Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2020
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 6th, 2020

ኒው ዮርክ | ግዙፍ እሳት የ፲፱ ኛው ክፍለዘመን ታሪካዊ ቤተክርስቲያንን አጠፋ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2020

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በመድኃኔ ዓለም ዕለት እንድናየው | ትግሬዋን ለተሰንበትን አገቷት ፥ ኦሮሞዋን ገንዘቤን ላኳት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2020

ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ይታገታሉ፣ ይገረፋሉ፣ ይራባሉ፣ ይገደላሉ፤ ከስራዎቻቸው ይፈናቀላሉ፣ በርሃ ለበርሃ እየተንከራተቱ ከሃገራቸው ይሰደዳሉ። የኢትዮጵያ ጠላቶች ግን ኢትዮጵያውያንን በገዛ አገራቸው እያገቱ፣ እየገረፉ፣ እያስራቡና እየገደሉ ተንደላቅቀው በሰላም ይኖራሉ፤ በአገርም በውጭም በኢትዮጵያ አየር መንገድ በነጻነት ይዘዋወራሉ።

ለተሰንበት ግድይ ከሁለት ወራት በፊት በመስከረም ፳፯/ ፪ሺ፲፫ ዓ.ም በ ቫሌንሲያ ከተማ ስፔይን የአምስት ሺህ ሜትር የዓለም ሬከርድን ሰበረች። ያኔም፤ ገና ትኩሱ የጥቃት ጦርነት ሳይጀምር ኢትዮጵያን ለቅቃ እንዳትወጣና ወደ ቫሌንሲያ እንዳትጓዝ ብዙ መሰናክሎችን ፈጥረውባትና አጉላልተዋትም ነበር። ልብ እንበል፤ ሬከርዱን ረቡዕ በመድኃኔ ዓለም ዕለት ነበር የሰበረቸው።

መኮረጅ የሚወደው ዲያብሎስ ነገሮችን አስመስሎ ነገር ግን አገለባብጦ ነው የሚያቀርባቸው፤ ለምሳሌ እኛ ከግራ ወደ ቀኝ ስንጽፍ ከዲያብሎስ የሆኑት ግን ከቀኝ ወደ ግራ ይጽፋሉ፣ እኛ ፍቅር ስናሳያቸው ከዲያብሎስ የሆኑት ጥላቻን፣ እኛ እውነቱን ከዲያብሎስ የሆኑት ሐሰትን፣ እኛ በስተቀኝ ከዲያብሎስ የሆኑት በስተግራ…([የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፭፡ ፴፪፥፴፫፟]“አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።”)

በአረብኛው ቍጥር 27፤ ሲገለበጥ 72፤ ይህችን ቁጥር ዲያብሎስ ይወዳታል፤ መሀመድ ለተከታዮቹ ክርስቲያኖችን እና አይሁዶችን ከገደሉ72 ልጃገረዶችን በእስልምና ጀነት እንደሚጠብቋቸው ቃል ገብቶላቸዋል። ግራኝ አብዮት አህመድ አሊም በትግራይ ላይ በሚያካሂደው “ዘመቻ አክሱም ጽዮን” ጦርነት 72 ቁጥርን በመጠቀም ላይ ነው፤ (72 ሰዓታት ውስጥ እጃችሁን ስጡ!)

ለተሰንበት በመድኃኔ ዓለም ዕለት ሬከርድ ሰብራ ድል ስለተቀዳጀች ዲያብሎስ አልተደሰተም፤ የድል ዕድሉ ከደቡብ ተነጥቆ ወደ ሰሜን የዞረ መሰለው፤ ስለዚህ የሞትና ባርነት መንፈሱን በጦርነት መልክ ወደ ሰሜን ወሰደው።

በዛሬው እሑድ ኅዳር ፳፯ / ፪ሺ፲፫ ዓ./መድኃኔ ዓለም ዕለት የግማሽ ማራቶን ሩጫ በድጋሚ በቫሌንሲያ ከተማ ስፔይን የጥሩነሽ ዲባባን ሬከርድ የሰበረችው ለተሰንበት ትሳተፍ ዘንድ ተጋብዛ ነበር፤ ግን በተከፈተው ጦርነት ሳቢያ ወደ ቫሌንሲያ ልትጓዝ አልቻለችም።

ነገር ግን በዚሁ ዕለት የጥሩነሽ እህት ገንዘቤ ዲባባ ወደ ቫሌንሲያ ተላከች፤ ሬከርድ ባትሰብርም ሩጫውን ግን አሸነፈች።

👉 አሁን ነጠብጣቦቹን እናገናኛቸው…

_______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንወርሳለን የሚሉትን፤ አምላኬ ሆይ፥ እንደ ትቢያ በነፋስ ፊትም እንደ ገለባ አድርጋቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2020

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹፬]

፩ አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።

፪ እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።

፫ ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።

፬ ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።

፭ አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ፤ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፤

፮ የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥

፯ ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤

፰ አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው።

፱ እንደ ምድያምና እንደ ሲሣራ፥ በቂሶንም ወንዝ እንደ ኢያቢስ አድርግባቸው።

፲ በዓይንዶር ጠፉ፥ እንደ ምድርም ጕድፍ ሆኑ።

፲፩ አለቆቻቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፥ ታላላቆቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው።

፲፪ የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንወርሳለን የሚሉትን።

፲፫ አምላኬ ሆይ፥ እንደ ትቢያ በነፋስ ፊትም እንደ ገለባ አድርጋቸው።

፲፬ እሳት ዱርን እንደሚያቃጥል፥ ነበልባልም ተራሮች እንደሚያነድድ፥

፲፭ እንዲሁ በቍጣህ አሳድዳቸው፥ በመቅሠፍትህም አስደንግጣቸው።

፲፮ ፊታቸውን እፍረት ሙላው፥ አቤቱ፥ ስምህንም ይፈልጋሉ።

፲፯ ይፈሩ ለዘላለሙም ይታወኩ፤ ይጐስቍሉ ይጥፉም።

፲፰ ስምህም እግዚአብሔር እንደ ሆነ፥ በምድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ።

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: