Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for June 4th, 2020

በአሜሪካዋ ሚልዋኪ አንድ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት በአመጸኞች ተጎድቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 4, 2020

አለም የኢትዮጵያ መንደር” የተስኘውና በአሜሪካዋ ሚልዋኪ መሃል ከተማ / ዊስኮንሲን ግዛት ቅዳሜና እሁድ በተካሄደው የተቃውሞ አመጽ ወቅት ሰዎች ምግብ ቤቱ ገብተው በከፊል አውድመውታል ፡፡ ሁለት መስኮቶች ተሰባብረዋል።

ከአስር ዓመት በፊት የተከፈተው ይህ ምግብ ቤት በባለትዳሮቹ ሰለሞን በቀለ እና ሙሉ ሃብተ ሥልሴ የሚተዳደር ነው። ውድመቱ ባስከተለው ወጪ የተጨነቁት ሁለቱ ወገኖቻችን ከአካባቢው ነዋሪዎች በተካሄደ የመዋጮ ማራቶን እስከ 12 ሺህ ዶላር በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊሰበስብላቸው ተችሏል።

ተመስገን! አይዟችሁ ወገኖቼ!

_________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

ተዓምር በደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም | አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለማቱ መልአክ ዙሪያ ያፈነጥቃሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 4, 2020

በጣም ድንቅ ነው! ቪዲዮው ወደ መጨረሻ ላይ ይታያል። በያሬዳዊ ወረብ ወቅት ክቡሩ ባለሶስት ቀለማችን በበሩ መሃከል ያፈነጥቃል፤ በመልአክ የተመሰለውን ኃይለኛ ነጭ ብርሃንም ክንፎች ሠርቶለታል (መስቀል)፤ በ “ቀራንዮ”። ልብ ካልን፡ ቀለማቱ ከበስተ ውስጥ ነው የሚታዩት፡ ቤተመቅደሱ ውስጥም ቀለማቱም በሩ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ አልተቀቡም፤ በወቅቱም በዓይኔ በፍጹም አይታየኝም ነበር፡ ቪዲዮውን ሳዘጋጅ ነበር ልብ ያልኩት። እስከመጨረሻው መቅረጽ ሳልችል መቅረቴ ቢያሳዝነኝም፡ (ምክኒያቱም ዲያብሎስ መጥቶ አቋረጠኝ፡ ከለከለኝ)፡ ሆኖም ግን፡ ይህን አስገራሚ ክስተት ለመታዘብ በመብቃቴ መድኃኔ ዓለም ይመስገን!

ልክ እንደ ልደታ፡ ኮልፌ ቀራንዮም በጥቃት ላይ ይገኛል ፤ ዘንዶዎቹ እነ አብዮት አህመድ ነዋሪውን ያሰቃዩታል። ያው በዛሬው የመድኃኔ ዓለም ዕለት በኮልፌ ቀራንዮ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የእርዳታ ምግብ ሲያከፋፍሉ የነበሩት እስክንድር ነጋ እና ሌሎች 15 የባልደራስ አመራሮች ታሰረዋል። አዎ! በአውሬው ሰዓት አቆጣጥር ምግብ ማከፋፈል ያለበት እርሱ ብቻ ነው፤ ምክኒያቱም ዓላማው ሕዝቡን በዘረመል ምህንድስና የተመረቱትን ምግቦች ብቻ በማከፋፈል መመረዝና ማኮላሸት ነውና።

ክመንግስት ምግብ፣ ዳቦ፣ ዘይት፣ ወተት፣ ስኳር፣ መጠጥ ወዘተ ተቆጠቡ ብያለሁ!

እስክንድርን እና ባላደራዎቹን መድኃኔ ዓለም ይርዳቸው!

በዘንዶው ከሚለቀቅ ጎርፍ የሚተርፍ ብፁዕ ነው!

________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ደመራ በመስቀል አደባባይ ላይከበር ነውን? ወይስ ተቃውሞ መቀስቀሻ ሴራ ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 4, 2020

ያው ያልነው መጣ፦

👉 የመስቀሉ ጠላቶች መጀመሪያ በሬውን፣ ቀጥሎ የአቴቴ ኤሬቻን፣ ከዚያ ቡልዶዘሩን

ደመራ

ያን የደመራ ምስኪን በሬ እናስታውሳለን?

“….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸውየሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸውከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይብለህ ተርትባቸውእያለች አሽካካችብን እኮ የሰዶሟ ፒኮክ።

👉 አሁን የዘንዶዋን አቴቴን እንቁላል በመስቀል አደባባይ ሊቀብሩት ነው

እንግዲህ ያው፤ ይህን ያህል ነው ወራሪዎቹ የዲያብሎስ ልጆች የናቁንና የደፈሩን! ቀስበቀስአንድ ባንድነጥብ በነጥብ

ክረምቱ በመቃረቡና የቁፋሮ ሥራውንም በሰበባ ሰበቡ በማጓታት የሚቀጥለው ታላቅ ክርስቲያናዊ የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል በአደባባዩ እንዳይከበር ያደርጋሉ ማለት ነው። ለስቅለት ዕለትና ለትንሣኤ ክብረ በዓል ቤተ ክርስቲያንን ዘጉ፣ አሁን ክቡር መስቀሉ እንዳይከበር ወይ በወረርሽኝ፣ ወይ ደግሞ በዚህ ቁፋሮ መሰናክል ይፈጥራሉ ፥ ቀጥሎ ያለው ትልቁና ለሕዝበ ክርስቲያኑ በጣም አስፈላጊ የሆነው ክብረ በዓል ጥምቀት ነው ፤ አዎ! ለሱም ጃንሜዳን ለአህዛብ ነጋዴዎች በመስጠት ብሎም የሆቴልና ሱቅ ግንባታዎችን በማቀድ ላይ ናቸው።

ለዚህ ሁሉ ዲያብሎሳዊ ድፍረትና ንቀት ተጠያቂዎቹ ቤተ ክህነት፣ የክርስቲያኖችን ወኔ ያስነጠቁት ሰባኪያን እና “አባቶች” እንዲሁም እግዚአብሔርን በውስጣቸው ይዘው ወለም ዘለም በማለት ሁሌ ከላይ ትዕዛዝ የሚጠብቁት የተዋሕዶ ልጆች ናቸው። በአምላክህ ላይ፣ በሃገርህ ላይ፣ በአባቶችና እናቶችህ እንዲሁም ልጆችህ ላይ የተነሱትን አማሊቃውያን ጠላቶችህን አንድ ባንድ የመድፋት 100% መብት እያለህ እጅህን አጣጥፈህ ቁጭ የምትለው ለምንድን ነው?

____________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ኃይለኛ ህልም | አዲስ አበባ እንደ ሶርያዋ አሌፖ የመሆን ዕድል አላት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 4, 2020


ባለፈው ግንቦት ፳፩፡ በማርያም ዕለት ያየሁት የማስጠንቀቂያ ህልሙ በተለይ ያተኮረው በአዲስ አበባ ላይ ነበር።

አዲስ አበባ የሆነ ቦታ ላይ ቆሜ በዙሪያየ ያሉ ሰዎች ጥያቄዎች እየጠየቁኝ ንግግር የመሰለ ነገር እየጮህኩ አሰማለሁ። በዋናነት የተናገርኩትም ይህን ነበር፦

ውድ አዲስ አበቤዎች ይህ መንግስት የኢትዮጵያ ጠላት ነው፤ በጣም ሤረኛ ነው፤ ዛሬ አይታችሁት ለማታውቁት ጥፋት፣ ግፍና ሰቆቃ እያዘጋጃችሁ ነው፤ ከታች በኮሮና ሊጨርሳችሁ ፈቃደኛ ነው፤ ከላይ ደግሞ ቦንቡን ሊያወርድባችሁ ወስኗል። እነዚህን ሁሉ ህንጻዎችና ፎቆች ታያላችሁ? አዎ! ብዙ የተከማቹ ፎቆች ብቅ ብቅ ብለው እንዲታዩ ተደርገው የሚሠሩት በቦምብ ድብደባው ወቅት አፍርሰናል፣ አጥፍተናል ብለው ለመርካትና ምስክርነት ለመስጠት ነው፤ ሁሉን ነገር በውጩ ሃገር ቤታቸው ቁጭ ብለው የሚያዩት ሉሲፈራውያኑ ቀጣሪዎቻቸው ይህን ማድረግ እንዳለባቸው አዘዋቸዋል። የሚፈራርስ ነገር ማየት ይወዳሉ! ኢትዮጵያ መፈራረሷን በዚህ መልክ ለዓለም ማሳየት አለባቸው፤ አዎ ልክ እንደ ሶርያ፣ ኢራቅና ሊቢያ። እቅዳቸው ይህ ነው።

# ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዎቹ ደግሞ በዋናነት እኛው ክርስቲያኖቹ ነን፤ ምክኒያቱም

👉 . ይህን የአህዛብ መንግስት እልል ብለንና ካባ አልብሰን ሥልጣን ላይ ስላወጣነው

👉 . ምዕመናን እና ካህናት ሲታረዱ፣ እንዲሁም ዓብያተክርስቲያናት ሲቃጠሉ ሰልፍ ባለመውጣችን

👉 . ተማሪ እህቶቻችን ታግተው ሲሰወሩ፣ አረጋውያን እና አራስ እናቶች ከቤቶቻቸው ሲፈናቀሉ ዝምታን በመምረጣችን፤ የሰላም ሽልማት እንደሆነ እንኳን በሰማይ በምድርም እንደማይሰጡን እያየን ነው

👉 . በሰሞነ ፋሲካ ወደ ቤተ ክርስቲያን ባለመሄዳችን ፤ በስቅለት ዕለት የታየችው የማርያም መቀነት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዱና ለአማልካችሁ ጸልዩ እኔ አለሁ፡ እጠብቃችኋለሁ” ሊለን ነበር

👉 ፭ኛ. ስልጣን ላይ ያወጣችሁት መስተዳደር በቅድስት ኢትዮጵያ ምድር የአውሬው ማምለኪያ የሚሆን መስጊድ ለማሰራት በመወሰኑ፤ ሊሰራ የታቀደበት ቦታ (ከ ለቄራ እስከ ለጋሃርና ፍልውሃ ድረስ፡ ሸረተን የሚገኝበትን ቦታ ጨምሮ ) ፍል ውሃ ፀበላትና ሌሎችም ታሪካዊና ድብቅ የቤተ ክርስቲያን ቅርሶች የሚገኙበት ቦታ ነው

👉 ፮ኛ. ዓብያተ ክርስቲያናቱ ቀስ በቀስ ወድ ንግድ እና ጨረታ ቦታነት እየተለወጡ በመምጣታቸው። በተለይ ሱቆችንና ምግብ ቤቶችን ለተዋሕዷውያን ብቻ ማከራየት ሲገባቸው ለአህዛብና መናፍቅ ሳይቀር አሳልፈው በመስጠታቸው።

የሚሉትን ነበር በህልሜ የተናገርኩት። በውኔ ከማስበው ጋር ተመሳሳይ ነው። እነደ ፀሎት ይቁጠርልን!

____________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: