Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2020
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for March, 2020

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቸኛው የዓለማችን በራሪ የኮሮና አህያ ታክሲ | ጣልያኑ ፖምፔኦ አመሰገኑ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 31, 2020

ጣሊያን አሜሪካዊው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔኦ/ Mike Pompeo የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሜሪካኖችን ወደ አሜሪካ ለማምጣት ፈቃደኛ የሆነ ብቸኛ የአየር መንገድ ታክሲ ስለሆነ ለከሃዲ አብዮት አህመድ ስልክ ደውለው አመስግነውታል። ቅኝ ተገዥ ኢትዮጵያ ታመሚ! አየር መንገዱንም ከእንግዲህ “ኮሮና ኤር” ማለት ይችላሉ! አየር መንገዳችንን ለ75 ዓመታት ያህል ያለምንም መሰናከል ፣ በሁሉም የኢትዮጵያ መንግስታት ሲያዘጋጁት የነበሩት ለዚህ ዘመን እንደነበር እያየነው ነው።

____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Health, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እንቍለጣጣሽ | ኮሮና + ጣልያን + ኒው ዮርክ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 31, 2020

***UPDATE ዝመና***

+++ የኒው ዮርኩ አገረገዥ ወንድም የCNN ጋዜጠኛው ክሪስ ኮሞ/ Chris Cuomo (ከጁሊያኒ ጋር ግራ የተጋባው) በኮሮና መያዙ ታወቀ። አገረ ገዥው አንድሪው ኮማ ወንድሙ እናታቸውንም ሳይበክላት አይቀርም የሚል ስጋት አለው። ኦ! ! ይህን ቪዲዮ አይቶ ይሆን?

+++ ጣሊያን አሜሪካዊው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔኦ/ Mike Pompeo በመላው ዓለም የሚገኙ አሜሪካውያን ወደ ዩ.ኤስ አሜሪካ በአስቸኳይ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ።

+++ ጣሊያን አሜሪካዊው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔኦ/ Mike Pompeo የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሜሪካኖችን ወደ አሜሪካ ለማምጣት ፈቃደኛ የሆነ ብቸኛ የአየር መንገድ ታክሲ ስለሆነ ለከሃዲ አብዮት አህመድ ስልክ ደውለው አመስግነውታል። ኢትዮጵያ ታመሚ!።

+++ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቸኛው የዓለማችን የኮሮና አህያ ታክሲ


የኮሮና ጣጣ ሁለተኛ እንቁለጣጣሽ/ 911 ነው።

19ዓመታት በፊት በእንቅጣጣሽ ዕለት በኒው ዮርክ ላይ ጥቃት የፈጸሙት ሳውዲዎችና ግብጾች ነበሩ። ያመቻቸላቸውስ የጣልያን ማፍያ ይሆን?

ኒው ዮርክ ግዛትና ከተማዋ – በኮሮኖ ክፉኛ የተመቱት የአሜሪካ ክፍለ ሃገሮች ሆነዋል። ዝነኛው የኢምፓየር ስቴት ህንፃ “ዘውድ/ኮሮና” በዛሬው ዕለት ደም አብርቶ ይታያል። ይህን ቪዲዮ አዘጋጅቼ ስጨርስ በመላው የኒው ዮርክ ግዛት 66 ሺህ 600(666)ሰዎች በወረርሽኙ መለከፋቸው እና 1218 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

በአውሮፓ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቃችው ጣልያን በሰሜን አሜሪካ ደግሞ ኒው ዮርክ ግዛት ናቸው።

የጣልያን እና ኒው ዮርክ ግኑኝነት በጣም ምስጢራዊ ነው። የቀድሞው ኒው አምስተርዳም በእንግሊዞች ተይዛ ኒው ዮርክ ከተባለችበት ዘመን አንስቶ ጣልያኖች ከግንባታ ሥራ እስከ ማፍያ ንግድ የተቆጣጠሯት የጣልያን ዝርያ ያላቸው አሜሪካውያን ናቸው።

በኮሮና ክፉኛ የተጠቁት ጣልያን እና ኒው ዮርክ የሚከተለው የጣልያን ሰንሰለት ያስተሳስራቸዋል፦

👉 ጣልያን አሜሪካዊ ቍ.

የኒው ዮርክ አገረገዥ አንድሪው ኮሞ/Andrew Cuomo

👉 ጣልያን አሜሪካዊ ቍ.

የኒው ዮርክ ከተማ ከንቲባ ቢል ዴ ብላሲዮ /Bill de Blasio

👉 ጣልያን አሜሪካዊ ቍ.

በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ዕለት / እንቁጣጣሽ መስከረም፩ / ፲፱፻፺፬ / Sep 11, 2001 .

ኒው ዮርክ በሽብርተኞች ስትጠቃ የነበሩት ከንቲባ ሩዶልፍ ጁሊያኒ / Rudolph Giuliani

👉 ዘመነ ኮሮና አሜሪካዊ ግራ መጋባት

የአሜሪካው CBS ቴሌቪዥን በብሪታኒያው “SkY TV” ላይ ቀርቦ የነበረውን የጣልያን ሆስፒታልን

ምስል በመውሰድ የኒው ዮርክ ሆስፒታል እንደሆነ አድርጎ አቀረበው።

ወገኖች፡ ከባቢሎን ኒው ዮርክ፣ ከባቢሎን ሳውዲ አምልጡ!

_________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የወደቀው መልአክ በናይጄሪያ? | ተወርዋሪ ኮከብ በመናፍቃን ቸርቾች ላይ ወደቀ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 31, 2020

የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ/ሉሲፈር ኩሬ በ አኩሬ?

ባለፈው ቅዳሜ በደቡብ ምዕራብ ናይጀሪያ አኩሬ ከተማ ከሰማይ ወረደ የተባለ ተወርዋሪ ኮከብ ወይም ሚትዮራይትስ /ሜትዮሮይድስ ቸርቾችንና መቶ የሚሆኑ ቤቶችን ማፈራረሱ ታውቋል። በቦታው ከፍተኛ የፍንዳታ ድምጽ ተሰምቶና ጥልቅ የሆነ አዲስ ኩሬ ተገኝቶም ነበር። ምንም እንኳን አንዳንዶች፡ የአገረገዢውን ጨምሮ፡ ይህን ኃይለኛ ፍንዳታ የፈጠረው በጭነት መኪና የተወሰደ ቦምብ ነው ቢሉም ቅሉ በይፋ ግን፡ ባለሙያዎች አሁን እንዳረጋገጡትም፡ የ 43 ዲግሪዎች አንግል የሚሸፍን ስፍራ ላይ ኩሬ የሠራ ሜትዮሮይድስ / ሚትዮራይትስ ወይም ተወርዋሪ ኮከብ ነው።

በሰማይ ላይ የሚመላለሱ ልዩ ልዩ የሰማይ ሠራዊት ከዋክብት ተወርዋሪ ኮከብ ወይንም ሚትዮራይትስ/ ሜትዮሮይድስ የሚባሉት የሚባሉት ድንጋያማ አለቶች የኮሜትና አስትሮይዶች ቅሪቶች ናቸው። ኮሜትም አስትሮይድም ግዙፍ አለቶች ናቸው። እነዚህ አካላት ወደ መሬት ወይም ወደ ሌላ አካል ቀረብ ሲሉ እየተሰባበሩ፣ እየተሰባበሩ ይመጡና፤ መሬት በፀሐይ ዙሪያ ስትሽከረከር እነርሱን ስለምትስብ፣ ወደመሬት እየመጡ ብዙዎቹ ተቃጥለው ያልቃሉ።

የሚገርም ነው፤ ባለፈው ዓመት ላይ በዚህችው አኩሬ ከተማ የአንድ ዓመት ህፃን ልጅ በማምለኪያው ቦታ ተቀብሯል በሚል ያልተጣራ ወሬ ሰልፈኞች ሌላ የመናፍቃን ቸርች አቃጥለው ነበር ። ህፃኑ በቸርች ውስጥ ከእናቱ ጋር የታየው ከወር በፊት ሲሆን፤ ከቸርቹ ሳይወጣም በዚያው የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቶ ነበር።

___________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የዋልድባ ገዳም መነኩሴ አባ ሀብተወልድ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 30, 2020

እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በምህረት ተቀብሎ ከቅዱሳን ኅብረት ይደምርልን! አሜን!

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

በካቴድራልና መስጊድ ላይ የወደቀው መልአክ በረረ | በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ የእግዚአብሔር መልአክ ሠፈረ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 30, 2020

____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

፻፲፰ / 118ቀናት | ለማና አብይ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን እንደሚያግቱ አስቀድመው ጠቁመውን ነበር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 30, 2020

ሉሲፈራውያኑ ልክ ኮሮናን እንደሚፈጥሩ “ኮንታጂየን” የተባለውን ፊልም አስቀድመው እንደሰሩት፤ ሽብር ፈጣሪዎቹ የሉሲፈራውያኑ ወኪሎችም ከዓመት በፊት በደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ያሰቡትን ዲያብሎሳዊ ዕቅዳቸውን አስቀድመው ነግረውን ነበር። እንደተለመደው፡ እንደ እባብ በለሰለስ መልክ!

የእነዚህ ምስኪን እህቶቻችን መጥፋት ጉዳይ ለቅንጣት እንኳን ሳያሳስባቸውና በክርስቲያኖችም ላይ የሚካሄደው ሽብር ትንሽ እንኳን ሳይከነክናቸሁ አሁን ከኮሮና ጋር በተያያዘ ለዚህ ፀረኢትዮጵያ አውሬ መንግስት የገንዘብ መዋጮ ለማሰባሰብ ብቅ ብቅ ያላችሁ ከሃዲዎች ሁሉ በሳሙና የታጠባችሁትን እጃችሁን ኮሮና ትኮርኩርባችሁ!!! እንዴት ሰው ለልጆቹ አጋችና ገዳይ ድጋፍና ገንዘብ ይሰጣል? ወራዶች! ውዳቂዎች! አንድ ኦሮሞ ወይም እስላም ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞና እስላም ላልሆኑት ክርስትያን ኢትዮጵያውያን መጨፍጨፊያ ይሆን ዘንድ መሣሪያ መግዢያ ላይ ሊውል የሚችል ገንዘብ ለማሰባሰብ እንዴት ይነሳሳል? ምን ዓይነት መርገም ነው?! በየትኛው መንፈስ ቢለከፉ ነው? በዋቄዮአላህ?

 

_________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መምህር ገብረ መስቀል | ኮሮና ስትጠፋ እነዚህ ምልክቶች ይታዩናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 30, 2020

___________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Health, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ካቶሊኮች መሰከሩ | ጣልያን የዋቄዮ-አላህ ጣዖት አምልኮን በመፍቀዷ የኮሮና መቅሰፍት መጣባት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 29, 2020

👉 ፓቻማማ + አቴቴ + ሺቫ

ይህ የጣልያን አሳዛኝ ሁኔታ የሚያስተምረን ነገር ቢኖር ከተመሳሳይ መቅሰፍት ለመዳን መስቀል አደባባይ ላይ የተተከሉትን የኢሬቻ ዛፎች ዛሬውኑ ቁረጡ። አዲስ አበባ፣ ደብረዘይት፣ ናዝሬት መላዋ ኢትዮጵያ ከዋቄዮ አላህ፣ ከኢሬቻ ቃልቻ ቆሽሻ መንፈስ በፍጥነት መጽዳት እንዳለባቸውና መመለክና መፈራት ያለበት ብቸኛ አምላክ እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ነው። በመሰቀልደመራ ወቅት በመስቀል አደባባይ ሲፈረግጥ የነበረው በሬ እኮ እንደ አንድ ምልክት ሊሆነን በተገባ ነበር።

ዋቄዮአላህ የፈጠራቸው ሴት አማልክት በአፍሪቃ /በኦሮሞዎቹ አቴቴ፣ በደቡብ አሜሪካ አማዞናስ ዙሪያ ፓቻማማበህንድ ሺቫ ከእነ ሦስት ልጆቿ/ቹ፤ ሳትቫ፣ ራጃስ፣ ታማስ። ሁሉም የአልላት፣ አልኡዛ እና አልማናት አቻዎች መሆናቸው ነው።

የጨረቃው አምላክ አላህከፀሐይዋ አምላክ ጋር ተጋብቶ ያስገኛቸው ልጆች በአንድነትም “የአላህ (ሴት) ልጆች” የተባሉ ሦስት አማልክት ስምም፦

👉 አልላት

👉 አልኡዛ

👉 አልመናት

ነበር፡፡

👉 ..አ ጥቅምት 4 ቀን 2019 .. – ጣዖት አምልኮ ሥነስርዓት በቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስኮ እና ሌሎች ቀሳውስት በቫቲካን የአትክልት ስፍራዎች ላይ ያካሄዱት የዛፍ ተከላ ሥነስርዓት።

***በዓላቱ – መስከረም/ጥቅምት ላይ ተከታትለው ይውላሉ***

(ኢሬቻ + ሺቫ(ሙሩጋን) + ዱርጋ (ሴት የዛፍ አምላክ) + ፓቻማማ + ሃሎዊን)

በአምልኮ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከአማዞን የመጡ ሰዎች ሁለት ከእንጨት የተሠሩ እርጉዝ ሴቶች ሐውልቶች(ፓቻማማ)ጳጳሱ ፊት ተንበርክከው ሲያመልኩ ይታያሉ።

በዛፍ ተከላ ሥነ ስርዓት ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የጣዖቷን ፓቻማም ሐውልት ባረኳት

👉 ካርዲናል በርክ ጳጳስ ፍራንሲስኮን ወቀሱ፦

ታዋቂው የአሜሪካ ካርዲናልና የቫቲካን ከፍተኛ ዳኛ ሬይመንድ በርክ፦ የደቡብ አሜሪካው የአማዞን ሲኖድ ያመጣት ጣዖት ፓቻማማ፣ እና የዛፍ ተከላ ሥነስርዓቱ አጋንንታዊ ኃይልን በቫቲካን አስገብተውብናል፤ ከፓቻማማ ጋር ሰይጣን ቤተ ክርስቲያን ገባ፤ ብቸኛዋ ወላዲተ አማልክ ድንግል ማርያም ናት። ከዚህች ጣዖት ጋር የመጣው የሰይጣን መንፈስ ከቫቲካን ይወገድ ዘንድ በክርስቶስ ስም መጸለይ ያስፈልጋል፤ የቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ከእነዚህ የክፋት ኃይሎች መጽዳት አለበት።ሲሉ ብሶታቸውን ገና ኮሮና ከመታወቋ በፊት አሰሙ።

👉 የእስልምና ጣዖት አምልኮ በቫቲካን

ሮማን ካቶሊኮች እ..አ በ1960ዎቹ በ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ላይ ለአንድ ዓለም ሃይማኖት ምስረታ መሰረቱን ከጣሉበት ዕለት አንስቶ በተቻላቸው መጠን “ክርእስላም”/ “Chrislam” የተሰኘ የእነርሱን ክርስትና እና እስልምናን ያጣመረ አዲስ ሉሲፈራዊ ሃይማኖት ለመመስረት እየታገሉ ነው።

👉 ይህ በቫቲካን ታይቶ አይታወቅም፦

አንድ የቱርክ ኢማም ንግግር አድርግ ተብሎ ሲጋበዝ፤ ክርስቲያኖችን እና አይሁዶችን የሚረግመውንና አልፋቲሃየተሰኘውን የእስልምና ፀሎትክፍል “ እንደ እባብ እየነዘረ ለቀቀው።

👉 ሁለተኛው የፊሊፒንስ ካቶሊክ ቄስ፦

ጣዖታቱ ፓቻማማ” + “አቴቴ” + “ዮጋ” + “ሃሪ ፖተር” + “አላህቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባታቸው ሰይጣን ዛሬ ብዙ ክርስቲያኖችን በአጋንንቱ ሊበክላቸውና ሊለክፋቸው በቅቷል።

እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ፡፡[ዘጸ ፳፥፪፡፫፟]

የሚለውን ትዕዛዝ በመሻራችን ነው ኮሮናየመጣችብን።

ቸሩ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከዋቄዮአላህ መንፈስ እና ከታዘዘው መቅሰፍት ሁሉ ይጠብቅልን! ለዘለዓለሙ አሜን!

👉 ገነ ማስተዋሌ ነው፦

ቪዲዮው ልክ የ2200 ደቂቃዎች እርዝመት አለው። ፳፪ / 22 ማክሰኞ ይውላል– ኡራኤል

በዚህ ዕለት ምን ይከሰት ይሆን?

___________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Health, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጋዜጠኛ ያየሰው በዚህ ቪዲዮ ነው የታሠረው | የመሀንዲስ ስመኘው ደም ዳግማዊ ቃየል አብዮትን ይጣራል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 29, 2020

[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፬፥፰፡፲፩]

ቃየልም ወንድሙን አቤልን። ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም። እግዚአብሔርም ቃየልን አለው። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ። አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።

ከዳግማዊ ግራኝ፣ ዳግማዊ ቃየል አህመድ አፍም ልክ የቃየልን ዓይነት አነጋገር በተደጋጋሚ በመስማት ላይ ነን፦

👉 አንድ ስመኘው በቀለ የሚባል ሰው ሞተ…አልውቀውም እኮ…”

👉 እኔ ቤተ ክርስቲያን አላቃጠልኩም: ካህናትን አልገደልኩም: ግፍ አልሰራሁም ስለዚህ ይቅርታ አልጠይቅም

👉 አላየሁም አልሰማሁም!” (ለገጣፎ ለይ የድሆች ቤት በጠራራ ፀሀይ በቡልዶዘር ሲፈራርስና ሲደረመስ)

👉 እኔ የከተማ አስተዳዳሪ አይደለሁም”

___________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በኢትዮጵያ ያገለገሉ የመጀመሪያው የካቶሊክ ኤጲስ-ቆጶስ በኮሮና ሞቱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 28, 2020

ጣልያናዊው ኢጴስቆጶስ “አቡነ አንጄሎ ሞረሺ” ይባሉ ነበር። በደቡብ ኢትዮጵያ በዲላ እና ጋምቤላ ያገለገሉ ሲሆን ወደ ጣልያን ከተመለሱ በኋላ ነበር በኮሮና ቫይረስ የተያዙት። ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

የሚያሳዝን ነው፤ እስከ አሁን በአጠቃላይ ፷/ 60 የካቶሊክ ቀሳውስት በኮሮና ሞተዋል፤ ግን ለምን ጣልያን? ለምን ካቶሊኮች፣ ለምን ፕሮቴስታንትና ሙስሊም በሆኑት ሃገራት? እንግዲህ እስከ አሁን በይብለጥ እየተጠቁ ያሉት እንደ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዊዲ አረቢያና ቱርክ የመሳሰሉት ሙስሊም ሃገራት፣ እንደ ጣልያን፣ ስፔይን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ብሪታኒያ እና ዩ.ኤስ አሜሪካ የመሳሰሉት የካቶሊክ እና ፕሮቴስታንት ሃገራት ናቸው።

ግብዝነት እንዳሆንብን እና በይበልጥ እንዳይፈታተነን መጠንቀቅ ቢኖርብንም፤ አሁን ባለው መጠይቅ ያለብን በአውሮፓ እንኳን ለምን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በሆኑት ግሪክ፣ ቆጵሮስ ሩሲያ፣ ጆርጅያ፣ አርሜኒያ፣ ቡልጋርያ፣ ሩማኒያ ወይም ሰርቢያ እስካሁን የኮሮና ሰለባ የሆነ ሰው የለም። ለምን? እንዴት?

ለወገኔ እንደ ማጽናኛ የምለው በተቀደሱት የኢትዮጵያ ተራራዎች እንደ አዲስ አበባ ከባሕር ከሁለት ሺህ ሜትር በላይ ከፍታ ባላቸው ቦታዎች ኮሮና ቫይረስ ድርሽ የማለት አቅም ያለው አይመስለኝም። በተጨማሪ በእነዚህ ቦታዎች ወባ አለመኖሩ የሚጠቁመን ነገር አለ።

_______________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Health, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »