Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 16th, 2021

1960s Audio Describing Who Runs the World + Why a Pathetic Reaction from The UN to #TigrayGenocide

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 16, 2021

💭 ይህ ድንቅ የድምጽ መልዕክት (አይሁዶችን በሚመለከት መስተካከል ያለበት መረጃ አለ) ከሃምሳ አራት ዓመታት በፊት/ እ.አ.አ በ1967 ዓ.ም የተላለፈ ነው። ዓለማችን በማን እንደምትመራ በደንብ ነግሮን ነበር።

አሁን በአገራችን በተለይ በትግራይ የሚታየውን አሰቃቂ ሁኔታ መንስዔ በደንብ ያብራርልናል። አስከፊውን ሁኔታ ለማስተካከል የተባበሩት መንግስታት ለምን ብዙም ግድ እንዳልሰጠው፤ ግራኝ የ2019 የኖቤል ሽልማት ለምን እንደተሰጠው፣ የተበባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም የ2020 ዓ.ም የኖቤል ሰላም ተሸላሚ እንደሆነ፣ አሜሪካ እና አውሮፓ ለምን በተደጋጋሚ መል ዕክተኞቻቸውን ወደ አዲስ አበባ እና አስመራ እንደሚልኩ ነጠብጣቦቹን እያገናኘን እንገምግበው። ድንቅ ነው!

ቭዲዮው “አሜሪካ” ቢልም፤ ዒላማዋ ግን አክሱማዊት ኢትዮጵያ ናት፣ ጥንታዊው የክርስትና እምነት ነው፣ ጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት።

አሜሪካ የሚገኘውና ቪዲዮው ላይ የተወሳው የኢሉሚናቲዎቹ ተቋም፤ “የውጭ ግንኙነት ምክር ቤት“ (CFR) Council of Foreign Relations (CFR) ልሳን የሆነው “Foreign Policy’ የወቅቱን የኢትዮጵያ ሁኔታ አስመልክቶ ብዙ “መምሪያ” ጽሑፎችን እያቀረበ ነው።

እርስበርስ የሚባሉ የሚመስሉን ተጻራሪዎች ለአንድ ግብ (በጆርጅ ሄጌል Thesis-Antithesis-Synthesis ሞዴል) በአንድነት ተናብበው የሚሠሩ የሉሲፈራውያኑ ጭፍሮች ናቸው። ከኢሳያስ አፈቆርኪ እስከ ህወሃትና ብልጽግና ሁሉም በሉሲፈራውያኑ ፕሮግራም ተደርገው የአክሱም ጽዮንን ልጆች/ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የተዘጋጁ ኃይሎች ናቸው። ፕሬዝደንት ትራምፕ እንደጠቆሙን፤ “ህወሃትን ከአዲስ አበባ ወጥተውና ስልጣኑንም ለጦርነት አስተባባሪው አዲስ አገዛዝ አስረክበው ወደ መቀሌ እንዲገቡ ሲያደርጉ” ጦርነቱ የት እንደሚካሄድ ተጠቁመን ነበር።

ጦርነቱም ግራኝ አብዮት አህመድ በትግራይ ሕዝብ ላይ ማዕቀብ በመጣል፣ ከአማራ ክልል በኩል መንገዶችን በመዝጋት፣ ኢሳያስ አፈቆርኪን ፈጥኖ በማየት፣ ጳጳሳቱን “በማስታረቅ” እና ወደ ኢትዪጵያ እንዲመለሱ በማድረግ፣ ኤሚራቶች አሰብ ወደ ላይ የድሮኖች ጣቢያ እንዲከፍቱ በማድረግ ወዘተ ተጀመረ። ህወሃቶች ይህን ሳያውቁት ቀርተው ነው? ያውቁት ነበር፤ ታዲያ ሦስት ዓመት ለቆየው እገዳ ለምን በወቅቱ ለተባበሩት መንግስታት አላሳወቁም?

በዘመነ ሂትለር እንደተጨፈጨፉት አይሁዶች በትግራይም ትግራዋያን ‘አስፈላጊ መስዋዕት’ እንዲከፍሉ እየተደረጉ ይሆንን? “አስፈላጊ መስዋዕት፣ ብዙ መሰዋዕት” የሚሉትን ቃላት በተደጋጋሚ እየሰማን ነው። ለምንስ ይሆን አንድም የአረመኔው አብዮት አህመድ አሊ አገዛዝ አባል በትግራይ ለፈጸሙት ግፍና በደል የበቀል እርምጃ ያልተወሰደባቸው? እስከ ሃያ ሺህ ትግራዋያን የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ታስረዋል። እንዴት ነው የወታደራዊ ትምህርት የወሰዱት እነዚህ የሰራዊቱ አባላት እራሳቸውን አድራጅተው በአዲስ አበባ የበቀል እርምጃ ሊወስዱ ያልቻሉት? በሕዝቡ ላይ ግፍ እየተሰራበት የሚያይና የሚሰማ የታጠቀ አንድ ትግራዋይ ብቻ ብዙ የበቀል እርምጃ በአዲስ አበባ መውሰድ በቻለና የጦርነቱን አቅጣጫ ከትግራይ መለወጥ በቻለ ነበር።

ኢሳያስ አፈቆርኪ በኤርትራ ያሉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን በማዳከም እና በመጨፍጨፉ ረገድ ለሉሲፈራውያኑ ትልቅ ባለውለታቸው ነውና እስካሁን ድረስ አላስወገዱትም፤ ከቃኛው ጣቢያ እስከ ሳዋ የወታደሮች ሥልጠና ዝግጅት እንዲያደርግና ዛሬ በአክሱም ጽዮን ላይ እኒዘምት ያደረጉት እነዚሁ ኢሉሚናቲ ሉሲፈራውያን ናቸው። ከሁለት ዓመታት በፊት አሜሪካ ኤርትራን ከሽብርተኝነት ውንጀላ ስታወጣት እና የተባበሩት መንግስታትም በኤርትራ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ሲያነሱ ኤርትራ በአክሱም ጽዮን ላይ ወረራውን እንድትጀምር አረንጓዴ መብራት ማብራታቸው ነበር።

አስገራሚ ነው፤ ከሁሉም “ሰሜናዊ” ከሆኑ ወገኖች ጋር ተናብቦ እየሰራ ያለ ብቸኛው ቡድን ኦነግ ነው። ኦነግ ከኢሳያስ አፈቆርኪ ጋር፣ ከደብረጽዮን ጋር፣ ከአብዮት አህመድ ጋር፣ ከሙስጠፌ ጋር፣ ከአዴፓ ጋር፣ ከአብን ጋር፣ ከሲዳማ እና ወላይታ እንቅስቃሴዎች ጋር፣ ከግብጽ ጋር፣ ከሳውዲ እና ኤሚራቶች ጋር፣ ከአውሮፓውያን እና አሜሪካውያን ጋር አብሮ ይሰራል። ስለዚህ አይሳካላቸውም እንጂ፤ የገሃነም እሳት ይጠብቃቸዋል እንጂ፤ ሁሉም ተናብበው የአክሱም ጽዮንን ልጆች በረሃብ፣ በበሽታ እና ጦርነት ለመጨረስ እየሰሩ እንደሆነ አንድ ቀን ብናውቅ አይግረመን።

ይህ በአክሱም ጽዮን ላይ ያነጣጠረው ጦርነት የጀመረው ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት ነው። ፤ ኢትዮጵያ በኮሪያው ጦርነት ለምን እንደተሳተፈች ቪዲዮው ይጠቁመናል?

የሶስት የዓለም ጦርነቶች እቅድ የነደፈው ነፃ ግንበኛው/Freemason አልበርት ፓይክ

አልበርት ፓይክ ከአዳም ዌሻፕት እና ጁሴፔ ማዚኒ በመቀጠል የምስጢር ማህበሩን ኢሉሚናቲን የመራ እና የሶስት የዓለም ጦርነቶችን እቅድ የነደፈ በሰይጣን መንፈስ ይመራ የነበረ ሰው ነው ፡፡ሁለቱን የዓለም ጦርነቶች በእቅዳቸው መሰረት ያሳኩ ሲሆን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እንደ እቅዳቸው ከሆነ በዓይሁድ ደጋፊዎች እና በሙስሊሙ ዓለም (political Zionists vs Moslem world) መካከል ይደረጋል፡፡የወቅቱን የዓለም ሁኔታ ስንመለከትም ጦርነቱ በመካሄድ ላይ ነው። በትግራይ ሉሲፈራውያኑ በጥንታውያኑ ክርስቲያኖች ላይ የሞት ፍርድ ፈርደውባቸዋል።

💭 በትግራይ ላይ ጦርነቱን እንደተጀመረ የሚከተለውን ጽሑፍና ቪዲዮ አቅርቤ ነበር፦

👉 “ግራኝ በቅዱስ ያሬድ ልጆች ላይ ጦርነት መክፈቱን የሚደግፉትአባቶችእነማን ናቸው?”

👉 “ለመሆኑ ይህ ጦርነት ማንን ነው “የሚጠቅመው”?”

፩ኛ. የምዕራቡን ኤዶማውያንን እና የምስራቁን እስማኤላውያንን(ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ እስላም፣ ኢአማኒ፣ ግብረሰዶም)

ምክኒያቱም፦ ሁለቱም ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን አጥፍተው የራሳቸውን ዲያብሎሳዊ ርዕዮተ ዓለማት ማስፋፋትና በኢትዮጵያ የሚገኘውን የሕይወት ዛፍም ለሳጥናኤል ስም፣ ክብርና ዝና ሲሉ መውረስ ይሻሉና ነው።

፪ኛ. ዋቀፌታን/ኦሮሙማን

ምክኒያቱ፦ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን አጥፍተው የራሳቸውን ርዕዮተ ዓለማት ማስፋፋት ይሻሉና ነው። የፕሮቴስታንቲዝም አባት ማርቲን ሉተር ወደ ጀርመንኛ በተረጎመው መጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያን‘ ‘ኩሽብሎ ነው የጻፋት። ይህ ቀላል ነገር እንዳይመስለን። እ..አ ከ 1837 እስከ 1843 .ም ባለው ጊዜ ፕሮቴስታንቱ ጀርመናዊ ዮኻን ክራፕፍ ኦሮሚያ የተባለውን ግዛት ለመመሥረት የተነሳሳው ክርስትናን ለማስፋፋት ሳይሆን፡ እንደ አንድ ፕሮቴስታንት የኢትዮጵያ ቀጥተኛ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለመዋጋት ነው። ለዚህም በወራሪነት ባሕርይ ከጀርመኖች ጋር ይስማማሉ በሚል ሃሳብ “ጋላ” ተብለው ሲጠሩ የነበሩትን ጎሳዎች ለማደራጀት በመነሳሳት በ ኢትዮጵያፋንታ ኩሽየሚለው ትርጉም ያለበትን መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ ወደ ምስራቅ አፍሪቃ/ኢትዮጵያ ተጓዝ፤ በዚህም የኦሮሙማ እንቅስቃሴን ጀመረው። ተልዕኮው ፀረኢትዮጵያ፣ ፀረተዋሕዶ እና የክርስቶስ ተቃዋሚ ተልዕኮ መሆኑን ዛሬ እያየነው ነው። ዋናው ዲያብሎሳዊ ዓላማቸው፤ ኢትዮጵያን አፍርሰው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትንም በተለይ ከአማራና ትግሬ በመንጠቅ “መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰችው ኩሽ እኛ ነን” የሚለው ነው።

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም”[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥፲]

፫ኛ. የአማራ ብሔርተኝነትን

ምክኒያቱ፦ ከኦሮሙማዎች፣ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ትግሬዎችንና ትግርኛን አጥፍተው ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን፣ ግዕዝን፣ ሰንደቁን፣ አክሱም ጽዮንን፣ ቅዱስ ያሬድና አቡነ አረጋዊን ከተቻለም መላው ትግራይንና ኤርትራን ወርሰው ለራሳቸው ብቻ ለማድረግ ይሻሉና ነው። በነገራችን ላይ፤ ኦሮሞዎች በኬኛ ቅዠታቸው ሙጭጭ ያሉበትንና “ፊንፊኔ/ ፊልፊሌ” የሚለውን ስያሜ ለአዲስ አበባ ፍልወሃ ክፍለ ከተማ እቴጌ ጣይቱ እንደሰጡት፤ “አማራ” የተባለውን የአማራ ከንቱ ብሔርተኞች ክልልን መጠሪያ ስም የሰጡት ደግሞትግሬው/ሚ መለስ ዜናዊ ነበሩ። የሕይወት ምፀት!

፬ኛ. የትግሬ ብሔርተኝነትን

ምክኒያቱ፦ ኢአማንያኑ ሻእቢያ እና ህዋሀት ቡድኖች ከኦሮሙማዎች፣ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን፣ ቅዱስ ያሬድን፣ አቡነ አረጋዊን፣አባ ዓቢየ እግዚእን፣ነገሥታቱን ኢዛናን፣ ዮሐንስን፣ ሰንደቁን፣ ግዕዝን፣ አክሱምን አጥፍተው በሃምሳ ዓመታት ውስጥ በተገኘ ጣዖታዊ ማንነት “ኢአማኒ የትግራይ ሶሻሊምዝብልጽግና” ርዕዮተ ዓለምን በመከተልና የሉሲፈር ኮከብ ያረፈበትን የቻይና ባንዲራም በማውለብለብ ከኤርትራ ጋር ለብቻቸው መኖር ይሻሉና ነው። በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የግራኝ አብዮት አህመድ እና የስብሃት ነጋ ጦርነት ነው። መንግስቱን ለኦሮሙማዎች እንዳስረከቡት፣ ቤተ ክህነትንም ለእነ ኤሬቻ በላይ በማስረክብ ላይ ያሉ ይመስላሉ። በትግራይ ላይ የተከፈተውን ጦርነት የደገፉበት አንዱ ምክኒያትም ይህ ሊሆን ይችላል፤ ዋናው ፍላጎታቸው ግን የትግርኛ ተናጋሪ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን ልብ በመስበርና ተስፋ በማስቆረጥ፡ ተዋሕዶ ክርስትናን እና ኢትዮጵያን እንዲተው ማድረግ ነው። በነገራችን ላይ፤ ዛሬ የትግራይ ከንቱ “ትግራይ! ትግራይ!” ብሔርተኞች ለሚጮሁለት ክፍለሃገር “ትግራይ” የሚለውን መጠሪያ የሰጡት ድንቁ አማራኢትዮጵያዊ ንጉሥ አፄ አምደ ጽዮን ናቸው። የሕይወት ምፀት!

ሉሲፈራውያኑ እና ቆሻሻው ወኪላቸው አብዮት አህመድ አሊ ትግራይን ከኢትዮጵያ ገንጥለው የስጋ ማንነትና ምንነት ባላቸው ጠላቶቿ የምትመራዋን የዛሬዋን ኢትዮጵያን አፈራርሰው ከሞያሌ እስከ መተከልና ጎንደር ያለውን ግዛት ለኦሮሞዎች ለማስረከብ ተግተው በመሥራት ላይ ናቸው። አማራው የስጋ ማንነትና ምንነት ካላቸው ኦሮሞዎቹ ጎን ተሰልፎ የመንፈስ ማንነትና ምንነት ባላቸው ትግሬ ወንድሞቹ ላይ በመቶ ዓመት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ጦርነት በማወጁ አብቅቶለታል! አክሱም ጽዮንን ክዷልና የሆነ ተዓምር ካልመጣ በቀር ምንም ተስፋ የለውም፤ በቅርቡ ሃገር አልባ ነው የሚሆነው። እነ ግራኝ እየሠሩ ያሉት ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያዊነታቸው፣ ከአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቃቸው እና ከተዋሕዶ ክርስትናቸው እንዲላቀቁ ብሎም አእምሯቸውን ተቆጣጥረው፣ መንፈሳቸውን አድክመውና ሞራላቸውን ሰብረው ልክ እንደ “ኤርትራውያን” ለአውሮፓውያን አረጋውያን የኩላሊትና መቅኒ መለዋወጫ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። ሰሞኑን “አማራ” የተባለው ክልል ባንዲራውን ለመቀየር መወሰኑ ከዚህ ሤራ ጋር የተያያዘ ነው። ከኦሮሞዎቹ ከእነ አብዮት አህመድ ጋር ተናበው በመስራት ላይ ያሉት ሀወሃቶች የዚህ ዲያብሎሳዊ ሤራ አካል ቢሆኑ አይገርመንም። ዋ! ! !

በዓለማችን ያሉ ብዙ ሕዝቦች በተቻለ መጠን በሃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በባህልና በመልክ የሚመስሏቸውንና የሚቀርቧቸውን ሕዝቦች እየፈለጉ ማስጠጋትና መውደድ በጀመሩበት በዚህ ዘመን ትንሿ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔሮች ግን ጥላቻን አንግሦ አንዱ ከሌላው የሚለይበትንና የሚረቅበትን፣ አንዱ ሌላውን የሚጠላበትንና የሚያርቅበትን ሰበባ ሰበብ እየፈላለገ እርስበርስ መባላቱንና ውድቀቱን መርጧል። ሞቃዲሾን አልፎ ኪጋሊንና ካምፓላን፣ ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ኤደንና ሙስካትን “ የኛ ነበሩ! የኛ ይሆናሉ!” በሚል ወኔ ታላቅነትንና አርቆ አሳቢነትን እንደ ቀደሙት አያቶቹ ይዞ “ኢትዮጵያ እርስቴ” በማለት ፈንታ እራሱን አጥብቦና በጣም አውርዶ በወልቃይትና ራያ ሚጢጢ“እርስቶች” ላንቅው እስኪበጠስ ይነታረካል። ዛሬማ ሰው ከ“አዲስ አበባ የማን ናት?” አሰልቺና አላስፈላጊ ንትርክ ወርዶ ጉልበቱንና ጊዜውን በመስቀል አደባባይና ጃን ሜዳ ላይ ብቻ እንዲያጠፋ ተደርጓል። ጃን ሜዳን እና መስቀል አደባባይን ያረከሱትን ግራኝ አብዮት አህመድን እና ታከል ዑማን አድኖ እንደመድፋት፤ “ጮኸን ጮኸን ጃን ሜዳ ተፈቀደልን!” ይልና ሆያሆየን ጨፍሮ ለቀጣዩ እንቅልፉ ወደ አልጋው ይመለሳል። በከሃዲዎቹ የሉሲፈራውያኑ ባሪያ ልሂቃኖቹ አዕምሮው እስኪጠብብ ድረስ መታጠቡ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ የለም።

የሕዝቡን ስነልቦና በልተውታል፤ ስለዚህ “አዲስ አበባ ኬኝ” ይሉና መስቀል አደባባይን እና ጃን ሜዳን በመቆፈር የተዋሕዷውያኑን ሃሳብ በነዚህ ትንንሽ ቦታዎች ላይ ብቻ እንዲቀር ያስሩታል፣ ወደ ወልቃይት፣ ራያና ሁመራ ልጆቹን እየላከ ትግሬዎች ወገኖቹን እንዲገድል፣ የራሱንም ደም እንዲያፈስ፣ የአክቲቪስቱ ሃሳብም በእነዚህ ትንንሽ ቦታዎች ብቻ ተወስኖና ታስሮ እንዲቀር፣ የቀረውም እንዲኮላሽና ሰፊዋን ኢትዮጵያን ከጠላቶቿ ነፃ ለማውጣት አቅም እንዳይኖረው፤ ብዙም እንዳይጠይቅ፣ በጥቃቅን ነገሮች ላይ ብቻ ጊዜና ጉልበቱን እያባከነ ለባርነት እንዲዘጋጅ አድርገውታል። ትልቅ ቅሌት! ወዮላችሁ!

👉 አንድን ሀገር/ሕዝብ ለመቆጣጠር ሉሲፊራውያኑ የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች፦

ተስፋ ማስቆረጥ/ሞራል መስበር

አለመረጋጋትን መፍጠር

አመፅ መቀስቀስ

መደበኛነትን/መረጋጋትን ማምጣት

👉 A Luciferian Plan of Controlling a nation by the tools of

Demoralization

Destabilization

Insurgency

Normalization

👉 “በኮርያ የጋየው ባለ33/ ፴፫ ፎቅ ሕንጻ የሉሲፈራውያኑን ደመራያሳየናል”

በቪዲዮው፦

👉 Albert Pike 33° Freemason

አልበርት ፓይክ 33/ ፴፫ ዲግሪ ነፃ ግንበኛ “ሦስት የዓለም ጦርነቶችን” “የተነበየ” የዓለማችን ተፅእኖ ፈጣሪ

(የሉሲፈራውያኑ ወኪል አብዮት አህመድ የሰውየው ተከታይ ነው)

👉 “የአክሱም ጽዮን አንዱ ጠላትና የግራኝ ሞግዚት ኢሉሚናቲው ሮትሺልድ ሞተ”

በአክሱም ጽዮን ፯፻፶፰/758 ምዕመናን ሲጨፈጨፉ ትንፍሽ ያላላችሁ ስውር የጽዮን ጠላቶች፡ ጽላተ ሙሴ በስውር የእያንዳንዳችሁንም ልብ ቀጥ የማድረግ ኃይል እንዳለው በስውር ማሕበረሰባት ዓባላት ላይ በሚቀጥሉት ቀናት፣ ሳምንታትና ወራት የሚፈጥረውን ትልቅ ትርምስ አይታችሁ ተማሩ። ይህ አንዱ ነው።

______________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 16, 2021

መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤ ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል። የሚያውቀኝ የኢትዮጵያም ሕዝብ በዚያ ተወለደ።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹፮]

፩ መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤

፪ ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል።

፫ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ በአንቺ የተከበረ ነገር ይባላል።

፬ የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ፤ እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ፥ እነዚህ በዚያ ተወለዱ።

፭ ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።

፮ እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል።

፯ በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል።

የትግራይ ወገኖቼ የዋሺንግተን ዲሲ ሉሲፈራውያኑ ነፃ ግንበኞች የሰጧችሁንና ባለ አምስት ማዕዘን ኮከብ ያረፈበትን ባለ “ሁለት ቀለም ብቻ”(ፀረ-ሥላሴ/Antitrinitarian፣ ሁለትዮሽ/Dualistic) ባንዲራ ከማውለብለብ ተቆጠቡ፤ ይህ በጣም ቁልፍ የሆነ መለኮታዊ ጉዳይ ነው።

🔥 ሁለት ተቃራኒ ቀለሞች ፣ ሁለትዮሽን ይወክላሉ። Luciferianism /ሉሲፊሪያኒዝም/ ሉሲፈራዊነት/= Dualism/ሁለትዮሽ/ዱአሊዝም።

😈ይህ አምልኮ ደግሞ ከአዲሱ ዘመን እንቅስቃሴ ፣ ከፍሪሜሶናዊነት/ከነጻ ግንበኝነት ፣ ከተባበሩት መንግስታት እና ከቴክኖክራሲ በስተጀርባ ያለ የ “ልሂቃኑ/ምርጦች/ቁንጮዎች” ድብቅ ሃይማኖት/አምልኮ ነው።

የተሟሉ የቀለም ጥንዶች የሆኑት “ቀይ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ” ግን፤ ቅድስት ሥላሴን እና ተዋሕዶን ይወክላሉ(ትክክለኛው የኢትዮጵያ/አክሱም ሰንደቅ ቀይ ከላይ ፣ በመኻል ቢጫ እና አረንጓዲ ከታች፤ ጽዮን ማርያም መኻል ላይ ያለችበት ነው)። ይህን አባታችን ኖኽ፣ እምበቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና አክሱማውያን ኢትዮጵያውያን የጽዮን ማርያም ልጆች እንጂ የተቀበልነው ከዋቄዮ-አላህ ልጆች ወይም ዛሬ “አማራ ነን” ከሚሉት ኦሮማራዎች አይደለም። በተለይ የአስኩም ጽዮን ልጆች የተቀደሰውን ለውሾች በመስጠት ከእግዚአብሔር ጋር እንዳንጣላ እና መጪው ትውልድ እንዳይረግመን እንጠንቀቅ! አውሬው እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋ እና በረከት አንድ በአንድ ለመንጠቅ ባልጠበቅነው መልክ እየመጣ ተግቶ በመስራት ላይ ነው። ይህን አስመልክቶ “ኢትዮጵያዊነታችሁን ነጥቀው እራሳቸውን “ኩሽ” ለማለት የሚሹት ፕሮቴስታንቶች የፈጠሯቸው ኦሮሞዎች በማህበረሰባዊ ሜዲያዎች “የትግራዋይ ስሞችን” በብዛት በመጠቀም “ኢትዮጵያ በአፍንጫዬ ትውጣ!፣ይህች ጋለሞታ ኢትዮጵያ ገደል ትግባ ወዘተ…” እያሉ እንደ ሕፃን ልጅ በማታለል ላይ ናቸው። ለመሆኑ የልጅ ልጆቻችሁ፤ “አባዬ፣ አማዬ እስኪ ሃገራችንመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አሳዩኝ” ሲሏችሁ ልክ እንደ ዛሬዎቹ ኤርትራውያን፤ “አይ ወስደውብን እኮ ነው! ግን እኮ በሉሲፈር መጽሐፍ ተጠቅሳለች!” ልትሏቸው ነውን? ዋ! አውሬው ለአጭር ጊዜ ስልጣን እና አፍ ተሰጥቶታልና ከሁሉም አቅጣጫ አደን ላይ ነው፤ “ተጠንቀቁ! እንጠንቀቅ! እስከ መጨረሻው እንጽና፣ ጥቂት ነው የቀረን” እላለሁ፤ ትግራይ የአክሱም ኢትዮጵያ አንዷ ክፍለሃገር እንጂ ሃገር አይደለችም ፥ እግዚአብሔርም፤ ልክ ‘ኤርትራ’፣ ‘ሱዳን’፣ ‘ኦሮሚያ’፣ ‘ሶማሊያ’ የሚባሉትን የአክሱም ኢትዮጵያን ግዛቶች በሃገርነት በጭራሽ እንደማያውቃቸው ሁሉ ‘ትግራይንም’ በሃገርነት አያውቃትም። ዛሬ ኤርትራውያን ይህን ሃቅ በውስጣቸው በደንብ ተረድተውታል። እኔ እንኳን በአቅሜ “ሬፈረንደም ሲያደርጉ” ገና ተማሪ እያለሁ የኤርትራ ወገኖቻንን ስለዚህ ጉዳይ በወቅቱ ሳስጠነቅቅ ነበር። ዛሬ ተጸጽተው የሚደውሉልኝ አሉ። 

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፫፥፬፡፱]

ለዘንዶውም ሰገዱለት፥ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም። አውሬውን ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት። ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው። እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ። ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው። ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል። ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።”

ዛሬ ብዙ ነገርድብቅ እንዳለሆነና በግልጽም ስለሚታየን በደንብ ማስተዋል አለብን። “አሐዳዊ /Unitary/ሥርዓትእና “ፈደራል” /Federal/ሥርዓት እየተባለ የሚቀበጣጠረው ነገር ካለፈው የሶሻሊዝም፣ ኮሙኒዝም፣ የገባ ካፒታሊዝም፣ ሊበራሊዝም ቅብርጥሴ የሉሲፈራውያን የማታላየና ክርስቲያኖችን የማጥፊያ ርዕዮተ ዓለማት ፍልስፍና የቀጠለ ነው። ይህምልክ እንደ ጣዖት አምላኪዎቹ የሒንዱ፣ የዋቀፌታ እና እስልምና በርካታ አማላክት ባለብዙ ሹሮች እና እጆች አሉት፤ ሊበላቸው ሊሰለቅጣቸው የሚፈልጋቸውን ሰዎችና ሕዝቦች ግን፤ Luciferianism /ሉሲፊሪያኒዝም/ ሉሲፈራዊነት/= Dualism/ሁለትዮሽ/ዱአሊዝም በተሰኘው አምልኮታዊ እና ፍልስፍናዊ ሥርዓት ነው መልኩን እየቀያየረ በመምጣት የሚያሳውራቸውና የሚያስራቸው። /Unitary/ሥርዓት እና “ፈደራል” /Federal/ሥርዓት እየተባባለ ሕዝብ የሚያልቅባት ብቸኛዋ የዓለማችን ሃገር ኢትዮጵያ ናት። በዚህ ፍልስፍና ላይ ህሊናውን የሚበክል ሕዝብ በዓለም ላይ የለም። ሉሲፈራውያኑ በኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ቤተ ሙከራ/ እንደ ጊኒ አሳማ እያዩት ነው። በኢትዮጵያ መዘርጋት የሚገባው ሥርዓትና መንግሥት የእግዚአብሔር መንግስት ብቻ ነው፤ ይኽም ለሁሉም በአክሱም ጽዮን ልጆች አማካኝነት ከካርቱም እስከ ሞቃዲሾ በሚገኙ እና በኢትዮጵያ እንዲኖሩ እግዚአብሔር በፈቀደላቸው ጎሣዎች ዘንድ ለሁሉም ሲባል በመለኮታዊ አስገዳጅነት በሥራ ላይ መዋል አለበት። ከአክሱም ጽዮን የሚነሳው ንጉሥ ቴዎድሮስ ይህን ነው የሚፈጽመው። ይህን አልቀበልም የሚል ወይንም “ዲሞክራሲ፣ ዲሞክራሲ” እያለ የሉሲፈራውያኑን የባርነትና ሞት ፍልስፍና ካልተከተልኩ የሚል ሁሉ በዚህም በዚያም በእሳት ይጠረጋል።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹፱]

፩ አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን።

፪ ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ።

፫ ሰውን ወደ ኅሳር አትመልስም፤ የሰው ልጆች ሆይ፥ ተመለሱ ትላለህ፤

፬ ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ትጋት ነውና።

፭ ዘመኖች የተናቁ ይሆናሉ፥ በማለዳም እንደ ሣር ያልፋል።

፮ ማልዶ ያብባል ያልፋልም፥ በሠርክም ጠውልጎና ደርቆ ይወድቃል።

፯ እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና።

፰ የተሰወረውን ኃጢአታችንን በፊትህ ብርሃን፥ በደላችንንም በፊትህ አስቀመጥህ።

፱ ዘመናችን ሁሉ አልፎአልና፥ እኛም በመዓትህ አልቀናልና፤ ዘመኖቻችንም እንደ ሸረሪት ድር ይሆናሉ።

፲ የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፤ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፤ ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንገሠጻለንና።

፲፩ የቍጣህን ጽናት ማን ያውቃል? ከቍጣህ ግርማ የተነሣ አለቁ።

፲፪ በልብ ጥበብን እንድንማር፥ ቀኝህን እንዲህ አስታውቀን።

፲፫ አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው? ስለ ባሪያዎችህም ተምዋገት።

፲፬ በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለን፤ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን።

፲፭ መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ ይለናል።

፲፮ ባሪያዎችህንና ሥራህን እይ፥ ልጆቻቸውንም ምራ።

፲፯ የአምላካችን የእግዚአብሔር ብርሃን በላያችን ይሁን። የእጆቻችንንም ሥራ በላያችን አቅና።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: