[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፫፥፲፭፡፲፮]
“በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።”
አንድ የክርስቶስ አርበኛ እንዲህ ትኩስ መሆን ነው ያለበት። በተለይ ነገሮች ሁሉ ግልጥልጥ ብሎ በሚታዩበትና በቂ መረጃዎችም ማግኘት በሚቻልበት በዚህ ዘመን ሙስሊሞች ወደ ክርስቶስ ሊመጡና ሊድኑ የሚችሉት ብቸኛው መንገድ ይህ ነው። “እንቻቻችል! እንከባበር! የሃይማኖት እኩልነት! የሌላውን ሃይማኖት አለመንካት … ቅብርጥሴ” የሚሉትን የዲያብሎስ የማታለያ ዘዴዎች መከተል የለብንም። ምን በጎ ነገር አምጥተውልን?