ቪዲዮው ላይ ፴፫/33ን እስኪ ፈልጓት፡ ወገኖቼ…
ከትናንትና ወዲያ ባቀረብኩት ጽሑፍ በነካ ነካ ያወሳሁት፦ የ ፴፫/33 ቁጥር ሚስጥር
❖ “የእግዚአብሔር መልአክ ገብርኤል በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ፥ ያድናቸውማል”
የዘመናችን አማሌቃውያን የሆኑትና በግራኝ አብዮት አህመድ የሚመሩት የዋቄዮ–አላህ አርበኞች አማራውንና ትግሬውን በተጠና እና እባባዊ በሆነ መንገድ ወደሚቆሰቁሷቸው የጦርነት እሳት ውስጥ አንድ በአንድ እየማገዱ ከኢትዮጵያ ምድር ሊያጠፏቸው ከወሰኑ ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በላይ ሆኗቸዋል። የዛሬው ከቀድሞው የሚለየው ስልጣኑን ተረክበውታል ለጥፋትና ጭፍጨፋ ዘመቻቸውም በቂ ገንዘብና መሳሪያ ከኤዶማውያኑ ምዕራባውያን እና እስማኤላውያን አግኝተዋል።
በትግራይ ላይ የከፈቱት የጭፍጨፋ ጦርነት ሆነ አሁን ቪዲዮው በቅደም ተከተል እንደሚያሳየው ከሱዳን ጋር የተቀነባበረው “ግጭት” የዚሁ አማራን እና ትግሬን ከማስጨፍጨፊያ መንገዶቻቸው መካከል አንዱ ነው። ደጋግሜ የምለው ነው፤ እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ከምናስበው በላይ እጅግ በጣም አረመኔዎች ናቸው፤ ዕድሉን ካገኙ በአማራና ትግሬ ላይ ኬሚካልና ኑክሌር መሳሪያዎችን ከመጠቀም ወደ ኋላ አይሉም። እግዚአብሔር አያድርገውና በትግራይ ላይ ተጠቅመዋል የሚል ስጋት አለኝ።
ከሱዳን ጋር በሚደረገው ግጭት ገላጣማ በሆነው የሱዳን በርሃ በአረቦቹ በኩል ከምዕራባውያኑ የተገኙትን የጨረር መሣሪያዎችን እንደሚጠቀሙ አንጠራጠር። በኤሚራቶችና ቱርኮች በኩል በትግራይ የተጠቀሟቸው ድሮኖች ሙቀት መለኪያ ነበሩ። አፍጋኒስታንን ከወረሩበት ከአስራ ዘጠኝ ዓመታት በፊት አንስቶ “ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ ተራራማ የመልክዓ ምድር አቀማመጥ ያላት አፍጋኒስታን ለኢትዮጵያ መለማመጃቸው ነው” ስል ነበር። ያው ዛሬ ሁሉም በጂቡቱ እየሰፈሩ ናው፤ እነ አሜሪካም ከ፳/20 ዓመታት በኋላ ወታደሮቻቸውን ከአፍጋኒስታን ነቅለው ለማስወጣት በመዘጋጀት ላይ ናቸው።
👉 ሁለቱ ጄነራሎች፤ የግብጹ አል–ሲሲ & የሱዳኑ አል–ቡርሃን እና ፮–አለቃ ብርሃኑ ቁራ ጁላ ፥ ወይንም አብዮት አህመድ አሊ ባባ እና ፴፫/33ቱ ሌቦች–ጄነራሎች
☆ መጋቢት ፫/ ፪ሺ ፲፪ ዓ.ም – March 12, 2020
ጄኔራል የተባለው‘፮–አለቃ‘ ብርሃኑ ቁራ ጁላ ወደ ሱዳን አመራ፤ ከሱዳን መንግስትና ሰራዊት ጋር ተመካከረ።
☆ ሚያዚያ ፳፮/ ፪ሺ ፲፪ ዓ.ም – May 04,2020
ኢሳያስ አፈቆርኪ ‘በድንገት‘ ወደ ኢትዮጵያ ተጓዘ፤
በዚሁ ወር የኤርትራ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ በድብቅ ወደ አዲስ አበባ አቅንቶ ነበር
☆ ሰኔ ፲፰/፪ሺ ፲፪ ዓ.ም – June 25, 2020
ኢሳያስ አፈቆርኪ ወደ ሱዳን አመራ
☆ ሰኔ ፳፰/፪ሺ ፲፪ ዓ.ም-July 5, 2020
ኢሳያስ አፈቆርኪ ወደ ግብጽ አቀና።
☆ ሐምሌ ፲፩/፪ሺ ፲፪ ዓ.ም – July 18th, 2020
ግራኝ አብዮት አህመድ ወደ ኤርትራ አመራ የሳዋን ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከልን ጎበኘ፤ ከወር በኋላም ወደ ኤርትራ ተመልሶ ነበር።
☆ ሐምሌ ፲፫/ ፪ሺ ፲፪ ዓ.ም – 20.07.2020
የኤርትራ ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ ጄነራሎቹን ሁሉ ይዞ ወደ ሱዳን አመራ።
☆ ነሐሴ ፲፱/፪ሺ ፲፪ ዓ.ም – August 25, 2020
የቀድሞው የሲአይኤ አለቃ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ሱዳንን ጎበኘ። ከሱዳን የሉዓላዊው ምክር ቤት ኃላፊ ከሌተናል ጄኔራል አብደል ፈታህ አል–ቡርሃን ጋር ተገናኘ። ከግራኝ ጋር ቀጠሮ ይዟል።
☆ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ፦“እንደ አንድ የሲ.አይ.ኤ አገልጋይ
እንዋሽ፣ እናታልልና እንሠርቅ ነበር”። ይለናል በግልጽ።
☆ ነሐሴ ፲፱/፪ሺ ፲፪ ዓ.ም – August 25, 2020
ግራኝ አብዮት አህመድ ወደ ሱዳን አቀና፤ ከሱዳን መሪዎች ጋር ተገናኘ፤ ከቀድሞው የሲ.አይ.ኤ
አለቃ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ ጋር ተገናኘ፤ ትዕዛዝም ተቀበለ፤ ለትግራይ ጦርነትም በኤሚራቶች በኩል ድሮኖችን እንደሚያቀርቡለትና የሳተላይት መረጃም እንደሚሰጠው ተረጋገጠለት ፤ ሱዳን ከእስራኤል ጋር ግኑኝነት ለመጀመር ቃል ገባች።
☆ጳጉሜን ፪ /፪ሺ ፲፪ ዓ.ም – September September 08,2020
የሱዳን የሉዓላዊው ምክር ቤት ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብደል ፈታህ አል–ቡርሃን ኤርትራን ጎብኘ።
የሱዳንና ኤርትራ መሪዎች የሁለትዮሽ የፀጥታ ሥምምነት ተግባራዊነት ላይ ተወያዩ
☆ ጥቅምት ፪/፪ሺ፲፫ – October 12, 2020
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገባ፤ የወታደራዊ ተቋማትን እና ማዕከላትን + የሕዳሴውን ግድብ ጎበኘ + የኦሮሚያን ሲዖል ቃኘው።
☆ ጥቅምት ፲፬/፪ሺ፲፫ ዓ.ም / – October 24, 2020
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለህዳሴው ግድብ ከሱዳኑ ጠቅላይ ሃምዶክ ጋር ባደረገው አስደንጋጭ ንግግር “ግብፆች የህዳሴውን ግድብ ያፈነዱታል” አለ።
☆ ጥቅምት ፳፪/፪ሺ፲፫ ዓ.ም / ኡራኤል – November 1, 2020
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄኔራል አብዱልፈታህ አል–ቡርሃን
አዲስ አበባ ገባ ፤ በግራኞች አብዮት አህመድ እና ሽመልስ አብዲሳ
ታጅቦ የጋሎችን ካባ፣ ጦርና ጋሻ ተሸለመ ፤ “ሕዳሴ ግድብ ኬኛ!” አሉ።
☆ ጥቅምት ፳፬/፪ሺ፲፫ ዓ.ም / ተክለ ሐይማኖት – November 3, 2020
ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ በትግራይ ላይ ጦርነት አወጀ
☆ ኅዳር ፳፱ /፪ሺ፲፫ ዓ.ም – 08 December 2020
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኦስማን እና
የኢሳያስ አማካሪ የማነ ለጉብኝት ወደ ሱዳን አመሩ
☆ ታህሣሥ ፲፫/፪ሺ፲፫ ዓ.ም – December 13, 2020
የሱዳኑ ጠቅላይ ሃምዶክ ወደ አዲስ አበባ አመራ
☆ ታኅሣሥ ፯/፪ሺ፲፫ ዓ.ም – December 16, 2020
የሱዳኑ መሪ ከግራኝ ጋር በተገናኘ በሦስተኛው ቀን፤
ሱዳን በኢትዮጵያ ሰራዊት ‘ተጠቃሁ፣ ወታደሮቼ ተገደሉ‘ አለች
በበነገታው ግብጽ ከሱዳን ጋር በመቆም ኢትዮጵያን አወገዘቻት
☆ ታኅሣሥ ፲/፪ሺ፲፫ ዓ.ም – December 19, 2020
ሱዳን ወታደሮቿን ወደ ኢትዮጵያ አስገባች
_____________________________