Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • December 2020
  M T W T F S S
   123456
  78910111213
  14151617181920
  21222324252627
  28293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for December 7th, 2020

‘ጌቶቻችን’ በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው ‘ጦርነት’ (ምላሽ) እስላሙን ሎርድ “አህመድን” መድበውልናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 7, 2020

ቪዲዮው የሚያሳየን “የጌቶች/ልዑሎች ቤት – የእንግሊዝ ፓርላማ የላይኛው ምክር ቤት” በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው ጦርነት (ምላሽ) ሲሰጡ እስላሙን ሎርድ “ታሪክ አህመድን” መመደባቸውን ነው።

“ችግር – ምላሽ – መፍትሔ / “Problem – Reaction – Solution

ችግሩን ፈጥረውብናል አሁን ምላሽ እየሰጡ ነው፤ መፍትሔው፤ “የክርስቶስ ተቃዋሚውን ተቀበሉ፤ ሃይማኖቱን፣ ባሕሉን፣ ቋንቋውን፣ ኤኮኖሚውን፣ ምግቡን፣፣ ክትባቱን።

በቋንቋ ላይ የተመሰረቱ ክልሎችን እንቀበል ዘንድ የ666ቱን ‘ህገ-መንግስት’ እና ኮከቡን እ.አ.አ በ1991 ዓ.ም ላይ በለንደኑ ስብሰባ የሰጡን ሉሲፈራውያኑ ያቀዱት ሁሉ በቅደም ተከተል ተሳክቶላችው ዛሬ በግራኝ አህመድ አማካኝነት ኢትዮጵያን የመበታተኛው የመጨረሻው ደረጃ ላይ ተደርሷል። በግራኝ እና በህወሃት(ተናበው ነው የሚሠሩት)እንዲጀመር የተደረገው ጦርነት የዚህ ከመቶ ሃምሳ ዓመታት/ አምስት መቶ ዓመታት በፊት የተጀመረው የፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ ሂደት የማገባደጃው ቁልፍ ተግባር ነው።

መጀመሪያ የኢትዮጵያን ጭንቅላት ኤርትራን ቆርጠው ወሰዱ፣ ከዚያም ግራ እጇን ጅቡቲን ቆርጠው ወሰዱ፣ ዛሬ ደግሞ የጀርባ አጥንቷን ትግራይን ፈልቅቀው በማውጣት ለመገንጠል በመስራት ላይ ናቸው። ይህን ማድረግ ከቻሉ “ኢትዮጵያ” የምትባል አገር አትኖርም። ምናልባት የሉሲፈራውያን ዕቅድ ሊጨናገፍና ኢትዮጵያም ማንሰራራት የምትችለው ኤርትራ፣ ትግራይና ላስታ/ላሊበላ (ቤተ አምሐራ)የተባሉት ክፍለ ሃገራት ሰሜን ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር መመስረት ሲችሉ ብቻ ነው። ስለዚህ ዛሬ ከሚታየው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ኢሳያስ እና ሀወሃት ተወግደው መጀመሪያ ትግርኛ ተናጋሪዎቹ ኢትዮጵያውያን አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማቱ ያረፉበት ሰንደቃችንን ይዘው ሰሜን ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ቢመሠርቱ የሉሲፈራውያኑን ፍኖተ ካርታ ለመቀዳደድ እና ኢትዮጵያንም ለማዳን ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ እምነት አለኝ። ጀርመን ስትለያይ ምስራቅ እና ምዕራብ እንጅ ሌላ መጠሪያ አልነበራቸውም፤ ኮርያ ስትለያይ ሰሜን እና ደቡብ ኮርያ እንጂ ሌላ መጠሪያ የላቸውም።

ፀረ-ኢትዮጵያ ሴራው የጀመረው ከ፻፶/150 /፬፻፶/450 ዓመታት በፊት ነው። በተለይ ከአድዋው ድል በኋላ ኢትዮጵያ መንፈሳዊ የሆነ የሰሜን ሰው እንዳይገዛት በዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ተወስኗል። አፄ ቴዎድሮስን እና አፄ ዮሐንስን ከገደሏቸው በኋላ በሃገራችን የሰሜን ኢትዮጵያ ተጽዕኖ ያደረበት መንግስት ሃገሪቷን እንዳይመራ ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነውን ሤራ ለመጠንሰስና ለመተግበርም ተችሏቸዋል። አፄ ምኒሊክን፣ አፄ ኃይለ ሥላሴን፣ መንግስቱ ኃይለ ማርያምን፣ እስክገደሉት ድረስ መለስ ዜናዊን፣ ኃይለ ማርያም ደሳለኝን፣ ዐቢይ አህመድን ስልጣን ላይ በማውጣት ስጋውያኑ የቆላማው ደቡብ ኢትዮጵያ ወገኖች ብቻ ሥልጣኑን እንዲቆጣጠሩት አድርገዋል። ይህም ማለት ለአለፉት መቶ ሃምሳ ዓመታት ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሯት እነዚህ ሉሲፈራውያን እና ከኦሮሞ ጎሳ የሚመለመሉት ፀረ-ኢትዮጵያ ረዳቶቻቸው ናቸው። አፄ ምኒሊክ ከአደዋው ድንቅ ድል በኋላ ለአውሮፓውያንና ለኦሮሞዎች የኢትዮጵያን በር ብርግድ አድርገው በመክፈትና ኦሮሞዎችም እንዳሰኛቸው ግዛቶችን ወርረው እንዲይዙ፣ የቦታዎች መጠሪያ ስሞችን እንዳፈቀዳቸው እንዲቀይሩ፣ ኦሮሞ ያልሆኑትን ኢትዮጵያውያን እንዲጨፈጭፉ በማድረጋቸው እስከ እና ዘመን ድርስ የዘለቀውን ችግር ፈጥረዋል፤ ይህ የሆነውም ለአደዋው ድል ያበቃቸውን እግዚአብሔር አምላክን በመተዋቸው ነው። አፄ ምኒሊክ ንስሐ ገብተዋል የሚል እምነት አለኝ፤ ተመሳሳይ ነገር የፈጸሙት አፄ ኃይለ ሥላሴ እናል ሌሎቹ መሬዎች ግን የነበራቸውን ዕድል አልተጠቀሙበትም።

____________________________

Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኃይለኛ ዝናብ + በረዶ + ጎርፍ + መብረቅ በኩዌት እና በኢራን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 7, 2020

[ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፴፰፥፳፪]

በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍም የበረዶም ድንጋይ እሳትና

ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ።

___________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ማንን ለመምታት ነው ወደ ሰማይ ጥይት የተኮሳችሁት? ለየትኛው ድል? ለማን ሠራዊት?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 7, 2020

👉 ጦርነት እና ሰላም

ጦርነቱ የተጀመረው እኮ ኦርቶዶክሳውያንን እርስበርሱ አጋጭቶ፤ በትግራይ እና አማራ ክልሎች የሚገኙትን ኦርቶዶክሳውያንን ሆድ እና ጀርባ ለማድረግ ነው፤ ደግሞ ተሳክቶላቸዋል።

☆ “ክፉ ትውልድ ደረቅ ሴትን ይመስላል፤ እግዚአብሔርን “ቅሰፈኝ!” ይለዋል”

በጦር አንደበት፣ በፈረስ ጉልበት ያሸነፍን ይመስል ሙሉ አማራ ክልል እንዲህ ሲጨስ ያደረ ለምንድን ነው? በሰንበት ምድር ሰው ማሕሌትና ቅዳሴ ይስማ ወይስ የእነሱን ጥይት ይስማ? እያንዳንዷ የቀልሃ ጠብታ አንድ ቀን ትጠማዋለች። ፈጽሞ የሚያሳዝን፣ የሚያሳፍር ነገር ነበር።

ዛሬ እኮ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ ተብሎ የተከለለው ክልል ጣልያን የከለለው እንጂ እንዲህ የሚባል ክልል እኛ አናውቅም፤ ጠላት ያሰመርልን ክልል አንቀበልም። እኛ የምናውቀው አንዲ አገር፤ ከዚያ ባለፈ ክፍለ ሃገር ነው የምናውቀው፤ በጌምድር፣ ጎጃም፣ ትግራይ፣ ወሎ፣ ሸዋ፣ ወለጋ፣ አርሲ፣ ሲዳሞ፣ ሐረርጌ፣ ኢሉባቡር፣ ጋሞጎፋ የሚባሉትን ክፍለ ሃገራት ብቻ ነው።

ፖሊስ ሌባ እያባረረ ወደላይ ቢተኩስ ለማስፈራራት ነው፤ ተኩሶ ላለመምታት ነው፤ ግን በባዶ ሜዳ ለደስታ ተብሎ ጥይት ወደ ሰማይ የሚተኮሰው ወደ ሰማይ ያለው ማን ነው? እግዚአብሔር አይደልን? ማንን ፍለጋ ነው ወደ ሰማይ የምንተኩሰው? ይህ እኮ ባቢሎናውያኑ የነ ናምሩድ የነ ሰናኦር ሥራ ነው፤ ኑ እግዚአብሔርን እንውጋው! ወደ ሰማይ ጦር ይወረውሩ የነበሩ እነርሱ ናቸው። እንዴት አንድ አማኝ ክርስቲያን ቁጭ ብሎ ወደ ሰማይ ጥይት ይተኩሳል? ለስድስት ሰዓት ሙሉ እንዴት ጥይት በከንቱ ያለማባራት ወደ ሰማይ ይተኮሳል። በገንዘብ ደረጃ እንኳን ሲታሰብ እያንዳንዱ ጥይት በሚሊየን ብር ዋጋ ያወጣል፤ በዚህ እንኳን ብልጠት የለም። ሲጀመር እኮ ጦርነቱ ተጀመረ እንጂ አላለቀም፤ መቀሌን ለመቆጣጥር? መቀሌ እኮ የጠላት ከተማ አይደለችም የእኛው ናት፤ አስመራን፣ ካርቱምን ወይ ናይሮቢን አይደለም እኮ የያዝነው። እኛ የያዝነው እኮ የገዛ ከተማችንን ነው፤ እዚያም ያሉት እኮ ወገኖቻችን ናቸው፤ ምኑ ነው ተዓምሩ? ለመሆኑ እስካሁን በተደረገው ጦርነት ስንት ወገን የሞተ ይመስላችኋል? ስንት ተዋጊ፣ ስንት ንጹሐን ተገድለዋል? ቀላል አይደለም! እንደው የሰውን ጨለማ ልብ፣ የሰውን አለማስተዋል ለመግለጥ ቃል ያጥረኛል። እነርሱ እንደሚሉት እሺ ቲፒኤልኤፍ ጠፋች፤ ግን ተውትና መንግስት ጡጦ የሚያጠባው የእሷ ትንሽ ወንድሟ ኦነግ አለ አይደለም እንዴ?! ኧረ ኦነግንም ተውት፤ እራሱ ብልጽግና ብሎ የሚጠራው ፓርቲ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ይመስላችኋልን? ዋናው ጠላት እሱ አይደለ እንዴ!

ደግሞ እኮ “ቅዱስ ገብርኤል ነው በዕለተ ቀኑ ለድል ያበቃን!” እያሉ በየፌስቡኩ በመለቅለቅ ሊቀ መላዕክቱን የእነርሱ ወራዳ ሥራ ተሳታፊ ያደርጉታል፤ እንዴ ምኑን ከምኑ ነው የሚያገናኙት? ቅዱስ ገብርኤል ነው እንዴ ጦርነቱን ያስጀመረው? ሠራዊቱ ገብርኤል እርዳኝ እያለ ነው የተዋጋው? እንደው ያሳዝናል፤ “ክፉ ትውልድ ደረቅ ሴትን ይመስላል” እንዲሉ ይህ ክፉ ትውልድ እግዚአብሔርን “ቅሰፈኝ” ይለዋል።

ለመሆኑ የጦርነቱ ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን ለማገዝ ነው? እኛ “ቲፒኤልኤፍ ትጥፋ ከተጀመረ ላይቀር” አልን እንጅ ጦርነቱ የተጀመረው እኮ ኦርቶዶክሳውያንን እርስበርሱ አጋጭቶ፤ በትግራይ እና አማራ ክልሎች የሚገኙትን ኦርቶዶክሳውያንን ሆድ እና ጀርባ ለማድረግ ነው፤ ደግሞ ተሳክቶላቸዋል።

ወገን፤ ወታደር አያድንም፣ መከላከያ ሰራዊት አያድንም፣ ፋኖ አያድንም፣ ሚሊሺያ አያድንም፣ ልዩ ኃይል አያድንም፣ የሚያድን መድኃኔ ዓለም ብቻ ነው።

ቃለ ሕይወት ያሰማልን፤ መምህር ዮርዳኖስ! አስተዋይ ወገን አያሳጣን! “አባት፣ መምህር፣ ሊቅ” የተባለ ሁሉ ስንቱ ልሂቃን ከንቱ ነገር እየተናገረ፣ ከንቱ እንደሆነ፣ የተሳሳቱ ምልክቶችን እያሳየና ስጋዊ የሆኑ መል ዕክቶችን እያስተላለፉ እንደሆነ እያየንና እያዘንን ነው።

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: