[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፫፥፲፭]
“የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።”
እግዚአብሔር ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ሁሉንም ይጠብቃቸው። የፍጻሜ ዘመን ላይ ደርሰናል፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢታዊ ምስክርነት የፍጻሜ ዘመን ቃጭል እንደሆነ እያየን ነው።
የኮሮና ቫይራስ ክስተት ባስከተለው ስጋት በቻይና፣ በደቡብ ኮሪያ፣ በጣልያን ዓብያተ ክርስቲያናት በሮቻቸውን ዘግተዋል፤ የተለመደውን የሰንበት አገልግሎት ሁሉ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ይህን የማንቂያ ደወል ስነ ሥርዓት ስመለከት ብልጭ ብሎ የሚታየኝ ዲያብሎስ በዚህ ሁሉ ብርሃን እንዴት ቅጥል እንደሚል ነው። ከሳምንታ በፊት በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን የተከሰተው ይህ ነበር። “ይህች ዓለም የኔ ነች” ብሎ የሚያምነው ዲያብሎስ አይተኛም፣ መሸነፍን አይወድም፤ ዛሬም በንዴት እንዳጓራ ነው፤ ስለዚህ እንዲህ የመሳሰሉትን የፍቅር፣ የሰላምና የብርሃን መድረኮችን፣ እንዲሁም ክርስቲያናዊ አገልግሎቶችን ሁሉ ከቤተ ክርስቲያን ለማራቅ የተቻለውን ሁሉ ይሞክራል።
ቅዱስ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፡፡” ፣ “ከእኔ በኋላ የሚመጣው በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ያጠምቃችኋል”፣ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ” እያለ ምሥጢራትን / ምስጢረ ጥምቀት፣ ምስጢረ ንስሐን እና ምስጢረ ቁርባንን / እንድንካፈል ያስተምረናል፡፡
ጥምቀት፣ ቁርባን፣ ንስሐ ስንት መንፈሳዊ ሀብትና ጸጋ እንደሁም ከፍ ያለ የእግዚአብሔር ልጆች ክብር ስለሚሰጡን በተለይ በአሁኑ ጊዜ ተቀዳሚዎቹ የዲያብሎስ ጥቃት ዒላማዎች ናቸው። ባሕረ ጥምቀተን በመከልከል፣ የጥምቀት በዓልን በመተናኮል፣ ፀበላቱንና የሕይወት ህብስትን በመመረዝ፣ ብሎም ለንስሐ የተዘጋጁትን የክርስቶስ ልጆች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በመግደል በፀረ–ቤተ ክርስቲያን ዘመቻው ዲያብሎስ ምን ያህል ርቆ ለመሄድ እንደበቃ ዓይናችን እያየው ጆሮአችንም እየሰማው ነው።
በድጋሚ እግዚአብሔር ይጠብቀን እንጂ በቀጣዩና በቅርቡ ዲያብሎስ አውሬው በሃገራችን ሊፈጽመው ያቀደው ክስተት እርሱን የማይቀበለውንና ለእርሱ የማይሰግድለትን ሕዝበ ክርስቲያኑን ከቤተ ክርስቲያን ማራቅ ለዚህም እንደ ኮሮና ቫይረስ የመሳሰሉትን ተላላፊ በሽታዎች ከማሰራጨት ጋር የተያያዘ ነው። ልክ ዛሬ በቻይና፣ ደቡብ ኮርያ እና ጣልያን እንደሆነው በሃገራችንም ዓብያተ ክርስቲያናት በሮቻቸውን የሚዘጉበት፣ የሰንበት ቅዳሴዎች የሚቋረጡበትና እነደእነዚህ የመሳሰሉት ድንቅ “የማንቂያ ደወል መርሀ ግብራት” የሚቆሙበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። እግዚአብሔር እስከፈቀደልን ድረስ እንዲህ በትጋት እንቀጥልበታለን፤ ነገር ግን ለሁሉም ነገር አስቀድመን ብንዘጋጅ ጥሩ ነው!
የሚገርም ነው፤ “የማንቂያው ደወል መርሐ ግብር” በብዛት በዓርብ ዕለት ነው የሚካሄደው። ይህም በተጨማሪ ትልቅ “የማንቂያ መልዕክት” ይኖረዋል። በዚህ ዕለት የአዲስ ኪዳን ሥርዓት ክቡር ደሙ የፈሰሰበት የሕይወት ህብስት ቅዱስ ሥጋው የተቆረሰበት ዐረፍተ ማእከል የተናደበት እጸ መድኃኒት ቅዱስ መስቀሉ ተሰጠን። የክርስቶስ ተቃዋሚው፣ የመስቀሉ ጠላት አውሬው ግን የሚሰግዱለትን ልጆቹን (ሙስሊሞችን) በየመስጊዱ በዚሁ ዕለት ለመሰብሰብ ሆን ብሎ ይህን ዓርብ ዕለት መርጦታል። የእኛ የመንቂያ ቀን አርብ የእረፍት ቀን ሰንበት፤ የአውሬው “የዕረፍትና” ድል የተነሳበት ቀን ዓርብ ነው።
2012 – የኢትዮጵያ ግመሎች – ሳውዲ አረቢያ – ኮሮና ቫይረስ
በነገራችን ላይ፤ ኮሮና ቫይረስ አሁን ሁላችንም እንደሰማነው በቻያና መቀስቀሱን ነው። ይህም ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። ነገር ግን ኮሮና ቫይረስ የጀመረው ከሰባት ዓመታት በፊት፡ በአውሮፓውያኑ 2012 ዓ.ም ላይ በሳውዲ አረቢያ ነው (ከኢትዮጵያ ወደ ሳውዲ የተላኩ ግመሎች ያመጡት ፤ “MERS‐CoV / መርስ–ኮሮና–ቫይረስ”)። በፈረንጁም በኛም 2012 ብዙ ነገሮች ያየንበት / የምናይበት ቁልፍ ዓመት ነው።
_________________________________
Like this:
Like Loading...