Archive for May, 2020
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 31, 2020
ከሁለት ቀናት በፊት በማርያም ዕለት ስለ አዲስ አበባ የታየኝን አስገራሚ ህልም ከማውሳቴ በፊት ይህ ልዩ የሰንበት እይታየ ነው፦
በጣም የሚገርም ነው፤ ልክ በአድዋው ታሪካዊ ድል ማግስት ነበር የኢትዮጵያ ውድቀት የጀመረው። የአደዋው ድል የአሁኑን ከሃዲ ትውልድ አፍርቷል! ረባሽ ዓረፍተ ነገር፡ አደል?!
ግን ምክኒያቱ፦ በወቅቱ ታይቶ በነበረው አስከፊ ረሃብና እስካፍንጫው በታጠውቀው በአህዛብ ጠላት ላይ ድል ያጎናጸፈውን እግዚአብሔር አምላኩን በመክዳት ለስጋዊው የአህዛብ ዓለም እውቀትና ጥበብ እጁን በመስጠቱ የቀጣዮቹን ሦስትና አራት ትውልዶች ለመፈጠር በመብቃቱ፤ በዚህም ሃገር አጥፊ ስጋዊ የዲቃሎች መንጋ ስልጣኑን እንዲቆጣጠረውና የሃገሪቱንም ውድቀት እንዲያፋጥነው ዋናውን ሚና በመጫወቱ ነበር/ነው። ልከ እንደ ምስጋና–ቢሶቹ እስራኤላውያን!
ወቅቱ አሁን ያለው አራተኛው ከሃዲ ትውልድ ተገርስሶ በቅርቡ የኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚታይበት ወቅት ነው። ነገር ግን፡ አሁንም ይህ ትውልድ ለአህዛብ ኤዶማውያን እና እስማኤላውያን ምድራዊ እውቀትና ጥበብ መገዛቱን እስካላቆመ ድረስና ይህ አሁን የሚታየው አራተኛው ዲቃላ ትውልድ ስጋዊ ማንነቱንና ምንነቱን በመካድ፣ ንሥሐ ገብቶ የቀደሙ አባቶቹን ለድል ያበቃቸውን እግዚአብሔርን እና ዘላለማዊ ሕጉን ካልተከተለ ሰቆቃው፣ ባርነቱ፣ ሰቆቃውና ውድቀቱ ይቀጥላል። ይህን የማያይ ዛሬም ስጋዊ ነው!
የፈረሰኛው ሰማእት የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤትና ምልጃ አይለየን!
_________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ቅዱስ ጊዮርጊስ, አዲስ አበባ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, የኢትዮጵያ ጠላት, ፀረ-ተዋሕዶ ዘመቻ, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 30, 2020
እህቴ፤ የእኔ እህት ተዋሕዶ በመሆኗ፣ ማህተብና መስቀል በማጥለቋ በአገሯ ባሰቃቂ መልክ ተገደለች። ወይኔ!
[ትን.ኤር.፱፥፳፩፡፳፬]
“ሕፃናቱን ከመንገድ ጕልማሶቹንም ከአደባባይ ያጠፉ ዘንድ ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ አዳራሻችንም ውስጥ ገብቶአል።የሰውም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንምም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው። ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር።“
በተዋሕዶ ጠላቶች መገደሏ ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለም… ነጥብጣቦችቹን እናገናኝ…የተዋሕዶ ተማሪዎች፣ ካህናት፣ ምዕመናን፣ ሕፃናት፣ እናቶች፣ አባቶች ብሩህ ተስፋ ያላቸው ወጣቶች ናቸው እየተገደሉ፣ እየታገቱ፣ እየተፈናቀሉና እየተሰደዱ ያሉት። አምንስቲ የተባለው ወስላታ ድርጅት ትናንትና ባወጣው መግለጫ ላይ የግራኝን መስተዳደር የኮነነ በማስመሰል ኦሮሞዎችን ከተበዳይነት ላለማውጣት ሲል ሲለሳለስ አይተነዋል፤ ምክኒያቱም የግራኝ መስተዳደር እየፈጸመው ያለው በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ወንጀል በተዋሕዶ ልጆች ላይ እንደሆነ ድርጅቱ በደንብ ያውቀዋል፣ ይፈልጉታልና ነው።
ስለ ሃይማኖት፣ ስለ እርቀ ሰላም፣ ስለነ ሰማእታት ሳህለ ማርያም እና ኃይለ ሚካኤል፣ ስለ ደምቢደሎ ተማሪዎች፣ በትንሣኤ ዕለት ናዝሬት ተመርዘው ስለተገደሉት የተዋሕዶ ሕፃናት ወዘተ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አንዲት ቃል እንኳን ትንፍሽ አላለም።
የሃይማኖት እና የናዝሬት ቤተ ክርስቲያን ህፃናት አሟሟት ተመሳሳይ ነው፤ የዋልድባ ገዳም መነኩሴ አባ ሀብተወልድም በተመሳሳይ አሰቃቂ ሁኔታ ነበር የተገደሉት። በጊዘው፤ “የዋልድባ መነኵሴ በ ሔሮድሳዊው ግራኝ አህመድ ነው ተገድለው የሚሆኑት” በማለት ጠቁሜ ነበር።
በቲም ኢሬቻ በአብይ፣ በለማ፣ በበላይና በጀዋር ዘንድ ኦሮምኛ ተናጋሪ የተዋሕዶ ልጆች ከተቀረው ኢትዮጵያ የተዋሕዶ ልጅ በይበልጥ የተጠሉ ናቸው። እንኳን “ሃይማኖት” የሚል ስም ኖሯቸው፣ እንኳን ማህተብ እና መስቀል አጥልቀው፣ እንኳን ከጥቁሩ አንበሣ ጋር ተዛምደው። ቪዲዮውም ይህን ይጠቁመናል። የተዋሕዶ ልጆችን ደም ለዲያብሎስ ለመገበር ጥቁር አንበሣ ሆስፒታል አመቺ ቦታ ነው። ሰውዬው በርግጥም ለተዋሕዶና ለአንበሣ ከፍተኛ ጥላቻ አለው።
የኔ እህት ሃይማኖት፤ እንዴት ተሰቃይታ እንደተገደለች ሳስበው በቁጣና ንዴት እንባየ ዱብዱብ ይላል።
እህት ሃይማኖትን ነፍሷን በአብርሐም በይስሐቅ በያዕቆብ እቅፍ ያኑርልን!
ኢትዮጵያን ተረካቢ አሳጥታችኋት፤ የምኒሊክ ቤተ መንግስትን በደንብ እያወቃችሁ ለእነዚህ አውሬዎች አስረክባችሁ የፈረጠጣችሁ የህዋሃት ሰዎች እግዚአብሔር ይይላችሁ!
👉 በእሳት መጠረግ ያለባቸው ገዳዮቿ፦
አብይ አህመድ ፣ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ ለማ መገርሳ ፣ ታከለ ኡማ ፣ ሽመልስ አብዲሳ ፣ ጃዋር መሀመድ ፣ በቀለ ገርባ ፣ ህዝቄል ገቢሳ ፣ ዳውድ ኢብሳ ፣ አምቦ አርጌ ፣ ፀጋዬ አራርሳ ፣ አደነች አቤቤ ፣ ሞፈሪያት ካሜል ፣ መአዛ አሸናፊ ፣ ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ ብርቱካን ሚደቅሳ ፣ ታዬ ደንደአ ፣ ሌንጮ ባቲ ፣ ሌንጮ ለታ ፣ ዳንኤል ክብረት ፣ አለማየሁ ገብረ ማርያም፣ ብርሀኑ ነጋ ፣ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ ደመቀ መኮንን ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ ፣ አንዱዓለም አንዳርጌ ፣ ታማኝ በየነ ፣ አበበ ገላው
______________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: ሃይማኖት በዻዻ, ርኩስ መንፈስ, አብይ አህመድ, አውሬው መንግስት, ኢትዮጵያ, ኦሮሚያ, ከሃዲ ትውልድ, የዲያብሎስ ሤራ, ጥቁር አንበሣ, ፀረ-ተዋሕዶ ዘመቻ, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 30, 2020
ኡራኤል መላክ ዓለምን መዞርህ ፤ ኡራኤል መላክ ማዳንህ ተገልፆል በቅዱስ ፀበልህ
ቢዮንሴን፣ ሪሃናን ወይም አንጄሊና ጆሊን ስላልመሰለች እንዳንንቃት። ጥቁሮች ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ እንደ ጥንቸል ታድነው በሚደፉበት በዚህ አስከፊ ዘመን፡ በእኔ በኩል፡ እንደ ባራክ እና ሚሼል ኦባማን፣ አል–ሻርፕተንን፣ ቢል ጌትስን ወይም ሉዊስ ፋራክንን የመሳሰሉትን ከሃዲያን የሰዶምና ገሞራ ልዑካን ከማዳምጥ ይልቅ ይህችን ምስኪን እህታችንን ማዳመጥ እመርጣለሁ፡ ብዙ ቁምነገር የያዙ መልዕክቶችን ነውና የምታካፍለን።
እህታችን ከሞላ ጎደል እንዲህ ትላለች፦
👉 የኢትዮጵያ መላእክት ሁሌ በሕልሜ ይታዩኛል። እንደ ካተሪና እና ሳንዲ ከመሳሰሉት የዓውሎ ንፋሶች፡ ጥፋት ያዳኑኝ የኢትዮጵያ መላእክት ናቸው
👉 በሰው ልጅ የባርነት ቀንበር ያልወደቁት ኢትዮጵያውያን ብቻ መሆናቸው ያስገርመኝ ነበር። አሁን መላእክቱ ነገሩኝ።
👉 ብዙ የተሳሳቱ ክርስቲያን ነን ባዮች እዚህ አሜሪካ እንዳሉ ታሪክ አስተምሮናል፡ አሁንም እያየን ነው።
ከሌሎች ጋር ያልተቀየጡና ንጹህ ክርስትናን የሚከተሉ ሁልጊዜ ለተበደሉ ሕዝቦች ይቆረቆራሉ፡ ይታገላሉ።
👉 ብዙ ጥቁሮች ግን ተታለዋል፡ ከሚበድሏቸው ጋር አብረው መሰለፍና ለነርሱም መቆም መርጠዋል።
የኔሽን ኦፍ ኢስላም የሚባለው ድርጅት ብዙዎችን እያታለለ ነው። ባርነት ሁሌ የእስልምና አካል ነበር፤ አሁንም እስላሞች ብቻ ናቸው ባርነትን የሚያካሂዱት፤ ታዲያ የእነርሱን አምልኮ የተቀበሉትና ከእነርሱ ጋር የሚተባበሩት ጥቁሮች የወደቁት ብቻ መሆን አለባቸው። ብዙ ጥቁሮች በቩዱ ጣዖት አምልኮ ሥር ስለወደቁ ከሉሲፈራውያኑ እና ከሙስሊሞች ጋር አብረው ይጓዛሉ። ያሳዝናል!
👉 አይሁዶች እንደሚያሸንፉና ወደክርስቶስ እንደሚመጡ ታይቶኛል፤ ታዲያ ሁሉም እስራኤልን የሚጠሉት ክርስቶስ ከአይሁዶች በኩል እንደሚመጣ ሰይጣን አለቃቸው ስለሚያውቅ ነው።
👉 ባለፈው ሳምንት የጸሀይ–ግርጆሽ ወቅት የታየኝ ነገር፤ በመሰከረም አንድ በኒዮርክ የሽብር ጥቃት ጊዜ የታየኝን ዓይነት ነገር ይመስላል። በዚያን ጊዜ፡ ትዕቢተኞች የነበሩት የኒውዮርክ ከተማ ነዋሪዎች፤ ከሽብሩ በኋላ፤ መተሳሰብና መፈቃቀር ጀምረዋል፤ ስለዚህ፣ ምናልባት አደጋው ሁሉ ለጥሩ ነገር ሊሆን ይችላል።
👉 ዲሞክራቶችን ወይም ሌሎች ፓርቲዎችን ስለመረጥን ነፃ አንሆንም መጽሐፍ ቅዱስ ነው ለነፃነታችን ቁልፍ ሚና የሚጫወተው።
👉 ቀይ ሕንዶች በሚባሉት የአሜሪካ አንጡራ ነዋሪዎች እና በጥቁሮች ላይ የደረሰው በደል ይህችን አገር እሥሯታል፤
👉 ለእነዚህ ህዝቦች የሚደረገውን ፍትህ የሆነ እንቅስቃሴ ሊበራሎች፥ ዘረጆች፥ ፊሚንስቶችና ጂሃዲስቶች ጠልፈውታል፤ ሁሉም ሰይጣናውያን ናቸው!
👉 ዌልፌር (መንግስታዊ የበጎ አድራጎት ገንዘብ) የአውሬው ምልክት ነው! ዌልፌርን (መንግስታዊ የበጎ አድራጎት ገንዘብ) አልደግፍም፤ ምክኒያቱም ወንጀለኛ ያደርጋልና፣ ሂፕሆፕ ሙዚቃንም አልደግፍም ሰይጣናዊ ሙዚቃ ነውና!
👉 አል ሻርፕተንና ኦባማን፤ ጥቁር ስለሆኑ ብቻ አልደግፋቸውም፥ ሂላሪ ክሊንተንንም ሴት ስለሆነች ብቻ አልደግፋትም።
👉 ከጸሀይ–ግርጆሹ በኋላ የታየኝ አንድ ጥሩ ነገር አለ፦
👉 ሁሉም ዓይነት ዘረኞች፥ ፊሚኒስቶች፥ ኢ–አማንያን ሊበራሉች፥ ጂሃዲስቶችና ሉሲፈራውያን ሁሉ ይገረሰሳሉ!!!
👉 ዘረኞች፥ ናዚዎች፣ ወንጀለኞችና ሙስሊም ሽብርተኞች ሁሉ በቅርቡ ይፈረድባችኋል፤ ወዮላችሁ!
______________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: African American, መንፈሳዊነት, አውሎ ንፋስ, አደጋ, ክርስትና, የኢትዮጵያ መላእክት, ጥቁር አሜሪካዊት, Christian Life, Ethiopian Angels, Hurricane | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 30, 2020
ይሄ እኮ ሁሉም ሊያነሳውና ሊነጋገርበት የሚገባው ትልቅ መረጃ ነው። ምን እየተካሄደ ነው? ቤተ ክርስቲያን በማን እየተመራች ነው? አባቶች ምን እየጠበቁ ነው? ሌሎች መምህራን የት ገባችሁ? ማንንስ/ምንንስ እየፈራችሁ ነው? የቤተ ክርስቲያን ሜዲያዎች የት ተደበቃችሁ? ኧረ ባካችሁ ከምስራቅ አውሮፓ ኦርቶዶክስ አባቶች ተምራችሁ ይህን የአህዛብ መንጋ ህገ–ወጥ መንግስት በአግባቡ ገስጹት።
“ትንፋሽ የሌለው ሰው የሞተ እንደሆነ ሁሉ፣ የማትናገር ቤተክርስቲያንም የሞተች ነች” – አባ መዓዛ ክርስቶስ በየነ
______________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: ህገ-ወጥ መንግስት, መምህር ደረጀ, ቤተክርስቲያን መዝጋት, ኮሮና ቫይረስ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን, ፀረ-ተዋሕዶ ዘመቻ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 29, 2020
በዛሬው ዕለት የጦጣዎች ቡድን በሕንድ ወደ አንድ የህክምና ኮሌጅ በመግባት የላብራቶሪ ቴክኒሺያኖቹን ካጠቁ በኋላ ከሰዎች የተወሰዱትን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ናሙናዎችን ሰርቀዋል፡፡
ጦጣዎቹ ዛሬ ጠዋት በህንድ ግዛት በኡታራ ፕራዴሽ ከሚገኘው ኮሌጅ ሶስት የሙከራ ናሙናዎችን ወስደው ዛፍ ላይ ወጥተዋል። ጦጣዎቹ ቢልቃቶቹን ይዘው በዛፍ ላይ ሲወዛወዙ ይታያሉ፡፡ አንደኛው ጦጣ እንዲያውም ናሙና የያዘውን ቢልቃጥ ሲያኝከው ይታያል።
አሁን ጦጣዎቹ ናሙናዎችን ስለወሰዱ ቫይረሱ በመኖሪያ አካባቢዎች ዙሪያ ሊሰራጭ ይችላል የሚል ከፍተኛ ፍራቻ አለ፡፡
ዝንጆሮዎችና ላሞች በሕንድ “ቅዱስ” ናቸው፤ በጣም ይመለካሉ፤ ሕንዶች (ሂንዱዎቹ)”ሃኑማን” የተባለ ዝንጀሮ–አምላክ አላቸው።
ቀደም ሲል “ድምጻችን ይሰማ!” የሚል መፈክር የነበራቸው ዝንጆሮዎች በኮሮና ቫይረስ ፕሮፓጋንዳ ባለመደሰታቸው ጭር ወዳሉት የህንድ ጎዳናዎች ለተቃውሞ ሰልፍ በመውጣት ሲንጎራደዱ ታይተው ነበር። (ምናለ ወደ አዲስ አበባ ቢሄዱ?!)
ሆኖም ድምጻቸውን የሚሰማቸው ስላጡ ጦጣዎቹ የሕንድን ፓርላማ በቁጥጥራቸው ሥር ለማድረግ ተገደው ነበር።
Monkey Business!
_________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Health, Infos | Tagged: ሕንድ, መስረቅ, ኮሮናቫርየስ, ዝንጆሮዎች, የዝንጀሮ-አምላክ, ጦጣዎች, Corona, COVID19, India, Monkeys | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 29, 2020
ይህ አጥንትን አለምላሚ የእመቤታችን ክብረ በዓል በ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም / ፭ኪሎ አዲስ አበባ ፥ መስከረም ፳፩ / ፪ሺ፲፪ ዓ.ም ነበር የተካሄደው።
የዲቃላው ግራኝ አህመድ አውሬ መንግስት ተቀዳሚ ፍልሚያ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር እንደሆነ የሚጠራጠር የተዋሕዶ ልጅ ካለ በጣም አዝናለሁ።
አሁን የአህዛብ ረመዳን አልቋል፤ ከንቱዎቹ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችም የፀሎትና ቅዳሴ መርሐ ግብርን ማስተላለፋቸውን አቁመዋል (እሰየው!) … ስለዚህ በመጪዎቹ ቀናትና ሳምንታት የጤና ሚንስትሯ ወይዘሮ ኮሮና በቀን አንዴ ብቅ እያለች “በወረርሽኝ ታሟል” የሚባለውን ሰው ቁጥር ከፍ፣ ከፍ በጣም ከፍ እያደረጉ ይመጣሉ። ዋናው ዓላማቸው ለዲያብሎሳዊ ተግባራቸው እንቅፋት የሆነችባቸውን ቤተ ክርስቲያንን እንደገና ማዘጋት ነው።
እንግዲህ ልብ በሉ፤ አደጉ በተባሉት አገራት አሁን የወጣ መረጃ እንደሚጠቁመን፤ “ስዎች በተቀራረቡና በተገናኙ ቁጥር በኮሮና ቫይረስ የመጠቃት ዕድላቸው በጣም ዝቅ ያለ ነው።” ስለዚህ ሰዎች በተቃራኒው አሁን በጣም ቢቀራረቡና ቢገናኙ ይመረጣል ማለት ነው!
በአዲስ አበባ ልደታ ማርያም (ሜክሲኮ) አካባቢ ችግር መፍጠራቸው ያለ ምክኒያት አይደለም። ላለፈው መስከረም ፬/4 ተጠርቶ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በዋናነት ያካሄደችው ቅድስት ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን ብቻ ነበረች። የመንፈሳውያኑ ኢትዮጵያውያን ጠላት የሆነው የግራኝ አህመድ መንግስት ይህን ያውቀዋል፣ ይህን ደግሞ በጣም ይፈራዋል። ስለዚህ አሁንም የእንቅስቃሴ እገዳውን በልደታ ሠፈር ጀምሯል። ባለፈው ኅዳር ወር እነ ታከለ ዑማ ልክ በአንቦ ተዋሕዷውያን ላይ እንደሚያደርጉት በአዲስ አበባም የመረዟቸው የተዋሕዶ ህፃናት ተማሪዎች የሚገኙት በልደታ ነው። እዚህ ገብተው ያንብቡ፦ የሞት ፍሬ በ ፍሬህይወት | ወገን፡ እነ ታከለ ልጆቻችሁን እየመረዙባችሁ ነው”
ሌላ የሚገርመው ነገር፤ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የሚገኘው የሜክሲኮ ኤምባሲ ለግብረ–ሰዶማውያን የድጋፍ መግለጫ ማውጣቱ ነው። በአጋጣሚ?
እናታችን ቅድስት ማርያም ከሚታየው እና ከሚሰማው ክፉ ነገር ሁሉ ትጠብቀን፣ ረድኤትና በረከቱ፣ ምልጃና ፀሎቷ አይለየን። አሜን! አሜን! አሜን!
________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: መስቀል, ቅድስት ማርያም, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ገዳም, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2020
- 👉 ቅድስተ ቅዱሳን
- 👉 ሰዓሊተ ምሕረት
- 👉 ተላኪተ እግ ዚአብሔር ወ ሰብእ
- 👉 ቤዛዊተ አለም
- 👉 ኪዳነ ምህረት
- 👉 ንጽሕይተ ንጽሐን
- 👉 ድንግል በክልኤ
- 👉 ድንግል ወእም
- 👉 ፍጽምተ ሥጋ ወነፍስ
- 👉 በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች
- 👉 እመብርሃን
- 👉 ምልዕተ ጸጋ
- 👉 እመቤታችን
- 👉 ወላዲተ አምላክ
__________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሰዓሊተ ምሕረት, ቅድስት ማርያም, አዲስ አበባ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን, ደብር / ካቴድራል, ግንቦት ማርያም | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2020
በኒው ዮርክ ማዕከላዊ የመናፈሻ ፓርክ ከእህቱ ጋር እየተዘዋወረ ወፎችን ፎቶ የሚያነሳው ጥቁር አሜሪካዊ ክርስቲያን ኩፐር/ Christian Cooper በገመድ ያልተያዘውን ውሻዋን የለቀቀችውን ነጯን ኤሚ ኩፐር / Amy Cooper ውሻዋን እንድታስር ሲጠይቃት ነበር የኒው ዮርክ ከተማ ፖሊስ መምሪያን ደውላ ድራማ የሠራችው፡፡
ግጭቱ የተከሰተው በኒው ዮርክ ከተማ ማዕከላዊ ፓርክ ክፍል ሲሆን ውሾች እንዳይለቀቁና ታስረው እንዲንቀሳቀሱ የሚያዙ ህጎች ባሉበት የመናፈሻው ጫካማ የሆነ ቦታ ላይ ነው።
ቪዲዮውን የቀረጸችው የክርስቲያን ኩፕር እህት ሜሎዲ ኩፐር / Melody Cooper ስትሆን፡ ወንድሟ መቀረጽ የጀመረውና ግጭቱም የተቀሰቀሰው ኤሚ ኩፐር ውሻዋን ለማሠር ፈቃደኛ ሳትሆን በመቅረቷ ነበር።
ከቪዲዮው እንደሚሰማው ክርስቲያን ኩፐር ኤሚ ኩፐር ወደ እሱ እንዳትቀርብ ጠየቃት ፣ እናም ልውውጡ ተባባሰ። ከዚያ ለፖሊስ በመደወል ጥቁር ሰው ሕይወቷን አደጋ ላይ እንደጣለው ነገረቻቸው ፡ ሴትየዋ በ 911 ጥሪዋ ላይ በተደረገው ንግግር የክርስቲያን ኩፐርን ዘር ደጋግማ እየገለጸች “ፖሊሶች ወዲያውኑ እንዲላኩ” ጠይቃለች፡፡
“አንድ አፍሪካዊ አሜሪካዊ ሰው እዚህ አለ ፣ በቪዲዮ እየቀረጸኝ እኔንና ውሻዬን ስጋት ላይ ጥሎናል” አለች ፡፡ ቪዲዮው ሴቲቱን ሲያስፈራራት አያሳይም፡፡
በዚህ መላዋ አሜሪካን ኡ!ኡ! ባሰኝ ቪዲዮ ምክኒያት ሴትዮዋ አሁን ከፍተኛ ደሞዝ ከሚሰጠው ስራዋ ተባርራለች፡፡ አሁን “ህይወቴ ተበላሸ፤ ይቅርታ!” ማለት ጀምራለች። ሰውዬም “ይቅርታዋ እውነተኛ ከሆነ ይቅር እላታለሁ” ብሏል።
በትንሽና በማይረባ ነገር በየትኛውም ቀን ሳናስበውና ሳንዘጋጅበት ሕይወታችን ግልብጥብጥ ሊል እንደሚችል ነው ይህ ታሪክ የሚያስተምረን፤ በተለይ እንደ ዘረኝነት ያለ ጋኔን ተሸካሚዎች ከሆንን።
የሚገርመው፦
- 👉 ፎቶው ላይ እንደሚታየው ነጯና ጥቁሩ የሆነ የሚመሳሰል ነገር አላቸው
- 👉 የሁለቱም ስም “ኩፐር / Cooper“ ነው
_________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Life | Tagged: መናፈሻ, ማዕከላዊ ፓርክ, ኒው ዮርክ, አሜሪካ, ውሻ, ዘረኝነት, ጋኔን, ጥላቻ, Central Park, New York, Racism | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2020
ዕርገት› በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡
በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዘመነ ዕርገት ውስጥ በሚገኘው እሑድ (ሰንበት) ሌሊት ሊቃውንቱ የሚያደርሱት መዝሙርም ‹‹በሰንበት ዐርገ ሐመረ›› የሚል ሲኾን ይኸውም ጌታችን በሰንበት ወደ ታንኳ በመውጣት ባሕርንና ነፋሳትን እንደ ገሠፀ፤ ሐዋርያቱንም ‹‹ጥርጥር ወደ ልቡናችሁ አይግባ፤ አትጠራጠሩ›› እያለ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዳስተማራቸው፤ እንደዚሁም ወንጌልን ይሰብኩ፣ ያስተምሩ ዘንድ በመላው ዓለም እንደሚልካቸው፤ በሰማያዊ መንግሥቱ ይኖሩ ዘንድም ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው የሚያስገነዝብ መልእክት አለው (ሉቃ.፰፥፳፪–፳፬፤ ዮሐ.፲፬፥፪፤ ፳፥፳፩)፡፡
በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ ሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከው የነግህ ምስባክም፡– ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል›› የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲኾን፣ ቀጥተኛ ትርጕሙ፡– ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል፤›› ማለት ነው (መዝ.፷፯፥፴፫)፡፡ ምሥጢራዊ ትርጕሙ ደግሞ ‹‹ነፍሳትን ይዞ ከሲኦል ወደ ገነት ለወጣ፤ አንድም በደብረ ዘይት በኩል ላረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ›› የሚል መልእክት አለው፡፡ እንደዚሁም ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን ‹የኀይል ቃል› የተባለ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከላቸው፤ በተጨማሪም ጌታችን በሕያዋን እና በሙታን (በጻድቃን እና በኃጥአን) ላይ ለመፍረድ ዳግም እንደሚመጣ፤ እኛም ይህንን የጌታችንን የማዳን ሥራ እያደነቅን ለእርሱ ምስጋና፣ ዝማሬ ማቅረብ እንደሚገባን ያስረዳናል – ምስባኩ፡፡
በነግህ (ከቅዳሴ በፊት የሚነበበው) ወንጌል ደግሞ ሉቃስ ፳፬፥፵፭ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት እንደሚወርድ፣ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ ወደ ሰማይ እንደሚያርግና ዳግም እንደሚመጣ በነቢያት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን፤ ለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክሮች መኾናቸውን ማለትም በመላው ዓለም እየዞሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ እንዲሰብኩና በሰማዕትነት እንዲያልፉ፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትንና ዕውቀትን እስኪያገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ መታዘዛቸውን ያስረዳል (ትርጓሜ ወንጌል)፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው የሐዋርያትን ተልእኮ የሚመለከት ይኹን እንጂ ለፍጻሜው ግን ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩትን ቃል አብነት አድርገን የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና የማዳኑን ሥራ አምነን፣ ሌሎችንም በማሳመን በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር እንደሚገባን፤ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይሉን፣ ጸጋውን፣ ረድኤቱን እንዲያሳድርብንም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለየት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ መልእክት አለው፡፡
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ዕብራውያን ፩፥፩ እስከ ፍጻሜው ድረስ፤ ከሌሎች መልእክታት ደግሞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፫፥፲፰ እስከ ፍጻሜው፤ የሐዋርያት ሥራ ፩፥፩–፲፪ ሲኾኑ፣ ምስባኩም ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ›› የሚለው ነው፡፡ ትርጕሙም ‹‹በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ›› ማለት ነው (መዝ.፵፮፥፭–፮)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ፣ ማርቆስ ፲፮፥፲፬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ሲኾን ቃሉም በነግህ ከተነበበው የወንጌል ክፍል ቃል ተመሳሳይነት አለው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን ይህ ቅዳሴ ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነውን የእግዚአብሔር ወልድን (የኢየሱስ ክርስቶስን) ዘለዓለማዊነት የሚያስረዳ፤ ሥጋዌዉን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና ዳግም ምጽአቱንም የሚናገር በመኾኑ በዘመነ ትንሣኤ፣ በዘመነ ዕርገትና በበዓለ ኀምሳ ሰሙን ይቀደሳል፡፡
ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴዉ መጀመሪያ ላይ ሀልዎተ እግዚአብሔርንና ምሥጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ካቀረበ በኋላ፣ ቍጥር ፴፩ ላይ ‹‹… ወበ፵ ዕለት አመ የዐርግ ሰማየ አዘዞሙ እንዘ ይብል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ፤ … ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በዐርባኛው ቀን በብርሃን፣ በሥልጣን፣ በይባቤ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ አብ የሚሰድላችሁ መንፈስ ቅዱስን እስክትቀበሉ ድረስ ከዚህ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው፤›› በማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ በኾነ ቋንቋ የጌታችንን ወደ ሰማይ ማረግና ለሐዋርያት የሰጠውን አምላካዊ ትእዛዝ ይናገራል (ሉቃ.፳፬፥፵፱)፡፡
ምንጭ
___________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ተዋሕዶ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, እርገት, ኦርቶዶክስ, ክርስትና, ዕርገት, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 27, 2020
ይህ EBS/ኢ.ቢ. ኤስ የሠራው ቪዲዮ ነው። ካሜራው ወደ አቃቂ አድቬንቲስት አዳሪ ተማሪ ቤት አምርቶ ነበር። እዚያም የተዋሕዶ ተማሪዎች ወደዚህ ተማሪ ቤት ለመግባት ማህተባቸውን መበጠስ አለባቸው ፥ ሙስሊሞቹ ግን ከእነ ሂጃባቸው መግባት ተፈቅዶላቸዋል።
ግን እያየን ነው፤ የአህዛብን፣ የመናፍቃንን እና የዘረኞችን በተዋሕዶ ላይ ያነጣጠረውን ሕብረት?! ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አንድ ላይ ይበራሉ ፥ ተኩላውም ቀስ በቀስ ለምዱን እየገፈፈ ነው።
ከጥቂት ዓመታት በፊት፤ በጥምቀት ከተራ ፪ሺ፱ ዓ.ም፡ እ.አ.አ በ1943 ዓ.ም በተቋቋመው የአቃቂ የአድቬንቲስት አዳሪ ተማሪ ቤት “ተማሪዎች” የሆኑት የተዋሕዶ ልጆች ከግቢው መውጣት ስላልተፈቀደላቸው፤ ወደ በሩ ተጠግተው፤ “የኛ!” እያሉ በመዘመር ለጥምቀት በዓል ከመንበራቸው በክብር የወጡትን ታቦታት ይቀበሏቸው ነበር። በወቅቱ ጠይቄ እንደተረዳሁት ከሆነ፡ የተዋሕዶ አዳሪ ተማሪዎች ውደ ትምህርት ቤቱ ሲመዘገቡ፡ ማሕተባቸውን እንዲያወልቁ ተደርገው ነው፤ አልያ መግባት አይችሉም።
የኢቢ ኤስ ቪዲዮ እራሱ እንደሚያሳየው መሀመዳውያኑ ግን ከነሂጃባቸው እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፤ ጉድ የሚያሰኝ አሳዛኝ ጉዳይ ነው። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ልክ እንደ ቅኝ ተገዢዎች ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው መብትና ምጫ የላቸውም ፤ የተዋሕዶ በሆነቸው በሃገረ ኢትዮጵያ! ያው እንግዲህ የደቡባውያኑ የእነ አፄ ኃይለ ሥላሴ ፈረንጅ አፍቃሪነትና ሁሉን አቃፊነት እምቧይና እሾህ አፍርቶ ይታያል።
_________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: ምንፍቅና, አህዛብ, አዳሪ ተማሪ ቤት, አድቬንቲስት, ኢቢኤስ, እስልምና, ዋቄዮ አላህ, ጣዖት አምልኮ, ፀረ-ተዋሕዶ ዘመቻ, EBS | Leave a Comment »