Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 31, 2021
VIDEO
ይሄ ደም የጠማው የሌሊት ወፍ የብዙ ንጹሐን ክርስቲያኖችን ደም ሳያፈስ ወደ ኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ባፋጣኝ መጣል ይኖርበታል። አጋጣሚው ያላችውና “ኢትዮጵያን እንወዳታለን” የምትሉ ወገኖች ሁሉ ይህን አውሬ በእሳት መጥረግ ግዴታችሁ ነው። ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተላክ አውሬ መሆኑን ስንቴ ይንገራችሁ? ስንቴስ ያሳያችሁ? ኦሮሞዎቹም እንደተለመደው ተናብበው ሆን ብለው የለቀቁትም ድምጽ ሊሆን ይችላል። ሆኖም እንዲህ ይቀበጣጠር ዘንድ አፉን ለሚከፍትልን አምላካችን ምስጋና ይድረሰው!!! የጊዮርጊስን ስለት የበላ ሳይገረፍ ይጮሃል።
😈 Leaked audio from recent closed meeting in which war criminal vampire-in-Chief Abiy Ahmed Ali asserts he will remain in power for 10 years using whatever means at his disposal. He told his cabinet members to prepare for more bloodshed as it is necessary to keep them all in power.
🔥 A Billion Wicked Thoughts as it’s meant to be heard. 😈 Abiy Ahmed Ali & Isaias Afewerki 😈 are the most evil monsters of this planet.
This monster is a vicious sociopath and will do anything he can to stay in power. His bloodlust – his desire for violence and bloodshed in vampire-like behavior is similar to vampire myths. He is a menace not only to Ethiopia, but to Africa and the entire world – he must be standing in the docks at The Hague, or thrown into the bottomless pit of The Erta Ale Lava Lake. The sooner the better!
___________ ___________ ____________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Infos , Psychology , War & Crisis | Tagged: 666 , Abiy Ahmed , Aksum , Anti-Ethiopia , Axum , ስልጣን , ቫምፓየር , ትግራይ , አረመኔነት , ኤርታ አሌ , እሳተ ገሞራ , የጦር ወንጀል , ደም መጣጭ , ግራኝ አህመድ , ግድያ , ግፍ , ጠላት , ጥላቻ , ጦርነት , ጭካኔ , ጭፍጨፋ , ጽላተ ሙሴ , ጽዮን ማርያም , ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ , ፋሺዝም , Erta Ale , Genocide , Iceland , Monster , Murderer , Power , Tigray , Vampire , Volcano , War Crimes | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 31, 2021
VIDEO
✝✝✝ ለድንቅ ዝማሬው ቃለ ዝማሬ መላዕክት ያሰማልን፤ እኅታችን !✝✝✝
🌞🌞🌞 ጊዮርጊስ ማለት “ኮከብ ብሩህ፣ ፀሐይ” ማለት ነው፡፡🌞🌞🌞
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም
አቤቱ አምላካችን ሆይ፤ ለታላቁ ሰማዕት ለቅዱስ ጊዮርጊስ በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን በአላውያን / አህዛብ እና በመናፍቃን ዘንድ የመፈራትን ግርማ እንዳጎናጸፍከው ለእኛ የወንጌል ልጆች የምንሆን አገልጋዮችህም በግዙፍ አካልና በረቂቅ መንፈስ ሊተናኮሉን በሚመጡ ጠላቶቻን ላይ ድል የመንሣትን አክሊል አቀዳጀን፤ አሜን !
ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀገሩ ፍልስጤም ልዩ ስሟ ልዳ ሲሆን የተወለደው በ፪፻፸፯/277 ዓ.ም ጥር ፳/20 ቀን ነው፡፡ አባቱ ዞሮንቶስ ወይም አንስጣስዮስ የልዳ መኳንንት ሆኖ ተሹሞ ይኖር ነበር፤ እናቱ ቴዎብስታ ወይም አቅሌስያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሌላ ማርታና እስያ የሚባሉ ሁለት ሴት ልጆችን ወልዳለች፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ አባቱ ስለሞተ ሌላ ደግ ክርስቲያናዊ መስፍን ወስዶ አሳደገው፡፡ መስፍኑም በጦር ኃይል አሰለጠነው፡፡ ፳ ዓመትም በሞላው ጊዜ መስፍኑ የ፲፭/15 ዓመት ቆንጆ ልጅ ነበረችውና እርሷን አግብቶ ሀብቴን ወርሶ ይኑር ብሎ ድግስ ሲያስደግስ ጌታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዚህ አላጨውምና የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስም ኀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ሀገር ሄደ፡፡ በቤሩት ደራጎንን ያመልኩና ሴት ልጆቻቸውን ይገብሩለት ስለነበር ሰማዕቱ ደራጎኑን በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል፡፡
ወደፋርስ ቢመለስ ዱድያኖስ ሰባ ነገሥታት ሰብስቦ ሰባ ጣዖታት አቁሞ ሲሰግድ ሲያሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖቱ ቀናዒ ነውና ከቤተመንግስቱ ገብቶ በከሃዲያኑ ሰባው ነገሥታት ፊት ክርስቲያን መሆኑን በመመስከር የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡ ዱድያኖስም ማንነቱን ከተረዳ በኋላ “አንተማ የኛ ነህ በዐሥር አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ” አለው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም “ሹመት ሽልማትህ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም” አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ዱድያኖስ እጅግ ተናዶ ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰበት፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ጌታችንን “ይህን ከሃዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰዳት” በማለት መከራውን ይታገስ ዘንድ ለመነው፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ፈቃዱን ይፈጽምለት ብዙ በመከራው ሁሉ ጽናትን ሰጥቶታል፡፡ ሦስት ጊዜም ከሞት አስነሥቶታል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም የደረሱበት እጅግ አሠቃቂ መከራዎች የሰው ኅሊና ሊያስባቸው እንኳን የማይችላቸው ናቸው፡፡
በመጀመሪያም ዱድያኖስ በእንጨት ላይ ካሰቀለው በኋላ ሥጋውን በመቃን አስፈተተው፣ ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምቶት ሂድ አለው፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል፡፡ ዳግመኛም በሰባ ችንካሮች አስቸንክሮ በእሳት አስተኩሶ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ፡፡ ሥጋውንም በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ነሰነሰበት፡፡ ሥጋውም ተቆራርጦ መሬት ላይ ወደቀ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ ከፈወሰውና “ገና ስድስት ዓመት ለስሜ ትጋደላለህ፣ 3 ጊዜ ትሞታለህ፣ በ4ኛውም ታርፋለህ” ካለው በኋላ በመከራውም ሁሉ እርሱ እንደማይለየው ነገረው፡፡
ዱድያኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከዚያ ካደረሰበት አሠቃቂ መከራዎች ሁሉ ድኖ ፍጹም ጤነኛ መሆኑን በተመለከተ ጊዜ እጅግ ደንግጦ “የሚያሸንፍልኝ ቢኖር ብዙ ወርቅ እሰጠዋለሁ” ብሎ ተናገረ፡፡ አትናስዎስ የተባለ መሰርይ(ጠንቋይ) አንዲትን ላም በጆሮዋ ሲያንሾካሹክባት ለሁለት ተሰንጥቃ ስትሞት ለንጉሡ አሳየውና ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲሚያሸንፍ ምልክት አሳየ፡፡ ንጉሡም ያሸንፍልኛል ብሎ ደስ አለው፡፡ መሰርይውም ሆድ በጥብጦ አንጀት ቆራርጦ የሚገድል መርዝ ቀምሞ አስማተ ሰይጣን ደግሞበት እንዲጠጣው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ቢጠጣው እንደ ጨረቃ ደምቆ እንደ አበባ አሸብርቆ ተገኝቷል፡፡ በዚህም ጊዜ ጠንቋዩ ማረኝ ብሎ ከእግሩ ሥር ወደቀ፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በመንኰራኩር አስፈጭቶ ከትልቅ ጉድጓድ ጥሎት ደንጊያ ዘግቶበት አትሞበት ሄደ፡፡ ጌታችንም የተፈጨውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋ በእጁ ዳስሶ ፈውሶታል፡፡ ወደ ከሃዲውም ንጉሥ ተመልሶ “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” በማለት መሰከረ፡፡ ንጉሡም ዳግመኛ በብረት አልጋ አስቸንክሮ ከበታቹ እሳት አነደደበት ነገር ግን እሳቱ ደሙ ሲንጠባጠብበት ጠፍቷል፡፡ ጌታችንም ፈወሰው፡፡ ከዚህም በኋላ ዱድያኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስን “ኢየሱስ አምላክ መሆኑን አሳየኝ” ቢለው የለመለሙትን ዕፅ አድርቆ፣ የደረቁትን ደግሞ አለምልሞ፣ ከሞቱ 430 ዓመት የሆናቸውን ሙታንን አስነሥሰቶ አሳይቶታል፡፡ ነገር ግን ንጉሡ ልቡ ክፉ ነውና በርኃብና በጽም ይሙት ብሎ ምንም ከሌላት መበለት ቤት አሳስሮታል። እርሷም የሚቀመስ ስትፈልግ ቤቷን በእህል አትረፍርፎ የታሰረበትን ግንድ ማለትም የቤቱን ምሰሶ አለምልሞታል፡፡ ልጇም ጆሮው የማይሰማ ነበርና ፈወሰላት፡፡ መበለቲቷንም ከነልጆቿ አጥምቆአቸው መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ከእስራቱ ፈትቶት ተመልሷል፡፡
ዳግመኛም ንጉሡ ዱድያኖስ ጭፍሮቹን “በመንኰራኩር ፈጭታችሁ አጥንቱን ደብረ ይድራስ ተራራ ላይ ወስዳችሁ ዝሩት” ብሎ አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥጋ በመንኰራኩር ፈጭተው ወስደው በተራራው ላይ ቢረጩት ሥጋው ያረፈበት ሳር፣ ቅጠሉ፣ ደንጊያው፣ እንጨቱ ሁሉ “ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር፣ ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር” እያሉ አመስግነዋል፡፡ አሁንም ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አስነሣውና ሥጋውን ፈጭተው በተራራም ላይ ሥጋውን በትነውት ወደ ንጉሡ የሚመለሱትን ወታደሮች በመንገድ ከኋላቸው ሄዶ ደረሰባቸውና “ቆዩኝ ጠብቁኝ” አላቸው፡፡ እነርሱም እጅግ ደንግጠው ይህ እንዴት እንደሆነ ሲጠይቁት “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” አላቸው፡፡ ጭፍሮቹም እጅግ ደንግጠው ከእግሩ ስር ወድቀው ይቅር በለን ብለው በአምላኩ እንደሚያምኑ መሰከሩለት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ከመሬት ላይ ውሃ አመንጭቶ በጸሎት ጌታችንን ቢጠይቅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ አጥምቋቸዋል፡፡ እነርሱም በንጉሣቸው ፊት ሄደው ስለጌታችን በመመስከር በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዐፅሙ ተቃጥሎ አጥንቱ ተፈጭቶ በደብረ ይድራስ ተራራ ላይ የተበተነው በዛሬዋ ዕለት ነው፡፡
አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ማረን፤ አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ራራልን፤ አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ይቅር በለን። ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን ሰማዕታትን በደም ቅዱሳንን በገዳም ሐዋርያትን በአጽናፍ ዓለም መላዕክትን በአጽራርያም እንዳጸናቸው እኛ ሁላችንንም በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን በቅድስት ቤተክርስቲያን በበጎ ምግባር በጾም በጸሎትና በትሩፋት ያጽናን አሜን።
🌞🌞🌞“ሦስት ፀሐይ” በኦሮሚያ ሲዖል | የፀሎተ ትግራይ ፍሬ ? | የዋቄዮ – አላህ ጭፍሮች ወዮላችሁ !“
VIDEO
_____________ ____________ _____________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith , Life , War & Crisis | Tagged: Aksum , Axum , ቅዱስ ጊዮርጊስ , ብሩክታዊት ገብረ መድህን , ተዋሕዶ እምነት , ትግራይ , አህዛብ , አማራ , አብይ አህመድ , አክሱም , አደዋ , ኢትዮጵያ , ኦርቶዶክስ , ኦሮሞ , ክርስትና , የዘር ማጥፋት , ያሬዳዊ ዜማ , ጀነሳይድ , ጄነሳይድ , ግፍ , ጥላቻ , ጭፍጨፋ , ጽዮን ማርያም , Ethiopia , Genocide , Massacre , St.George , St.George Gallery , Tewahedo , Tigray | Leave a Comment »