ተዓምር በደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም | አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለማቱ መልአክ ዙሪያ ያፈነጥቃሉ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 4, 2020
በጣም ድንቅ ነው! ቪዲዮው ወደ መጨረሻ ላይ ይታያል። በያሬዳዊ ወረብ ወቅት ክቡሩ ባለሶስት ቀለማችን በበሩ መሃከል ያፈነጥቃል፤ በመልአክ የተመሰለውን ኃይለኛ ነጭ ብርሃንም ክንፎች ሠርቶለታል (መስቀል)፤ በ “ቀራንዮ”። ልብ ካልን፡ ቀለማቱ ከበስተ ውስጥ ነው የሚታዩት፡ ቤተመቅደሱ ውስጥም ቀለማቱም በሩ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ አልተቀቡም፤ በወቅቱም በዓይኔ በፍጹም አይታየኝም ነበር፡ ቪዲዮውን ሳዘጋጅ ነበር ልብ ያልኩት። እስከመጨረሻው መቅረጽ ሳልችል መቅረቴ ቢያሳዝነኝም፡ (ምክኒያቱም ዲያብሎስ መጥቶ አቋረጠኝ፡ ከለከለኝ)፡ ሆኖም ግን፡ ይህን አስገራሚ ክስተት ለመታዘብ በመብቃቴ መድኃኔ ዓለም ይመስገን!
ልክ እንደ ልደታ፡ ኮልፌ ቀራንዮም በጥቃት ላይ ይገኛል ፤ ዘንዶዎቹ እነ አብዮት አህመድ ነዋሪውን ያሰቃዩታል። ያው በዛሬው የመድኃኔ ዓለም ዕለት በኮልፌ ቀራንዮ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የእርዳታ ምግብ ሲያከፋፍሉ የነበሩት እስክንድር ነጋ እና ሌሎች 15 የባልደራስ አመራሮች ታሰረዋል። አዎ! በአውሬው ሰዓት አቆጣጥር ምግብ ማከፋፈል ያለበት እርሱ ብቻ ነው፤ ምክኒያቱም ዓላማው ሕዝቡን በዘረመል ምህንድስና የተመረቱትን ምግቦች ብቻ በማከፋፈል መመረዝና ማኮላሸት ነውና።
ክመንግስት ምግብ፣ ዳቦ፣ ዘይት፣ ወተት፣ ስኳር፣ መጠጥ ወዘተ ተቆጠቡ ብያለሁ!
እስክንድርን እና ባላደራዎቹን መድኃኔ ዓለም ይርዳቸው!
በዘንዶው ከሚለቀቅ ጎርፍ የሚተርፍ ብፁዕ ነው!
Leave a Reply