ቤተ እስራኤል በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስራኤል ፥ ቤተ ኢትዮጵያ በእግር ወደ ሱዳን
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 8, 2020
👉 ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ
☆ ኢትዮጵያን የከዱት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘና ብለው ወደ እስራኤል ይበርራሉ
☆ ኢትዮጵያውያን ግን ከአየር መንገዱ በትግሬነታቸው ይባረራሉ፤ ሴቶች በየጫካው እይወለዱ በበርሃ በእግራቸው ሄደው ወደ ሱዳን ይሰደዳሉ
እነዚህ ሁለት ሁኔታዎች ከ፴፭/35 ዓመታት በኋላ በአንድ ወቅት እንደገና መደገማቸው በአጋጣሚ? እስራኤል፤ “ለልጆቼ ቆሚያለሁ” ፥ “ኢትዮጵያ ግን ለልጆቿ ደንታ የላትም!” የሚለውን መልዕክት ለማስተላለፍ የተሞከረ ይመስለኛል።
በቪዲዮው፦
👉 የቤተ እስራኤል ስደተኞች ከ፴፭/35 ዓመታት በፊት ከሱዳን ወደ እስራኤል ሄዱ
👉 የቤተ እስራኤል ስደተኞች ዛሬ ከ፴፭/35 ዓመታት በኋላ ከአዲስ አበባ ወደ እስራኤል በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረሩ
👉 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሱዳን ከ፴፭/35 ዓመታት በፊት፤ የጋላ/ጋላማራ የደርግ መንገስት በጥይትና ምግብን/ ረሀብን እንደ ጦር መሣሪያ በመጠቀም በሚሊየን የሚቆጠሩትን ትግሬ ኢትዮጵያውያንን ቀጠፋቸው፤ የተረፉት ወደ ሱዳን ተሰደዱ፤ ዓለም “የልደት በዓል መሆኑን ያውቃሉን?” Do they know it’s Christmas? ብላ ዘፈነችልን።
👉 ከ፴፭/35 ዓመታት በፊት ወደ ሱዳን ተሰደው ከነበሩት መካከል፤ አቶ እስክንድር ነጋሽ
👉 ዛሬ ከ፴፭/35 ዓመታት በኋላ፤ በልደት በዓል ዋዜማ፤ ኢትዮጵያውያን እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር እየተበደሉ፣ እየተንገላቱ፣ እየተጨፈጨፉ እና እንደገና ያኔ ወደነበሩበት የሱዳን ስደተኞች ካምፕ ተመልሰው በእግራቸው ሄደው እንዲሰደዱ እየተደረጉ ነው።
ታዲያ ዛሬ ዓለም “የልደት በዓል መሆኑን ያውቃሉን?” Do they know it’s Christmas? ብላ በድጋሚ ትዘፍንልን ይሆንን?
ህወሃቶች የሰሩት ትልቅ ወንጀል ሃገረ ኢትዮጵያን ለጠላቶቿ ጋሎች ማስረከባቸውና ዛሬ ቅድስት የኢትዮጵያ ምድር የሆነችውን ትግራይን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ መወሰናቸው ነው። እንደው ጦርነት መካሄድ ካለበት እንኳን ህገ–ወጥ በሆኑት ሶማሊያ እና ኦሮሚያ በተባሉት ክልሎች መሆን ነበረበት። ምክኒያቱም የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላቶች የሚገኙት በእነዚህ ሁለት ክልሎች ነውና። ጀግናው አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን በድጋሚ ታላቅ ለማድረግ መጀመሪያ ከእነዚህ ሁለት ክልሎች ነበር ፀረ–ኢትዮጵያውያኑን ጠራርገው የሚያስወጧቸው።
ህወሃቶች ሁሉም ነገር በእጃቸው ነበር፤ ሰራዊቱ፣ መሳሪያው፣ ተቋማቱ ወዘተ በቁጥጥራቸው ስር ነበሩ። እንደው እውነት ቆሻሻው ግራኝ አብዮት አህመድ ጠላታቸው ቢሆን ኖሮ በአንድ ሰዓት ውስጥ ሊደፉት በቻሉ ነበር፤ ነገር ግን ይህን አይፈልጉም፤ ምክኒያቱም የግራኝ ብልጽግና እና ህወሃት ኢትዮጵያን ለማፈራረስና በትግራይ የሚኖሩትን ጥንታውያኑን ኢትዮጵያውያንን በጥይት፣ በስደት፣ በበሽታ እና በረሃብ ፈጅተው ለመጨረስ ተናብበው እየሰሩ ነውና ነው። ሁሉም ይህን ዲያብሎሳዊ ተልዕኮ ለማስፈጸም ከሰላሳ ዓመታት በፊት በደማቸው ፈርመዋልና ነው።
ከአደዋው ድል በኋላ ከአፄ ምኒሊክ ስጋዊ ማንነት የመነጨውን የብሔር ብሔረሰብ ርዕዮት ዓለም የተረከቡት የስጋ ማንነት ያላቸው ህወሃት (ራያ) እና ኦነግ ህገ-መንግስት ተብየውን ከሉሲፈራውያኑ ሲቀበሉና ክልሎችን ሲመሰርቱ “እናንተ ለሃያ ሰባት ዓመት ትገዙና ወደ መቀሌ ትሄዳላችሁ፤ ከዚያም በእናንተ ላይ ጦርነት እናውጅና ተዋሕዶ ትግሬ ኢትዮጵያውያንን እናናውጣቸዋለን፣ እያዋረድን እና ሞራላቸውንም እየሰበርን እናዳክማቸዋለን፣ እናጠፋቸዋለን፤” በሚል ስውር ስምምነት ነበር።
ዛሬ እኮ የምናየው ልክ ይህን ነው፤ እስኪ ተመልከቱ፤ ከሰላሳ ዓመታት በፊት ኦነግ ከህወሃት ጋር ሆን መንግስት መሰረተ፣ ቀጥሎ ጊዜውን ጠብቆ ከመንግስት በስልት እንዲገለል ተደረግ፣ ከዚያም አስመራ ገባ፣ አሁን ጊዜው ሲደርስ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ ብልጽግና የሚባል ፓርቲ መሰረተ በመጨረሻም በትግራይ ላይ ጦርነት አወጀ።
አስገራሚ ነው፤ ከሁሉም “ሰሜናዊ” ከሆኑ ወገኖች ጋር ተናብቦ እየሰራ ያለ ብቸኛው ቡድን ኦነግ ነው። ኦነግ ከኢሳያስ አፈቆርኪ ጋር፣ ከደብረጽዮን ጋር፣ ከአብዮት አህመድ ጋር፣ ከሙስጠፌ ጋር፣ ከአዴፓ ጋር፣ ከአብን ጋር፣ ከሲዳማ እና ወላይታ እንቅስቃሴዎች ጋር፣ ከግብጽ ጋር፣ ከሳውዲ እና ኤሚራቶች ጋር፣ ከአውሮፓውያን እና አሜሪካውያን ጋር አብሮ ይሰራል። ግራኝ አብዮት አህመድ እኮ እንዲህ ብሎናል፤ “ኦሮሞ እስኪነቃ ነው እንጂ፣ እስኪነሳ ነው እንጂ ሲነሳ ሚዳቋ አትበላንም፤ እኛ ዝሆን ነን፤ እንሰብራለን፤ እንበላለን፤ እንገዛለን፣ ሃሳብ አለን፤ ድርጅት አለን፤ ከአለም ጋር ግንኙነት አለን።”
የስጋ ማንነት ያለው አጋሩ ራያው ጌታቸው ረዳ ደግሞ ሰሞኑን “በአልሞት ባይ ተጋዳይነት”፡ እንዲህ ብሎናል፤ “ጦርነቱ የሚያበቃው ሁሉም የትግራይ ሕዝብ ሲያልቅ ነው”
አዎ! እንደምናየው የትግራይን ሕዝብ ሊያስጨርሱት የወሰኑ ይመስላሉ፤ ዛሬ ሳሰላስል የመጣልኝ ጥያቄ፡ “ላለፉት ሁለት ዓመታት ሀወሃት የጦር ሠራዊቱን ጡንቻ ለማሳየት ብዙ ልምምዶችን ሲያካሂድ ነበር፤ ይህን ልምምድ በተለይ የትግራይ ሕዝብ ነው እንዲያየው የተደረገው፤ ይህን የልምምድ ትዕይንት የተከተለው ባለፈው በትግራይ ተካሂዶ የነበረው ምርጫ ነበር፤ ታዲያ ልምምዱ “እኔ ነኝ አለኝታችሁ፤ እኔን ከመረጣችሁ እከላከላችኋለሁ፤ ካልመረጣችሁ ለጠላት አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” የሚል መልዕክት ኖሮት ይሆን? ምናልባት ህወሃት እንደጠበቁት በትግራይ ነዋሪዎች ዘንድ ባለመመረጣቸው፤ አሁን ሕዝቡን እየተበቀሉት ይሆን? እንግዲህ እንኳን ትግራይን መላው ምስራቅ አፍሪቃን የመከላከል ብቃቱ እንዳላቸው ለሰላሳ ዓመታት ያህል አሳይተዋል፤ ታዲያ ዛሬ ያሰለጠኑትን ልፍስፍስ የግራኝን ሠራዊት እንዴት ሰተት ብሎ ወደ ትግራይ እንዲገባ ፈቀዱለት? ጦርነት መምጣቱስ ላልቀረ ገና አዲስ አበባ አራት ኪሎ እያሉ መዋጋት ይችሉ አልነበረምን? ለምን ወደ ትግራይ ሄደው መሸጉ? ሆን ብለው ይህን ጦርነት ወደ ትግራይ ለማምጣት አይደለምን? ዋ!
__________________________
Leave a Reply