ቫይረሱ ጋኔን መሆኑን አረጋገጠልን!
ምን እንደሆነ አላውቅም እስከ አለፈው ነሃሴ ወር ድረስ ምናልባት በወር አንዴ ብቻ ነበር እጣን የማጤሰው፤ ካለፈው ጥቅምት ወር አንስቶ ግን በቤትም በመሥሪያ ቤትም በጣም አዘውትሬ አጤሳለሁ፤ የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው፤ ቅዱስ መንፈስ ማድረግ የሚገባንንና የሚጠቅመንን ነገር ሳናስበውና ሳንዘጋጅበት እንድናደርገው ወደ በጎው ነገር ይመራናል።
ዛሬ ወደዚህ አይሁድ ቪዲዮ እንዴት እንደገባሁ ሁሉ አላውቅም፣ ያውም እጣንን በሚመለከት የገባሁበት ገጽ አልነበረም ፤ ግን ያው! ለኮሮና ጋኔን መፍትሄ ይሆናሉ ብዬ ሳስባቸው ከነበሩት ከጸበል፣ ከጸሎት ጎን እጣን እና ከርቤ እንደሚኖሩበት አረጋገጠለን። አሁን በዚህ በጣም እርግጠኛና ደስተኛ ነኝ።
ደካሞችና ምስጋና ቢሶች ሆነን ነው እንጂ አምላካችን እኮ የሚጠቅሙንን ነገሮች ሁሉ ሰጥቶናል፤ ጸበሉንም፣ ጸሎቱንም፣ እጣኑና ከርቤውንም በነጻ ሰጥቶናል። እጣንና ከርቤ ከወርቅ በላይ የሆኑበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ለብዙ በሽታዎች ፈውስ እንደሆኑ ሳይንሱ ሳይቀር እያረጋገጠልን ነው። Seeing the Unseen of the Combination of Two Natural Resins, Frankincense and Myrrh
እጣኑን በአግባቡ እናጢስ፤ ወገኖቼ፤ ነገር ግን ከተለመደው የቡና ስነ ሥርዓት ወቅት፣ በተለይ ከኦጋዴን እና አረብ ዕጣኖች ጋር አብሮ ማጤሱን ዛሬውኑ ማቆም አለባችሁ! አባቶች ይህን አስመልክቶ አንድ ይበሉን!
አየን አይደለም?! ጠላት ዲያብሎስ ለብዙ ሳምንታት በቂ የኮሮና ቫይረስ በአውሮፕላን እንዲረጭ ካደረገ በኋላ ወሮበላው መንግስት “በረራዎችን አቁሜአለሁ ፣ ይቅርታ ቅብጥርሴ” አለን። ቫይረሱ ልክ እንደ አንበጣ እስኪፈለፈል የሁለት ሳምንታት ጊዜ ይወስድበታል ተብሏል። ስለዚህ አባቶች ልክ እንደ ጆርጂያ ኦርቶዶክስ አባቶች በተለይ አዲስ አበባን በመኪና እና በሄሊኮፕቶር እየዞሩ ዛሬውኑ ደጋግመው ጸበል ቢረጩና እጣን ቢያጤሱ ትልቅ ሥራ ይሆን ነበር። በተለይ ምዕመናን ለቅዳሴ የማይመጡ ከሆነ ይህ መደረግ አለበት። ቀዝቃዛዎቹ የጉንፋን ወራት ከመጀመራቸው በፊት አስቀድሞ መደረግ ያለበት አንዱ ተግባር ይህ ሊሆን ይገባል።
UPDATE
የመንፈስ ቅዱስን ሥራ እያየን ነው፡ ወገኖቼ? ዋው! የሚገርም ነው፦ ያው መምህር ጳውሎስም እንዲህ ይለናል፦
“የማዕጠንት ጊዜ ነው፤ ማዕጠንት ጥሩ ነው፤ በሽታ የሚያርቅ ነው፤ እጣኑንን እያሸተታችሁ…ካህናት በየቤቱ በመዞር ጸሎተ ማርያም እየደገሙና ማዕጠንት እያደረጉ ቢያልፉ በሽታው ያልፋል …ከተማው ይታጠላንል አስፈላጊ ከሆነ”።
ወደ እዚህ እንግባና ሙሉውን እናዳምጥ፦
“አስደናቂ ስብከት በሽታው የሚርቀው በማዕጠንት ነው መምህር ጳውሎስ መልካሥላሴ ክፍል፪
ቃለ ሕይወት ያሰማልን!