Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2020
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 20th, 2020

ግራኝ በቅዱስ ያሬድ ልጆች ላይ ጦርነት መክፈቱን የሚደግፉት ‘አባቶች’ እነማን ናቸው?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 20, 2020

👉 ብዙ ጠቃሚ ትምህርቶችንና ወቅታዊ መልዕክቶችን የያዘ ቪዲዮ ነው፤ እንደምንም ፩ ሰዓት ገዝተን እያነጻጸረን እናዳምጠው።

በኢትዮጵያዊነት ወንድማችን የሆነው አስተዋዩ ኤድመንድ ብርሃኔ፤ “እነ መምህራን ዘበነ ለማ + ምህረተአብ የት ገባችሁ? በትግራይ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ላይ ስለተከፈተው ጦርነት ውጡና መልስ ስጡ እንጂ፤ በኋላ ስብከታችሁን እና ትምህርታችሁን ማን ሊሰማችሁ ነው?” በማለት የጠየቀው ጥያቄ ተገቢና በጣም ትክክለኛም ነው። ከደምቢዶሎ ታግተው ለተሰወሩት የደምቢዲሎ ተዋሕዶ ተማሪዎች በመቆም አንዴም ትንፍሽ ያለ መምህር ወይም “አባት” አልሰማሁም፤ ሞጣ በተባለው ቦታ አንድ መስጊድ ሲቃጠል ግን “የአባቶች” መግለጫና ማስተዛዘኛ ሬዲዮና ቴሌቪዥኑን አጣብቦት ነበር። መግለጫ፣ ማስተዛዘኛና ትምህርት የሚሰጡት ልክ ግራኝ አህመድ አሊ ማስተዛዘኛ ከሰጠ ብቻ ነው። ይህ የኢንሳ አውሬ ስለ “አባቶች” ምን የሚያውቀው ምስጢር ቢኖር ነው?

ዓለም አስከፊ ለሆነው የኮሮና ወረርሽኝ በተጋለጡበት በእነዚህ ቀናት እነ ግራኝ በሰሜን ኢትዮጵያውያን ላይ ኮሮና ቅብርጥሴ ሳይሉ ጦርነት አወጁበት፤ ባለፈው ፋሲካ ግን በኮሮና አሳብበው ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይሄዱ አደረጓቸው። በእኔ በኩል ይህን በመቃወም “አባቶች ምዕመናኑን ዛሬ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዛችሁት ካልሄዳቸው በኋላ ስብከታችሁን ማን ሊሰማ?” በማለት ለመጠየቅ ደፍሬ ነበር።

አሁን ግን አገር ቤት ያላችሁ የተዋሕዶ ልጆች ትናንትና የማርያም መቀነትን አይታችሁታልና ወደ ቤተ ክርስቲያን ተሰባስባችሁ አምሩ። የማርይም መቀነቱ “ወደኔ ኑ! ምንም አትሆኑም!” የሚለውኝ ምልክት ነው ያሳያችሁ! በዚህ በትንሣኤ ወቅት ኮሮኖ የተባለው ቫይረስ ቤተ ክርስቲያን ድርሽ አይልም! እግዚአብሔርን እንጅ ሌላ ማንንም/ምንንንም አትፍሩ! አባታችንን አብርሃምንና ይስሐቅን አስታውሱ! አሁን ትንሽ ሰዓት ነው የቀረውና ባካችሁ የማንንም ፈቃድ ሳትጠይቁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሂዱ! መላው ዓለም “ኢትዮጵያውያኖች ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዱን?” ብሎ በመጠየቅ ላይ ነው። ባለፈው ሳምንትም ተናግሬው ነበር፤ ይህ ሌላ ጊዜ ተመልሶ የማይመጣ ልዩ አጋጣሚ ነው! በዚህ ጊዜ ከተሰቀለላችሁ አምላካችሁ ጋር ካልሆናቻሁ መቼ?! ለብርሃነ ትንሣኤ ቤተ ክርስቲያንን አጥለቅልቋት!”

👉 በትናንትናው ድንቅ የታኅሣስ ፲/፪ሺ፲፫ ዓ.ም ዕለት (ገና አሁን ልብ አልኩት ፥ ❖❖❖መስቀለ ኢየሱስ❖❖❖) በጸሎት ቤቴ ውስጥ የመጣልኝ ሃሳብና መልዕክት የሚከተለው ነው

ለመሆኑ ዛሬ በአክሱም ጽዮን ልጆች ላይ፣ በቅዱስ ያሬድ ልጆች ላይ፣ በአቡነ አረጋዊ ልጆች ላይ፣ በአባ ዓቢየ እግዚእ ልጆች ላይ፣ በንጉሣን ኢዛና እና ዮሐንስ ልጆች ላይ የተከፈተውን ጦርነት ሊደግፍ የቃጣው ‘ተዋሕዶ ክርስቲያን’ ምን ዓይነት ክርስቲያን ነው? ተዋሕዶ? በጭራሽ! ክርስቲያን? በፍጹም ሊሆን አይችልም።

ወደ ስልጣን ከመጣበት ዕለት አንስቶ በየቦታው ቦንብ በማፈንዳት ላይ ያለው አሸባሪው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ በአክሱም ጽዮን እና በደብረ ዳሞ ላይ የቀሰቀሰውን ጦርነትን የሚደግፉት ሁሉ አወቁትም አላወቁትም የኢትዮጵያ እና ተዋሕዶ ክርስትናዋ ጠላቶች ብቻ ናቸው። ፻/100%

👉 ለመሆኑ ይህ ጦርነት ማንን ነው “የሚጠቅመው”?

፩ኛ. የምዕራቡን ኤዶማውያንን እና የምስራቁን እስማኤላውያንን(ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ እስላም፣ ኢአማኒ፣ ግብረሰዶም)

ምክኒያቱም፦ ሁለቱም ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን አጥፍተው የራሳቸውን ዲያብሎሳዊ ርዕዮተ ዓለማት ማስፋፋትና በኢትዮጵያ የሚገኘውን የሕይወት ዛፍም ለሳጥናኤል ስም፣ ክብርና ዝና ሲሉ መውረስ ይሻሉና ነው።

፪ኛ. ዋቀፌታን/ኦሮሙማን

ምክኒያቱ፦ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን አጥፍተው የራሳቸውን ርዕዮተ ዓለማት ማስፋፋት ይሻሉና ነው። የፕሮቴስታንቲዝም አባት ማርቲን ሉተር ወደ ጀርመንኛ በተረጎመው መጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያን‘ ‘ኩሽብሎ ነው የጻፋት። ይህ ቀላል ነገር እንዳይመስለን። እ..አ ከ 1837 እስከ 1843 .ም ባለው ጊዜ ፕሮቴስታንቱ ጀርመናዊ ዮኻን ክራፕፍ ኦሮሚያ የተባለውን ግዛት ለመመሥረት የተነሳሳው ክርስትናን ለማስፋፋት ሳይሆን፡ እንደ አንድ ፕሮቴስታንት የኢትዮጵያ ቀጥተኛ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለመዋጋት ነው። ለዚህም በወራሪነት ባሕርይ ከጀርመኖች ጋር ይስማማሉ በሚል ሃሳብ “ጋላ” ተብለው ሲጠሩ የነበሩትን ጎሳዎች ለማደራጀት በመነሳሳት በ ኢትዮጵያፋንታ ኩሽየሚለው ትርጉም ያለበትን መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ ወደ ምስራቅ አፍሪቃ/ኢትዮጵያ ተጓዝ፤ በዚህም የኦሮሙማ እንቅስቃሴን ጀመረው። ተልዕኮው ፀረኢትዮጵያ፣ ፀረተዋሕዶ እና የክርስቶስ ተቃዋሚ ተልዕኮ መሆኑን ዛሬ እያየነው ነው። ዋናው ዲያብሎሳዊ ዓላማቸው፤ ኢትዮጵያን አፍርሰው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትንም በተለይ ከአማራና ትግሬ በመንጠቅ “መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰችው ኩሽ እኛ ነን” የሚለው ነው።

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም”[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥፲]

፫ኛ. የአማራ ብሔርተኝነትን

ምክኒያቱ፦ ከኦሮሙማዎች፣ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ትግሬዎችንና ትግርኛን አጥፍተው ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን፣ ግዕዝን፣ ሰንደቁን፣ አክሱም ጽዮንን፣ ቅዱስ ያሬድና አቡነ አረጋዊን ከተቻለም መላው ትግራይንና ኤርትራን ወርሰው ለራሳቸው ብቻ ለማድረግ ይሻሉና ነው። በነገራችን ላይ፤ ኦሮሞዎች በኬኛ ቅዠታቸው ሙጭጭ ያሉበትንና “ፊንፊኔ/ ፊልፊሌ” የሚለውን ስያሜ ለአዲስ አበባ ፍልወሃ ክፍለ ከተማ እቴጌ ጣይቱ እንደሰጡት፤ “አማራ” የተባለውን የአማራ ከንቱ ብሔርተኞች ክልልን መጠሪያ ስም የሰጡት ደግሞትግሬው/ሚ መለስ ዜናዊ ነበሩ። የሕይወት ምፀት!

፬ኛ. የትግሬ ብሔርተኝነትን

ምክኒያቱ፦ ኢአማንያኑ ሻእቢያ እና ህዋሀት ቡድኖች ከኦሮሙማዎች፣ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን፣ ቅዱስ ያሬድን፣ አቡነ አረጋዊን፣አባ ዓቢየ እግዚእን፣ነገሥታቱን ኢዛናን፣ ዮሐንስን፣ ሰንደቁን፣ ግዕዝን፣ አክሱምን አጥፍተው በሃምሳ ዓመታት ውስጥ በተገኘ ጣዖታዊ ማንነት “ኢአማኒ የትግራይ ሶሻሊምዝብልጽግና” ርዕዮተ ዓለምን በመከተልና የሉሲፈር ኮከብ ያረፈበትን የቻይና ባንዲራም በማውለብለብ ከኤርትራ ጋር ለብቻቸው መኖር ይሻሉና ነው። በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የግራኝ አብዮት አህመድ እና የስብሃት ነጋ ጦርነት ነው። መንግስቱን ለኦሮሙማዎች እንዳስረከቡት፣ ቤተ ክህነትንም ለእነ ኤሬቻ በላይ በማስረክብ ላይ ያሉ ይመስላሉ። በትግራይ ላይ የተከፈተውን ጦርነት የደገፉበት አንዱ ምክኒያትም ይህ ሊሆን ይችላል፤ ዋናው ፍላጎታቸው ግን የትግርኛ ተናጋሪ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን ልብ በመስበርና ተስፋ በማስቆረጥ፡ ተዋሕዶ ክርስትናን እና ኢትዮጵያን እንዲተው ማድረግ ነው። በነገራችን ላይ፤ ዛሬ የትግራይ ከንቱ “ትግራይ! ትግራይ!” ብሔርተኞች ለሚጮሁለት ክፍለሃገር “ትግራይ” የሚለውን መጠሪያ የሰጡት ድንቁ አማራኢትዮጵያዊ ንጉሥ አፄ አምደ ጽዮን ናቸው። የሕይወት ምፀት!

ሉሲፈራውያኑ እና ቆሻሻው ወኪላቸው አብዮት አህመድ አሊ ትግራይን ከኢትዮጵያ ገንጥለው የስጋ ማንነትና ምንነት ባላቸው ጠላቶቿ የምትመራዋን የዛሬዋን ኢትዮጵያን አፈራርሰው ከሞያሌ እስከ መተከልና ጎንደር ያለውን ግዛት ለኦሮሞዎች ለማስረከብ ተግተው በመሥራት ላይ ናቸው። አማራው የስጋ ማንነትና ምንነት ካላቸው ኦሮሞዎቹ ጎን ተሰልፎ የመንፈስ ማንነትና ምንነት ባላቸው ትግሬ ወንድሞቹ ላይ በመቶ ዓመት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ጦርነት በማወጁ አብቅቶለታል! አክሱም ጽዮንን ክዷልና የሆነ ተዓምር ካልመጣ በቀር ምንም ተስፋ የለውም፤ በቅርቡ ሃገር አልባ ነው የሚሆነው። እነ ግራኝ እየሠሩ ያሉት ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያዊነታቸው፣ ከአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቃቸው እና ከተዋሕዶ ክርስትናቸው እንዲላቀቁ ብሎም አእምሯቸውን ተቆጣጥረው፣ መንፈሳቸውን አድክመውና ሞራላቸውን ሰብረው ልክ እንደ “ኤርትራውያን” ለአውሮፓውያን አረጋውያን የኩላሊትና መቅኒ መለዋወጫ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። ሰሞኑን “አማራ” የተባለው ክልል ባንዲራውን ለመቀየር መወሰኑ ከዚህ ሤራ ጋር የተያያዘ ነው። ከኦሮሞዎቹ ከእነ አብዮት አህመድ ጋር ተናበው በመስራት ላይ ያሉት ሀወሃቶች የዚህ ዲያብሎሳዊ ሤራ አካል ቢሆኑ አይገርመንም። ዋ! ! !

በዓለማችን ያሉ ብዙ ሕዝቦች በተቻለ መጠን በሃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በባህልና በመልክ የሚመስሏቸውንና የሚቀርቧቸውን ሕዝቦች እየፈለጉ ማስጠጋትና መውደድ በጀመሩበት በዚህ ዘመን ትንሿ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔሮች ግን ጥላቻን አንግሠው አንዱ ከሌላው የሚለይበትንና የሚርቅበትን፣ አንዱ ሌላውን የሚጠላበትንና የሚያርቅበትን ሰበባ ሰበብ እየፈላለጉ እርስበርስ መባላቱንና ውድቀቱን መርጠዋል። ሞቃዲሾን አልፎ ኪጋሊንና ካምፓላን፣ ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ኤደንና ሙስካትን “የኛ ነበሩ! የኛ ይሆናሉ!” በሚል ወኔ ታላቅነትንና አርቆ አሳቢነትን እንደ ቀደሙት አያቶቹ ይዞ “ኢትዮጵያ እርስቴ” በማለት ፈንታ እራሱን አጥብቦና በጣም አውርዶ በወልቃይትና ራያ ሚጢጢ“እርስቶች” ላንቅው እስኪበጠስ ይነታረካል። ዛሬማ ሰው ከ“አዲስ አበባ የማን ናት?” አሰልቺና አላስፈላጊ ንትርክ ወርዶ ጉልበቱንና ጊዜውን በመስቀል አደባባይና ጃን ሜዳ ላይ ብቻ እንዲያጠፋ ተደርጓል። ጃን ሜዳን እና መስቀል አደባባይን ያረከሱትን ግራኝ አብዮት አህመድን እና ታከል ዑማን አድኖ እንደመድፋት፤ “ጮኸን ጮኸን ጃን ሜዳ ተፈቀደልን!” ይልና ሆያሆየን ጨፍሮ ለቀጣዩ እንቅልፉ ወደ አልጋው ይመለሳል። በከሃዲዎቹ የሉሲፈራውያኑ ባሪያ ልሂቃኖቹ አዕምሮው እስኪጠብብ ድረስ መታጠቡ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ የለም።

የሕዝቡን ስነ-ልቦና በልተውታል፤ ስለዚህ “አዲስ አበባ ኬኝ” ይሉና መስቀል አደባባይን እና ጃን ሜዳን በመቆፈር የተዋሕዷውያኑን ሃሳብ በነዚህ ትንንሽ ቦታዎች ላይ ብቻ እንዲቀር አድርገው ያስሩታል፣ ወደ ወልቃይት፣ ራያና ሁመራ ልጆቹን እየላከ ትግሬዎች ወገኖቹን እንዲገድል፣ የራሱንም ደም እንዲያፈስ፣ የአክቲቪስቱ ሃሳብም በእነዚህ ትንንሽ ቦታዎች ብቻ ተወስኖና ታስሮ እንዲቀር፣ የቀረውም እንዲኮላሽና ሰፊዋን ኢትዮጵያን ከጠላቶቿ ነፃ ለማውጣት አቅም እንዳይኖረው፤ ብዙም እንዳይጠይቅ፣ በጥቃቅን ነገሮች ላይ ብቻ ጊዜና ጉልበቱን እያባከነ ለባርነት እንዲዘጋጅ አድርገውታል። ትልቅ ቅሌት! ወዮላችሁ!

👉 አንድን ሀገር/ሕዝብ ለመቆጣጠር ሉሲፊራውያኑ የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች፦

ተስፋ ማስቆረጥ/ሞራል መስበር

አለመረጋጋትን መፍጠር

አመፅ መቀስቀስ

መደበኛነትን/መረጋጋትን ማምጣት

👉 A Luciferian Plan of Controlling a nation by the tools of

Demoralization

Destabilization

Insurgency

Normalization

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ፥ አድነን ፣ ከአሕዛብ መካከል ሰብስበን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 20, 2020

❖❖❖ መዝሙረ ዳዊት ከ ምዕራፍ ፻፩ እስከ ምዕራፍ ፻፭ ❖❖❖

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፭]

፩ ሃሌ ሉያ፤ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።

፪ የእግዚአብሔርን ኃይል ሥራ ማን ይናገራል? ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ያሰማል?

፫ ፍርድን የሚጠብቁ፥ ጽድቅንም ሁልጊዜ የሚያደርጉ ምስጉኖች ናቸው።

፬ አቤቱ፥ በሕዝብህ ሞገስ አስበን፥ በመድኃኒትህም ጐብኘን፤

፭ የመረጥሃቸውን በጎነት እናይ ዘንድ፥ በሕዝብህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከርስትህም ጋር እንጓደድ ዘንድ።

፮ ከአባቶቻችን ጋር ኃጢአትን ሠራን፥ ዐመፅንም፥ በደልንም።

፯ አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ ተኣምራትህን አላስተዋሉም፥ የምሕረትህንም ብዛት አላሰቡም፤ በኤርትራ ባሕር ባለፉ ጊዜ ዐመፁብህ።

፰ ኃይሉን ግን ለማስታወቅ። ስለ ስሙ አዳናቸው።

፱ የኤርትራንም ባሕር ገሠጸ እርሱም ደረቀ፤ እንደ ምድረ በዳ በጥልቅ መራቸው።

፲ ከሚጠሉአቸውም እጅ አዳናቸው፥ ከጠላትም እጅ ተቤዣቸው።

፲፩ ያሳደዱአቸውንም ውኃ ደፈናቸው፥ ከእነርሱም አንድ አልቀረም።

፲፪ በዚያን ጊዜ በቃሉ አመኑ፥ ምስጋናውንም ዘመሩ።

፲፫ ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥ በምክሩም አልታገሡም።

፲፬ በምድረ በዳም ምኞትን ተመኙ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።

፲፭ የለመኑትንም ሰጣቸው፤ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።

፲፮ ሙሴንም እግዚአብሔር የቀደሰውንም አሮንን በሰፈር ተመቀኙአቸው።

፲፯ ምድርም ተከፈተች ዳታንንም ዋጠችው፥ የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፤

፲፰ በማኅበራቸውም እሳት ነደደች፥ ነበልባልም ኅጥኣንን አቃጠላቸው።

፲፱ በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።

፳ ሣርም በሚበላ በበሬ ምሳሌ ክብራቸውን ለወጡ።

፳፩-፳፪ ታላቅ ነገርንም በግብጽ፥ ድንቅንም በካራን ምድር፥ ግሩም ነገርንም በኤርትራ ባሕር ያደረገውን ያዳናቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ።

፳፫ እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።

፳፬ የተወደደችውን ምድር ናቁ፥ በቃሉም አልታመኑም፥

፳፭ በድንኳኖቻቸውም ውስጥ አንጐራጐሩ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።

፳፮-፳፯ በምድረ በዳም ይጥላቸው ዘንድ፥ ዘራቸውንም በአሕዛብ መካከል ይጥል ዘንድ፥ በየአገሩም ይበትናቸው ዘንድ፥ እጁን አነሣባቸው።

፳፰ በብዔል ፌጎርም ተባበሩበት፥ የሙታንንም መሥዋዕት በሉ።

፳፱ በሥራቸውም አስመረሩት፥ ቸነፈርም በላያቸው በዛ።

፴ ፊንሐስም ተነሥቶ ፈረደባቸው፥ ቸነፈሩም ተወ፤

፴፩ ያም እስከ ዘላለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።

፴፪-፴፫ በክርክር ውኃ ዘንድም አስቈጡት፥ መንፈሱን አስመርረዋታልና፤ ስለ እነርሱም ሙሴ ተበሳጨ፤ በከንፈሮቹም በስንፍና ተናገረ።

፴፬ እግዚአብሔርም እንዳላቸው አሕዛብን አላጠፉም፤

፴፭ ከአሕዛብም ጋር ተደባለቁ፥ ሥራቸውንም ተማሩ።

፴፮ ለጣዖቶቻቸውም ተገዙ፥ ወጥመድም ሆኑባቸው።

፴፯ ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠው፤

፴፰ የወንዶች ልጆቻቸውንና የሴቶች ልጆቻቸን ደም፥ ለከነዓን ጣዖቶች የሠውአቸውን ንጹሕ ደም አፈሰሱ፥ ምድርም በደም ረከሰች።

፴፱ በሥራቸው ረከሱ፥ በማድረጋቸውም አመነዘሩ።

፵ የእግዚአብሔርም ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፥ ርስቱንም ተጸየፈ።

፵፩ ወደ አሕዛብም እጅ አሳለፋቸው፥ የሚጠሉአቸውም ገዙአቸው።

፵፪ ጠላቶቻቸውም ግፍ አደረጉባቸው፥ ከእጃቸውም በታች ተዋረዱ።

፵፫ ብዙ ጊዜ አዳናቸው፤ ነገር ግን በምክራቸው አስመረሩት፥ በኃጢአታቸውም ተዋረዱ።

፵፬ እርሱ ግን ጩኸታቸውን በሰማ ጊዜ ጭንቃቸውን ተመለከተ፤

፵፭ ለእነርሱም ኪዳኑን አሰበ፥ እንደ ምሕረቱም ብዛት ተጸጸተ።

፵፮ በማረኩአቸውም ሁሉ ፊት ሞገስን ሰጣቸው።

፵፯ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ አድነን፤ ቅዱስ ስምህን እናመሰግን ዘንድ፥ በምስጋናህም እንመካ ዘንድ፥ ከአሕዛብ መካከል ሰብስበን።

፵፰ ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ ሕዝብም ሁሉ አሜን ይበል። ሃሌ ሉያ።

________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: