Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Mariam’

A Meteor Has Crashed in The Canary Islands, Big Explosion Heard | ተዓምረ ኅዳር ጽዮን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 1, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 😇 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

🔥 በካናሪ ደሴቶች ተወርዋሪ ኮከብ ወድቋል፣ ትልቅ ፍንዳታም ተሰምቷል

🛑 የእሳት ኳሱ በስፔይን ደሴቶች በ ላስ ፓልማስ እና ቴነሪፌ እንደ ተወርዋሪ ኮከብ ሰማዩን ሲሻገር የታየ ሲሆን ከባቢ አየርን ሲያቋርጥ ያስከተለው የድምጽ ሞገድ በተለይ በግራን ካናሪያ ከፍተኛ ድምጽ አሰምቷል። አንድ ቀን በእሳተ ገሞራም ሆነ በተወርዋሪ ኮከብ አማካኝነት ከእነዚህ ደሴቶች ሊነሳ የሚችለው የባሕር ሞገድ “የበስተ ምስራቁን የአሜሪካ ጠረፍን ሙሉ በሙሉ የማውደም ብቃት አለው” ተብሏል።

🛑 The fireball was seen crossing the sky like a shooting star from Las Palmas and Tenerife, and the sonic wave that it caused when crossing the atmosphere was heard as a loud noise, especially in Gran Canaria

👉 Source / ምንጭ

💭 ቪዲዮው መጨረሻ ላይ የቀረበውን ሰውዬ ምስል እናስታውስ! ሰሞኑን ካጋጠመኝ አስደናቂ ክስተት ጋር የሚያያዝ ነገር አለ። አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምናልባት

የቀረበው ሥዕል ላይ እንደሚታየው ሳይመስል አይቀረም የሚሉ አሉ። በትናንትናው የኅዳር ጽዮን ዕለት ገላጣ በሆነ መንገድ ላይ ስራመድ በሰማይ የሚበሩ እርግቦች ከአካባቢዬ ከነበሩ ሰዎች ሁሉ ነጥለው ‘ሸክማቸውን’ መላው ሰውነቴ ላይ አራገፉብኝ። አንዳንዶቹ፤ “በል ሎተሪ ተጫወት!” ይሉኝ ነበር፤ በመገረም።

ኮከብ እንደ ፀሐይ የራሷ ብርሃን አላት፤ ታበራለች ፥ ጨረቃ ግን ብርሃን ትሰርቃለች እንጅ የራሷ ብርሃን የላትም፣ ጨለማ ናት።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፱፡፩፥፪]

ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል። ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።

ቅዱስ ኡራኤል ምስጢረ ሰማይንና እውቀትንም ሁሉ ለሔኖክ እንደገለጸለት ሁሉ ለሔኖክ የልጅ ልጅ ለኖኅም በዚያ መከራ ቀን መርከብ ለመስራት በሚያዘጋጅበት ጊዜ ምክር በመለገስ ቁሳቁስ በማቅረብ ከመርከብም ከወጣ በኃላ በሽምግልናው ዘመን ቅዱስ ኡራኤል አልተለየውም ነበር።

  • 👉 ኡራኤል የሚለው ስም `ኡር‘ እና ‘ኤል‘ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
  • 👉 ኡር ማለት በእብራይስጥ ብርሃን ማለት ሲሆን ኤል–ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው ።
  • 👉 አንድ ላይ ሲነበብ –ኡራኤል ማለት የብርሃን አምላክ ወይም የብርሃን ጌታ ማለት ነው ።

ቅዱስ ኡራኤል ከ፯/7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ፣ ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልዓክ ነዉ። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። [መጽሐፈ ሔኖክ ፮፥፪] ፣ ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሀይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። ፟[መጽሐፈ ሔኖክ ፳፰፥፲፫]

❖ ድርሳነ ኡራኤል ❖

ምድረ ኢትዮጵያ ፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሴፍና ሰሎሜ በደመና ተጭነው ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ናግራን ከተባለ ሀገር ደረሱ። በናግራን ሳሉ ጌታ እንዲህ አለ። ከቀኝ ጎኔ የሚፈሰው ደሜ በብርሃናት አለቃ በዑራኤል እጅ ተቀድቶ በቅድሚያ በዚች ሀገር ይፈሳል ወይም ይረጫል። እናቱንም እንዲህ አላት አንቺ በድንግልና ጸንሰሽ በድንግልና እንደወለድሽኝ አምነው የሚያከብሩሽ በእኔም የሚያምኑ ብዙ የተቀደሱ ሰዎች በዚህ ሀገር ይወለዳሉ። ከናግራን ተነስተው ለትግራይ ትይዩ ከሚሆን ሐማሴን ከሚባለው ሀገር ሲደርሱ በምሥራቅ በኩል ከፍተኛ ተራራ ተመለከቱና ወደ ተራራው ሄዱ። ጌታም በተራራው ላይ ሳሉ እናቱን እንዲህ አላት ይቺ ተራራ ምስጋናሽ የሚነገርባት ቦታ ትሆናለች። የተራራዋም ስም ደብረ ሃሌ ሉያ ወይም ደብረ ዳሞ ይባላል። ትርጓሜውም የአምላክ ልጅ የመስቀሉ ቦታና የስሙ መገኛ ወይም አደባባይ ማለት ነው።ከዚያም በኋላ ታቦተ ጽዮን ወደምትኖርበት ወደ አክሱም ደረሱ። ታቦተ ጽዮን ባለችበት ቦታ ሳሉ ባዚን የተባለው የኢትዮጵያ ንጉሥ ታቦተ ጽዮንን ለመሳለም መጣ። የካህናቱ አለቃ አኪን ለንጉሡ የኢሳይያስን መጽሐፍ አነበበለት። የተነበበውም የመጽሐፍ ክፍል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወንድ ልጅ ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች የሚል ነበር። ስደተኞቹ ግን ለንጉሡም ሆነ ለካህናቱ ሳይገለጡ የመጽሐፉን ቃል ከሰሙ በኋላ በደመና ተጭነው ወደ ደብረ ዐባይ ሄዱ ። ጌታም እናቱን እንዲህ አላት ይህች ሀገር እንደአክሱም ለስምሽ መጠሪያ ርስት ትሁን በኋላ ዘመን በቀናች ሃይማኖት ጸንተው ሕጌን የሚያስተምሩ አንቺን የሚወዱ ሰዎች ይኖሩባታል። ከዚያም በኋላ ከደብረ ዐባይ ተነስተው ዋሊ ወደ ሚባለው ገዳም /ወደ ዋልድባ / ሄዱ። በዋልድባ በረሃም ሳሉ በራባቸው ጊዜ ጌታ በዮሴፍ ብትር የአንዱን ዕንጨት ስር ቆፈረ። ሦስት መቶ አስራ ስምንት ስሮችን አወጣና ለእናቱ ብይ ብሎ ሰጣት። እናቱም ይህን የሚመር ዕንጨት አልበላም አለችው። ጌታም በኋላ ዘመን ስምሺን የሚጠሩ አንቺን የሚያከብሩ ብዙ መናንያን ይህን እየበሉ በዚህ ቦታ ይኖራሉ። ዕንጨቱም የሚጣፍጥ ይሆንላቸዋል አላት። ከዚህ በኋላ በደመና ተጭነው ከዋልድባ ወደ ጣና የባሕር ወደብ ሄዱ። በጣና ደሴትም ደጋግ ሰዎች ተቀብለዋቸው ሦስት ወር ከአስር ቀን ተቀመጡ። የኢትዮጵያ ሰዎች በደስታ ተቀብለዋቸዋል እንደ ግብፃውያን አላሰቃዩአቸውም ። በጥር አስራ ስምንት /፲፰/18/ ቀን ዑራኤል መጥቶ የሄሮድስን መሞት ነገራቸው ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ በደመና ከተጫኑ በኋላ ጌታ እናቱን እንዲህ አላት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎች ሁሉ ለስምሽ መታሰቢያ ይሆኑሽ ዘንድ አሥራት አድርጌ ሰጥቼሻለሁ ። ብሎ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎችን ሜዳዎችን ኮረብታዎችን አሳያት። እመቤታችን ሁሉንም ቦታዎች እየተዘዋወረች እንድታይ ልጅዋን ጠየቀችው። ልጅዋም የሚመለሱበት ጊዜ እንደደረሰ ነገራት። በብሩህ ደመና ላይ ተቀምጠው ክፍላተ አህጉር እየተዘዋወሩ ተራራዎችን ወንዞቸን አስጐበኛት የኢትዮጵያን ምድር ከጐበኙ በኋላ በደመና ተጭነው ጥር 29 ቀን ምድረ ግብፅ ደረሱ። ወደ ኢትዮጵያ የገቡት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው። ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ታሪክ በድርሳነ ዑራኤል ላይ በስፋት ተጽፏል።

❖❖❖ የቅዱስ ኡራኤል ፀሎት በያለንበት ይድረስ!ቅዱስ ኡራኤል ኢትዮጵያን የጽዮንን ልጆችን አደራ፤ በእሳት ሰረገላ በነበልባል ታጅበህ ለተልዕኮ የምትፋጠን የአምላካችን አገልጋይ ወራዙተ ኢትዮጵያን በብርሐናዊ ክንፍህ ሸፍነህ ከመርዘኞች የሞት ቀስት ከቀሳፊ ነገር ሁሉ ሰውረን!❖❖❖

❖ Colors of Zion / የጽዮን ቀለማት

የኅዳር ጽዮን ማርያም / Annual feast of St. Mary of Zion

This is a feast colorfully celebrated every year on Hidar 21 (November 30) at every church dedicated to St. Mary. The day is observed with special fervor particularly in Axum Tsion where the Ark of the Covenant is housed safely. The occasion is attended by massive Christian pilgrimages from all over Ethiopia and also foreign visitors making it one of the most joyous annual pilgrimages in Axum, the sacred city of Ethiopians.

The Church of Our Lady Mary of Zion claims to contain The original Ark of the Covenant.The Feast of the Ark of the Covenant (locally known as Tabote Tsion) is held in commemoration of different historical events including the coming of The Ark of the Covenant to Ethiopia and the construction of the first church dedicated to St. Mary in Axum.

The day also marks the destruction of Dagon by the power of The Ark of God, as recorded in the Bible, and the return of The Ark to Israel after seven months of exile at the Dagon’s house in Philistine. (1 Samuel 4; 6)

________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ልደታ ለማርያም ወረብ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2022

❖❖❖በሰንበት ተማሪዎች የቀረበ ወረብ❖❖❖

የቅድስት ልደታ ለማርያም ክብረ በዓል ፩ ግንቦት ፪ሺ፱ ዓ.ም

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ይህች ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀባት ዕለት ናት | ምስጋና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2022

❖❖❖ ልደታ ለማርያም፡ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች ❖❖❖

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም “የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት” ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ “ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች” [ኢሳ ፯፡፲፬] ብሎ ትንቢት የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡ ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ” የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።” [መዝ ፵፬፡፱] ብሎ የተናገረላት ንግሥት የተገኘችባት ዕለት ናት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ “ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት።”[ራዕ ፲፪፡፩] ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡ የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ ነው፡፡

የድንግል ማርያም ልደት በነቢያት አንደበት

መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡ መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፡፡ [መዝ ፹፮፥፩፡፯]

እግዚአብሔር የዝማሬና የትንቢት ጸጋን ያበዛለት ክቡር ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥርወ ልደት አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት ተገልጾለት “መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን /መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው/” በማለት ትንቢት ተናግሯል፡፡ “የተቀደሱ ተራሮች” ያለውም የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ከሆኑት ከተቀደሱት ከኢያቄምና ከሐና የመሆኑን ነገር ሲያመለክት ነው፡፡ ይህንን ትንቢትና እውነተኛውን የእመቤታችንን የትውልድ ሀረግ አስማምታ ቤተክርስቲያን “የእመቤታችን ማርያም ትውልዷ ባባቷ በኩል ከንጉሡ ከዳዊት ወገን ነው፤ በናቷም በኩል ከካህኑ ከአሮን ወገን ነው፤ የአባቷ ስም ኢያቄም ነው፤ የእናቷም ስም ሐና ነው፡፡” ብላ ታስተምራለች፡፡

ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ፡ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል፡፡ [ኢሳ. ፲፩፡፩]

ቁጥሩ ከዐበይት ነቢያት ወገን የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስም ጥበብንና እውቀትን በሚገልጽ ስለሚመጣውም ነገር ትንቢትን በሚያናግር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ከነገደ ዕሴይ እንደሚሆንና እርሷም ጽጌ (አበባ) የተባለ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በሕቱም ድንግልና እንደምትወልድ ተገልጾለት “ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ /ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል/” በማለት ታላቅ ትንቢትን ተናግሮ ነበር፡፡ ይህች በትርም ከእሴይ ዘር የተገኘችው በዚህች ዕለት ነውና ልደቷን በታላቅ ድምቀት እናከብራለን፡፡ ይህንን መሰረት በማድረግ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም “መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ከእሴይ ሥር የተገኘሽ መዓዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ” በማለት በውዳሴ አመስግኗታል፡፡ “በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ” [መዝ.፻፴፩፡፲፫]” የተባለልን የአባቶቻችን ልጆች እኛም እንዲሁ እያልን እናመሰግናታለን፡፡

ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ፡ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፡፡ [መኃ ፬፡፰]

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት መሰረት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡ በሊባኖስ ስለመሆኑ አስቀድሞ ጠቢቡ ሰሎሞን “ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት /ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች/” በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ የዚህ ትንቢት ምስጢርም የእመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸው የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ትንቢቱም ሲፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት ፩ ቀን በ፲፭ ዓ.ዓ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡

ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ የተባለው የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እመቤታችን በሊባኖስ እንደምትወለድ አስቀድሞ ሰሎሞን የተናገረው ቃልም መፈጸሙን ሲገልጽ “….የአናብስት ልጅ አልኩሽ፡፡ ሰሎሞን እንዲህ ሲል እንደተናገረ፡- ሙሽራዪት ሆይ ከሊባኖስ ተራራ ነዪ፤ ከአንበሶች ጒድጓድ ወጥተሽ ነዪ፤ ከምርጥ ነገድነት የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ዜና እጅግ ግሩም ነው፡፡” በማለት አመስጥሮታል፡፡ እመቤታችንም በሊባኖስ ተራራ እንድትወለድ ምክንያት የሆነው በማሕፀን ሳለች የአርሳባንን ልጅ ዓይን በማብራቷና ሳሚናስ የሚባለውን የጦሊቅን ልጅ ከሞት በማስነሳቷ አይሁድ በቅናት ተነሳስተውባቸው ስለነበር ሐናና ኢያቄም ወደ ሊባኖስ ተራራ እንዲሄዱ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ስለነገራቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡

የድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌ

ከትንቢቱ በተጨማሪም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌም አስቀድሞ የተገለጸ ነበር፡፡ ከእነዚህም መካከል ከእርሷ ሰባት ትውልድ አስቀድሞ ለነበሩት ደጋግ ሰዎች እንዲሁም ለእናትና ለአባቷ የተገለጹት ምሳሌዎች በቅዱሳት መጻሕፍት በሰፊው ሰፍረው ይገኛሉ፡፡

ሰባተኛዪቱ እንቦሳ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየሁ (ቴክታ)

በቅድስና የሚኖሩ ነገር ግን መካን የነበሩት ቴክታና ጴጥርቃ ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ ፤ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ስትደርስ ፤ ስድስተኛዪቱ ጨረቃን ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አይተው በሀገራቸው መፈክረ ሕልም (ሕልም ፈች ሊቅ) አለና ሂደው ነገሩት፡፡ ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ፤ ጨረቃይቱ ከፍጡራን በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ፡፡ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም፤ እንደ ነቢይ እንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል አላቸው፡፡ እነርሱም ጊዜ ይተርጉመው ብለውት ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላ ልጅ ወለዱ፡፡ ስሟንም “ረከብኩ ስእለትዬ፤ ረከብኩ ተምኔትዬ” /የተሳልኩትን አገኘሁ፤ የተመኘሁትን አገኘሁ/ ሲሉ “ሄኤሜን”አሏት፡፡ ሄኤሜን ዴርዴን፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡ ሐና ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ ከኢያቄምና ከሐናም በጨረቃ የተመሰለች ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡

ፀዓዳ ርግብ ሰባቱ ሰማያትን ሰንጥቃ መጥታ በማሕፀኔ ስታድር አየሁ (ቅድስት ሐና)

ኢያቄምና ሐና መካን ስለነበሩ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ጸልየው፤ ሲሰጣቸውም መልሰው ለእርሱ እንደሚሰጡ ስዕለትን ተስለው ነበር፡፡ ጸሎታቸው ሲደርስ ለሐና በሕልም ተገልጾላት ለባለቤቷ ለኢያቄም “ብእሴሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ /ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብቶ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ፡፡” ብላዋለች፡፡ የዚህ ራእይ ምስጢርም ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትሆን፤ ፀዓዳ (ነጭ) መሆኗ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ” ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መሆኗን ሲያጠይቅ ነው::

ከሰባተኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ (ቅዱስ ኢያቄም)

በተመሳሳይ ኢያቄምም በሕልሙ ያየውን ለባለቤቱ ለሐና “እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ /ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” ብሎ በሕልሙ የተገለጸለትን ነግሯታል፡፡ የዚህም ራዕይ ምስጢር ዖፍ የተባለው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፡፡ ኢያቄም “ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ የሚያጠይቅ ሲሆን ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ባህርይው፣ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው።

የድንግል ማርያም ልደት በሐዲስ ኪዳን ሊቃውንት

የሐዲስ ኪዳን ሊቃውንትም ትንቢተ ነቢያትንና ወንጌልን በማጣጣም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት አመስጥረው አስተምረዋል፤ አመስግነዋል፤ ተቃኝተዋልም፡፡ የእርሷን ልደት እጅግ ብዙ ሊቃውንት በስፋትና በጥልቀት ያመሰጠሩት ሲሆን ለምሳሌ ያህል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡

ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች (ቅዱስ ያሬድ)

ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለእመቤታችን ልደት “ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ/ ማርያምስ (ማርያም ግን) ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች፡፡” በማለት እርሷ በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና፣ በቅድስናና በድንግልና ስታበራ እንደነበርና ኋላም የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷን አመስጥሮ ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም ስለ ሥርወ ልደቷ “እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ…ሐረገ ወይን/ ሥሮቿ በምድር ጫፎቿም በሰማይ ያሉ…የወይን ሐረግ” በማለት የተወለደችው በምድር ከነበሩት ኢያቄምና ሐና መሆኑን የወለደችው ግን ሰማያዊውን ንጉሥ እንደሆነ በማመስጠር ዘምሯል፡፡ በዚህም ሰውና እግዚአብሔርን ያገናኘች መሰላል መሆኗል ገልጾ አስተምሯል፡፡

ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ (አባ ሕርያቆስ)

የብህንሳው ሊቀ ጳጳስ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም “ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ/ ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ” በማለት የድንግል ማርያም ጽንሰትና ልደት እንዴት እንደነበር በድርሰቱ አስፍሮታል፡፡ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚላት የሁላችን እናት ድንግል ማርያም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ነሐሴ ፯ ቀን ተፀንሳ ከዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በኋላ ግንቦት ፩ ቀን ተወልዳለች፡፡ እርስዋም ስትፀነስ ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከጥንተ አብሶ (original Sin) ጠብቋታል፤ አበሳው አልነካትም፡፡ ይህንንም ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በኃጢአት በተከበበ፣ መርገም በሞላበት ዓለም ውስጥ ከኃጢአት ከበደል ርቃ (ተለይታ) እንደ ጌዲዮን ጸምር በንጽህና የጠገኘች ንጽህት ዘር መሆኗን ሲያስረዳ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር፡፡”[ኢሳ.፩፡፲፱]በማለት ተናግሯል፡፡ እንዲሁም ጠቢቡ ሰሎሞን ንጽህናዋን በትንቢት መነጽር አይቶ “ወዳጄ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፣ ምንም ነውር የለብሽም፡፡ ሙሽሪት ሆይ ከሊባኖስ ነዪ፡፡”[መሓልይ ፬፡፯፡፲፮] በማለት በንጽህና በቅድስና ያጌጠች፣ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያልነካት፣ የድህነታችን ምክንያት፣ የንጽህናችን መሰረት የሰው ባህርይ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲዋሀድ ምክንያት የሆነች ንጽሕት የሰርግ ቤት ድንግል ማርያም በሊባኖስ የመወለዷን ነገር አስቀድሞ ነግሮናል፡፡

ይህች ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀባት ዕለት ናት (ቅዱስ እንድርያስ)

የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ የከበረ ስለሆነው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ታላቅነት “ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል፤ የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ ዕለት (ጌታ) መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” በማለት ገልጾታል፡፡ በእውነት የእርሷ ልደት የልዑል ማደሪያው መቅደስ የተሰራበት ዕለት ነውና ሁላችን እናከብረዋለን፡፡ በዚህም ዕለት “ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም/ እነሆ ዛሬ በእመቤታችን ልደት ደስታ ሆነ” እያልን እንዘምራለን። ይህችን የልዑል ማደሪያ እናቷ ሐናና አባቷ ኢያቄምም በእጅጉ ተደስተው በተወለደች በስምንተኛ ቀኗ ስሟን “ማርያም” ብለው ሰይመዋታል፡፡

የእመቤታችን የልደት በዓል አከባበር

አባታችን አዳም በኃጢአት ከወደቀ በኋላ፣ ንስሃ በገባ ጊዜ አምላካችን ጌታ እግዚአብሔር የድህነት ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ቃል ኪዳኑም “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚል ነበር፡፡ ስለሆነም አዳም ፶፻፭፻/5500 ዘመን የሕይወት ምክንያት የሆነች የልጅ ልጁ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአብራኩ ከተከፈሉ ቅዱሳን ልጆቹ የምትወለድበትን ቀን ተስፋ እያደረገ ኖረ፡፡ የእመቤታችንን የድንግል ማርያምን የመወለዷን ዜና ተስፋ በማድረግ “ሴት” ይላት የነበረውን ሚስቱን ሔዋንን በእመቤታችን ምሳሌነት “ሔዋን”፣ የሕያዋን ሁሉ እናት ብሎ ሰየማት፡፡ [ዘፍ.፫፡፳] ዳግማዊ አዳም የተባለ ክርስቶስም የአዳምን ተስፋ በመስቀል ላይ በፈጸመ ጊዜ እውነተኛዋን ሔዋን (ዳግሚት፣ አማናዊት ሔዋንን) ድንግል ማርያምን በዮሐንስ ወንጌላዊ በኩል ለሕያዋን ምዕመናን ሁሉ እናት አድርጎ ሰጠ፡፡ [ዮሐ. ፲፱፡፳፮] ይህን የከበረ ምስጢር የማይረዳ “ክርስቲያን” እንዴት ያሳዝናል!? እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን የቀዳማዊ አባታችንን የአዳምን፣ እንዲሁም በዳግም ተፈጥሮ ያከበረንን ዳግማዊ አዳም የተባለ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ተቀብለን “የሕያዋን ሁሉ እናት” ድንግል ማርያምን ልደቷን በፍፁም ደስታ እናከብራለን፣ ከተወደደ ልጇ ምሕረትን ትለምንልን ዘንድም ወደ እርሷ እናንጋጥጣለን፡፡

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለን ምዕመናን ከጌታችን ልደት ቀጥሎ በታላቅ ድምቀት የምናከብረው የልደት በዓል የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ቀን ነው፡፡ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ “በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።”[ሉቃ ፩፡፲፬] ከተባለ የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ የሚያስደስት ይሆን?! የነቢያቱ ትንቢት የተፈፀመበት፣ የታየው ራዕይም በገሀድ የተከናወነበት፣ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጆች ሁሉ (ለሕያዋን ሁሉ) ታላቅ የደስታ ቀን ነው፡፡ ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም በንጽህናዋ በቅድስናዋ ተደንቀው “እህትነ ነያ/እህታችን እነኋት” ብለው ያመሰግኗታል፡፡ በዘመናችን ያሉ የሰዎች ልደት በድምቀት የሚከበር ከሆነ ለሰው ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ምንኛ ሊከበር ይገባው ይሆን?! ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ከዚህ ታላቅ በዓል በረከት ረድኤትን እንድናገኝበት ነው፡፡ የሕይወት ክርስቶስ እናት ዛሬ ተወልዳለችና፡፡

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ፡፡ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ “ንፍሮና ጥራጥሬ” ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ነገር ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡ በዚህ ዕለት አንዳንዶች ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ በድፍረት “ለአድባር አዉጋር ነዉ፤ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ” እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡ እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን፤ በምሕረቱ የጎበኘንን አምላካችንን ብቻ እያመለክን፤ የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምንም እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ አሜን፡፡

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 11, 2021

...በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥ ለሚያጭደው እጁን፥ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ እቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።

💭 አዎ! ኢትዮጵያ ማለት የአዲስ ኪዳኗ እስራኤል ዘ-ነፍስ ማለት ናት። የአክሱም ጽዮንን ልጆች የሚጠሉ ጽዮን ማርያም እናታችንንና ኢትዮጵያንም ይጠላሉ ማለት ነው። ይህም ዛሬ ፺/90% የሚሆኑትን “ኢትዮጵያውያን ነን፣ ክርስቲያን ነን” የሚሉትን ግን ኢትዮጵያውያንም ክርስቲያንም ያልሆኑትን የወደቁትን ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ ይመለከታል።

አባታቻን አባ ዘ-ወንጌል ካስጠነቀቁን ነገሮች መካከል፤

ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ መሆናቸውን፤ ስለዚህ እነ አረመኔው ግራኝ የነገሱባት ‘ኢትዮጵያ’ ‘ጽዮናዊቷ ኢትዮጵያ’ ሳትሆን የዋቄዮ-አላህ ‘ኦሮሚያ’ መሆኗን

በዚህ የፈተና ወቅት ፀረትግራዋይ/ፀረጽዮናውያን የሆነ አቋም እንዳይኖረን

/10% የሚሆኑት ተዋሕዷውያን ብቻ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማየት እንደሚተርፉ

የሚሉት ይገኙበታል። ለሁላችንም በጣም ቁልፍ የሆነ ነጥብ ስለሆነ በደንብ እናስተውል!

💭 ቅዱሱ ነብይ አባታችን ንጉሥ ዳዊትም ይህን ኃይለኛ መልዕክት ነበር ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት ያስተላለፈልን፤ ድንቅ ነው!

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፳፰]✞✞✞

፩ እስራኤል። ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ ይበል፤

፪ ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም።

፫ ኃጢአተኞች በጀርባዬ ላይ መቱኝ፥ ኃጢአታቸውንም አስረዘሙአት።

፬ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ የኃጢአተኞችን አንገታቸውን ቈረጠ።

፭ ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።

፮ በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥

፯ ለሚያጭደው እጁን፥ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ እቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።

፰ በመንገዱም የሚያልፉ። የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችኋለን አይሉም።

💭 ጉብኝት ወደ ፤ ❖❖❖ታላቁ ገዳም ጉንዳ ጉንዶ ማርያም❖❖❖ ፲፬ኛው ምዕተ ዓመት ተመሠረተ

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፳፮]✞✞✞

፩ እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።

፪ በማለዳ መገሥገሣችሁም ከንቱ ነው። ለወዳጆቹ እንቅልፍን በሰጠ ጊዜ፥ እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ከተቀመጣችሁበት ተነሡ።

፫ እነሆ፥ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፥ የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።

፬ በኃያል እጅ እንዳሉ ፍላጾች፥ የጐልማስነት ልጆች እንዲሁ ናቸው።

፭ ከእነርሱ ዘንድ ምኞቱን የሚፈጽም ብፁዕ ሰው ነው፤ ጠላቶቻቸውን በአደባባይ በተናገሩ ጊዜ እርሱ አያፍርም።

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፳፯]✞✞✞

፩ እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።

፪ የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም ይሆንልሃል።

፫ ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።

፬ እነሆ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።

፭ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ።

፮ የልጆችህንም ልጆች ታያለህ። በእስራኤል ላይ ሰላም ይሁን።

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች። ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 4, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፳፫]✞✞✞

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥

ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤

በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤

በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።

ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ።

ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች። ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።

ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ስም ነው።

❖❖❖ታላቁ ገዳም ጉንዳ ጉንዶ ማርያም❖❖❖ ፲፬ኛው ምዕተ ዓመት ተመሠረተ

💭 በጉንዳ ጉንዶ ገዳም ሃያ ሁለት ሺህ ያህሉ የተሰወሩ ቅዱሳን መፃህፍቶች አሉበት

እንዴት ተሰወሩ ለሚለው ደግሞ ግራኝ አሕመድ በግዜው ብዙ ቤተ ክርስትያናት እያቃጠለ ሳለ ለሚስቱ ብዙ ቅዱሳን መፃህፍት እንድታቃጥልለት ይሰጣት ነበር።በግዜው ሚስቱ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ግራኝ አህመድ የሰጣትን መፃሕፍቶች ሳታቃጥልባቸው ትሰበስባቸው ነበር። ፳፪ ሺህ/22,000 መፃሕፍት ከሰበሰበች በኋላ ደግሞ ተሰወረች።

በኢትዮጵያ ትንሳኤ ዘመን ደግሞ እነዚህ መፃሕፍትና የግራኝ አሕመድ ሚስት ከተሰወሩበት እንደሚገለጡ እዛው ያሉ የገዳሙ መነኮሳን ነግረውናል።

በእረግጥ አሁንም ቢሆን በየትም ገዳም የማይገኙ መፃሕፍት በገዳም ጉንዳ ጉንዶ ይገኛሉ።

በገዳም ጉንዳ ጉንዶ ከየት መጣ? ማን አመጣቸው የማይባሉ የነገስታት መቃብሮች ይገኛሉ።

በቅርብ ግዜ የመጣ የአንድ ንጉስ አዲስ መቃብሮም አለ።ይህ አዲስ የንጉስ መቃብር አዲስ መሆኑን በጣም ያስታውቃል።ሽፋኑ አዲስ እምብዛም ያልቆሸሸ መቃብር ነው። በየግዜውም ማን እንደ ቀበራቸው የማይታወቁ አዳዲስ መቃብሮች ይገኛሉ።

ገዳም ጉንዳ ጉንዶ ሶስት የተላየዩ ስሞች አሉበት እነርሱም፤

፩ኛ. ደብረ ገሪዛ ነው ትርጉሙም የበረከት ቦታ ማለት ነው።

ይህ ስም በአካል ሄደህ መረጋገጥ ይቻላል እዛው ያሉ መኖኮሳን ለነገ የሚል ሀሳብ የላቸውም ያላቸው ሁሉ ለነገ የለንም ሳይሉ ለመጣ ሰው ይሰጣሉ። ማንም ሰው በቦታው ሆኖ አንድ ዳቦ ከበላ ጭራሽ አይራብም።

፪ኛ. ደብረ ካስባ ይባላል

ማርያም በራእይ ገዳሙ ለሰሩት በተገለጠችላቸው ግዜ ገዳሙ የሚሰራበት ቦታ ተናግራ ተሰወረች።

ነገር ግን የገዳሙን የሚሰራበት specific ቦታ ስላላወቁት ልክ ንግስት ኢለኒ የጌታችን የመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስቅለተ መስቀሉ ያለበትን ቦታ ለማወቅ እንዳደረገችው በዳሜራ ነበር ያወቁት። ዳሜራው በተቃጠለ ግዜ የዳሜራው ጡሽ ወደ ገዳሙ የሚሰራበት ቦታ አረፈ።

በግዜው ከሷ ላይ ምልክት እናድርግባት ተባባሉ ደብረ ከስባ ማለት ከሷ ላይ ከሚል የአማርኛ ቃል የመጣ ሁለተኛወ የገዳም ጉንዳ ጉንዶ ማርያም ስም ነው።

፫ኛ. ሶስተኛው ደግሞ ራሱ ጉንዳ ጉንዶ ነው ትርጉሙም የሃይማኖት ግንድ ማለት ነው።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከትዋና ረዲኤትዋ ይድረሰን።

የገዳም ጉንዳ ጉንዶ ደጅን የረገጠ ሰው እንኳን ለፅድቅ ብሎ ከሩቅ የተጓዘ ሰው አጋጣሚ ገዳም መሆኑን ሳያውቅ በእዛው ያለፈ ሰው እንኳን ምህረት ያገኛል። የማርያም ጉንዳ ጉንዶ ገዳም ቃል ኪዳን እንዲህ ይላል፦

ደጅሽ የረገጡ ሁሉ የዘላለም የመንግስተ ሰማያት መንበር ይዘው ይመለሳሉ” ይላል ቃል ኪዳንዋ።

ደጅዋን እንረግጥ ዘንድ ቅድስት እናታችን ትርዳን። አሜን አሜን አሜን

💭 Gunda Gundo – The Monastery That Embraces Astounding Architectural Masterpieces

The monastery of Gunda Gundo is found in the eastern zone of Tigray. Everyone could access the monastery via the town of Edagahamus, 100 km from Tigray’s capital Mekelle. From Edagahamus, 24 km travel on rough roads by car leads to Geblen, a village situated on the top of the cliff. From Geblen, tourists and local the Orthodox faithful could access it on foot since it is found between upright side cliffs. When one descends down the cliff, one can find a river. In addition to this, there are beautiful mountains, canyons and abundant fruits produced by monks. The people of Irob, who live there, are friendly and welcoming people. They know no reserve in giving everything they have to their guests.

The monastery bears its name Mariam Gunda Gundo by way of adoration of St. Marry. The church is a combination of two old mud houses that are constructed with four cruciform pillars and twelve arches. The aging church is well noted for its time honored parchments, crosses and crowns. It was constructed in the 14th century during Emperor Zerayakob. It was built by Abune Ezra also known by his nickname as ‘Ezra the wise’. The church has a rectangular shape. About 150 monks were believed to be the first dwellers of the monastery. Their leader was Aba Estifanos. The monks in general are known as Deqiqe Estifanos, meaning ‘followers of Estifanos’. Deqiqe Estifanos had faced barbaric persecution because of their theological teaching. As to historical manuscripts, Deqiqe Estifanos had a very progressive idea that could transform or upturn attitude of medieval period Ethiopian society.

When irreplaceable heritages had been ransacked and gutted down by fires invaders and intruders across Ethiopia set on, the artifacts which being kept in Gunda Gundo were spared such tragedy. Its geographical location has contributed a lot in this regard. As a result, it was named Gunda Gundo to show its preserving capability and religious significance. Before it was named Gunda Gundo, it was known as Debre Gerizen. Gunda Gundo is the oldest and famous monastery next to Debre Damo. Nevertheless, it is yet to be visited by more visitors due to the difficult geographic position.

Gunda Gundo has kept plenty of relic books, crosses, thrones and other heritages. Nevertheless, the heritages have been vulnerable to looting and damage for hundreds of years. Not only the heritages, the church.

_____________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: