Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

አይይ ‘እኅተ ማርያም’! እኛም እኮ፤ ‘ተመለሽ ንስሐ ግቢ፤ እኅታችን!’ ብለን ነበር፤ አሁን መናፍቁን ይላክብሽ?!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 19, 2021

✞✞✞የአክሱም ጽዮን ልጆችን ለሚተናኮሏቸው፤ ከጉማሬው ብርሃኑ ነጋ እስከ ጦጣው ታዲያስ ታንቱ ለእያንዳንዱ ከሃዲ የመናፍቃን እና የአህዛብ ሰይፍ አንድ በአንድ እየተላከለት ነው… ✞✞✞

ዋቄዮ-አላህ-አቴቴ እና ተመሳሳይ እርኩስ መናፍሳት በመላው ዓለም ተለቅቀዋል። እንግዲህ ከጴርጋሞን ቱርክ ወደ አራት ኪሎ ለገባው ለሰይጣን ዙፋን የሚሰግዱትንና በአክሱም ጽዮን ላይ የዘመቱትን ሁሉ ሲያቅበዘብዛቸውና እርስበርስ ሲያባላቸው እያየን ነው። በአክሱም ጽዮን ላይ የተከፈተውን ጂሃድ ተከትሎ ለጦርነቱ ድጋፍ ሰጥተው የነበሩትና የራሳቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንታኔ እየሰጡ በትግራይ ሕዝብ ላይ ሲፈርዱ በነበሩት በ ‘ባህታዊ አባ’ ገብረ መስቀል እና በ ዘመድኩን በቀለ መካከል የተከፈተውን የቃላት ጦርነት ሰምተናል፤ እራሳችንንም በሃዘንና በመገረም ነቅንቀናል፤ ታዲያ ይህ ሁሉ ከየት መጣ? ለማንም መጥፎውን አንመኝ፤ በፈቃዳቸው ያሳዩንንም ድክመቶቻቸውን እራሳቸው በበጎ ይመልከቷቸውና፤ ካልዘገየ፤ “ተጸጸቱ!” እላለሁ፤ ንስሐ ግቡ፤ እንግባ፣ ተመለሱ እንመለስ!” እላለሁ። ይህ ለሁላችንም ነው፤ ከአክሱም ጽዮን ውጭ ላሉትና በግልጽ ለሚታዩን ከሃዲ ጠላቶቿ ብቻ አይደልም፤ በአክሱም ጽዮን እና በአቅራቢያዋ አግባብ ያልሆኑ አምልኮቶችን (‘አል-ነጃሽ’ የተባለውን መስጊድ ጨምሮ) ፣ ቡና ቤቶችን፣ ጠላ ቤቶችን፣ ጭፈራ ቤቶችን ወደ አክሱም ጽዮን ያስገቡትንም ወገኖቻችንን ሁሉ ይመለከታል። ይህ ለእኔም ለራሴም ጭምር ነው!

✞✞✞[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፪]✞✞✞

፲፩ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል የነሣው በሁለተኛው ሞት አይጐዳም።

፲፪ በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል።[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፪]

፲፫ የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።

፲፬ ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።

፲፭ እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።

፲፮ እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።

፲፯ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፥ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፥ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።

፲፰ በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል።

፲፱ ሥራህንና ፍቅርህን እምነትህንም አገልግሎትህንም ትዕግሥትህንም ከፊተኛውም ሥራህ ይልቅ የኋለኛው እንዲበዛ አውቃለሁ።

፳ ዳሩ ግን። ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤

፳፩ ንስሐም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሐ እንድትገባ አልወደደችም።

፳፪ እነሆ፥ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፥ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤

፳፫ ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።

፳፬ ዳሩ ግን ይህን ትምህርት ለማትይዙ ሁሉ የሰይጣንንም ጥልቅ ነገር እነርሱ እንደሚሉት ለማታውቁ ለእናንተ በትያጥሮን ለቀራችሁት እላለሁ፤ ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም፥

፳፭ ነገር ግን እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ።

፳፮-፳፯ ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤

፳፰ የንጋትንም ኮከብ እሰጠዋለሁ።

፳፱ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።

_________________________________________

Leave a comment