👉 እኔ የምጠረጥረው ነገር አለ፤ አምና ላይ ይህን ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፤ ወደ ጦማሬ ይግቡ፦
“ታላቅ ጉዳይ | በኢትዮጵያ ሕፃናት ላይ ያነጣጠረው ሉላዊ የሉሲፈራውያን ሕፃናት-ዸፋሪ አውታር መሪ ታሠረ”
ስለ እህታችን ትምኒት ይህን የቢቢሲ መረጃ እናንብበው፦
በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ኤአይ (ሰው ሠራሽ ልህቀት) ዘርፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ባለሙያዎች አንዷ የሆነችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ትምኒት ገብሩ ከጉግል መባረሯን በትዊተር ገጿ አስፍራለች።
የጉግል የኤአይ የሥነ ምግባር ቡድን አጋር መሪ የነበረችው ትምኒት፤ ከጉግል እንደተባረረች በትዊተር ገጿ ያስታወቀችው ያሳለፍነው ረቡዕ ነበር።
ትምኒት እንዳለችው፤ በሰው ሠራሽ ልህቀት ዘርፍ ላለው መድልዎ ትኩረት እንዲሰጥና በዘርፉ እምብዛም ውክልና ያላገኙ ሰዎች እንዲቀጠሩ የሚያሳስብ ኢሜል ከላከች በኋላ ነው እንደተባረረች የተነገራት።
ዜናውን እንደ ዋሽንግተን ፖስት፣ ብሉምበርግ እና ኒው ዮርክ ታይምስ ያሉት ግዙፍ የአሜሪካ የሚዲያ ተቋማት ይዘውት ወጥተዋል።
በሰው ሠራሽ ልህቀትና ተያያዥ የቴክኖሎጂ ዘርፎች የሚሠሩ እውቅ ባለሙያዎች የትምኒትን መባረር በመቃወም ትዊተር ላይ ድምጻቸውን እያሰሙም ይገኛሉ።
ትምኒት በከዚህ ቀደም ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የጥቁር ሴቶች ቁጥር አነስተኛ እንደሆነና መድልዎውን ለመቅረፍ እንደምትታገል ገልጻ ነበር።
ኤአይ ውስጥ ካሉ ጥቂት ጥቁር ሴቶች አንዷ የሆነችው ትምኒት መባረሯ በጉግል አመራሮችና መድልዎን የሚቃወሙ ሠራተኞች መካከል የተፈጠረው ውጥረት አንድ ማሳያ ነው ተብሏል።
በአሜሪካ የሠራተኞችን መብት ለማስጠበቅ የተቋቋመው ገለልተኛው ‘ናሽናል ሌበር ሪሌሽንስ ቦርድ‘ እንዳለው፤ ጉግል የሠራተኞች ማኅበር ሊመሰርቱ የተንቀሳቀሱ ተቀጣሪዎቹን በሕገ ወጥ መንገድ ከሥራ አሰናብቷል።
ይህ ተቋም ስለ ሠራተኞች መባረር ቅሬታውን ይፋ ባደረገበት ቀን ነበር የትምኒት ከሥራ መባረር የተሰማው።
ጉግል ሠራተኞቹን ያባረረው የመረጃ ደኅንነት መርህን ስለጣሱ ነው ቢልም፤ ሥራቸውን ያጡት ማኅበር ለመመስረት የወሰኑ ተቀጣሪዎች እንደሆኑ ገለልተኛው ተቋም አስታውቋል።
ጉግል በበኩሉ በሕገ ወጥ መንገድ ሠራተኞች አላባረርኩም ብሏል።
ተቋሙ ያወጣው የቅሬታ ደብዳቤ ከዓመት በፊት የተባረሩ አራት ሠራተኞችን የሚመለከት ነው። ጉግል ሠራተኞቹ ማኅበር ለማቋቋም “የድርጅቱን የስብሰባ አዳራሽ ተጠቅመዋል” በሚል ነበር ከሥራ ያሰናበታቸው።
ጉግል፤ ሠራተኞቹ ስለ ማኅበሩ መረጃ እንዲያወጡ እንዳስገደደና ይህም በሠራተኞች መብት መርህ መሠረት ከሕግ ውጪ እንደሆነ ተገልጿል።
“ከሥራ ጋር የሚገናኝ ቅሬታ በመደበኛ መንገድ ብቻ ነው መገለጽ ያለበት” ሲልም ጉግል ተቀጣሪዎቹን ማስፈራራቱ ተዘግቧል።
በተጨማሪም ለሠራተኞች ማኅበር ሊቀርብ የነበረ ሰነድን ጉግል በርብሯል። ተቀጣሪዎቹ አንዳቸው የሌላቸውን የቀን መቁጠሪያ እንዳያገኙ በማድረግ ስለ እቅዳቸው መረጃ እንዳይለዋወጡ ማፈኑም ተገልጿል።
ገለልተኛው ተቋም እንሚለው፤ ጉግል ሠራተኞችን በማባረር ሌሎች ተቀጣሪዎች ማኅበር እንዳይፈጥሩ ለማስፈራራት ሞክሯል።
ትምኒት በትዊተር ገጿ እንዳለችው፤ ጉግል የሥራ ኢሜል አድራሻዋን አግዷል።
ድርጅቱ “ትላንት ምሽት ከአመራር ውጪ ለሆኑ ተቀጣሪዎች የላክሽው ኢሜል የጉግል አስተዳደር ከሚፈቅደው አሠራር ውጪ ነው” የሚል ኢሜል እንደላከላት ተናግራለች።
የትምኒት መባረር የሶፍትዌር መሀንዲሶችን፣ የሰው ሠራሽ ክህሎት ሥነ ምግባር ባለሙያዎችንና ሌሎችም የዘርፉ ሙያተኞችን አስቆጥቷል።
ትምኒት፤ በኤአይ የጥቁር ሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ‘ብላክ ኢንኤአይ‘ የተባለ ተቋምን ከመሰረቱ አንዷ ናት።
የፈጠራ ሥራዎችን አካታችነት በሚፈትሹ ጥናቶቿ፤ እንዲሁም ቴክኖሎጂና የሰብአዊ መብት ጥያቄን በማስተሳሰርም ትታወቃለች።
ከጥናቶቿ መካከል ስለ ‘ፌሽያል ሪኮግኒሽን ሲስተም‘ (የሰዎችን ፊት ገጽታ በማየት ማንነታቸውን የሚያሳውቅ መተግበሪያ) የተሠራው በዋነኛነት ይጠቀሳል።
መሣሪያው የጥቁር ሰዎችን በተለይም ደግሞ የጥቁር ሴቶች ገጽታ አይቶ ማንነታቸውን ለመለየት እንዲችል ተደርጎ አለመሠራቱን በጥናቱ ጠቁማለች።
_________________________
Like this:
Like Loading...