Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2021
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April, 2021

የጌታችን ስቅለት በዓል የአዲስ አበባ አድባራት በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው በነበሩበት ዘመን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2021

ዛሬስ? ዛሬማ የአርዮስ ኢሬቻ በላይና አጋንንት መንጋው መፈንጫዎች ሆነዋል።

✞✞✞ዓርብ ስቅለት በደብረ ቤቴል አበ ብዙሃን-አብርሃም ገዳም✞✞✞

✞✞✞ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን✞✞✞

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ የድኅነት ቀንይባላል፡

👉 ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

፩. ፀሐይ ጨለመ፤

. ጨረቃ ደም ኾነ፤

. ከዋክብት ረገፉ፤

. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤

. አለቶች ተፈረካከሱ፤

. መቃብራት ተከፈቱ፤

. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩፶፬)፡፡

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የጌታችን ስቅለት ከ፸፫/73 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅዱስ ኡራኤል ዕለት ዋለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2021

✞✞✞ዓርብ ስቅለት ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ነው✞✞✞

ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡ ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?” ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡

“ክፉ የሠራ ባይኾንስ ወደ አንተ ባላመጣነውም ነበር በሚል የሸፍጥ ቃል ሲያጕረመርሙ ጲላጦስ መልሶ እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተ ወስዳችሁ እንደሕጋችሁ ፍረዱበት፤ አላቸው፡፡ አይሁድም ኦሪት ኢትቅትል ብእሴጻድቀወኀ ጥአ ኢታኅዩ፤ ጻድቅን ሰው አትግደል፤ ኀጥኡንም ከፍርድ አታድን፤ ትላለችና እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፤ብለዋል (ዮሐ. ፲፰፥፳፰-፴፩)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ በሕጋችን ጻድቀ ባሕርይ ክርስቶስን መግደል አይገባንም ሙሉ በሙሉ ጥፋተኞች ነን፤ሲያሰኛቸው ነው፡፡ በኋላም እርሱ ሞቶ ዓለም ይድን ዘንድዳ ምድር መጥቷልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጥፋቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ ስለዚህም ገርፈው ሰቀሉት፡፡

ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ የድኅነት ቀንይባላል፡

👉 ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

፩. ፀሐይ ጨለመ፤

. ጨረቃ ደም ኾነ፤

. ከዋክብት ረገፉ፤

. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤

. አለቶች ተፈረካከሱ፤

. መቃብራት ተከፈቱ፤

. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩፶፬)፡፡

👉 ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)”

. “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ

. “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው

፬. እመቤታችንን “ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ”፤ ደቀ መዝሙሩንም “እናትህ እነኋት” በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤

፭. “አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ”

. ተጠማሁ

፯. “ዅሉ ተፈጸመ (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡

ከሰድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ሁኖአል፡፡ “ወፍና ሠርክ ይበርህ ብርሃነፀሐይእንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡

ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም “ንሴብሖለእግዚአብሔር እየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

በዕለተ ሥቅለት በደመ ወልድ ዓለምን ለመቀደስ ከሁሉ ይልቅ የተሰየመው ቅዱስ ኡራኤል ነው።

ቅዱስ ኡራኤል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በፍጹም መጠበቅን ጠብቆ ለዚህ ያደረሰን አምላካችን ክብርና ምስጋን አምልኮትና ውዳሴ ይድረሰውና ይህን ታላቅ መልአክ በችሎታችን መጠን እንድናመሰግን እግዚአብሔር ይርዳን፤ አምላክ ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን፤ ምስጢሩን ይግለጥልን አሜን፡፡

ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡” [/ዕዝ. ሱቱ. ]

በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።

በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ

በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውለሁ። ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ። መዝ. [/፺፩/፥፲፩፡፲፮]

አፈቅሮ ፈድፋደ፡ዑራኤል ሆይ፣ ከመልኮች ሁሉ ይልቅ ያንተን መልክአ ጸሎት እወዳለሁ፡፡ የመልክህ ስነ ጸዳል በደመ ወልድ እግዚአብሔር የታተመ ነውና፡፡

ዑራኤል ሆይ፣ እግዚአብሔር ሀይሉን የሚገልጽብን መልአከ ብርሃናት አንተ ነህ፡፡ በዕለተ ሥቅለት በደመ ወልድ ዓለምን ለመቀደስ ከሁሉ ይልቅ አንተ ተሰይመሃልና፡፡ ስለክብርህ የሰማይ መላእክት አደነቁ፡፡

ለተፈጥሮትከ፡

ዑራኤል ሆይ፡ያለ መናገር በጥንት አርምሞ ከነፋስና ከእሳት ለተፈጠረ ተፈጥሮህ ሰላም እላለሁ፡፡ ዑራኤል ሆይ የተፈጥሮና የይቅርታና የቸርነት ክቡር መልአክ ነህና ስለኛ ስለሰው ልጆች ወደ ልዑል እግዚአብሔር ማልድ አማላጅነትህ ዘወትር ከጥፋት ያድናልና፡፡

ለዝክረ ስምከ፡

ዑራኤል ሆይ፡ከማርና ከወተት ይልቅ ለሚጥመው ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡

ዑራኤል ሆይ፡ክፍልህ /ክንፍህ/ በደመ ወልድ እግዚአብሔር የተከበረ /የታለለ/ ነውና፡፡ ለዓለሙ ሁሉ መድሃኒት ትሆን ዘንድ ግሩም የሚሆን የእግዚአብሔር ሥልጣን በክብር ከፍ ከፍ አደረገ፡፡ (መልክአ ዑራኤል)

የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” [መዝ.፴፫/፴፬/፥፯]የሊቀ መልአኩ የክዱስ ዑራኤል ረድኤቱ በረከቱ ፍጹም አማላጅነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡

በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡ ሌሊትና ቀን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑና ሳይሰለቹ የሚጠብቁን ሊቀነ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሩፋኤል ቅዱስ ዑራኤል ቅዱስ ራጉኤል ቅዱስ ፋኑኤል እልፍ አእላፋት የሆኑ ጠባቂ መላእክት ሳመሰግን በደስታ ነው፡፡

በጸሎታቸው ያልተለዩኝን ጻድቃን አባቶቼን አቡነ ተክለሃይማኖትን አቡነ ገብረምንፈስ ቅዱስን አቡነ ሀብተማርያምን አቡነ አረጋዊን አቡነ ኪሮስንና ሌሎች ቅዱሳን አባቶቼን እንዲሁም እናቶቼን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራን ቅድስት አርሴማን ብዙ ያልጠቀስኳቸው ቅዱሳንን ለማመስገን ቃላት የለኝም፡፡

በሰማኝትነታቸው የጥንካሬ ምሳሌ የሆኑልኝ በጸሎታቸው የረዱኝን ቅዱሳን ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ቅዱስ እስጢፋኖን መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስንና ሌሎችን ቅዱሳን ሰማዕታትን ሁሉ በእጅጉ አመሰግናለሁ ለዘላለሙ አሜን፡፡

የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

___________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጸሎተ ሐሙስ / የነጻነት ሐሙስ ፪ሺ፲፫ ዛሬ በኢየሩሳሌም፤ እስራኤል | ግብጾች የኢትዮጵያን ገዳም አወኩት!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 29, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

👉 ማክሰኞ 👉 ሐሙስ 👉 ዓርብ 👉 ቅዳሜ 👉 እሑድ

በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ገዳም ግብጾች “መውረስ አለብን” እያሉ አሁን ኢትዮጵያውያን ምዕመናንን በመበጥበበጥ ላይ እንደሆኑ ከደቂቃዎች በፊት የደረሰኝ መልዕክት ይጠቁማል። ዋው! በእርግጥም አጋንንቱ ተለቅቀዋል!

ሕማማተ እግዚእ ዕለተ ሰሉስ/ማክሰኞ በገብርኤል፣ ጸሎተ ሐሙስ በማርያም፣ ዓርብ ስቅለት በኡራኤል፣ ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ) በጊዮርጊስ እንዲሁም እሑድ ትንሣኤ በተክለ ሐይማኖት ዕለታት ሲውሉ ከ፸፫/73 ዓመታት በኋላ (፲፱፻፵/1940ዓ.ም)ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። ዘንድሮ በትግራይ ሕዝብና በአክሱም ጽዮን ላይ ጦርነት የታወጀው በእነዚህ ቀናት ነበር፤ በቅዱስ ጊዮርጊስና በአባታችን በአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለታት።

👉 በ ፲፱፻፵/1940ዓ.ም የታዩ ቁልፍ ታሪካዊ ክስተቶች፦

☆ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከግብጽ ነፃ ወጥታ የራሷን ፓትርያርክ ትመርጥ ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ፤ በ፲፱፻፶፩/1951 ዓ.ም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመጀመሪያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ (ገብረ ጊዮርጊስ)ቀዳማዊ ሆኑ።

☆ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንደገና ትቀላቀል ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ

☆ አይሁዶች በ ፪ሺ፱፻/2900 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተባበረ እና ሉዓላዊ ሀገር በመሆን ለእስራኤል ነፃነት አወጁ – እስራኤል አገር ሆነች

👉 እነዚህ ታሪካዊ ክስተቶች ምንን እየጠቆሙን ይሆን?

❖ በኦሮማራው ንጉሥ አፄ ምኒልክ የተለያያኡት የትግራይ እና ኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪ ሰሜን ኢትዮጵያውያን መዋሐድና አንድ መሆን?

❖ የሰሜን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምስረታ?

_______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጸሎተ ሐሙስ | “ይህ ሥጋዬ ነው፤ ይህ ደሜ ነው” | ወገኔ ሆይ! የዳንኸውና ልጅነትን ያገኘኸው በክርስቶስ ሞትና ደም ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 29, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

👉 ማክሰኞ 👉 ሐሙስ 👉 ዓርብ 👉 ቅዳሜ 👉 እሑድ

ሕማማተ እግዚእ ዕለተ ሰሉስ/ማክሰኞ በገብርኤል፣ ጸሎተ ሐሙስ በማርያም፣ ዓርብ ስቅለት በ ኡራኤል፣ ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ) በጊዮርጊስ እንዲሁም እሑድ ትንሣኤ በተክለ ሐይማኖት ዕለታት ሲውሉ ከ፸፫/73 ዓመታት በኋላ (፲፱፻፵/1940ዓ.ም)ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። ዘንድሮ በትግራይ ሕዝብና በአክሱም ጽዮን ላይ ጦርነት የታወጀው በእነዚህ ቀናት ነበር፤ በቅዱስ ጊዮርጊስና በአባታችን በአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለታት።

👉 በ ፲፱፻፵/1940ዓ.ም የታዩ ቁልፍ ታሪካዊ ክስተቶች፦

☆ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከግብጽ ነፃ ወጥታ የራሷን ፓትርያርክ ትመርጥ ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ፤ በ፲፱፻፶፩/1951 ዓ.ም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመጀመሪያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ (ገብረ ጊዮርጊስ)ቀዳማዊ ሆኑ።

☆ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንደገና ትቀላቀል ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ

☆ አይሁዶች በ ፪ሺ፱፻/2900 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተባበረ እና ሉዓላዊ ሀገር በመሆን ለእስራኤል ነፃነት አወጁ ፥ እስራኤል አገር ሆነች

👉 እነዚህ ታሪካዊ ክስተቶች ምንን እየጠቆሙን ይሆን?

❖ በኦሮማራው ንጉሥ አፄ ምኒልክ የተለያያኡት የትግራይ እና ኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪ ሰሜን ኢትዮጵያውያን መዋሐድና አንድ መሆን?

❖ የሰሜን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምስረታ?

የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ

በጸሎተ ሐሙስ የተፈጸሙ ተግባራት

በዕለተ ሐሙስ ከተፈጸሙ ዐበይት ተግባራት አንዱ መድኃኒታችን ክርስቶስ ‹‹ይህ ሥጋዬ ነው፤ ይህ ደሜ ነው፤›› ብሎ አማናዊ ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ ነው (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፰)። እንደዚሁም ይህ ዕለት ሰፊ ጸሎት የተደረገበት የጸሎት ቀን ነው። ጌታችን ሐሙስ ዕለት ወዙ እንደ ውኃና እንደ ደም ወርዶ መሬቱን ጭቃ እስኪያደርገው ድረስ መላልሶ ስለ ጸለየ ዕለቱ ‹ጸሎተ ሐሙስ› ተብሎ ተጠርቷል። ጌታችን የጸለየበትን ቦታም ወንጌላውያኑ በተለያየ ስያሜ ጠርተውታል፤ ማቴዎስና ማርቆስ – ‹ዐፀደ ወይን›፣ ‹ጌቴሴማኒ›፤ ሉቃስ – ‹ደብረ ዘይት›፤ ዮሐንስ – ‹ማዕዶተ ቄድሮስ›፣ ‹ፈለገ አርዝ›፣ ‹ዐፀደ ሐምል› በማለት ሰይመውታል (ማቴ.፳፮፥፴፮፤ ማር.፲፬፥፴፪፤ ሉቃ. ፳፩፥፴፯፤ ፳፪፥፴፱፤ ዮሐ. ፲፰፥፩)።

በተጨማሪም ይህ ዕለት (ሐሙስ) ያለ እርሱ ፈቃድ ሊይዙት እንደማይችሉ ለማስረዳት ጌታችን በመለኮታዊ ኃይሉ እንደ ቅጠል እንዲረግፉ ካደረጋቸው በኋላ በይቅርታው ብዛት መልሶ በማስነሣት በፈቃዱ ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠበት ዕለት ነው (ዮሐ. ፲፰፥፭-፰)። በዕለተ ሐሙስ ከተከናወኑ ዐበይት ተግባራት መካከል ሠራዔ ሕግ፣ ፈጻሜ ሕግ የኾነው ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕገ ኦሪትን እየፈጸመ አድጓልና በኦሪት ሥርዓት የሚፈጸመውን የመጨረሻውን በግዐ ፋሲካ (የፋሲካ በግ) ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መመገቡ አንደኛው ነው። ይሁዳ እንደሚያስይዘው ለሐዋርያት በምልክት ማስረዳቱ ሁለተኛው ሲኾን (ዮሐ. ፲፫፥፳፩)፤ እንደ አገልጋይ ራሱን ዝቅ አድርጎ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ ደግሞ ሦስተኛው ነው።

ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር የማጠቡ ምሥጢር

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ካጠበ በኋላ ‹‹እናንተ መምህራችን፣ ጌታችን ትሉኛላችሁ፤ መልካም ትላላችሁ። እኔ ጌታችሁ መምህራችሁ ስኾን ዝቅ ብዬ እግራችሁን ካጠብኋችሁ እናንተም ዝቅ ብላችሁ የወንድሞቻችሁን እግር ልታጥቡ ይገባችኋል። ምሳሌ ኾኛችኋለሁና፤›› በማለት የትሕትና ሥርዓት ሠርቶ እነርሱም በሥራ እንዲገልጡት አዝዞአቸዋል (ዮሐ. ፲፫፥፲፭)። በግእዝ የተጻፈ አንድ ትርጓሜ ወንጌል ‹‹እዘርእ ፍቅረ ወትሕትና ውስተ አልባቢክሙ፤ ፍቅርንና ትሕትናን በልባችሁ እዘራለሁ፤›› እንዳላቸው ይናገራል።

ሠለስቱ ምእትም በአንቀጸ መነኮሳት ‹‹ወኢትትሐከይ ኀፂበ እግረ አኃው ሶበ መጽኡ ኀቤከ እስመ በእንተ ዛቲ ትእዛዝ ይትኀሠሥዎሙ ለእለ ያጸርዕዋ ለዛቲ ግብር ወለእመ ኮኑ ኤጲስ ቆጶሳተ እስመ እግዚአብሔር ኀፀበ እግረ አርዳኢሁ ቅድመ ወአዘዞሙ ከማሁ ይግበሩ፤ ወንድሞች ወደ አንተ በመጡ ጊዜ እግራቸውን ማጠብን ቸል አትበል። ይህችን ሥራ ቸል የሚሏትን ስለዚህች ትእዛዝ ሥላሴ በፍዳ ይመረምሯቸዋልና። ኤጲስቆጶሳትም ቢኾኑ እግዚአብሔር አስቀድሞ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቦ እንዲሁ ያደርጉ ዘንድ አዝዟቸዋልና፤›› (ሃይማኖተ አበው ፳፥፳፱፤ ፩ኛ ጢሞ. ፭፥፱-፲)።

የጌታችንን ትሕትና በተናገረበት ክፍል፣ ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግ ‹‹የማይታዩ ረቂቃን መላእክቱ አደነቁ፤ ከልዑል ዙፋኑ ወርዶ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያገለግል ባዩት ጊዜ አገልጋዮቹ መላእክት ደነገጡ። ትሕትና ወዳለበት ፍቅር የአሕዛብ እግረ ልቡናን ያቀና ዘንድ ግሩም እሳት በትሕትና መገለጡን ባዩ ጊዜ ብርሃናት ደነገጡ፤›› ይላል (ሃይማኖተ አበው ፹፰፥፰)። ፊልክስዩስም ‹‹ወኅፅበተ ፋሲካ ትትሜሰል በምሥጢረ ትሕትና ፍጽምት፤ የፋሲካ ኅፅበት ፍጹም በኾነ የትሕትና ሥራ ትመሰላለች፤›› ብሏል (መጽሐፈ መነኮሳት)።

አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ‹‹… ጌታችን ወደ ስምዖን ጴጥሮስ በደረሰ ጊዜ ጴጥሮስም ‹አቤቱ እግሬን የምታጥበኝ አንተ ነህን? አለው። እርሱም መልሶ ‹እኔ እግርህን ከላጠብሁህ አንተም ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም› አለው። ይህም ማለት ‹እኔ በአገልጋይ ምሳሌ እግርህን ካላጠብሁ አንተም ከበታችህ ላሉ ራስህን ዝቅ ማድረግ አትችልም። ራስህን ዝቅ ካላደረግህም የእነርሱ አለቃ መኾን አትችልም። በሰማያት ባለው መንግሥቴስ ከእኔ ጋር እንዴት አንድ ለመኾን ትችላለህ?››› በማለት ራሱ ትሑት ኾኖ ጴጥሮስን ትሑት ይኾን ዘንድ አጥብቆ እንደ መከረው ይናገራል።

በቅዱሳት መጻሕፍት መነሻነት ዘወትር በግልጥ ሲከናወን የኖረውን፤ አሁንም ባለ ማቋረጥ እየተከናወነ የሚገኘውን፤ ለወደፊትም የሚከናወነውን ቅዱስ የኾነውን የኦርቶዶከሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ሥርዓት ወደ ጐድን በመተው ግምታዊ ልማድን እየተከተለ ‹‹የሐዋርያት ጥምቀት በኅፅበተ እግር ነው፤ እኛ የዳነው በኅፅበተ እግር ነው፤›› የሚሉ ሰዎች አሉ። ቤተ ክርስቲያናችን ስታጠምቅም፣ ቅብዐ ቅዱስ ስትቀባም ከራስ ጀምራ ነው። በመጨረሻም በራስ ላይ እፍ ብላ መንፈስ ቅዱስን በማሳደር ነው እንጂ እግርን በማጠብ አጥምቃ አታውቅም።

ይኸውም ከሐዋርያት የተገኘ፤ ከሐዋርያት ሲያያዝ የመጣ ትውፊታዊና ቅዱስ ሥርዓት ነው እንጂ አሁን የተፈጠረ አዲስ ባህል አይደለም። ስለዚህም የጸሎተ ሐሙስ ኅፅበተ እግር ጥምቀት ሳይኾን ፍጹም ትሕትናን ሠርቶ ለማሠራት ጌታችን የፈጸመው ተግባር ነው። ይህንም ያለ ጥርጥር ልንቀበለውና ልንተገብረው ይገባል። ከዚህ ሌላ የሐዋርያት ጥምቀት አንዳንዶቹ ‹‹ተከተሉኝ›› ሲላቸው ነው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ በበዓለ ኀምሳ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ነው ይላሉ። ይህ ዅሉ አባባል ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። በቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃነት ያልተደገፈ ግምታዊ አሳብ ነው እንጂ።

በዕለተ ሐሙስ በተከናወነው ኅፅበተ እግር ሐዋርያት እንደ ተጠመቁ የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው። ነገር ግን ይህ ኅፅበት መድኃኒታችን ክርስቶስ ወሰንና አቻ የሌለው ፍጹም ትሕትናውን የገለጠበት ምሥጢር እንጂ ጥምቀት እንዳልኾነ ብዙ መጻሕፍት ይስማማሉ። ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ መጻሕፍት በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ ፍጹም ትሕትናውን ለመግለጥ እንደ ኾነ በማያሻማ ኹኔታ አረጋግጠዋል።

ሐዋርያት በዚህ ጊዜ (በኅፅበተ እግር) ተጠመቁ የሚል ግን ማኅበረ ሐዋርያት ከባስልዮስ መጽሐፍ አገኘን ብለው ከጠቀሷት አንዲቷ ጥቅስ በስተቀር ሌላ አልተገኘም። ከዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባ ቁም ነገር ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ አንድ ነው፤ ሃይማኖት አንዲት ናት፤ ጥምቀትም አንዲት ናት፤›› (ኤፌ. ፬፥፭) ባለው መሠረት ሠለስቱ ምእት በጉባኤ ኒቅያ በተናገሩት የሃይማኖት ጸሎት ‹‹ኀጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን›› (ሃይማኖተ አበው ፲፯፥፲፪) ከማለታቸውም ባሻገር ጥምቀት እንዳይደገም፣ እንዳይከለስ በፍትሕ መንፈሳዊ ከልክለዋል።

ኅፅበተ እግር በቤተ ክርስቲያን

በየዓመቱ የሕማማት ሐሙስ በየአብያተ ክርስቲያናቱ፣ ዘወትር በየቀኑ በየገዳማቱና ትምህርት ቤቶች ለሚስተናገዱ እንግዶች ዅሉ ኅፅበተ እግር ይከናወናል። ኅፅበት ጥምቀት ነው ከተባለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሠለስቱ ምእትም ኅፅበተ እግሩ ባለማቋረጥ ዅልጊዜ ሲተገበር (ሲከናወን) ሰዎች ዅሉ በየጊዜው ይጠመቃሉ ማለት ነው። ይህም ሐዋርያትና ሠለስቱ ምእት ጥምቀት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲፈጸም ከወሰኑ በአንድ ምላስ ሁለት ምላስ ያሰኛል። በአንዲት ቤተ ክርስቲያን የሚጣረሱ ተቃራኒ ሥርዓቶችን ማራመድ አይቻልምና። ከዚሁ ዅሉ ጋር ደግሞ የእግር መታጠብ ጥምቀት ከኾነ ጌታችን እግራቸውን አጥቦ ‹‹እንዲህ አድርጉ›› ብሎ አዞናልና አዲስ ተጠማቂዎችን አብሶም ሕፃናትን መላ አካላቸውን እያጠመቅን ለምን በቅዝቃዜ እናሰቃያቸዋለን? እግራቸውን ብቻ አጥበን ‹‹ተጠምቃችኋል›› እያልን አናሰናብታቸውም? እስኪ በማስተዋል እንመርምረው።

መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያከናወናቸው አምላካውያት ተአምራት እንዳይገለጡ ‹‹ይህን ለማንም እንዳትናገሩ፤›› እያለ አጥብቆ ይከለክል ነበር (ማቴ. ፰፥፬፤ ፱፥፴፤ ፲፮፥፳፤ ፲፯፥፲፱)። ይኸውም ገደቡ ካሣ እስከሚፈጸም እስከ ትንሣኤ ድረስ ኾኖ ከዚያ በኋላ ግን ተአምራቱ መነገር እንዳለበት ‹‹ወልደ እጓለ እመ ሕያው ክርስቶስ ከሙታን እስኪነሣ›› ብሎ ግልጽ አድርጎታል (ማቴ. ፲፯፥፲፱)። ይህንም ‹‹መከራን ከፊት አስቀምጦ፣ ደስታን፣ ክብርን መናገር ስለሚገባ ነው›› ብለው ሊቃውንቱ አትተውታል።

በዚህ አንጻር ጌታችን እስከ መስቀል ሞት ድረስ ከፊቱ ከባድ መከራ ተደግሶለት እያለ ‹‹በኅፅበተ እግር ሐዋርያትን አጠመቀ፤ ልጅነትን ሰጠ›› ማለት አያስሔድም። ምክንያቱም አንድ መንግሥት ሕገ መንግሥቱን የሚያውጀው፤ ሹመት፣ ሽልማትን መስጠት የሚጀምረው ጠላቱን ድል አድርጎ መንግሥቱን ካደላደለ በኋላ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዓለሙን ያዳነውና ልጅነትን የሰጠው ዲያብሎስን በመስቀል ድል ከነሣው በኋላ ነው እንጂ በኅፅበተ እግር አይደለም።

ከኅፅበተ እግር በኋላ ሊይዙት ወደ እርሱ የመጡትን የካህናት አለቆችን፣ የቤተ መቅደስ ሹሞችንና ሽማግሌዎችን ጌታችን እንዲህ ብሏቸዋል፤ ‹‹ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን? ዘወትር ከእናንተ ጋር በቤተ መቅደስስኖር እጃችሁን እንኳ አልዘረጋችሁብኝም፤ ነገር ግን ጊዜያችሁ ይህ ነው። የጨለማው አበጋዝም ሥልጣኑ ይህ ነው፤›› (ሉቃ. ፳፪፥፶፪-፶፫)። ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ካጠበበት እና በአትክልት ቦታ ከጸለየበት ከሐሙስ ማታ እስከ ዓርብ እኩለ ቀን ድረስ ለመግለጽ እጅግ የሚከብድና የሚያሰቅቅ ሥቃይና መከራን በፈቃዱ ተቀብሏል።

ከዚህ አሰቃቂ መከራና ሞት በፊት ቅዱሳን ሐዋርያት ተጠመቁ፤ ልጅነትን አገኙ ማለት ከጋብቻ በፊት ልጅ መውለድ እንደ ማለት ከመኾኑም በላይ የዓለም ቤዛ የኾነውን የጌታችንን ሞት ከንቱ ዋጋ አልባ ማድረግ ነው። እንዴት ቢባል በክርስቶስ ክርስቲያን የተባለ በሙሉ ከሐዋርያት በተገኘ ልጅነት ነው፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በፊት በተከናወነ ኅፅበተ እግር ተጠመቁ ከተባለ ሞቱ ምንም ሥራ አልሠራም ማለት ነውና። ወገኔ ሆይ! ከዚህ በላይ እንደ ተገለጠው የዳንኸውና ልጅነትን ያገኘኸው በክርስቶስ ሞትና ደም እንጂ በእግር መታጠብ እንዳልኾነ ልታስተውል ይገባል።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰሙነ ሕማማት – ረቡዕ ፤ የይሁዳ ክህደት፥ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 28, 2021

ለምን የምክር ቀን ተባለ?

ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ [ማቴ. ፳፮፥፩፡፲፬ ፣ ማር. ፲፬፥፩፡፪ ቁ ፲.፲፩፣ ሉቃ. ፳፪፥ ፩፡፮]

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል

ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ “ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ” ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ነው ረቡዕ የመዓዛ ቀን የተባለው፡፡

የእንባ ቀንም ይባላል

ይህም ይህቸው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ [ማቴ.፳፮፥፮፡፲፫ ፣ ማር.፲፬፥፫፡፱፣ ዮሐ.፲፪፥፩፡፰] ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው። ምህሩንና ጌታውን ክዶ፣ ስሞ ለግርፋት እና ለመስቀል ሞት ተስማማ። ይህንን የጌታን ሕማማት፣ ስቅላት፣ ሞትና ትንሣኤ በምናስብበት በአሁኑ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ለሕማም፣ ለስቅላት እና ለሞት አሳልፎ ተስጥቷል። ይሁዳ ለ፴/30 ዲናር ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው፤ ከዚያም ዲናሩን መልሶ እራሱን አጠፋ። የዘመናችን ሰቃልያን የሆኑት ኦሮማራዎቹ የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮች ደግሞ “አክሱም ጽዮን ለብዙ ሺህ ዓመታት ያፈራችውን እውቀት፣ ስልጣኔና ሀብት በሙሉ ለመዝረፍ፣ አሳልፎ ለመስጠትና ለማውደም ጊዜው አሁን ነው” ብለው የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ከሆኑት አህዛብ፣ መናፍቃንና ግብረ-ሰዶማውያን ጋር ተባበሩ። በዚህም በዚያም ትልቅ ክህደት እና ስቅለት። በተለይ ተዋሕዶ ክርስትናን የተቀብሉትና ማሕተብ ያጠለቁት አማራ ወገኖች ክህደት ታሪክ የማይረሳው ነው፤ ብዙ ዋጋም የሚያስከፍላቸውና ከሌሎቹ ሁሉ የከፋው ክህደት ነው። ከይሁዳ ይልቅ የጴጥሮስ ዓይነት ክህደት ያድርግላቸው።

የአስቆሮቱ ይሁዳ ክህደት + የቃኤል ቅናት = ☠️

አወቁትም አላወቁትም፤ ዛሬ በአማራዎችና ኦሮሞዎች ህብረት በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለው ጂሃዳዊ የጭፍጨፋ ዘመቻ የመጨረሻው ግብ፤ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ትግራዋያንን ከአኩም ጽዮን አጽድቶ የሕይወት ዛፍ እና ጽላተ ሙሴ የሚገኙበትን ቅድስት ምድር ለተለከፉት ባዕዳውያኑ ውሾች ማስረከብ ነው። አዎ! ኢትዮጵያን/አክሱም ጽዮንን ለባዕዳውያኑ ሉሲፈራውያን ለማስረከብ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነት ከፈቱ። እስኪ እናስበው! ዋው!

በሰባዎቹ ዓመታት ሉሲፈራውያኑ ድርቅና ረሃብ ፈጥረው በዚህ አካባቢ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሃገራት፤ በተለይ ብሪታኒያ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ ሰራዊቶቻቸውን በእርዳታ ስም አስፍረው እንደነበር እናስታውስ። ከዚያ በሰማኒያዎቹ እና በባድሜው ጦርነት የተባበሩት መንግስታት “ሰላም አስከባሪዎች” እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ዛሬም ዓለም የተራቡ የትግራይን ሕፃናት ምስሎች በበቂ እንድታይ ከተደረገች በኋላና የተረፉትንም ትግራይ ወገኖቼንም በስደት የተቀደሰችውን ምድር እየለቀቁ እንዲወጡ (የአውሮፓን እና አሜሪካን ድንበሮች ይከፍቱላቸዋል፤ ከጥቂት ከፍተኛ ቦታ ላይ ከሚገኙት የዓለማችን ቦታዎች በቀር አውሮፓና አሜሪካ ሌሎችም አኅጉራት ይጠፋሉ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል) ከተደረጉ በኋላ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሠራዊቶች በትግራይ ይሰፍራሉ።

ገና ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት “ኔቶ በአፍጋኒስታን የሚገኘው ለኢትዮጵያ ለመለማመድ ነው፤ ተመሳሳይ የመልከዓ ምድር አቀማመጥ ስላላቸው…” በማለጥ ጽፌ ነበር። ምዕራባውያኑ እዚያ መስፈር ከጀመሩ በኋላ ቀስ በቀስ ዜጎቻቸውን ማስገባት ይጀምሩና በመጨረሻም “ኢትዮጵያውያኑም ተዋሕዶ ክርስቲያኖቹም እኛ ነን” በማለት እያታለሉና ደማቸውን እያፈሰሱ ለብዙ ሺህ ዓመታት ጠብቀውት የነበረውን ብኩርናቸውን በምስር ወጥ እንዲሸጡ ብሎም የመንፈስ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን እየተነጠቁ “ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን” ቀስበቀስ እንዲከዱ ይደረጓቸውን “የቀድሞ ኢትዮጵያውያን” “አናስገባም!” ብለው ከኢትዮጵያ ድንብር ይመልሷቸዋል። ይህ ትንቢት ሳይሆን የሉሲፈራውያኑ ግልጽ የሆነ ተልዕኮ ነው። እግዚአብሔር ይህን ተልዕኳቸውን እንደሚያጨናግፈው አልጠራጠረም፤ ነገር ግን በኢትዮጵያውያኑ ደንቆሮነት፣ ስንፍና እና እንደ ግራኝ ያሉትን የውስጥ ጠላታቸውን በሰዓቱ ለማስወገድ ባለመድፈራቸው ብሎም አክሱም ጽዮንን ለመከላከል ባለመሻታቸው ብዙ መስዋዕት ይከፍሉ ዘንድ ግድ ይሆናል። በተለይ ከሃዲዎቹ ኦሮማራዎች!

የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የፈረንሳይ ጄኔራሎች “አገሪቱን ከእስልምና ለማዳን አንድ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል” ይላሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 27, 2021

🔥 ተቀጣጣዩ ደብዳቤ እንዲህ ይላል፤ “ፈረንሳይ አደጋ ላይ ናት ፡፡ በርካታ የሟቾች ቁጥር ሊያመጡ የሚችሉ አደጋዎች ከፊቷ ተደቅነው እያሸበሯት ነው፡፡ በጡረታ ጊዜም ቢሆን እኛ የፈረንሳይ ወታደር ሆነን እንቆያለን እናም አሁን ባለው ሁኔታ በጎ ለሆነ የሀገራችን ዕጣ ፈንታ ግድየለሾች መሆን አንችልም፡፡”

እባቡ ግራኝ ከአክሱም እና ላሊበላ ጂሃዳዊ ጉብኝቱ በኋላ በኢትዮጵያ የዋቄዮ-አላህ መፈንቀለ ሥርዓት እያደረገ ሲሆን፤ በፈርንሳይ ደግሞ የመፈንቅለ መንግስት ጥሪ በግራኝ ግብረ-ሰዶማዊ ሞግዚት በኢማኑኤል ማክሮን ላይ እንዲካሄድ ጥሪ ቀርቧል። ዋው! መቅደም የነበረበት ግን አንድ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ጀግና ጄነራል በጨፍጫፊው የግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ኦሮሞ አገዛዝ ላይ መፈንቅለ መንግስት ማካሄዱ ነው! እንደ ፈረንሳይ ጄነራሎቹ የመሰለ አገር-ወዳድ ጥሪ ለማድረግ የሚችልና ኢትዮጵያን ያድን ዘንድ ላለፉት ሦስት ዓመታት በባትሪ ሲፈለግ የነበረው ኢትዮጵያዊ ጄነራል የት አለ?

ፕሬዝዳንት ማክሮን በእስልምና እምነት ተከታዮች የተፈጠረውን የህብረተሰብን “መበታተን” ማስቆም ካልቻለ ሃያ ጡረታ የወጡ የፈረንሣይ ጄኔራሎች በአገሪቱ ውስጥ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ይደረግ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል። ይህም ጥሪ ቀጣዩ ምርጫ ከመጀመሩ ከዓመት በፊት የፖለቲካ ሁከት አስነስቷል።

በቀጣዩ ዓመት ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታትሞ በወጣው ግልጽ ደብዳቤ ኢማኑኤል ማክሮን በእስልምና እምነት ተከታዮች እጅ ‘የአገሪቱን መበታተን’ ማስቆም ካልቻለ በወታደራዊ ቁጥጥር ሥር እንዲደረግ ሃያ ጡረታ የወጡ የፈረንሣይ ጄኔራሎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በቀኝ ክንፍ የዜና መጽሔት በቫለርስ አክቱዌለስ የታተመው ክፍት ደብዳቤ በፈረንሣይ ‘የእርስ በእርስ ጦርነትን’ ለማስቆም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ይላል፡፡

ደብዳቤው በማክሮን መንግስት የተወገዘ ሲሆን ከ ፷/60 ዓመታት በፊት በፕሬዚዳንት ዴ ጎል ላይ ጄኔራሎች ከከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ጋር በማነፃፀር አውግዘውታል፡፡

የመሪው ፈራሚ የ ፹/ 80 ዓመቱ ክርስቲያን ፒኩማል ሲሆን እ.ኤ.አ. በ 2016 በፀረ-ኢስላም ሰልፍ ላይ ሲሳተፍ ከታሰረ በኋላ የጡረታ መኮንን መብቱን ከማጣቱ በፊት የታዋቂው የፈረንሳይ የውጭ ሌጌዎን አዛዥ ነበር፡፡

የተፃፈው በቀድሞው መኮንን ዣን-ፒየር ፋብሬናናዳክ ሲሆን በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ባሉ ፩ሺህ/1000 ሌሎች ሰዎች ተፈርሟል።

🔥 French Military Generals Say a MILITARY COUP MAY BE NECESSARY to Save The Country From Islam

Twenty retired French generals have called for military rule if Emmanuel Macron fails to halt the ‘disintegration’ of the country ‘at the hands of Islamists’, in an open letter published ahead of next year’s presidential election.

The open letter, published in Valeurs Actuelles, a right-wing news magazine, claims a military coup might be necessary to stop a ‘civil war’ in France.

The letter has been condemned by Macron’s government, who compared it to the failed coup by generals against President de Gaulle 60 years ago.

The lead signatory was Christian Piquemal, 80, who commanded the Foreign Legion before losing his privileges as a retired officer after being arrested while taking part in an anti-Islam demonstration in 2016.

It was written by Jean-Pierre Fabre-Bernadac, a former officer, and signed by 1000 others who were in lower ranks.

The incendiary letter reads: ‘France is in danger. Several mortal perils threaten her. Even in retirement, we remain soldiers of France and cannot in the present circumstances remain indifferent to the fate of our beautiful country.’

👉 የተመረጡ አስተያየቶች/ Selected Comments:

☆ ሌሎች ፹/80 ጡረታ የወጡ መኮንኖች እንዲሁም በ ፳/20 ጄኔራሎች ተፈርሟል ፡፡ ይህ ትንሽ ነገር አይደለም፡፡ አንድ መንግስት ችላ ሊለው የሚፈልገው ነገር አይደለም።

☆ ይህ በእውነቱ በጣም ከባድ ነው። እነዚህን ስጋቶች በትክክል ለመናገር እና በዚህ መልክ እርምጃ ለመውሰድ ማስፈራራት በጣም ያልተለመደ ነው፡፡ ሰዎች በጣም ሊያሳስባቸው ይገባል፡፡

☆ በአውሮፓ ውስጥ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት፡፡ ለረጅም ጊዜ ያለተደረገ ተግባር፡፡

☆ አደገኛ ጊዜያት

☆ ወደዚህ እንደሚመጣ ሁልጊዜ የሚጠበቅ ነው፡፡ ደካማ ፖለቲከኞች የማይነገር ሰቆቃ አስከትለዋል፡፡

☆ በአብዮት ሂደት በጣም ረዥም የጥቃት ታሪክ ያላትን ፈረንሳይ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህንን ስጋት በጭራሽ አላጣጥለውም፡፡ መቼም!

☆ ፈረንሳይ ኩሩ ሀገር ናት ዜጎቿ ማክሮን እና ፓርቲያቸው በማይረባ ፖሊሲዎቻቸው አገሪቱን ሲያጠፉ ለመመልከት መጥፋት አለባቸው ፣ በእውነቱ ይህ ሊከሰት እንደሚችል ማየት ችያለሁ አንድ አብዮት ነበራቸው ታዲያ ለምን ሌላ አብዮት አይኖራቸውም፡፡

☆ “አስቂኙን ማክሮን”ን ብቻ አስወግዶ ማሪ ሌፔንን ፕሬዚደንት ማድረግ ነው

☆ ዓለማችን እጅግ በጣም ግዙፍ የጊዜ ፈንጂ እየሆነች ነው ፣ ምናልባት ወደ አርማጌዶን መንገዳችንን ጀምረን ይሆናል።

☆ “Signed by 80 other retired officers, as well as the 20 generals.” That is no small thing. It is not something a government would want to ignore..

☆ This is actually quite serious. To actually voice these concerns and threaten action is highly unusual. People must be very concerned.

☆ A military coup in Europe. Not had one of those for a while.

☆ Dangerous times

☆ It was always destined to come to this. Weak politicians have caused untold misery.

☆ Given France’s very long history of violence in revolution, I would never discount this threat. Not ever.

☆ France is a proud nation its citizens must be devastated to stand by and watch Macron and his party ruin the country with their useless policies,I can actually see this happening they have had one revolution why not another vive la France

☆ Just get rid of the CLOWN MACRON and put Le Penn in charge

☆ Our world is becoming a huge ticking time bomb, we may already have started our road to Armageddon.

Source/ ምንጭ

______________________________________

Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሕማማተ እግዚእ †ዕለተ ሰሉስ/ማክሰኞ | ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 27, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

✞✞✞ ሰሙነ ሕማማት ዕለተ ማክሰኞ (ዘሰሉስ)✞✞✞

የጥያቄና የትምህርት ቀን❖

በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማድረጉን ተያይዞ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ሰኞ ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ያላገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፤ በማስከተል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ [ማቴ.፳፩፥፳፫፡፳፭ ፤ ማር.፲፩፥፳፯ ፣ ሉቃ.፳፥፩፡፰]፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራትና የኃይል ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀናቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡

ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነው፡፡ በአንድ አገር የንግድ ቦታን የሚያጸድቅ መንግሥት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡት ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አልመለሰም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሷል፡፡ “በመባሕተ መኑ ትገብር ዘንተ፤ በማን ሥልጣን ነው ይህን የምታደርገው?” ነበር ያሉት፡፡ በራሴ ሥልጣን ቢላቸው ፀረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው፡፡

ጌታችን እኩይ የሆነውን የፈሪሳውያንን አሳብ በመረዳት “የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር ሲል” ጠይቋቸዋል፡፡ ከሰማይ ያልነው እንደ ሆነ ለምን አላመናችሁበትም ይለናል÷ ከሰው ያልነው ከሆነ ሕዝቡ ይጣላናል፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ከዚህ የተነሣ ያቀረቡት የፈተና ጥያቄ ግቡን ሳይመታ ከሽፎባቸዋል፡፡ [ማቴ.፳፩፥፳፭]፤ [ማር.፲፩፥፳፯፡፴ ፤ ሉቃ.፳፥፩፡፰]፡፡

ዛሬም ቢሆን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊሆን እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን ዐሳባችን ከዓለም ዘንድ የተገላቢጦሽ ነገር እንደ ሚጠብቀን “ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው” የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ ይህ በመሆኑ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልን ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡

በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

👉መድኅንኤል 👉ሕይውታኤል 👉አውካኤል 👉ተርቡታኤል 👉ግኤል 👉ዝኤል 👉ቡኤል

የቅዱስ ገብርኤል ድርሳን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከልዩ ድንጋፄና ፍርሃት እድን ዘንድ ይህን የቅዱስ ገብርኤልን ድርሳን እንዲህ እያልኩ እጸልያለሁ፤ መድኅንኤልሕያውታኤልአውካኤልተርቡታኤልግኤልዝኤልቡኤል ፤ ይህን አስማተ መለኮት እግዚአብሔር ለቅዱስ ገብርኤል የሰጠው መልአኩ ከዲያብሎስ ጋር ክርክር በጀመረ ጊዜ ድል እንዲነሣበት፤ እንዲሁም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለማብሠር በተላከ ጊዜ ከቃሉ ግርማ የተነሣ እንዳትደነግጥና እንዳትፈራ መጽንዔ ኃይል እንዲሆናት ነው።

አቤቱ ለእኔ ለአገልጋይህም እንደዚሁ ኃይልና ጽንዕ ሰጥተህ ከመዓልትና ከሌሊት ድንጋፄ አድነኝ፤ አሜን።

ከላይ ከሰማይ ወደ ድንግል የተላክህ ገብርኤል ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ደስታን አብሣሪ መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ፅንሰ ቃልን አስተምረህ የምታሳምን መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ሰማያዊ ነደ እሳት ዖፈ ርግብ ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ፍጹም ደስታን ተናጋሪ መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ከእደ ሞት የምታድን መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። የአንተን አማልላጅነት በመዓልትም በሌሊትም ተስፋ ስለምናደርግ ጥበቃህ አይለየን። በነፍስም በሥጋም ታደገን። የእግዚአብሔር ልዩ ባለሟል ነህና፤ ለዘላለሙ አሜን።

አቡነ ዘመሰማያት።

__________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Sec. Blinken Presses PM Abiy for Immediate, Full & Verifiable Withdrawal of Eritrean Troops From Tigray

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 26, 2021

Blinken presses Ethiopia’s Abiy on withdrawal of Eritreans from Tigray — End Hostilities Immediately

U.S. Secretary of State Antony Blinken on Monday pressed Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed for troops from Eritrea involved in the Tigray conflict to be withdrawn “immediately, in full, and in a verifiable manner,” according to a statement.

Blinken said Eritrean forces and Amhara regional forces in the Tigray region are contributing to the growing humanitarian disaster and committing human rights abuses, according to a statement by U.S. State Department spokesman Ned Price describing a phone call with Abiy.

“The Secretary also stressed the need for all parties to the conflict to end hostilities immediately,” Price said.

Washington said last week that it had seen no evidence of a troop withdrawal promised by both Ethiopia and Eritrea.

Blinken also expressed concern in the call about the humanitarian and human rights crisis in Ethiopia, including the growing risk of famine in the Tigray region, Price said.

Source

_________________________________

Posted in Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሆሣዕና ፪ሺ፲፫/ 2013 ዓ.ም | ሁለት ጨረቃዎች? | Two Moons?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 26, 2021

በትናንትናው ዕለት ቴዎድሮስ “ርዕዮት” ፀጋዬን እና አቶ ታምራት ላይኔን እያዳማጥኳቸው (ስለ ትግራይ እነደሚጠበቅባቸው ብዙ አልተናገሩም፤ በተለይ የአማራ ፋሺስት ፋኖ ሚሊሺያ በምዕራብ ትግራይ ስለሚፈጽመው ወንጀል: ይሉኝታ/PC?) የምሽት ሰማዩ ላይ የታየኝ ይህ አስደናቂ ክስተት ነበር። አምና ልክ በዚሁ በሆሣዕና ዕለት እመቤታችንን እና ልጇን አማላካችንን ጨረቋዋ ላይ “ታዩኝ” በማለት ቪዲዮ አንስቼ የዲያብሎስ ጭፍሮች ባዘጉብኝ ዩቲውብ ቻኔሌ ላይ ለቅቄው ብዙ አድናቂዎችን አግኝቶ እንደ ነበር አስታውሳለሁ። ዘንድሮ ደግሞ ያው!

በነገራችን ላይ ዘንድሮም ልክ በዚሁ የሑዳዴው ጾም ወቅት እነ ግራኝ + የተባበሩት መንግስታት ወኪሎቹ ይህኛውን ቻነሌንም ለማዘጋት ሞክረው ነበር፤ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።

_____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰሙነ ሕማማት ሰኑይ | መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 26, 2021

✞✞✞ የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ስያሜዎች ✞✞✞

ሰኞ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ፤ አንጽሖተ ቤተ መቅዳስ የተፈጸመበት ሰኞ::

ማግሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን::

ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን::

ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ::

ዐርብ፤ የስቅለት ዐርብ::

ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ

__________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: