VIDEO
R.I.P ነፍሳቸውን ይማርላቸው!
ሰሜን እስራኤል ውስጥ ትናንትና ጠዋት አይሁዶች በዓል በሚያከብሩበት ሥፍራ በደረሰ መገፋፋትና መረጋገጥ ፵፬/44 ሰዎች መሞታቸው ታወቀ። ሚሮን በተባለችው ከተማ ውስጥ ላግ ባኦመር የተባለው የአይሁዶች በዓል በመከበር ላይ ሳለ በደረሰው በዚሁ አደጋ ከ፻፶/150 በላይ ሰዎችም መቁሰላቸውን የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ግፍያና መረጋገጡ የደረሰው በስፍራው በርካታ ሰዎች በአንድ ጠባብ መሿለኪያ ውስጥ ለማለፍ ሲሞክሩ በተፈጠረ መጨናነቅ ነበር። ስፍራው ማስተናገድ የሚችለዉ ሰዎች ቁጥር ፲/10ሺህ መሆኑን ባለሥልጣናት ቢናገሩም ከተባለው ዐሥር እጥፍ በላይ ሰዎች በቦታው እንደነበሩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። አንድ ምእመን እንደተናገረው በአካባቢው ፶/50 ሰዎች ሊይዝ በሚችል ቦታ ላይ ቁጥራቸው ፭፻/ 500 የሚሆን ሰዎች ነበሩ። የዐይን ምስክሮች ሰዉ ወደ ተጣጣበበው ስፍራ እንዲገባ የፈቀዱትንና መውጫዎችንም በፍጥነት አልከፈቱም ያሏቸውን ፖሊሶች ወቅሰዋል። በሀገሪቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ያወጁት የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፦ በአደጋው ሥፍራ በሔሊኮፕተር ፈጥነው በመገኘት ንግግር አሰምተዋል። «በሜሮን ተራራ ላይ የተከሰተው አደጋ በእሥራኤል ሐገረ መንግሥት ታሪክ ከከፉት ክስተቶች አንደኛው ነው። በአደጋው ለሞቱት ሐዘናችን እንገልጣለን። ለሟቾች ቤተሰቦች መጽናናትን፣ ለቁስለኞች ደግሞ ፈጽሞ እንዲሻላቸው እንመኛለን።»ወደ ራቢ ሺሞን ባር ዮቻይ የመቃብር ሥፍራ መጓዝን የሚያካትተው በዓል አይሁዶች በሮማውያን ወራሪዎች ላይ ያካሄዱት አመጽ መታሰቢያ ነው። ሜሮን ተራራ ላይ የሚገኘው በአመጹ ተሳታፊ የነበሩት የራቢ ሺሞን ባር ዮቻይ የመቃብር ስፍራ በየዓመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን የሚጎበኙት ስፍራ ነው። ዛሬ በቦታው የተገኙትን ሰዎች ብዛት መገናኛ ብዙኃን ፲/10 ሺህ እንደሚጠጋ ገምተዋል።
“ሕልም ይሆን?” በማለት እራሴን ተገርሜ በመጠየቅ ላይ ነኝ። በሚሮን ከተማ ይህ አሳዛኝ ዕልቂት ሲፈጸም፤ “ሕማማተ መስቀልን” እያነበብኩ ነበር።
የሙሴ አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ በመሰሪዎቹ ከነዓናውያን ነገሥታት ላይ ድል የነሣበት ቦታ ‘ሚሮን’ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሷል።
[መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ ምዕራፍ ፲፪፥፳ ]
“የአሶር ንጉሥ፥ የሺምሮን ሚሮን ንጉሥ፥ “
በአክሱም ጽዮን ላይ ጦርነት ከፍተው የእግዚአብሔርን ልጆች በመጨፍጨፍ ላይ ያሉት እነ ግራኝ አብዮት አህመድ የተረገሙት ከነዓውያን የዋቄዮ-አላህ ልጆች ናቸው። እነዚህ የእግዚአብሔር ጠላቶች (ነገሥታት)በመጭዎቹ ቀናት ጽላተ ሙሴን በያዙትና በቅዱስ ጊዮርጊስ በሚመሩት በአክሱም ጽዮን ልጆች ድል ይነሳሉ ማለት ነው!
የሚገርም ነው፤ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት ይህን አውስቼ ነበር፤
👉 በ ፲፱፻፵/1940ዓ.ም የታዩ ቁልፍ ታሪካዊ ክስተቶች፦
☆ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከግብጽ ነፃ ወጥታ የራሷን ፓትርያርክ ትመርጥ ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ፤ በ፲፱፻፶፩/1951 ዓ.ም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመጀመሪያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ (ገብረ ጊዮርጊስ)ቀዳማዊ ሆኑ።
☆ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንደገና ትቀላቀል ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ
☆ አይሁዶች በ ፪ሺ፱፻/2900 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተባበረ እና ሉዓላዊ ሀገር በመሆን ለእስራኤል ነፃነት አወጁ – እስራኤል አገር ሆነች
👉 እነዚህ ታሪካዊ ክስተቶች ምንን እየጠቆሙን ይሆን?
❖ በኦሮማራው ንጉሥ አፄ ምኒልክ የተለያዩት የትግራይ እና ኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪ ሰሜን ኢትዮጵያውያን መዋሐድና አንድ መሆን?
❖ የሰሜን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምስረታ?
👉 ሌላው አስገራሚ ነገር፤
በዚህ የጌታችን የትንሣኤ እሁድ ዕለት የፎርሙላ አንድ ሞተር ስፖርት እስቅድምድም ወደ ፖርትጋሏ ፖርቲማኦ ተመልሷል። ዋው ! ከዚህ ጋር በተያያዘና 👉 ፵፬ /44 ቁጥርን አስመልክቶ የሚከተሉትን ጽሑፍና ቪዲዮ ልክ ከአምስት ወራት በፊት በዲሴምበር መግቢያ ላይ አቅርቢያቸው ነበር።
👉 “የዓለም ቻምፒየኑ የመርሰድስ ሾፌር የ 666 ቱን ‘ ድብቅ ‘ ዋሻ አሳየኝ”
VIDEO
ይህን ባለፉት ቀናት እንደማቀርብ ቃል የገባሁትን ቪዲዮ ሳዘጋጅ አንድ “ክው !” ያደረገኝን ሰበር ዜና ሰማሁ፤ እሱም፤ “ሉዊስ ሃሚልተን በኮሮና ተያዘ”የሚለው ነበር። ትናንትና ባቀረብኩት ቪዲዮ ላይ የተካሄደው የባሕሬኑን ውድድር ሉዊስ ሃሚልተን ነበር ያሸነፈው። “የፈረንሳይ ሁከት፣ ብጥብጥና እሳት ከአክሱም ጽዮን ጋር ምን ያገናኛቸዋል ? https://youtu.be/ZtLqhNtQ09s
ላለፉት ሳምንታት ሾፌር ሉዊስ ሃሚልተን ያሳየኝ የ 666 ቱ ድብቅ ዋሻ ይህን ይመስላል ፥ ቁጥሮቹ ላይ እናተኩር፦
ውቦቹን የግዕዝ ቍጥሮቻችንን ባለመጠቀሜ ይቅርታ …
👉 25 ኦክቶበር 2020 ዓ . ም ፖርቲማኦ ፖርቱጋል ፎርሙላ 1/F1 ሉዊስ ሃሚልተን የ 6 ጊዜ የዓለም ቻምፒየን፤ ከ 1 ኛ ቦታ ጀመረ፤ 66 ዙሮች መነዳት አለባቸው፤ በዚህ ቦታ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ
ነው የፎርሙላ 1 ውድድር ሲካሄድ፤ አሸናፊው ቍ . 44 ሉዊስ ሃሚልተን ሆነ። በፎርሙላ 1 ታሪክ ለ 92 ኛ ጊዜ ውድድሩን በማሸነፍ ሉዊስ ሃሚልተን የታላቁን ጀርመናዊ ሚካኤል ሹማከር ሬከርድ ሰበረ። የሚገርም ነው፤ ይህ በደቡብ ፖርቱጋል የሚገኘው ቦታ፤ ፖርቲማኦ በኮሮና ምክኒያት የአሜሪካን ከተሞች ተክቶ ነው በድንገት እንዲያዘጋጅ የተደረገው። ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት ወደ እዚህ አካባቢ ለጥቂት ወራት ለስራ ሄጄ ነበር፤ በጣም ድንቅ ቦታ ነው፤ በተለይ “ላጎሽ” የተባለችው ትንሽ ከተማ በዓለም ካየኋቸው ውብ ከተሞች መካከል የምትመደብ ናት።
በዚሁ ዕለት ጎረቤቴ “ላሊበላ” ወደተባለው የሃበሻ ምግብ ቤት “እንሂድ፤ እንጀራ፣ እንጀራ” ( ነጭ ናት፤ ምግባችንን ይወዱታል ) ብላኝ ሄድን፤ አጠገባችን የነበሩ እንግዶች ለምግባቸው 66 ዩሮ ከፍለው እንደወጡ፤ መሸት ሲል የቴሌቪዥኑ ዜና አንድ ታዋቂ ጀርመናዊ ፖለቲከኛ በ 66 ዓመታቸው ማረፋቸውን ተናገረ። “አሃ !” አልኩ “ዛሬ 66 ዙር በፖርቲማኦ፤ ምግብ ቤት 66 ዩሮ አሁን ደግሞ ይህ ታዋቂ ፖለቲከኛ በ 66 ዓመቱ አረፈ” በማለት ተገረምኩ። ነጠብጣቦቹ እስኪገጣጠሙልኝ ድረስ ለጎረቤቴ አልነገርኳትም።
👉 15 ኖቬምበር 2020 ዓ . ም ፥ ኢስታንቡል ቱርክ ፎርሙላ 1/F1 ፤ ቱርክም በኮሮና ምክኒያት ነው እንድታዘጋጅ የተደረገችው እንጂ ፕሮግራም ውስጥ አልተካተተችም ነበር። በኢስታንቡል ፓርክ ሉዊስ ሃሚልተን የ 6 ጊዜ የዓለም ቻምፒየን፤ ያለተለምዶው ከ 6 ኛ ቦታ ይጀምራል፤ ሁልጊዜ 1 ኛ ወይም 2 ኛ የሚጀምር ቻምፒየን ነበር፤ ዛሬ ግን 6 ኛ።
እንደሚታወቀው ቱርክ የክርስቶስ ተቃዋሚ 666 ሃገር ናት፤ በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተጠቀሱት 7 ቱ የእስያ
አብያተ ክርስቲያናት ታስረው የሚገኙትም እዚሁ ቱርክ ነው። ከሳምንታት በፊት የተከሰተውን ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ እናስታውሳለን ?
“በቱርክ ኢስታምቡልና ኢዝሚር ዛሬም በአስከፊ ማዕበል ተመቱ”
VIDEO
ለማስታወስ ያህል እ . አ . አ ከ 2007 ጀምሮ የሚሾፍረው የእንግሊዛዊው ክልስ ሉዊስ ሃሚልተን መለያ ቍ . 44 ነው።
ዝናባማ በነበረው የኢስታንቡል ፓርክ ሉዊስ ሃሚልተን ውድድሩን ክ 6 ኛ ቦታ ጀመረ፤ ወደ 3 ኛ ዘለለ፤
እንደገና ወደ 6 ኛ ተመለሰ፣ በመጨረሻም 1 ኛ ሆነ፤ በዚህም በፎርሙላ 1/F1 ታሪክ ለ 7 ኛ ጊዜ ቻምፒየን በመሆን ከታላቁ ጀርመናዊ ሚካኤል ሹማከር ሬከርድ ጋር እኩል ሆነ።
በዚህም ቍ 44 ሉዊስ ሃሚልተን በ 666 ቱ ቱርክ ሃገር አውሬውን በ 7 ሰበረው ! ስለ 7 ቱ ዓብያተ ክርስቲያናት ነበር ወዲያው ያሰብኩት።
👉 ከ 12 ዓመታት በፊት ይህን በጦማሬ ጽፌ ነበር
ቍ . 44 ሉዊስ ሃሚልተን የመጀመሪያው ጥቁር F1 ቻምፒየን፣ ባራክ ኦባማ 44 ኛውና የመጀመሪያው
ጥቁር የአሜሪካ ፕሬዚደንት። ባራክ ኦባማ በጦማሬ መልስ ሰጥቶ አይቼ ነበር። https://wp.me/piMJL-6o
👉 ይህን ቪዲዮ ሳዘጋጅ “ሉዊስ ሃሚልተን በኮሮና ተያዘ !” የሚለው ሰበር ዜና ደረሰኝ፤ ይገርማል ከአራት ወራት በፊት ሉዊስ ፀረ – ክትባት እና ፀረ – ቢል ጌትስ የሆነ አቋም እንዳለው ጭምጭምታ አሰምቶ ነበር ! ቢል ጌትስ ?
👉 አሁን ነጠብጣቦቹን እናገናኛቸው፦
☆ 666 = ቱርክ
☆ 666 = ባራክ ኦባማ
☆ 666 = ባለ 44 እድሜው አብዮት አህመድ አሊ
☆ 666 = የክትባት አባት ቢል ጌትስ
በዓለም በጣም ኃብታም ከሆኑት ስፖርተኞች መካከል አንዱ የሆነው ሉዊስ ሃሚልተን አጥባቂ ክርስቲያን ነው፤ እርዳታ ሰጭና ፀረ – ዘረኝነት ትግልን የሚያደርግ ትሁት ሰው ነው። አግዚአብሔር አምላክ ፈውሱን መድኃኒቱን ይላክለት !
ሌላ፦ ልክ “ 66% uploaded 6 minutes left” ላይ ሲደርስ ኢንተርኔቴ ያለወትሮው ተቋረጠ። እንደገና ስጀምረው፤ “ Woman says why she believes Monster Energy drinks are from Satan” / ሴትዮዋ የሞንስተር ኢነርጂ ወይንም የኃይል መጠጦች ከሰይጣን ናቸው ‘ ብላ እንደምታምን ትናገራለች” የሚለውን ቪዲዮ አየሁ። ዋው !
VIDEO
____________ ___________ ____________
Like this: Like Loading...