ ለገሰ ከሁለት ዓመት በኋላ ሞኙን ቴዎድሮስ ጸጋየን ለመጀመሪያ ጊዜ ልክ እንደጋበዘው ወዲያው ያተኮረው በሁኔታዎች ላይ ሳይሆን በቴዎድሮስ ብሔር እና ግለሰባዊ ማንነት ላይ ነው። ልክ የዘር ማጥፋት ጦርነት በጀመረ ማግስት ሲመረምሩትና ሊያዋርዱት ሲሞክሩ እንደነበሩት። ቴዎድሮስ ፀጋዬ በዚህ ወንጀለኛ ሜዲያ ላይ ቀርቦ እራሱን በማቅለሉ በጣም አዝኜበታለሁ።

አብዛኛው ክርስቲያን የሆነ ሕዝብ በሚኖርባት አገር አህዛብ እና መናፍቃን ይህን ያህል ሲጫወቱብን ማየት ትልቅ ቅሌት ነው! ምን ብናጠፋ ነው? ብለን እንጠይቅ!

👉 ከሳምንት በፊት ይህን ጽፌ ነበር፤ አሁን ያው እያየነው ነው፤

💭 እስራኤል እና ሱዳን የሰላም ስምምነት ለመፈራረም ተስማሙ | ሞሮኮውያን በተቃራኒው አገራቸው ከእስራኤል ጋር መደበኛ ግኑኝነት በመጀመሯ ተቃውሞ አሰሙ።

የኢትዮጵያን ግዛት ቆርሶ ለሱዳን አሳልፎ የሰጠውና በክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ላይ በታሪክ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ ግፍ፣ ወንጀልና ጭፍጨፋ የፈጸመው የፋሺስቱ ጋላኦሮሞ አገዛዝ ቁንጮ አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊም ከግብጽ ቀጥሎ ሰሞኑን ወደ ሱዳን፣ ኤሚራቶችና ሶማሊያ አምርቶ ነበር። ባፋጣኝ መወገድ የሚገባው የጋላኦሮሞው አገዛዝ ምን እንዳቀደና ምን እየተገበረ እንደሆነ በግልጽ እያየነው ነው፤ ነገር ግን በእስራኤል በኩል የጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያም ኔተንያሁ መንግስት ከዚህ ቆሻሻ መንግስት ጋር ዛሬም መሞዳሞዱን የሚቀጥል ከሆነ በእስራኤል ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መቅሰፍት ሊያስከትል እንደሚችል የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል።

አዎ! እስራኤል ሶስተኛውን የሰለሞን ቤተመቅደስ በኢየሩሳሌም ለመገንባት ታቦተ ጽዮንን ትፈልገዋለች። ጽላተ ሙሴን ካገኘንና ዛሬ በእየሩሳሌም ከተማ የሞርያን ኮረብታ ላይ የሚገኙትን የድንጋይ ጉልላት እና የአላቅሳ መስጊዶችን ካፈረስን በኋላ ነው ሦስተኛውን ቤተመቅደስ መገንባት የምንችለው የሚል እምነት አላቸው አክራሪዎቹ አይሁዶች። እንደነሱ ከሆነ የምጽዓት ሕልማቸውን እውን ለማድረግ እነዚህ ሁኔታዎች ለዓለም ፍጻሜ እንደ መቅደሚያ መከሰት አለባቸው።

መሀመዳውያኑ(ሺዓ ሙስሊሞች/ ኢራን)ደግሞ “የተደበቀው ኢማም (መህዲ) የቃል ኪዳኑን ታቦት አውጥቶ ወደ ኢየሩሳሌም መቅደሱ ተራራ መመለስ አለበት” ብለው ያምናሉ። በሺዓ ወግ ፣ በክፉና መልካም፣ በጥሩና መጥፎ መካከል በመጨረሻው ዘመን ጦርነት የሚካሄድ ነው። ይህም በኢራን ውስጥ ይተረጎማል ። እንደ የሺዓ እስላም ተረተረተኞች ከሆነ ጦርነቱ ከምዕራቡ ዓለም እና ከአይሁድ እምነት ተከታዮች ጋር ነው የሚካሄደው።

በአክራሪ የመሠረታዊ ፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ዘንድ ደግሞ የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍን ይጠቅሳሉ፤ ይህም የፍርድ ቀን ምልክቶች አንዱ የቃል ኪዳኑ ታቦት መምጣትና መመለስ ነው። እነዚህ ምዕራባውያን ተቋማት ታቦተ ጽዮንን ማግኘት እና መቆጣጠር፣ “ያለምንም ጥርጥር ለመጨረሻው አስከፊ ትግል ማበረታቻ ጥቅም ላይ ይውላል” ብለው ያምናሉ።

ሦስቱም ኃይሎች በሻዕቢያ፣ ሕወሓትና ብልጽግና/ኦነግ ከሃዲ ወኪሎቻቸው አማካኝነት ዛሬ በአክሱም ጽዮን ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነት የሚያካሄዱበት ዋናው ምክኒያት ይህ ነው። ነገር ግን ወዮላቸው! ላለፉት አምስት መቶ/ መቶ ሰላሳ/ ሦስት ዓመታት አክሱም ጽዮናውያን የታቦተ ጽዮን ጠባቂዎችን ከጠላት ጋር አብረው በማጥቃት ላይ ያሉ ኢትዮጵያ ዘስጋም ወዮላቸው! “የዚህ ሲኖዶስ፣ የዚያ ሲኖዶስ” በማለት አጀንዳና ድራማ እየፈጠሩ ከፈጸሟቸው ግፎችና ወንጀሎች ለመሸሽና ሕዝቡንም ለማታለል የሚያደርጉት ሙከራ በእግዚአብሔር ዘንድ ተጨማሪ ቁጣ ነው የሚያመጣባቸው። ፖለቲከኞቹና ከሃዲዎቹ ፓርቲዎች ጦርነት ቀስቅሰው ከሚሊየን በላይ ክርስቲያን ወገኖቼን ከጨረሱ በኋላ፤ “ለድርድር ተቀመጥን፣ ታረቅን” ብለው ሕዝቡን ለማታለል እንደሞከሩት የሃይማኖት ተቋማቱም በተመሳሳይ መልክ ቀጣዩን ድራማ ሠርተውና ምናልባት በብዙ ሚሊየን ዜጎች እንዲያልቁ ካደረጉ በኋላ፤ “እንደራደር! አንድ እንሁን፤ ሰላምና እርቅ አመጣን!” እንደሚሉን ለሰከንድ አልጠራጠረም። እያየነውና እየሰማነው እኮ ነው። ለምሳሌው የማይመቹኝ ኦሮሙማው ጳጳስአቡነ ናትናኤል፤ ሰሞኑን፤ “ሀይማኖቴ አትከፈልም!” ሲሉ ሰምተናል። ለመሆኑ ይህን ዓይነት ንግግር ከማን ነው የሰማነው? አዎ! ከአረመኔው ኦሮሞ ከግራኝ አብዮት አህመድ አሊ፤ “ኢትዮጵያ አትፈርስም! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አትፈርስም!” እያለን አይደለም። አይይይ!

በእውነት እኔ በእነርሱ ቦታ ብሆን ኖሮ “በቃኝ!” ብዬና ተንበርክኬ ቀን ተሌት እያነባሁ የአክሱም ኢትዮጵያውያንን ይቅርታ በጠየቅኩ ነበር። ንሰሐ በገባሁና አዲስ ሰው ለመሆን በተጋሁ ነበር። ጊዜውና አጋጣሚው እያመለጣቸው ነው፤ እንደው ቢጎብዙና መዳን ቢፈልጉ ያላቸው አማራጭ ይህ ብቻ ነው።

ሴረኞቹን ጂኒዎች ግራኝ አብዮትን፣ ግራኝ ጃዋርን፣ ግራኝ ለማ’ን እንዲሁም የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹን ቱርክን እና ግብጽን በደንብ ለማየት የንስር ዓይኖች ይስጠን

👉 ቀደም ሲል የቀረቡ፤

💭 ኢትዮጵያውያንን እያስጨፈጨፉ ያሉት አብዮት አህመድ እና ሽመልስ አብዲሳ ናቸው | ጋሎች፡ እሳቱን ያውረድባችሁ!!!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 2, 2020

“ በወለጋ ለተካሄደው አሰቃቂ ጀነሳይድ ቍ.፩ ተጠያቂው ግራኝ አብዮት አህመድ ነው!!! ጋሎቹ ከዓማሌቃውያን በከፋ ብሔራቸውን ወደ ሲዖል የሚወስድ ዲያብሎሳዊ ተግባር ነው እየፈጸሙ ያሉት። ይህ ትውልዳቸው ምናልባት ለመቀጠል ቢፈቀድለትም እንኳን በምድር ሲዖል ለመኖር የሚያበቃ የሃጢዓት ሸክም ተሸክሞ የሚኖር ትውልድ ነው የሚሆነው።

‘አብን’ የተሰኘው ሌላ የአውሬው ድርጅት ዛሬ በወለጋ ለተፈጸመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ መንደርደሪያ ነበር። የተቃውሞ ሰልፍ ትጠራለህ፣ ስልፉን ታስቀራለህ፣ የድጋፍ ሰልፍ ትጠራለሁ ቀጥሎ ጭፍጨፋውን በድፍረት ታካሂዳለህ። ሕዝቡ ብሶቱን ለመግለጽ ወደ አደባባይ እንዳልወጣ በተደጋጋሚ አዩት እኮ ስለዚህ ተደፋፈሩና ግድያቸውን ቀጠሉ። እያንዳንዱ ለተቃውሞ የሚጠራ ሰልፍ በአብዮት አህመድ ካድሬዎች በኩል እንዲጠራ የሚደረገውም ለዚህ ነው።

ላለፈው ሳምንት ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ ልክ እንደተሰረዘ፤ “ለመሆኑ “አብን” የተባለውና ከ666ቹ አንዱ የሆነው ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ይካሄዳል ብሎ በማመን እራሱን ያታለለ ወገን ይኖራልን?” በማለት ጠይቄ ነበር።

ከጅምሩ ዘንድሮ ቤተክህነት ሰልፍ ትጠራብን ይሆናል በሚል ስጋት ነው ገዳይ አብይ ለተባባሪው ፓርቲ ለአብን ሰልፍ እንዲጠሩ ያዘዛቸው! ወደ ቤተ ክርስቲያን “ተመለሱ” የተባሉትንም የኢሬቻ በላይ ቃልጫዎች ልክ ሲኖዶሱ ሲሰባሰብና ከባድ ውሳኔ ለማስተላለፍ በመዘጋጀት ባለበት ወቅት መሆኑ ያለምክኒያት አይደለም። ልብ እንበል፤ ይሁዳ እራሱን ሰቀለ እንጂ ከተቀሩት የክርስቶስ ሐዋርያት ጋር ተመልሶ እንዲሰለፍ አልተደረገም። የኛዎቹ ግን በተቃራኒው ከሃዲ ይሁዳዎቹን በድጋሚ ተቀብለዋቸዋል።

አብን የእነ እስክንድርን እና ልደቱን አጀንዳ ለመጥለፍ የተጠራ ሌላው የአብዮት አህመድ ብልግና “የሚቆጣጠረው ተቃዋሚ! ወይም Controlled Opposition” ፓርቲ ነው።”

💭 በአራት ቀናት ልዩነት “ክቡር“ መልአኩ ሰይጣን ሆነ | ምዕመናኑን የማስተኚያ ዲያብሎሳዊ ስልት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 14, 2020

“ሊቀ መልአክት የነበረው ሉሲፈርም እንዲህ ነው የወደቀው…የወደቁት ቤተ ክርስቲያናችንም ውስጥ ሰርገው ገብተዋል…እዩት…

ለመሆኑ እባባዊ የሆነውን የዲያብሎስን አካሄድ እየተከታተልን ነውን? ዘንዶው እዚህ እዚያ፣ ወዲያ ወዲህ እያለ ግራና ቀኝ ይዝለገለጋል፤ አንዴ እነደዚህ ሌላ ጊዜ እንደዚያ፣ አንዴ ሙቅ ውሃ ቆየት ብሎ ቀዝቃዛ፣ ትናንት ሽብር ፥ ዛሬ ፍቅር ፣ ዛሬ ደጋፊ፣ ነገ ተቃዋሚ፣ ዛሬ ኬኛ በበነገታው ኢትዮጵያ ሱሴ። ይህ እንግዲህ በቅርቡ ላዘጋጁት የዘር ጭፍጨፋ ሰውን በማለማመድ ላይ መሆናቸውንና፤ ሕዝቡም ከሲዖል ጣዕም ጋር እንዲተዋወቅ እየተደረገ መሆኑ ነው የሚነግረን። ነገሮችን ሁሉ በማዘበራረቅ የሰውን አንጎል ማጠብ፣ መበጥበጥና መቆጣጠር እንደሚቻል አውቀውታል / አምነውበታል። ሰው ነቅቶ ከአልጋው በመነሳት ለአመጽ እንዳይነሳሳና በአዲስ አበባ ለፈሩት የተቃውሞ ሰልፍ እንዳይወጣ የገዟቸውንና ያሰማሯቸውን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት፣ የስነ ልቦና እና የሜዲያ “ልሂቃን” ይጠቀማሉ። እንደምናየው “ተቃዋሚ ነን” ሲሉ የነበሩ ደካሞች ሳይቀሩ ሁሉም በገንዘብና በልጆቻቸው ሊከተል በሚችለው የግድያ ማስፈራሪያ ወይ አፋቸውን ዘግተውባቸዋል ወይ ወደ እነሱ ካምፕ አምጥተዋቸዋል።“

💭 The Church of England convened a synod this past week, a gathering of bishops, clergy and laypeople for the purpose of reviewing and possibly changing church doctrine.

The result of this particular gathering was that the national assembly voted, after two days of debate, to let Anglican priests bless same-sex weddings and civil partnerships. The blessings will come despite the fact gay and lesbian weddings will still be prohibited in the church.

Intended as a compromise measure after five years of discussions on the church’s position on human sexuality, the result is confusing to many. The ban on same-sex weddings is because the church believes it is sinful behavior, yet the church will now bless those same “sinful” partnerships?

That announcement wasn’t the most shocking to come out of the Church of England’s gathering, however.

The biggest news story to come out of the church’s gathering was that some within the Church of England are calling for 2000-year-old references to God as He, Him or Father to be banished, instead using gender-neutral or female alternatives.

Leaders at the synod took written questions from those attending. One question came from the Reverend Joanna Stobart, an Anglican minister, who wanted to know what steps were being taken to offer alternatives to God with male pronouns. Specifically, she hoped “to develop more inclusive language in our authorized liturgy.”

The Bishop of Lichfield, Michael Ipgrave, serving as Vice Chair of the church’s Liturgical Commission provided a reply that excited those seeking the change. “We have been exploring the use of gendered language in relation to God for several years in collaboration with the Faith and Order Commission. After some dialogue between the two commissions in this area, a new joint project on gendered language will begin this spring.”

The fact that The Church of England bills itself as a Christian church apparently isn’t slowing down this project intended to determine if the words of Christ should be believed or whether they should be tossed aside.

The story of Jesus Christ may be the best known and certainly the most read of any man to have ever set foot on planet earth. Christians believe Jesus was born to the ever-virgin Mary, sometimes referred to as “the mother of God.” She conceived Jesus through a miracle, thanks to the Holy Spirit. While some doubters have questioned her virgin status, virtually nowhere in history has there been any credible debate that Mary was Jesus’ mother. At no point has there been a serious discussion that Mary herself was God.

With those two points undisputed, it seems illogical that Christians could take to referring to God as She or Her. If one believes Jesus was the son of God and that Mary was His mother, and that she wasn’t God, simple logic tells us God can’t be referred to as She.

Far more importantly, though, are the words of Jesus himself. He spoke frequently about his Father in Heaven. He gave us the Lord’s Prayer, which begins with the words “Our Father.” He was not ambiguous.

Unless Jesus was lying to us, unless Jesus was intentionally misleading all of humankind, it seems incredibly arrogant to think that we know better, 2000 years later than the Savior. If Jesus was lying, or even if he was unintentionally mistaken when he referenced the Father, doesn’t that undermine the entire belief in him as the Son of God?

That is the quagmire the Church of England is leading itself into. In an effort to placate the current cultural whims of members of their clergy and laity, they would question whether Jesus, on whom their church is founded, was wrong. Toss out the Savior to fit the current cultural narrative.

No small irony, of course, and probably no coincidence, that the Church of England was created originally by King Henry VIII because of his own issues with sex and marriage. In 1536 King Henry wanted to get a divorce from his wife and marry his mistress. England was a Catholic nation at the time, and the Pope pointed out to Henry that trading in for a new wife was a no-no, even for a King. Unhappy that the Pope wouldn’t change the rules for him, Henry VIII and all of England left the Catholic Church. The King created his own church instead and then felt free to marry and carry on as he pleased.

Obedience to God and doing the right thing got lost somewhere in the process.

That’s where the Church of England finds itself again in 2023. There are some liberal Christians who, rather than adhere to 2000 years of scripture, four Gospels documenting the life of Christ, or to the words of Jesus himself, would rather change the rules. They want to do this because, like King Henry VIII, the change will make it more convenient for them and what they want.

Lost again is obedience to God and the serious study of scripture.

If the Church of England walks down the path of ignoring Jesus and instead referring to God in gender-neutral terms, it will have abandoned its role as a Christian organization.

👉 Courtesy: The Washington Times

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰሙነ ሕማማት – ረቡዕ ፤ የይሁዳ ክህደት፥ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 28, 2021

ለምን የምክር ቀን ተባለ?

ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ [ማቴ. ፳፮፥፩፡፲፬ ፣ ማር. ፲፬፥፩፡፪ ቁ ፲.፲፩፣ ሉቃ. ፳፪፥ ፩፡፮]

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል

ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ “ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ” ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ነው ረቡዕ የመዓዛ ቀን የተባለው፡፡

የእንባ ቀንም ይባላል

ይህም ይህቸው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ [ማቴ.፳፮፥፮፡፲፫ ፣ ማር.፲፬፥፫፡፱፣ ዮሐ.፲፪፥፩፡፰] ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው። ምህሩንና ጌታውን ክዶ፣ ስሞ ለግርፋት እና ለመስቀል ሞት ተስማማ። ይህንን የጌታን ሕማማት፣ ስቅላት፣ ሞትና ትንሣኤ በምናስብበት በአሁኑ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ለሕማም፣ ለስቅላት እና ለሞት አሳልፎ ተስጥቷል። ይሁዳ ለ፴/30 ዲናር ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው፤ ከዚያም ዲናሩን መልሶ እራሱን አጠፋ። የዘመናችን ሰቃልያን የሆኑት ኦሮማራዎቹ የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮች ደግሞ “አክሱም ጽዮን ለብዙ ሺህ ዓመታት ያፈራችውን እውቀት፣ ስልጣኔና ሀብት በሙሉ ለመዝረፍ፣ አሳልፎ ለመስጠትና ለማውደም ጊዜው አሁን ነው” ብለው የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ከሆኑት አህዛብ፣ መናፍቃንና ግብረ-ሰዶማውያን ጋር ተባበሩ። በዚህም በዚያም ትልቅ ክህደት እና ስቅለት። በተለይ ተዋሕዶ ክርስትናን የተቀብሉትና ማሕተብ ያጠለቁት አማራ ወገኖች ክህደት ታሪክ የማይረሳው ነው፤ ብዙ ዋጋም የሚያስከፍላቸውና ከሌሎቹ ሁሉ የከፋው ክህደት ነው። ከይሁዳ ይልቅ የጴጥሮስ ዓይነት ክህደት ያድርግላቸው።

የአስቆሮቱ ይሁዳ ክህደት + የቃኤል ቅናት = ☠️

አወቁትም አላወቁትም፤ ዛሬ በአማራዎችና ኦሮሞዎች ህብረት በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለው ጂሃዳዊ የጭፍጨፋ ዘመቻ የመጨረሻው ግብ፤ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ትግራዋያንን ከአኩም ጽዮን አጽድቶ የሕይወት ዛፍ እና ጽላተ ሙሴ የሚገኙበትን ቅድስት ምድር ለተለከፉት ባዕዳውያኑ ውሾች ማስረከብ ነው። አዎ! ኢትዮጵያን/አክሱም ጽዮንን ለባዕዳውያኑ ሉሲፈራውያን ለማስረከብ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነት ከፈቱ። እስኪ እናስበው! ዋው!

በሰባዎቹ ዓመታት ሉሲፈራውያኑ ድርቅና ረሃብ ፈጥረው በዚህ አካባቢ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሃገራት፤ በተለይ ብሪታኒያ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ ሰራዊቶቻቸውን በእርዳታ ስም አስፍረው እንደነበር እናስታውስ። ከዚያ በሰማኒያዎቹ እና በባድሜው ጦርነት የተባበሩት መንግስታት “ሰላም አስከባሪዎች” እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ዛሬም ዓለም የተራቡ የትግራይን ሕፃናት ምስሎች በበቂ እንድታይ ከተደረገች በኋላና የተረፉትንም ትግራይ ወገኖቼንም በስደት የተቀደሰችውን ምድር እየለቀቁ እንዲወጡ (የአውሮፓን እና አሜሪካን ድንበሮች ይከፍቱላቸዋል፤ ከጥቂት ከፍተኛ ቦታ ላይ ከሚገኙት የዓለማችን ቦታዎች በቀር አውሮፓና አሜሪካ ሌሎችም አኅጉራት ይጠፋሉ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል) ከተደረጉ በኋላ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሠራዊቶች በትግራይ ይሰፍራሉ።

ገና ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት “ኔቶ በአፍጋኒስታን የሚገኘው ለኢትዮጵያ ለመለማመድ ነው፤ ተመሳሳይ የመልከዓ ምድር አቀማመጥ ስላላቸው…” በማለጥ ጽፌ ነበር። ምዕራባውያኑ እዚያ መስፈር ከጀመሩ በኋላ ቀስ በቀስ ዜጎቻቸውን ማስገባት ይጀምሩና በመጨረሻም “ኢትዮጵያውያኑም ተዋሕዶ ክርስቲያኖቹም እኛ ነን” በማለት እያታለሉና ደማቸውን እያፈሰሱ ለብዙ ሺህ ዓመታት ጠብቀውት የነበረውን ብኩርናቸውን በምስር ወጥ እንዲሸጡ ብሎም የመንፈስ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን እየተነጠቁ “ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን” ቀስበቀስ እንዲከዱ ይደረጓቸውን “የቀድሞ ኢትዮጵያውያን” “አናስገባም!” ብለው ከኢትዮጵያ ድንብር ይመልሷቸዋል። ይህ ትንቢት ሳይሆን የሉሲፈራውያኑ ግልጽ የሆነ ተልዕኮ ነው። እግዚአብሔር ይህን ተልዕኳቸውን እንደሚያጨናግፈው አልጠራጠረም፤ ነገር ግን በኢትዮጵያውያኑ ደንቆሮነት፣ ስንፍና እና እንደ ግራኝ ያሉትን የውስጥ ጠላታቸውን በሰዓቱ ለማስወገድ ባለመድፈራቸው ብሎም አክሱም ጽዮንን ለመከላከል ባለመሻታቸው ብዙ መስዋዕት ይከፍሉ ዘንድ ግድ ይሆናል። በተለይ ከሃዲዎቹ ኦሮማራዎች!

የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሕማማተ እግዚእ †ዕለተ ሰሉስ/ማክሰኞ | ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 27, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

✞✞✞ ሰሙነ ሕማማት ዕለተ ማክሰኞ (ዘሰሉስ)✞✞✞

የጥያቄና የትምህርት ቀን❖

በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማድረጉን ተያይዞ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ሰኞ ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ያላገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፤ በማስከተል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ [ማቴ.፳፩፥፳፫፡፳፭ ፤ ማር.፲፩፥፳፯ ፣ ሉቃ.፳፥፩፡፰]፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራትና የኃይል ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀናቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡

ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነው፡፡ በአንድ አገር የንግድ ቦታን የሚያጸድቅ መንግሥት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡት ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አልመለሰም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሷል፡፡ “በመባሕተ መኑ ትገብር ዘንተ፤ በማን ሥልጣን ነው ይህን የምታደርገው?” ነበር ያሉት፡፡ በራሴ ሥልጣን ቢላቸው ፀረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው፡፡

ጌታችን እኩይ የሆነውን የፈሪሳውያንን አሳብ በመረዳት “የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር ሲል” ጠይቋቸዋል፡፡ ከሰማይ ያልነው እንደ ሆነ ለምን አላመናችሁበትም ይለናል÷ ከሰው ያልነው ከሆነ ሕዝቡ ይጣላናል፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ከዚህ የተነሣ ያቀረቡት የፈተና ጥያቄ ግቡን ሳይመታ ከሽፎባቸዋል፡፡ [ማቴ.፳፩፥፳፭]፤ [ማር.፲፩፥፳፯፡፴ ፤ ሉቃ.፳፥፩፡፰]፡፡

ዛሬም ቢሆን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊሆን እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን ዐሳባችን ከዓለም ዘንድ የተገላቢጦሽ ነገር እንደ ሚጠብቀን “ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው” የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ ይህ በመሆኑ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልን ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡

በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

👉መድኅንኤል 👉ሕይውታኤል 👉አውካኤል 👉ተርቡታኤል 👉ግኤል 👉ዝኤል 👉ቡኤል

የቅዱስ ገብርኤል ድርሳን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከልዩ ድንጋፄና ፍርሃት እድን ዘንድ ይህን የቅዱስ ገብርኤልን ድርሳን እንዲህ እያልኩ እጸልያለሁ፤ መድኅንኤልሕያውታኤልአውካኤልተርቡታኤልግኤልዝኤልቡኤል ፤ ይህን አስማተ መለኮት እግዚአብሔር ለቅዱስ ገብርኤል የሰጠው መልአኩ ከዲያብሎስ ጋር ክርክር በጀመረ ጊዜ ድል እንዲነሣበት፤ እንዲሁም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለማብሠር በተላከ ጊዜ ከቃሉ ግርማ የተነሣ እንዳትደነግጥና እንዳትፈራ መጽንዔ ኃይል እንዲሆናት ነው።

አቤቱ ለእኔ ለአገልጋይህም እንደዚሁ ኃይልና ጽንዕ ሰጥተህ ከመዓልትና ከሌሊት ድንጋፄ አድነኝ፤ አሜን።

ከላይ ከሰማይ ወደ ድንግል የተላክህ ገብርኤል ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ደስታን አብሣሪ መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ፅንሰ ቃልን አስተምረህ የምታሳምን መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ሰማያዊ ነደ እሳት ዖፈ ርግብ ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ፍጹም ደስታን ተናጋሪ መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ከእደ ሞት የምታድን መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። የአንተን አማልላጅነት በመዓልትም በሌሊትም ተስፋ ስለምናደርግ ጥበቃህ አይለየን። በነፍስም በሥጋም ታደገን። የእግዚአብሔር ልዩ ባለሟል ነህና፤ ለዘላለሙ አሜን።

አቡነ ዘመሰማያት።

__________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: