❖ ቆሻሻውና አረመኔው አብዮት አህመድ አሊ ሚስቱንና ልጆቹን ወደ አሜሪካ ልኮ ምስኪን የትግራይ እናቶችንና ሕፃናትን በቦምብ ይደበድባል!!! እንደው የትግራይ ወንዶች ይህን አውሬ ባፋጣኝ ካልቆራረጣችሁት ወንዶች አይደላችሁም!
ቤተሰቦቹን ያጣ ጨቅላ ህፃን፣ ራሷን ስታ ያለች ታዳጊ፣ የተገደሉ አዛውንት ሴት- እነዚህ ክስተቶች የመከላከያ ሠራዊት መቀለን ለመቆጣጠርና የትግራይ ክልል አስተዳደሪ የነበረውን ህወሓትን ለመጣል በተደረገው ውጊያ ከታዩ አደጋዎችና ሞቶች መካከል የተወሰኑት ናቸው።
እነዚህ ሕዳር 19/ 2013 ዓ.ም መቀለን ለመቆጣጠር በደረሰው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከተረፉ ነዋሪዎችና ዶክተር የተሰሙም ታሪኮች ናቸው።
ከ500 ሺህ በላይ ሕዝብ ነዋሪ ባለባት የትግራይ ክልሏ መዲና መቀለ ስለተፈጠረው ነገር ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎችና ዶክተሮቹ የሚናገሩት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ካሉት ጋር ይቃረናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወቅታዊ ሁኔታን አስመልከቶ በተናገሩበት ወቅት መካላከያ ሠራዊት ባደረገው ወታደራዊ ዘመቻ አንድ ንፁህ ዜጋም አልተገደለም ማለታቸው የሚታወስ ነው።
ከጊዜ ወደ ጊዜ ሻክሮ የነበረው የፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልል አስተዳደር ግንኙነት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ አምርቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይ ልዩ ኃይል በክልሉ የሚገኘውን የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀሙ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ይህም የምድር ውጊያና የአየር ጥቃቶችን ያካተተ ነበር።
ግጭቱ ከተነሳ በኋላ የኮሚዩኒኬሽን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ መረጃ ማግኘት አዳጋች የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት የስልክ አገልግሎት በመመለሱ ቢቢሲ በርካታ ነዋሪዎችን ማናገር ችሏል። ስማቸው ለደኅንነታቸው ሲባል አልተጠቀሰም።
ማስጠንቀቂያ፡ በፅሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ሁኔታዎች አንዳንድ አንባቢያንን ሊረብሹ ስለሚችሉ ከወዲሁ እንዲጠነቀቁ እናሳስበለን።
👉 በአይደር የሚገኙ የቤት አከራይ
እለቱ ቅዳሜ ሕዳር 19/2013 ዓ.ም ነበር። በግቢያችን ውስጥ በደረሰ የከባድ መሳሪያ ድብደባ አራት ቤቶች በሙሉ ወደሙ።
በአንደኛው ቤት ውስጥ ሙሉ ቤተሰቡ አልቆ አንድ ታዳጊ ልጅ ብቻ በህይወት ተረፈ። አባቱ፣ እናቱና ሁለት እህቶቹ ወዲያው ነበር የሞቱት። አስከሬናቸውም ተቆራርጦ ነበር። ለስድስት ዓመታት ያህል ተከራይተው ነው የኖሩት። የደረሰባቸውም ሁኔታ በጣም አሳዛኝና ልብ የሚሰብር ነው።
ባለቤቴም ብትጎዳም ይህን ያህል ለክፉ የሚሰጥ አይደለም። እኔም ደረቴ ላይ ጉዳት የደረሰብኝ ሲሆን እስካሁንም አላገገምኩም። በመቀሌ ከሚገኘው ዋነኛው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል የወጣነው ከቀናት በፊት ነው።
በሆስፒታሉ ባለው የመድኃኒት፣ የህክምና ቁሳቁሶች እንዲሁም የዶክተሮች እጥረት ምክንያት ተገቢ ህክምና ማግኘት አልቻልንም። በርካታ ጉዳት ደርሶባቸው የመጡም ስለነበሩ የሆስፒታሉ ዋነኛ ትኩረት ክፉኛ በቆሰሉት ላይ ነው።
ለኔእና ለባለቤቴ ሆስፒታሉ የታዘዘልንን መድኃኒት ከውጭ በሚገኝ ፋርማሲ እንድንገዛ በተነገረን መሰረት ብንፈልግም መድኃኒት እንዳለቀ ተነገረን። ጨርሰናል፤ በክምችት ክፍላችን የለም ተባልን።
ሕይወት አዳጋች ሆናብናለች። ለአርባ ቀናት ያህል ዋና ዋና ገበያዎች እንደተዘጉ ናቸው። መሰረታዊ የሚባሉ ቁሳቁሶችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው። ምግብ ማግኘት ራሱ ፈታኝ ነው።
ህይወታቸውን ለማዳን እግሬ አውጭኝ ብለው ከመቀሌ የሸሹ ነዋሪዎችም እስካሁንም አልተመለሱም። ደብዛቸው እንደጠፋ ነው። ያሉበትንም አናውቅም።
👉 የሁለት ልጆች እናቷ በሃወልቲ አካባቢ

ከፍተኛ የሆነ የከባድ ጦር መሳሪያ ጥቃትና የአየር ድብደባዎች ከሕዳር 19/2013 ዓ.ም በፊትም በመቀለ ላይ ነበር። ሕዳር 19 ግን በመኖሪያዬ አካባቢ ተከሰተ።
ጠዋት የጀመረ እሰከ ምሽት ድረስ አላባራም። በቤታችንም ላይ የከባድ ጦር መሳሪያ ድምፆች እያፏጨ ያልፍ ነበር። በከፍተኛ ፍርሐት ውስጥ ስለነበርን ልጆቼ ያለቅሱ ነበር።
በአካባቢው በሚገኝ ቤትም የከባድ ጦር መሳሪያ በማረፉ ቤቱ ሙሉ በሙሉ ወደመ።
አንዲት አዛውንት ተገደሉ፤ ልጃቸውም ከፉኛ ቆሰለች። በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል በሞትና በሕይወት መካከል በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ትገኛለች።
አብዛኛዎቹ ጎረቤቶቻችን መቀለ ላይ ከደረሰው ከባድ ጥቃት ከተፈጸመበት ከሕዳር 19 በፊት ነው፤ ለህይወታቸው ፈርተው የሸሹት።
እኔም፣ ልጆቼም እንዲሁም በቤታችን ተከራይተው የሚኖሩ ሰዎች ሳንሸሽ ቀረን። በቤታችን አካል ጉዳተኛና መሮጥ የማትችል ሰውም ስለነበረች ነበር ሁኔታውን የጠበቅነው።
ነገር ግን በዚያች ዕለት የከባድ መሳሪያ ጥቃቱና ድብደባው በከፍተኛ ሁኔታ ሲያስጨንቀን በአቅራቢያችን ወደሚገኝ በግንባታ ላይ ወዳለ ህንፃ ስር ገብተን ምሽቱን እዚያ አሳለፍን።
👉 የተራቡ የሠራዊቱ አባላት ምግብ አንድንሰጣቸው እየጠየቁን ነበር

በነገታው ጠዋት የሰዎች ድምፅ መስማት ጀመርን፤ ነገር ግን ሁሉ ነገር እስኪረጋጋ ከተደበቅንበት ለመውጣት አልደፈርንም። ወደ በኋላ ላይ ስንወጣ ግን ከተማዋን የተቆጣጠሯትን የፌደራል መከላከያ ሠራዊት አባላትን ማየት ጀመርን።
ገበያዎቹና ሱቆቹ በመዘጋታቸው ምክንያት የሚበላ ምግብና ውሃ እንድንሰጣቸው ጠየቁን።
እርስ በርስ የምንጋራት ትንሽ ምግብ ብትኖረንም ካለችን የተወሰነ ሰጠኋቸው።
በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ገበያዎች ቢከፈቱም ዋጋቸው ከመወደዱ የተነሳ የሚቀመስ አልሆነም። ካለው የሸቀጦች እጥረትም ጋር ተያይዞ ዋጋቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እያናሩት ነው።
በመቀለ በአንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው ውሃ፣ ኤሌክትሪክ ቢመለስም እኔ ግን የምኖርበት አካባቢ አልተመለሰም።
ምግብም ለማብሰል በእንጨትና በምድጃ ነው የምንጠቀመው። እንጀራም የምንጋግረው በእንጨት ነው። ጎረቤቶቼም መጥተው ይጠቀሙበታል። የውሃ አገልግሎትም ባለመኖሩ ከመቀለ ወጣ ብሎ ከሚገኙ ጉድጓዶች ውሃ እየቀዳን ነው የምንጠቀመው።
የፌደራል መከላከያ ሠራዊት አባላት ከተማውን እየዞሩ ቅኝት ያደርጋሉ። ነዋሪዎች ፊት ለፊት ወታደሮቹን ሲያዩ በከፍተኛ ሁኔታ ይደነግጣሉ።
በአንዳንድ የትግራይ አካባቢዎች ወታደሮቹ ነዋሪዎችን እንደገደሉና ንብረትም እንደዘረፉ ቢሰማም በመቀሌ ይህንን አላየሁም።
በአንዳንድ የከተማዋ ሰፈሮች ተፈላጊ ሰዎችን ለመያዝ የቤት ለቤት አሰሳ ቢያደርጉም እኔ በምኖርበት ሰፈር ይኼ አላጋጠመኝም።
👉 ነፃ የወጡ እስረኞች ከተማዋን መዘበሩ
በሰዓት እላፊ አዋጁ ምክንያት አሁንም ቢሆን ከማታ እስከ ጠዋት በከተማዋ መንቀሳቀስ አይቻልም። እሰከ ቅርብ ቀናትም ድረስ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እየሰማን ነበር። ወታደሮቹ የከተማዋን ወጣቶች እንደገደሉ ሰምተናል።
በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ ዝርፊያም ስለነበር ወጣቶቹ የሰዓት እላፊ አዋጁን ተላልፈው ከተማዋን እየጠበቁ ነበር። ወታደሮቹም የሰዓት እላፊውን ተላልፋችኋል በሚል በሚጠይቋቸውም ወቅት በተፈጠረ ፍጥጫ ተኩሰውባቸዋል።
በክልሉ አስተዳደር የነበሩትና በከተማዋ ተሰማርተው የነበሩት ፖሊሶች በጎዳናው ላይ አይታዩም።
በከተማዋ በከፍተኛ ሁኔታ ዝርፊያ ተፈፅሟል። በተለይም የክልሉ አስተዳዳሪ በከተማዋ ላይ ቁጥጥሩን ካጣ በኋላ የከተማዋ ዝርፊያው ቀላል የሚባል አልነበረም።
አብዛኞቹ ዘረፋዎች የተፈፀሙት በቅርቡ ከእስር ቤት በወጡ ታራሚዎች ነው። ታራሚዎቹ ከእስር ቤት በነፃ ይለቀቁ ወይም ያምልጡ የምናውቀው ነገር የለም። የከተማዋ ነዋሪዎችም በዝርፊያው ተሳትፈዋል። ነገር ግን አሁን ይኼ በአብዛኛው ቆሟል።
👉 ዶክተር-በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል

አሰቃቂ የሚባለውን ጊዜ አልፈን ይኸው በህይወት አለን። እኔ ከቤተሰቤ ጋር ደህና ነኝ። ነገር ግን በሆስፒታሉ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በከባድ መሳሪያ ጥቃቱ ተገድለዋል። ሕዳር 19/2013 ዓ.ም አራት ሰዓት አካባቢ የመከላከያ ኃይል መድፎችን ጨምሮ ከባድ መሳሪያ በከተማዋ ላይ መተኮስ ጀመረ፤ ይህም እስከ ምሽት ድረስ ሳያባራ ቀጠለ።
እኔ ራሱ የ22 ሰዎች አስከሬን ቆጥሬያለሁ። ሰባት ሟቾች ጥዋት እንዲሁም 15 ሰዎች ወደ አመሻሹ አካባቢ። ሁሉም ሰላማዊ ዜጎች ናቸው። የአንዳንዶቹ አስከሬኖች በጥቃቱ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ በመጎዳታቸው ምክንያት ማንነታቸውንም ማወቅ አልተቻለም።
ማወቅ ከቻልነውም ሰዎች ውስጥ አንዲት የ10 ዓመት ታዳጊ ልጅ አስከሬን እንዲሁም የ70 ዓመት አዛውንት ይገኙበታል።
ሟቾቹ ከከተማዋ ከተለያዩ ሰፈሮች የመጡ ናቸው፤ ቀበሌ 15፣ እንዳገብርኤል፣ መናኸሪያና ቀበሌ 12 ይገኙበታል።
የአንድ ዓመት ተኩል ጨቅላ ህፃንን ጨምሮ 70 ቁስለኞችን ተቀብለናል።
የመከላከያ ሠራዊት የመቀለ ከተማን ከመቆጣጠሩ ሁለት ሳምንት በፊት የአየር ጥቃት ነበር። በጥቃቱም አንደኛው የመቀለ ዩኒቨርስቲ ካምፓስ ተመትቷል።
በአየር ጥቃቱም የተጎዱ 22 ተማሪዎችን አክመናል። በሚያሳዝን ሁኔታም አንድ የሶሺዮሎጂ ተማሪ ህይወት አልፏል።
እንደርታ አካባቢ በደረሰም ሌላ የአየር ጥቃት አንዲት እናትና የሰባት ዓመት ልጇ ተገድለዋል።
እናቲቱ ወዲያው ህይወቷ ሲያልፍ፤ ልጇ ግን ጭንቅላቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት እንዲሁም አንድ አይኗ ጠፍቶ ነበር የመጣችው። ህይወቷን ለማትረፍ የሚቻለንን ነገር ሁሉ ብናደርግም አልተሳካልንም።
በከፍተኛ ደረጃ የህሙማን አልጋ፣ የመድኃኒትና እንዲሁም የህክምና ቁሳቁሶች ግብአት እጥረት አጋጥሞ ነበር። በአሁኑ ወቅት የፌደራል መንግሥቱ በተወሰነ መልኩ የህክምና ግብአቶችን ቢልክም ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ እየሰራ አይደለም።
____________________________