Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 30th, 2021

Ethiopia | The Luciferians Want War & The Ezekiel 38/Psalm 83 Prophecies Fulfilled

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 30, 2021

ሉሲፈራውያኑ የመዝሙር ፹፫/83 /ሕዝቅኤል ፴፰/38 ትንቢቶች ቶሎ ይሟሉ ዘንድ ሁኔታዎችን በጥድፊያ በመግፋት ላይ ናቸው፤ በተለይ በኢትዮጵያ።

ኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያን ጦርነት ይሻሉ። ለዚህ ደግሞ የዋቄዮ-አላህ ልጆች ጥሩ እረዳቶች ሆነው አግኝተዋቸዋል። ጂኒዋን አቴቴ አበቤን ዛሬ በአዲስ አበባ አየናት፤ በአረብኛ የተጻፉ መፈክሮች ተውለበለቡ፣ የክርስቶስ ተቃዋሚ አገር መሪ ኤርዶጋንን ምስሎች ከሩሲያው እና ቻይናው መሪዎች ምስሎች ጎን በሃገረ ኢትዮጵያ ለማሳየት ደፈሩ፣ ልክ በእስማኤላውያን ዓለም በተደጋጋሚ እንደምናየው የአሜሪካ ባንዲራ እንዲቃጠል ተደረገ፤። ፍልስጤማውያኑ እና ደጋፊዎቻቸው የአሜሪካን ባንዲራ ያቃጥላሉ፣ የሙአመር ጋዳፊ፣ የሳዳም ሁሴን እና የኢራን አያቶላዎች ደጋፊዎች የአሜሪካን ባንዲራ ያቃጥላሉ። በኦሮሞው ደርግ አገዛዝ ዘመን የነበረው የፀረ-አሜሪካ ዘመቻ ዛሬ ከሰላሳ ዓመታት በኋል በኦሮሞው ግራኝ አብዮት አህመድ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ተደገመ። ዋው! በኢትዮጵያ ኢትዮጵያን (ትግራይን + ኤርትራን) አጥፍተው ኩሽን(እስላማዊት ኦሮሚያ)ከመሠረቱ በኋላ ኩሽ ከሩሲያ እና እስማኤላውያኑ ዓለም ጋር አጋር እና በአርማጌዶኑ ተሳታፊ ሆና የመዝሙር ፹፫/83 /ሕዝቅኤል ፴፰/38 ትንቢቶች ቶሎ ይሟላል ማለት ነው። ይህን የፕሮቴስታንቱ መናፍቃን ዓለም እና የመሀመዳውያኑ አህዛብ ዓለም በጣምና እጅግ በጣም ይመኙታል።

እስራኤልም እስራኤል ዘ-ስጋ መሆኗን እና በእስራኤል ዘ-ነፍስ (አክሱም ጽዮን/ ኢትዮጵያ) ላይ በጣም ጥገኛ እንደሆነች መገንዘብ አለብን።

ከጽላተ ሙሴ ጋር ትልቅ ጉዳይ ስላላቸው፤ በትግራይ እና ቤተ እስራኤል ደም ውስጥ ይገኛል የሚል እምነት ስላላቸው በትግራይ ላይ ከፍተኛ ትኩረት አላቸው። ቤተ እስራኤላውያንን ወደ እስራኤል መውሰድ የጀመሩትና ዛሬም የትግራይ ስደተኞች በሚገኙባቸው የሱዳን የስደተኛ ካምፖች ውስጥ ተጠናክረው ለመሥራት የሚሹትም ለዚህ ይመስላል። 

💭 ዛሬ በአዲስ አበባ እና የዋቄዮአላህ ልጆች በሰፈሩባቸው የኦሮሚያ ከተሞች የታየው ይህ ነው።

የግብጽ ባንዲራ ቀለማት + አረብኛ ጽሑፍ + የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ መሬ ኤርዶጋን ምስል ከሉሲፈር ፔንታግራም ኮከብ ጋር። ከዚህ የበለጠ ምን ማስረጃ ይኖራል? አዎ! ለትክክለኛዋ ኢትዮጵያ፤ እግዚአብሔር ለሚያውቃት ኢትዮጵያ የስልጣኔ እና ክርስትና እምነት መሠረት የሆነችውን ትግራይን እየጨፈጨፏት ያሉት እነዚህን የመዝሙር ፹፫/83 /ሕዝቅኤል ፴፰/38 ትንቢቶች በጥድፊያ የማሟላት ፍላጎት ስላላቸው ነው። ለዚህም ነው ለትግራይ ኢትዮጵያውያን ያልቆመ፣ ድምጹን ያላሰማ፣ ያላለቀሰና ጦርነቱ እንዲቆም ያልታገለ “አህዛብ” ነው የምለው።

👉 አዎ! በትግራይ ላይ፣ በአክሱም ጽዮን ተራሮች ላይ ያመጸ ሁሉ ከክርስቶስ ተቃዋሚ ጎን ሆኖ የክርስቶስን ልጆች የሚጠላ፣ የሚያሳድድና የሚዋጋ እንዲሁም እራሱን ለገሃነም እሳት አሳልፎ የሚሰጥ ከንቱ አህዛብ ብቻ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይለናልና ይወቁት፤

በተራሮቼም ሁሉ በእርሱ ላይ ሰይፍን እጠራለሁ፥ የሰውም ሁሉ ሰይፍ በወንድሙ ላይ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍም የበረዶም ድንጋይ እሳትና ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ። ታላቅ እሆናለሁ እቀደስማለሁ በብዙ አሕዛብም ዓይን የታወቅሁ እሆናለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”

✝✝✝[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹፫]✝✝✝

፩ አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።

፪ እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።

፫ ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።

፬ ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።

፭ አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ፤ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፤

የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥

ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤

አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው

፱ እንደ ምድያምና እንደ ሲሣራ፥ በቂሶንም ወንዝ እንደ ኢያቢስ አድርግባቸው።

፲ በዓይንዶር ጠፉ፥ እንደ ምድርም ጕድፍ ሆኑ።

፲፩ አለቆቻቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፥ ታላላቆቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው።

፲፪ የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንወርሳለን የሚሉትን።

፲፫ አምላኬ ሆይ፥ እንደ ትቢያ በነፋስ ፊትም እንደ ገለባ አድርጋቸው።

፲፬ እሳት ዱርን እንደሚያቃጥል፥ ነበልባልም ተራሮች እንደሚያነድድ፥

፲፭ እንዲሁ በቍጣህ አሳድዳቸው፥ በመቅሠፍትህም አስደንግጣቸው።

፲፮ ፊታቸውን እፍረት ሙላው፥ አቤቱ፥ ስምህንም ይፈልጋሉ።

፲፯ ይፈሩ ለዘላለሙም ይታወኩ፤ ይጐስቍሉ ይጥፉም።

፲፰ ስምህም እግዚአብሔር እንደ ሆነ፥ በምድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ።

✝✝✝[ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፴፰]✝✝✝

፩ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።

፪ የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን በጎግ ላይና በማጎግ ምድር ላይ፥ በሞሳሕና በቶቤል ዋነኛ አለቃ ላይ አቅናበት፥ ትንቢትም ተናገርበት፥

፫ እንዲህም በል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የሞሳሕና የቶቢል ዋነኛ አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ።

፬ እመልስህማለሁ በመንጋጋህም ልጓም አገባብሃለሁ፥ አንተንና ሠራዊትህንም ሁሉ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን ሰይፍንም ያያዙትን ሁሉ፥ ታላቁን ወገን አወጣለሁ፥

ፋርስንና ኢትዮጵያን ፉጥንም ከእነርሱ ጋር ጋሻና የራስ ቍርን የለበሱትን ሁሉ፥

፮ ጋሜርንና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ በሰሜን ዳርቻም ያለውን የቴርጋማን ቤትና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ ብዙዎችንም ሕዝቦች ከአንተ ጋር አወጣለሁ።

______________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅዱስ ዑራኤል በደመና? | የትግራይ ጀነሳይድ እንዲቀጥል አህዛብ በአዲስ አበባ ሰልፍ በወጡበት ዕለት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 30, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

👉 ከደቂቃዎች በፊት ደመናው ልክ ወደ ኢትዮጵያ አቅጣጫ ባለው የደቡብ ምስራቅ ሰማይ ላይ

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፮፥፩፡፫]❖❖❖

እግዚአብሔር ነገሠ፤ ምድር ሐሤትን ታድርግ፥ ብዙ ደሴቶችም ደስ ይበላቸው። ደመና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው፤ ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሠረት ናቸው። እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ጠላቶቹንም በዙሪያው ያቃጥላል።

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፰፥፮፡፰]❖❖❖

ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው። እግዚአብሔርን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው። በደመና ዓምድም ተናገራቸው፤ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ። አቤቱ አምላክችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው፤አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥ ሥራቸውን ሁሉ ግን ተበቀልሃቸው።

የአሕዛብ አምልኮታቸው ከወርቅና ከብር፣ ከነሐስና ከመዳብ፣ ክድንጋይና ከእንጨት፣ ከኒኬልና ከሸክላ በሰው እጅ የተሠሩ ናቸው። አፍ እያላቸው አይናገሩም ዓይን እያላቸው አያዩም፣ ጆሮ እያላቸው አይሰሙም፣ አፍንጫ እያላቸው አያሸቱም፣ እጅ እያላቸው አይዳስሱም፣ እግር እያላቸው አይራመዱም/አይሄዱም፣ በጉሮሮአቸው አይናገሩም፣ በአፋቸውም ውስጥ ትንፋሽ የላቸውም። እንግዲህ ሠሪዎቻቸውና የሚያምኑባቸው ሁሉ እንደሱው ይሁኑ በዕውነት ለዘላለሙ አሜን።

✝✝✝አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን የቅዱስ ዑራኤል አምላክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በክርስቶስ ክርስቶሳውያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆች ከመከራ ሥጋ ፤ከመከራ ነፍስ ጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን።✝✝✝

___________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 30, 2021

💭 ድንቁ ገዳም ማርያም ታምባ ቆላ ተምቤን ትግራይ

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

❖ አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፤ እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፤ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ። እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

🌞መለአክ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤል🌞

ኡራኤል የሚለው ስም ‘ዑር’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ‘ዑራኤል’ ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ” ፣ “የአምላክ ብርሃን” ማለት ነው ። ከምወዳቸው መላዕክት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል ከ፯/7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ አለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው።

በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። [መጽሐፈ ሔኖክ ፮፥፪] ሚስጢር ሰማይና እዉቀትንም ሁሉ ለአባታችን ሔኖክ የገለፀለት፤ የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሔኖክ ነግሮታል። [መጽሐፈ ሔኖክ ፲፰፥፲፫] ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብፅ ስትሰደድ መንገድ የመራ ፤ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ፅዋ ተቀብሎ ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ ፤ እዉቀት ለተሰወረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ፅዋ ጥበብን ያጠጣ መለአክ ነው።

❖❖❖ ለትግራይ ጾም፣ ፀሎት፣ ምሕላ እና ስግደት በሚደረግባቸው በእነዚህ ሦስት ልዩ ዕለታት ሦስቱ የጽዮን ቀለማት ቀይ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ (ትክክለኛው ቅደም ተከተል) ሦስት ሆና የምትታየዋን ፀሐይዋን አጅበው እንዲህ አንጸባረቁ! የሥላሴ ሥራ ድንቅ ነው! ድንቅ ነው! ድንቅ ነው!❖❖❖

🌞🌞🌞 እግዚአብሔር በገናንነቱ ታላቅ ነው፤ ሦስት ስም አንድ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ ፀሐይን በቀን ጨረቃና ክዋክብትን በሌሊት ያሠለጠነ እሱ ከሃሊ ነው። የሚያስደነግጥ መለኮታዊ መብረቅ የተንቦገቦገ መለኮታዊ ፍሕም ተወርዋሪ መለኮታዊ ቀስት። የሚያቃጥል መለኮታዊ እሳት የሚያበራ መለኮታዊ ፋና አንጸባራቂ መለኮታዊ ፀሐይ። 🌞🌞🌞

💭“ሦስት ፀሐይ” በኦሮሚያ ሲዖል | የፀሎተ ትግራይ ፍሬ? | የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮች ወዮላችሁ!“

❖❖❖ የቅዱስ ኡራኤል በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን፤ አሜን!❖❖❖

✝✝✝[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፮]✝✝✝

፩ እግዚአብሔር ነገሠ፤ ምድር ሐሤትን ታድርግ፥ ብዙ ደሴቶችም ደስ ይበላቸው።

፪ ደመና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው፤ ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።

፫ እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ጠላቶቹንም በዙሪያው ያቃጥላል።

፬ መብረቆቹ ለዓለም አበሩ፤ ምድር አየችና ተናወጠች።

፭ ተራሮችም ከእግዚአብሔር ፊት፥ ከምድር ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።

፮ ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ።

፯ ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ መላእክቱ ሁሉ፥ ስገዱለት።

፰ አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፤

፱ አንተ፥ እግዚአብሔር፥ በምድር ላይ ሁሉ ልዑል ነህና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃልና።

፲ እግዚአብሔርን የምትወዱ፥ ክፋትን ጥሉ፤ እግዚአብሔር የቅዱሳኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥ ከኃጥኣንም እጅ ያድናቸዋል።

፲፩ ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ።

፲፪ ጻድቃን፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።

✝✝✝[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፰]✝✝✝

፩ እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፤ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።

፪ እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

፫ ግሩምና ቅዱስ ነውና ሁሉ ታላቅ ስምህን ያመስግኑ።

፬ የንጉሥ ክብር ፍርድን ይወድዳል፤ አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግህ።

፭ አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መረገጫ ስገዱ።

፮ ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው። እግዚአብሔርን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።

፯ በደመና ዓምድም ተናገራቸው፤ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ።

፰ አቤቱ አምላክችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው፤ አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥ ሥራቸውን ሁሉ ግን ተበቀልሃቸው።

፱ አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በቅዱስ ተራራውም ስገዱ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።

_____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: