Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith’

“በዚያ ወራት ስለ ሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል” [ዳን ፲፪.፩]

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 21, 2022

✞✞✞

እያንዳንዱ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ ቅዱሳን መላእክት አሉት

የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው … ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ

😇 ፈጣኑ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ፤ አስቀድሞ የተጣላህን በቀል ባለመርሳት ጋሻህን አንሣ፤ ፈጣኑ መልአክ ሆይ ነበልባላዊ ሰይፍህን በጠላታችን በዲያብሎስ ላይ መዘህ ተነሣሣበት።

ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ፤ ኃይልህን የስው ኃይል ሊተካከለው አይችልምና የክርስቶስን ልጆች ጽዮናውያንን፤ “እንግደላቸው፣ ከምድረ ገጽ እናጥፋቸው ብለው በአባቶቼና እናቶቼ ላይ፣ በወንድሞቼና እኅቶቼ እና ልጆቻቸው ሁሉ ላይ የዘመቱትን የዋቄዮ-አላህ-ዲያብሎስ ጭፍሮች ጠላቶቻችንን ጭጋን በቀላቀለ ዓውሎ ነፋስ በታትነህ ከገጸ ምድር አጥፋቸው። ሕፃናትን በርሃብ ለመፍጀት የጨከኑትን እነዚህን አውሬዎች በእሳት ጠራርጋቸው። ድል አድራጊው መልአክ ሆይ፤ ያ የቀድሞ አመፀኛው አውሬ ዲያብሎስ የጥንት ተንኰሉ ሊተው አልቻለምና የጦር መሣሪያህን ታጥቀህ፣ መጥተህ እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊንና ጭፍሮቹን ሁሉ ድምጥማጣቸውን አጥፋቸው።

😇 እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ የንግስ በዓል አደረሳችሁ። በዓሉን የበረከት በዓል ያድርግልን።

😇 ሊቀ መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ይጠብቅን

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰቆቃ ቤተ ክርስቲያን ትግራይ | ጂሃድ በአባ ዘ-ወንጌል ማዕቢኖ ደብረሲና መስቀለ ክርስቶስ ገዳም ላይ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 19, 2021

😠😠😠 😢😢😢

‘ክርስቲያን ነኝ! ኢትዮጵያዊ ነኝ!’ የሚል ወገን እንዴት ከአህዛብ ቱርክ ጋር አብሮ ክርስቲያንና ኢትዮጵያዊ የሆነውን ወንድሙን ይወጋል? ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት፤ በዘመነ ግራኝ ቀዳማዊ፤ ኦሮሞዎችና/ጋሎችና ሶማሌዎች ልክ እንደዛሬው ከክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ጋር መሰለፋቸው የሚታወቅ ነው፤ ግን “አማራ” የተባሉትስ በወቅቱ ተመሳሳይ ክህደት ፈጽመዋልን? ታሪክ እኮ የዛሬው እና የወደፊቱ መስተዋት ነው! እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ!!!

😈 በአማራዎች፣ በሶማሌዎች እና በኦሮሞዎች የሚደገፈው የፋሺስቱ ኦሮሞ እና ቤንአሚር ኤርትራ አገዛዝ አህዛብ ሰአራዊት እንዲህ ነበር አባቶቻችንን እናቶቻችንን የጨፈጨፋቸውና ✞ የቤተ ክርስቲያኑንም ሕንፃ ያፈራረሰው! ዋይ! ዋይ! ዋይ!

በትግራይ አሲምባ ተራሮች ላይ የሚገኘው እንዳ መስቀለ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ❖

Enda Meskel Kristos Church in the Asimba Mountains

[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፳]

ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?”

❖❖❖[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፯፥፳፩፡፳፫]❖❖❖

በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።”

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፲፱]✞✞✞

፩ በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ ሰማኝም።

፪ ከዓመፀኛ ከንፈር ከሸንጋይም አንደበት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።

፫ ስለ ሽንገላ አንደበት ምንም ይሰጡሃል? ምንስ ይጨምሩልሃል?

፬ እንደ በረሃ እንጨት ፍም የኃያላን ፍላጾች የተሳሉ ናቸው።

፭ መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፤ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ።

፮ ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ኖረች።

፯ እኔ ሰላማዊ ነኝ፤ በተናገኋቸው ጊዜ ግን በከንቱ ተሰለፉብኝ።

____________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ታሪካዊው ምስካየ ኅዙናን (የሐዘንተኞች መጠጊያ) መድኃኔ ዓለም ገዳም | መድኃኔ ዓለም በትግራይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያጽናናልን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 5, 2021

✞✞✞እንኳን ለዓመታዊው የመድኃኔ ዓለም ክብረ በዓል አደረሰን!✞✞✞

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ አስቀድሞ ለአዳምና ለሔዋን በሰጣቸው ተስፋ መሠረት ፭ሺ፭፻ /5500 ዘመን ሲፈጸም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ፪/2 ዓመት ከስድስት ወር በግብጽ በረሀ ተሰዶ ስደታቸውን ሻረላቸው በ፴/30 ዓመቱ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር ተጠምቆ ልጅነታቸውን መለሰ እንዲሁም በዮርዳኖስ ወንዝ “አዳም የዲያብሎስ ባሪያ” የሚል ጽሕፈት ስለነበረ በጥምቀቱ ደምስሶላቸዋል። ሦስት ዓመት ከ፯/7 ወር ወንጌል በእስራኤል ተአምራትን እያደረገ ሙታንን እያስነሳ፣ እውራንን እያበራ፣ ለምጻሞችን እያነጻ፤ ፴፫/33 ዓመት ከ፫/3 ወር በዚህች ዓለም ከተመላለሰ በኋላ መጋቢት ፳፯/27 ቀን በእፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ በሞቱ ሞታችንን ሻረልን።

መድኃኔ ዓለም ማለት የዓለም መድኃኒት ማለት ነው።

ቸሩ መድኃኔ ዓለም በግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የኦሮሞ አህዛብ አገዛዝ በተለይ በትግራይ የሚጨፈጨፉትን፣ የሚበደሉትን፣ የሚደፈሩትን፣ የሚሰደዱትንና የሚጎሳቆሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያጽናናልን!

በ፲፮ ኛው ክፍለ ዘመን በግራኝ አህመድ ወረራ ጊዜ፤ በወቅቱ ነግሠው የነበሩት አፄ ልብነ ድንግልም ሆኑ

እሳቸውን የተኳቸው ነገሥታት፤ በጦርነቱ ምክኒያት በቅድስት ሀገር ለተቋቋሙ አብያተ ክርስትያናት ዕርዳታቸውን ስላቋረጡ፤ ካህናቱ የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ፣ ምግብ ባለማግኘታቸው፤ ገዳማቱን ግማሹን በአደራ ለአርመንና ለግሪኮች እየሰጡ፤ ሌሎቹን ደግሞ ዘግተው ወደ አውሮጳ ተሰደዱ፡፡

ከዓመታት በኋላ ተመልሰው ሲመጡ ግን ሁሉንም ለማግኘት ባይችሉም አሁን በእጃችን ያሉትን ይዘው አገልግሎታቸውን ቀጠሉ፡፡ ግራኝ ድል ሆኖ ጦርነቱ ከቆመም በኋላ፣ አንድ ወጥ መንግሥት የነበረው ቀርቶ የዘመነ መሳፍንት አገዛዝ ስለቀጠለና ፣ አሁንም በቂ ዕርዳታ ማግኘት ስላልቻሉ፤ ድርጎ፣ ልብስ፣ የመሳሰሉትን የሚያገኙት ከአርመንና ከግሪክ ገዳማት ነበር፡፡

በ፲፱ ኛ ክፍለ ዘመን የነገሡት ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ቋሚ ገቢ እንዲኖራቸው በማሰብ እዚያው ኢየሩሳሌም ውስጥ ሕንፃ ተሠርቶ የሚከራይበት መሬትና ተጨማሪ ሌላ ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃ በሺ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓ.ም. በመግዛት አበርክተዋል፡፡ በዚያው ዓመት

የመድኃኔዓለምን ታቦት ዴር ሱልጣን መድኃኔዓለም በሚል ተሰይሞ መምህር ፈቃደ እግዚእ በተባሉ መነኩሴ ወደ ኢየሩሳለም ልከው በዴር ሡልጣን ገዳም ለ፴፬ ዓመታት ሲቀደስበት ሲወደስበት ኖሯል፡፡

በስደት የነበረው ታቦት መድኃኔዓለም ነሐሴ ፳፫ ቀን ፲፱፴፫/1933 ዓ.ም. እቴጌ መነን ወደ አዲስ አበባ በተመለሱ ቀን፤ አባ ኃይሌ ቡሩክ ታቦቱን ይዘው ተመልሰው በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት የአሁኑ የስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ጸሎት ቤት ውስጥ እያጠኑና እየጠበቁ ከቆዩ በኋላ፤ ሚያዚያ ፳፯/27 ቀን ፲፱፴፭/1935 ዓ.ም. የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ተብሎ ተሰይሞ

በቀድሞ ቤተ ሳይዳ ቀዳማዊ ኃ/ሥለሴ ሆስፒታል አሁን የካቲት ፲፪ ቀን ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ተተከለ፡፡

ምስካየ ኅዙናን ትርጓሜ ለተበደሉትና ላዘኑት ማረጋጊያ ማጽናኛ ማለት ነው፡፡

አዎ! የዘመናችን ግራኝ አህመድ በለገጣፎ ያፈናቀላቸውን ወገኖቻንን መጠለያ የሰጣቸው የመድኃኔ ዓለም ቤተክስቲያን ነው፤ ለሙስሊሙ ሳይቀር። ቸሩ መድኃኔ ዓለም ሁሌም ለሁሉም በሩን ይከፍታል።

ምስካየ ኅዙናን (የሐዘንተኞች መጠጊያ) መጠሪያ ስሙ ብቻ በጣም ይመስጣል፤ እግዚአብሔር የገዳሙን ደጅ መርገጥ ፈቅዶልኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ማየቴ ነበር፤ ይገርማል የአዲስ አበባ ሰው ሆኜ፤ በጣም ከተደሰትኩባቸው ዕለታት መካከል አንዱ ነበር።

የምስካየ ኀዙናን መድኃኔ ዓለም አፄ ምኒልክ ታቦቱን ወደ ቅድስት ሀገር ልከው፤ ከዚያም በእንግሊዝ ሀገር በስደት ለብዙዎች መጽናኛ ሆኖ ቆይቶ ወደ ሀገራችን ተመልሶ እስከመጣበትና እስከ አሁንም ድረስ፤ ታሪካዊና፣ በሥራ ሂደቱ፣ በእንቅስቃሴው፣ ልዩ ልዩ ሥራዎችን በመጀመር ለሌሎች አብያተ ክርስቱያናት አርአያ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ገዳም ነው፡፡

ይህ ድንቅ ገዳም ወደፊትም የበለጠ ሥራ የሚሠራና፤ ለእናት ቤተ ክርስቲያናችን የሚያኮራ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

መድኃኔ ዓለም ይህንን እና ሌሎቹን ገዳሞቻችንን እንዲጠብቅልን፤ ሀገራችንንም በበረከቱ እና ቸርነቱ እንዲጎበኝልን ዘወትር እንጸልያለን፡፡

መድኃኔ ዓለም ተብሎ መድኃኒታችን የሆነን አምላክ ይክበር ይመስገን። አሜን!

_____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን ፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አታጥፋ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 31, 2021

በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውም መማለጃ ተሞልታለች።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፭]

፩ አቤቱ፥ እኔ በየውሃቴ ሄጃለሁና ፍረድልኝ፤ በእግዚአብሔርም አምኛለሁና አልናወጥም።

፪ አቤቱ፥ ፍተነኝ መርምረኝም፤ ኵላሊቴንና ልቤን ፍተን።

፫ ምሕረትህ በዓይኔ ፊት ነውና፥ በእውነትህም ተመላለስሁ።

፬ በከንቱ ሸንጎ አልተቀመጥሁም፥ ከዓመፀኞችም ጋር አልገባሁም።

፭ የክፉዎችን ማኅበር ጠላሁ፥ ከዝንጉዎችም ጋር አልቀመጥም።

፮ እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፤ አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥

፯ የምስጋናን ድምፅ እሰማ ዘንድ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።

፰ አቤቱ፥ የቤትህን ስፍራ የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።

፱ ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አታጥፋ።

፲ በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውም መማለጃ ተሞልታለች።

፲፩ እኔ ግን በየውሃቴ ሄጃለሁ፤ አድነኝ ማረኝም።

፲፪ እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፤ አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።

______________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጠላቶችህ መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ፤ የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 29, 2020

አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፫]

፩ አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘወትር ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቍጣህን ስለ ምን ተቈጣህ?

፪ አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥ የተቤዤሃትንም የርስትህን በትር፥ በእርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ አስብ።

፫ ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜም በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ።

፬ ጠላቶችህ በበዓል መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ።

፭ እንደ ላይኛው መግቢያ ውስጥ በዱር እንዳሉም እንጨቶች፥ በመጥረቢያ በሮችዋን ሰበሩ።

፮ እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት።

፯ መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ፤ የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ።

፰ አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው። ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓሎች ከምድር እንሻር አሉ።

፱ ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ የለም፤ እስከ መቼ እንዲኖር የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም።

፲ አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህን ጠላት ሁልጊዜ ያቃልላልን?

፲፩ ቀኝህንም በብብትህ መካከል፥ እጅህንም ፈጽመህ ለምን ትመልሳለህ?

፲፪ እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ።

፲፫ አንተ ባሕርን በኃይልህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቦችን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ።

፲፬ አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።

፲፭ አንተ ምንጮቹንና ፈሳሾቹን ሰነጠቅህ፤ አንተ ሁልጊዜ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅህ።

፲፮ ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፤ አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ።

፲፯ አንተ የምድርን ዳርቻ ሁሉ ሠራህ፤ በጋንም ክረምትንም አንተ አደረግህ።

፲፰ ይህን ፍጥረትህን አስብ። ጠላት እግዚአብሔርን ተላገደ፥ ሰነፍ ሕዝብም ስሙን አስቈጣ።

፲፱ የምትገዛልህን ነፍስ ለአራዊት አትስጣት፤ የችግረኞችህን ነፍስ ለዘወትር አትርሳ።

፳ ወደ ኪዳንህ ተመልከት፥ የምድር የጨለማ ስፍራዎች በኅጥኣን ቤቶች ተሞልተዋልና።

፳፩ ችግረኛ አፍሮ አይመለስ፤ ችግረኛና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ።

፳፪ አቤቱ፥ ተነሥ በቀልህንም ተበቀል፤ ሰነፎች ሁልጊዜም የተላገዱህን አስብ።

፳፫ የባሪያዎችህን ቃል አትርሳ፤ የጠላቶችህ ኵራት ሁልጊዜ ወደ አንተ ይወጣል።

______________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ፈጣኑ መልአክ ሆይ ነበልባላዊ ሰይፍህን በጠላታችን በዲያብሎስ ላይ መዘህ ተነሣሣበት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 21, 2020

እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ የንግስ በዓል አደረሳችሁ። በዓሉን የበረከት በዓል ያድርግልን።

_______________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቤተ ክርስቲያን ሆይ መከራሽ መብዛቱ፤ ከአንቺው አብራክ ወጥተው ጎራዴ አነገቱ፤ ተባብረው ሊወጉሽ ባንቺ ላይ ዘመቱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 15, 2020

ሳሪስ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቤተክርስቲያን የባህል ጎዳና ሆነች | ራያዎች በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እንዲጨፍሩ ተደረጉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 3, 2020

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፡ ክብረ በዓል፤ የተዋሕዶ ጠላቶች የራያ ጨፋሪዎችን ወደ አዲስ አበባ አምጥተው፡ ምዕመናንን እንዲያውኩ ሲያደርጓቸው።

በተዋሕዶ ክርስትና እና ቤተ ክርስቲያን ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ከሁሉም አቅጣጫ እየመጣ ነው። አባቶቻችንን በየገዳማቱ ማጥቃትና መግደል የመጨረሻው ዒላማቸው እንደሆነ ብናውቅም፤ መጀመሪያ ግን ክርስቲያናዊ ሕይወትን በመላው የማሕበረሰብ ክፍሎች፣ በየመንገዱ፣ በየመስሪያ ቤቱ፣ በየጎረቤቱ በመቅረብ ብሎም ወደ ቤተክርስቲያን በሱቅ መልክ፣ በጎብኚ መልክ፣ የመስገጃ ቦታ በመሻማት (ሩፋኤል፣ ራጕኤል) ቀስ በቅስ ጠጋ ጠጋ በማለት ይዋጉታል።

ይህ ክስተት ላለፉት ዓመታት የምናየው ነው። በተለይ በአዲስ አበባ አድባራትና ዓብያተ ክርስቲያናት የሕዝበ ክርስቲያኑን መንፈሳዊ እርጋታና ሰላሙን ለማወክ ገበያዎችን ይከፍታሉ፣ የመዝሙር ሲዲዎችን በከፍተኛ ጭኸት የሚያስተዋውቁትን መኪናዎችን አምጥተው ያቆማሉ፤ ባሕላዊ ዘፋኞችን እና ጨፋሪዎችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ግቢ ያስገቧቸዋል። (ልክ እዚህ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ግቢ ራያዎችን እንደምናያቸው) የስከሩ ጨፋሪዎች ሁሉ ሲገቡ የሚታዩባቸው በዓላት አሉ። ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሌላ ቦት ባሕላቸውን ቢያስተዋውቁ ባልከፋ፤ ነገር ግን ያመጧቸው ሆን ተብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው “ሁሉም ባሕል ነው፣ ሁሉም አንድ ዓይነት ነው” የሚለውን አጀንዳ ለማራማድ ይጠቀሙባቸው ዘንድ ነው።

ከራያ ያመጧቸውን የባህል ጨፋሪዎች (ድሮም ወደ አክሱምና ላሊበላ አካባቢ አምጥተው እዚያ እንዲሰፍሩ መደረጋቸው የጣዖቱን ዋቄዮ አምልኮት ያስፋፉ ዘንድ በእባባዊ መልክ በማቀድ ነበር) በየአብያተ ክርስቲያናቱ እንዲገቡ በማድረግ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ለማበላሸትና እምነታችንንም ወደ ባሕላዊ ሥርዓት ለመለወጥ ይቻላቸው ዘንድ በደንብ አቅደውበት ነው።

በነገራችን ላይ፡ እንደ “መስቀል” እና “ጥምቀት” የመሳሰሉትን ክብረ በዓላት የየተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት፤ በምህጻሩ UNESCO በሚባለው ድርጅት እውቅናን እንዲያገኝ መደረጉ መንፈሳዊ የሆነችውን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ወደ ዓለማዊው የባህል፣ ወግና ልምድ ሥርዓት ይለወጥ ዘንድ የተጠነሰሰ ዲያብሎሳዊ ሤራ ነው። ቤተ ክርስቲያንን የባሕል ተቋም ለማድረግ የሚሠራ ሥራ ነው።

ቤተ ክህነትም ሆነች ምዕመናን ክርስቲያናዊ በዓላታቸውን በአውሬው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል ዕውቅና እንዲያገኙ ከመታገል መቆጠብ ይኖርባቸዋል፤ አሊያ ይህ ትልቅ ስህተት ነው የሚሆነው።

____________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰይጣን ጥልቅ ጉድጓድን አስቆፍሮ ፀሐይን (መስቀሉን) ለመሰወር ሞክሮ ነበር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 1, 2020

ነገር ግን ዲያብሎስ ድካሙ ከንቱ ሆኖ ቀረ ፥ ፀሐይን መስወር አይቻልም፤ ፀሐይን ማጥለቅም ማውጣትም የሚቻለው እግዚአብሔርን ብቻ ነው ፥ ስለዚህ ፀሐይን መሰወር እንደማይቻለው ሁሉ፤ ዓለምን ያበራው፣ ጨለማውን ዓለም ያስወገደ እውነተኛው ፀሐይ የተባለ መስቀል ተቆፍሮ ተቀብሮ አልቀረም፤ መስቀል ወጥቷል፣ የምንበላውን የምንጠጣውን አስገኘትቶልናል።

ግሩም ነው፤ ይህ ትምህርት የተሰጠው ዓምና ልክ በዛሬው ዕለት መስከረም ፳፩ / ፪ሺ፲፪ .ም በ እመቤታችን ክብረ በዓል ወቅት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም / ፭ኪሎ አዲስ አበባ ፥ ዓ.ም ነበር።

የሚገርም ነው! ልክ ከዓመት በኋላ በኦሮሚያ ሲዖል ውዳቂዎቹ የዋቄዮ-አላህ ልጆች መስቀሉን ጉድጓድ ቆፍረን እንቀብረዋለን ብለው ዛቱ።

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አዲስ አበባ ሰማይ ስር የሚሠራው ግዙፍ መስቀል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 28, 2020

ይህ ሥራ በጣም በጎ ነገር ነው፤ እንዲያውም አዲስ አበባ ዙሪያዋን በመስቀል ብትከበብ ነዋሪዎቿ ከብዙ መዓት ይድናሉ፤ በአቡነ ኃብተማርያም ገዳምም መሠራት ይኖርበታል።

ነገር ግን ዛሬ በአላጋጮችና ድራማ ሠሪዎች ተከብበናልና “ይህ ዜና በአዲስ ዓመት መግቢያ ላይ እንዲሁም በደመራና መስቀል ወቅት ከመውጣቱ ጀርባ ማን/ ምን ይኖር ይሆን?” የሚለውን ጥያቄ ከመጠየቅ መቆጠብ የለብንም። መቼስ ማጭበርበርና ማታለል ሙያው አድርጎ የያዘው የአውሬው አገዛዝ ቤተ ክርስቲያንን ለመፈታተን እና ለመተናኮል የማይቆፍረው ጉድጓድ የለምና።

ምናልባት፦

👉 የቆፋፈረውን የመስቀል አደባባይ ጉዳይ ለማረሳሳትና ህዝበ ክርስቲያኑን ለመደለል ይሆን?

👉 በጣም ሚስጢራዊ የሆነውን እና መስቀል አደባባይ እና ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የሚገኙበትን አካባቢ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር አቅዶ ይሆን?

👉 የመስቀል አደባባይን “አንድነት ወይንም ኢሬቻ አደባባይ” ብሎ ለመሰየም ዕቅድ ስላለው ይሆን?

👉 ከ “ሸገር ፕሮጀክት፣ እንጦጦ ፓርክ ቅብርጥሴ” ጋርስ የሚያገናኘው ምን ነገር ይኖራል?

ለማንኛውም በሚቀጥሉት ቀናት የምናየው ይሆናል። የአውሬው አገዛዝ ካድሬዎችና ወኪሎች ተዋሕዷውያንን አወናብዶ ወደካምፑ ለማምጣት የተለያዩ ቅስቀሳዎችን ሲያደርጉ የምንሰማበት አጋጣሚ ይኖራል።

________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: