Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2020
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 27th, 2020

የሳጥናኤል ጎል ቍ. ፬ ክፍል ፬ | እነ ግራኝ አብዮት አህመድ ከሉሲፈራውያኑ ጋር የደም ቃልኪዳን ፈጽመዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 27, 2020

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ

ይህ ከ አምስት ወራት በፊት ያቀረብኩት የማስጠንቀቂያ መልዕክት ነበር፦

ኢትዮጵያዊው በማይረቡ ነገሮች እየተጠመደ ጊዜ በመግዛት ላይ ያሉት በግራኝ ዐቢይ አህመድ የሚመሩት ኦሮሞዎች ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ የተባለውን ህገ-ወጥ ክልል ወርረው የቦታውን ነዋሪዎች ባፋጣኝ በመተካት አካባቢውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር በመጣደፍ ላይ ናቸው። ዋናው ዓላማቸው፦ ድኾቹ ኢትዮጵያውያን ቆጥበው ከሰበሰቡት ገንዘብ ያሠሩት የሕዳሴ ግድብ ነው። ገና ዱሮ መጠረግ የሚገባው ከሃዲው ዐቢይ አህመድ አሊ ሁሉን ነገር ከአረቦችና ከግብጾች ጋር ሆኖ ጨርሶታል። በኢትዮጵያ ላይ የሞት ፍርድ የፈረደባት ገና ወጣት እያለ ወደ ባድሜው የጦርነት ድንበር እንደተላከ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ በደንብ ነው ያዘጋጁት፤ ትግርኛውንም ቋንቋ እንዲያጠና ተደርጓል። ማየት የምንችለው እናየዋለን፤ ሰውዬው ጂኒ ጋኔን ነው! ባሁኑ ሰዓት ታላቅ ህልሙን ለማሳካትም የአምሐራና ተጋሩ ተዋሕዶ ወንድማማቾች እርስበርስ እንዲባሉ፣ በበሽታ፣ በረሃብና በስደት እየደከሙ እንዲያልቁ ተግቶ በመሥራት ላይ ነው። ህልማቸው በቤኒሻንጉል ብቻ አይወሰነም፤ ደቡብን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠሩ በኋላ ጎንደርንም፣ ላሊበላንም፣ አክሱምንም የመጠቅለል ትልቅ የወራሪዎች ምኞት አላቸው። ለማንኛውም በእርሱ እና በከሃዲዎቹ ኦሮሞ ወራሪዎች ላይ እሳት ከሰማይ የሚወርድበት ቀን ሩቅ አይደለም!

ከታሪክ የማይማር ታሪክን ለመድገም ይገደዳል! ታሪክ እየተደገመ ነው። ይህ ቪዲዮ በጣም ሊረብሸን ቢችልም ግን ጊዜ ወስደን በጥሞና እንመልከተው! በዚህ ዘመን እንደገና ማየቱ ግድ ነው!

በትናንትናው ዕለት “በትግራይ ጤፍ ጠፋ ስለዚህ ሰው ማሽላ ብቻ መብላት ጀምሯል፣ አንድ ኪሎ ጤፍ ፷/60 ብር ገባ” የሚለውን ዜና ስሰማ የታየኝ ልክ እንደ አባቱ እንደ መንግስቱ ኃይለ ማርያም ዐቢይ አህመድ አሊም ትግሬዎችን በጦርነት ማሸነፍ ስለማይችል ቀስበቀስ በረሃብ ለመቅጣት መወሰኑን ነው። ጤፍ ለኦሮሞና ኢሳያስ አፈቆርኪ፣ ማሽላ ለትግሬና አማራ። እንግዲህ ሕዝቡን “እንጠብቅሃለን!” የሚሉት በራያ ኦሮሞዎች የሚመራው ህወሃት ወይ ከጂኒው ግራኝ አህመድ ጋር አብሮ እየሠራ ነው፤ አሊያ ደግሞ የእንቅልፍ ኪኒን ወስዶ የዓመት እንቅልፍ ላይ መሆን አለበት። ሰውዬው የፈለገውን እንዲያደርግ ፈቅደውለታል!

ቪዲዮው እንደሚያሳየን በትግራይና በቤተ-አምሐራ ከ፵/40 ዓመታት በፊት ተከስቶ የነበረውና ዓለምን ጉድ ያሰኘው ሰው-ሰራሽ ድርቅ እና ረሃብ ነበር። ሰሜን ኢትዮጵያ በአስር ዓመታት ውስጥ ለሁለት በጣም አስከፊ ለነበሩ የረሃብ ክስተቶች ተጋልጣ ነበር። አባቶችና እናቶች በጣም አስከፊ ታሪክ ነው ዛሬም የሚነግሩን።

የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን (ኔቶ/NATO)አባላት(ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ብሪታኒያ)”በእርዳታ” ስም ሠራዊቶቻቸውን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ልከው እንደነበር ይነጉርናል። የኔቶ ወታደሮች በኢትዮጵያ? አዎ! ዋው! ስንቶቻችን እናውቅ ነበር?

እነዚህ የሳጥናኤል ሃገራት እንደ እነ መንግስቱ ኃይለ ማርያም እና ዐቢይ አህመድ አሊ የመሳሰሉትን “ኢትዮጵያ ትቅደም!” የሚሉ ነገር ግን ኢትዮጵያን የሚጠሉ ስጋውያን የደቡብ ሰዎች በመሪነት ወንበር ላይ ያስቀምጣሉ፤ ድብቅ በሚመስል መልክ ሃገሪቱን ለማድከምም፣ ሕዝቡ እንዲራብ፣ እንዲታመም፣ እንዲፈናቀልና እንዲሰደድ ያደርጉታል፤ በዚህም በቅድሚያ ሞራሉን ይሰብሩበታል፣ በዚህ ወቅት ሁኔታው በግልጽ እንዲታወቅ አይሹም፤ ከዚያም ከዚህ የከፋ ችግርና ግጭት እንዲፈጠር ያደርጋሉ፣ አሁን ህዝቡ ደክሞላቸዋልና ስለችግሩ የሜዲያ እና “መንግስታዊ ያልሆኑ” ተቋማቶቻቸው “ኡ!ኡ!እርርይ! ገንዘብ እናሰባስብ! እንድረስላቸው!” (ዛሬ ጎ-ፈንድ-ሚ ይሉታል)በማለት የችግሩን ዜና 24/7 እንዲለፍፉና እንዲያበስሩ ይደርጋሉ፤ ከዚያም ወታደሮቻቸውን (የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ፟) ወደ ሃገራችን ይልካሉ፤ ልክ እንደ አስከፊው ረሃብ ዘመን፣ እንደ ባደሜው ግጭት። የሚከተሉትን መመሪያ ተንኮለኛው ፈላስፋ ጆርጅ ሄገል፤ “ችግር – ምላሽ – መፍትሔ / “Problem – Reaction – Solution” ብሎታል።

ሉሲፈራውያኑ ለገዳይ አብይ የኖቤል ሰላም ሽልማት መሸለሟ ትልቅ ቅሌት መሆኑን በወቅቱ አሳውቀናል። ይህ የሉሲፈራውያን ወኪል የኢትዮጵያውያን ደም በመገበር ሰይጣን ስልጣኑን ይዞ እንዲቆይ ዋስትና ይሰጠዋል። ባለፈው ዓመት ላይ “ኢትዮጵያውያን ለመጭው ጭፍጨፋ ተዘጋጁ!” በማለት ጥሪ አቅርቤ ነበር። ለጊዜው ሰውዬው እና ሞግዚቶቹ የኢትዮጵያውያን ትዕግስትና የጦርነት ወኔ በመፈተን ላይ ይገኛሉ፤ ረዳቶቹም የተለያዩ ሽልማቶችን በመስጠት (ኖቤል፣ ሲ.ኤን.ኤን ሂሮ) ሁኔታዎችን ይቃኛሉ። ክ12 ዓመታት በኋላ ወደተዘጋጀው የመጨረሻ የጭፍጨፋ ዒላማ ከመዝለቃቸው በፊት በቅድሚያ የሕዝቡን የተዋጊነት/ የነፍጠኝነት መንፈስና ሞራል ቀስ በቀስ ማዳከምና ማኮላሸት አለባቸው፤ ለዚህም፦

+ የማደንዘዢያ የሜዲያ ዘመቻዎችን ማጧጧፍ(“የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032 ዓ.ም”)

+ ዓብያተ ክርስቲያናትን ማዳከም፣ ማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያኑን ተስፋ ማስቆረጥ

+ መንፈስ አድካሚ አምልኮዎችን (እስልምናን ፕሮቴስታንቲዝምን)ማስፋፋት

+ “ኢትዮጵያ ጠላት የላትም!” በሚል ዓይን ያወጣ ቅጥፈት ሕዝቡን ማዘናጋት

+ ኢትዮጵያውያን እንዲሰደዱና በባርነት እየተሸጡ ከሃገር እንዲወጡ ማድረግ

+ ስደተኞችን ከጎረቤት ሙስሊም ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ ማጉረፍ

+ አረቦችንና ቱርኮችን ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት

+ ትምህርት ቤቶችንና ካሪኩለማቸውን መቆጣጠር

+ ከዓለም አቀፍ ረዳቶቹ ገንዘብና ዕውቅናን በማግኘት በሽታዎችን ማስፋፋት

+ ኢትዮጵያውያን የሃገራቸውን ምግብና ውሃ እንዳይጠቀሙ ማድረግ

+ የኢትዮጵያን ምግብና ውሃ ወደ ውጭ መላክ

+ መርዛማ ምግብን፣ መጠጥን እና “መድኃኒቶችን” ከውጭ ማስገባት፤ ምግብንና ውሃን መበከል፣

+ ድርቅና ረሃብን መፍጠር፣

+ “ኦሮሚያ” ከተባለው ክፍለ ሃገር ንጹሕ ኢትዮጵያውያንን አጽድቶ የተረፉትን ወደ ሰሜኑ እንዲሸሹ መገፋፋት፣ እዚያም እርስበርስ እንዲባሉ ማድረግ (ኤርትራ እና ትግራይ ፥ ትግራይ እና አማራ)

+ ግብረ-ሰዶማዊ የሚያደርጉና የሚያልፈሰፍሱ ጨረር አፈንጣቂ ሞገዶችን ከጠፈር መልቀቅ (በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያውያን ላይ)። ኢትዮጵያን ለአውሬው አስረክባችሁ የፈረጠጣችሁት ከሃዲ ህውሀቶችም አትተርፏትም። የቀለባችሁት አዞ ተዝለግልጎ በመምጣት ላይ ነው። ልክ በመለስ ዜናዊና አቡነ ጳውሎስ ላይ እንዳደረጉት በደብረ ጺዮን እና አቡነ ማቲያስ ላይ ጨረሩን በመልቀቅ ላይ ናቸው። ሰሞኑን አቶ ደብረ ጽዮን አዙሮት ወደቀ ተብሎ ነበር አይደል?

ገዳይ ግራኝ አብይ አህመድ የኖቤል ሽልማት የተሰጠው የእግዚአብሔር የሆነችውን ኢትዮጵያን እንዲያጠፋላቸውና ጥንታውያኑን ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን እንዲጨፈጭፍላቸው መሆኑን በፍጹም አንጠራጠር። በተለይ ኢትዮጵያ/ ተዋሕዶ ክርስትና በምዕራባውያኑ ዔሳውያን እና በምስራቃውያኑ እስማኤላውያን ከማንም ሃገር በከፋ የምትጠላ የሳጥናኤል ጎል ናት።

እዚህ ይቀጥሉ፦ https://wp.me/piMJL-4OD

__________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በመልካም ፋንታ ክፉን በወደድኋቸውም ፋንታ ጠላትነትን መለሱልኝ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 27, 2020

[መዝሙረ ዳዊት ከ ምዕራፍ ፻፮ እስከ ፻፲]

ይህ መዝሙር ልጆቹንና ሚስቱን ወደ አሜሪካ የላከውንና ሆ! ብለው ወደርሱ በመምጣት ወድደውት የነበሩትን ንጹሐን ኢትዮጵያውያንን እንደ ዝንብ የሚጨፈጭፈውን ግራኝ አብዮት አህመድን ይመለከታል፦

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፰]

፩ አምላክ ሆይ፥ ምሥጋናዬን ዝም አትበል፥

፪ የኃጢአተኛ አፍና የተንኰለኛ አፍ በላዬ ተላቅቀውብኛልና፤ በሽንገላ አንደበትም በላዬ ተናገሩ፤

፫ በጥል ቃል ከበቡኝ፥ በከንቱም ተሰለፉብኝ።

፬ በወደድኋቸው ፋንታ አጣሉኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።

፭ በመልካም ፋንታ ክፉን በወደድኋቸውም ፋንታ ጠላትነትን መለሱልኝ።

፮ በላዩ ኃጢአተኛን ሹም፤ ሰይጣንም በቀኙ ይቁም።

፯ በተምዋገተም ጊዜ ተረትቶ ይውጣ፤ ጸሎቱም ኃጢአት ትሁንበት።

፰ ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ፤ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ።

፱ ልጆቹም ድሀ አደግ ይሁኑ፥ ሚስቱም መበለት ትሁን።

፲ ልጆቹም ተናውጠው ይቅበዝበዙ ይለምኑም፥ ከስፍራቸውም ይባረሩ።

፲፩ ባለዕዳም ያለውን ሁሉ ይበርብረው፥ እንግዶችም ድካሙን ሁሉ ይበዝብዙት።

፲፪ የሚያግዘውንም አያግኝ። ለድሀ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።

፲፫ ልጆቹ ይጥፉ፤ በአንድ ትውልድ ስሙ ይደምሰስ።

፲፬ የአባቶቹ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ትታሰብ፤ የእናቱም ኃጢአት አትደምሰስ።

፲፭ በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ ይኑሩ፤ መታሰቢያቸው ከምድር ይጥፋ።

፲፮ ምሕረትን ያደርግ ዘንድ አላሰበምና ችግረኛንና ምስኪንን ልቡ የተሰበረውንም ሰው ይገድል ዘንድ አሳደደ።

፲፯ መርገምን ወደደ ወደ እርሱም መጣች፤ በረከትንም አልመረጠም ከእርሱም ራቀች።

፲፰ መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፥ እንደ ውኃም ወደ አንጀቱ፥ እንደ ቅባትም ወደ አጥንቱ ገባች።

፲፱ እንደሚለብሰው ልብስ። ሁልጊዜም እንደሚታጠቀው ትጥቅ ይሁነው።

፳ ይህ ሥራ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሚያጣሉኝ በነፍሴም ላይ ክፉን በሚናገሩ ነው።

፳፩ አንተ ግን አቤቱ ጌታዬ፥ ስለ ስምህ ምሕረትህን በእኔ ላይ አድርግ፤ ምሕረትህ መልካም ናትና አድነኝ።

፳፪ እኔ ችግረኛ ምስኪንም ነኝና፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።

፳፫ እንዳለፈ ጥላ አለቅሁ፥ እንደ አንበጣም እረገፍሁ።

፳፬ ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።

፳፭ እኔም በእነርሱ ዘንድ ለነውር ሆንሁ፤ ባዩኝ ጊዜ ራሳቸውን ነቀነቁ።

፳፮ አቤቱ አምላኬ፥ እርዳኝ፥ እንደ ምሕረትህም አድነኝ።

፳፯ አቤቱ፥ እጅህ ይህች እንደ ሆነች፥ አንተም ይህችን እንዳደረግህ ይወቁ።

፳፰ እነርሱ ይራገማሉ አንተ ግን ባርክ፤ በእኔ ላይ የሚነሡ ይፈሩ፥ ባሪያህ ግን ደስ ይበለው።

፳፱ የሚያጣሉኝ እፍረትን ይልበሱ፤ እፍረታቸውን እንደ መጐናጸፊያ ይልበሱአት።

፴ እግዚአብሔርን በአፌ እጅግ አመሰግነዋለሁ። በብዙዎችም መካከል አከብረዋለሁ፤

፴፩ ነፍሱን ከሚያሳድዱአት ያድን ዘንድ በድሀ ቀኝ ቆሞአልና።

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: