Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2020
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for March 4th, 2020

የአባይ ጦስ | መለስን ካስገደሉት ነገሮች አንዱ ይህ ኢንተርቪው ነበር | የእስራኤል ቴሌቪዥን እንዳየው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 4, 2020

ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር ማድረግ የለባትም፤ ለምን? ኢትዮጵያዊ መንግስት በሚኒሊክ ቤተ መንግስት ቢኖር ኖሮ ለግብጽ፡ “እኔ የምልሽን ተቀበይ፤ የአባይን ውሃ ከፈልግሽ አንድ ትሪሊየን ዶላር በዓመት ክፈይ” የማለት ተገቢ ድረት ይኖረው ነበር።

ብዙ “ኢአማንያን አብዮተኞችን” ካፈራው የጄነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት የተመረቀው መለስ ዜናዊ ብዙ ስህተቶች ሰርቷል፤ ነገር ግን ከስህተቱ ተምሮ ለሃገራችን ጠቃሚ አስተዋጽዖዎችን ሊያበረክት የሚችል ፖለቲከኛ ነበር፤ ለዚህም ነው ነቃ ሲል የተገደለው። ጠላቶቻችን፡ በተለይ ነጮች ለነርሱ ይሰራ የነበረውንና ከስህተቱ የሚማረውን አፍሪቃዊ መሪ በጣም ይፈሩታልና። ኢትዮጵያን የጎዳው መንግስቱ ኃይለ ማርያምና ኢትዮጵያን እየጎዷት ያሉት እነ ኢሳያስ አፈወርቂ እና አብዮት አህመድማ ያው ምንም ሳይሆኑ እየተሸለሙ በሕይወት አሉ። ምንም ዓይነት ኢትዮጵያዊነትን የማያንጸባርቀው፤ አብዮት አህመድ ሳይሆን ሙሴ መባል የነበረበት፤ ዛሬ ቢኖር ኖሮ መለስ ነበር ሙሴ ወይንም ከስህተቱ የተማረው ሙሴ ጸሊም ሊባል የሚገባው።

_________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ግራኝ አህመድና ለማ መገርሳ አቡነ ማትያስን ከሩሲያ ለማስመለስ ፕሬዚደንት ግርማን ገድለዋቸው ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 4, 2020

ኢትዮጵያ ሃገራችን በአደገኛ ከሃዲ ጨቅላዎች እጅ መውደቋን እያየን ነው።

በወቅቱ የተሰማኝ ይህ ነበር። ፕሬዚደንት ግርማ ባለፉት ስምንት ዓመታት ሁለት ጊዜ “ሞተዋል” መባሉን፤ የተዛባ የጤና እና እድሜ መግለጫ መውጣቱን እናስታውስ። በጊዜው የእነ አብዮት አህመድ የፌስቡክ እና የዩቱዩብ የመልስ ሮቦቶች ደጋግመው ሲጽፉ የነበሩት፦ “ፓትርያርኩ ለፕሬዚደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ቀብር መመለስ አለባቸው!” የሚሉትን የትችት ቃላት ነበር።

ዲያብሎስ እህትማማች የኦሮቶዶክስ ማሕበረሰባት እንዲተባበሩና አንድ እንዲሆኑ አይሻም። ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ጥንታዊ የሆነ ታሪካዊ ግኑኝነት ቢኖራቸውም (የሥነ ጽሑፍ አምላኩአሌክሳንደር ፑሽኪን፣ ደራሲው አሌክሳንደር ቡላቶቪች፣ ድንቁ አሳሽና ከፍተኛ የሰብል ባለሙያው ኒኮላይ ቫቪሎቭ፣ ዛር ኒኮላስ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የነበረው ፍቅር) እስከ አሁን ድረስ አንድም የሩሲያ/ሶቪየት መሪ እና የሩሲያ ኦርቶዶክስት ተዋሕዶ ፓትርያርክ ኢትዮጵያን ጎብኝተው አያውቁም። ወደ ግብጽ አዘውትረው ሄደዋል፤ ወደ ኢትዮጵያ አንዴም!

ኤዶማውያኑ ምዕራባውያን እና እስማኤላውያኑ ምስራቃውያን ሃገራት በሉሲፈራዊ ሥርዓተ የሚመራውን የአንድ ዓለም መንግስት ለመመሥረት በቅድሚያ ጥንታዊቷን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለማስወገድ እየታገሉ እንደሆነ በግልጽ እያየነው ነው። ዓላማቸውም አሁን የተደበቀ አይደለም።

ኢትዮጵያን በመክዳት ለአረቦች እና ሶማሊያውያን መቀለጃ እንድንሆን ያደረገንን አመጸኛ ትውልድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እያገዘ ከፍተኛ ሚና ለመጫወት የበቃው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሪዚደንት የጂሚ ካርተር መስተዳደር ነበር። ይህን መስተዳደር ከጀርባ ሆነው ሲመሩት የነበሩት፡ እስከ ቅርብ ጊዜም የባራካ ሁሴን ኦባማን መስተዳደር የሚመሩት እርጉሙ የካርተር ብሔራዊ–ጸጥታ አማካሪ፡ ዜቤግኔው ብረዥንስኪ ነበሩ። እኚህ ሰው፡ ልክ እንደ ሄንሪ ኪሲንጀር በአፍሪቃውያን፣ በሩሲያውያን እና በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ነበራቸው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ አሁን እየተካሄድ ያለውን ጥቃት ለመረዳት በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ቀደም ሲል የፈጸሙትን ጽንፈኛ ተግባር ማየቱ ይጠቅመናል።

ዜቤግኔው ብረዥንስኪ ለምሳሌ የሚከተለውን በግልጽ ተናግረው ነበር፦

After the collapse of the USSR, the main enemy of the USA will be the Russian Orthodox Church.

ከሶቪየት ህብረት ውድቀት በኋላ የዩኤስ አሜሪካ ዋና ጠላት የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትሆናለች፡

We need a split of Orthodoxy and the breakdown of Russia, and Ukraine, where betrayal is the norm of public morality, will help us in this.

የኦርቶዶክስ ክፍፍል እና የሩሲያና ዩክሬይን መከፋፈል ያስፈልገናል ፣ እናም ክህደት የህዝብ ሥነ ምግባር በሆነበት ይህ በጣም ያግዘናል።

አዎ! በኦርቶዶክሶቹ ሃገራት በሩሲያና በዩክሬን መካከል የተፈጠረው ክፍፍል ወደ እኛም እየመጣ ነው። ሉሲፈራውያኑ፡“መጀመሪያ የኤርትራ ቀጥሎ የኦሮሚያ፣ ቆየት ብሎ የትግራይ፣ የወላይታ፣ የጋምቤላ ወዘተ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን መሥርቱ” በማለት ትዕዛዙን ከሰጡ ከሃምሳ ዓመታት በላይ ሆኗቸዋል።

አቡነ ማትያስ ከሩሲያ ጋር ለመቀራረብ መሞከራቸውን እነ አብዮት አህመድን ሥልጣን ላይ ያስቀመጡትን ሉሲፈራውያኑን አላስደሰታቸውም። ስለዚህ ኢትዮጵያን የሚጠቅሙትን ተቋማትን፣ ፕሮጀክቶችንና ግለሰቦችን ማጥቃት ይወዳሉ።

በደንብ ካስተዋልን፡ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በሚመለከት ግብጽን እና ኢትዮጵያን ለማደራደር ፍላጎት አሳይታ የነበረችው ሩሲያ ነበረች። ግብፅ አሜሪካ ታደራድረን በሚል ያቀረበችውን ሃሳብ የአብዮት አመራር ለይስሙላ አልቀበልም ማለቱ ይታወቃል። ብዙም ሳይቆይ ነገሮችን ማጨናገፍ እንደ ሆቢው አድርጎ የያዘው አብዮት አህመድና የግብፁ ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በሩሲያ፣ ሶቺ መገናኘታቸውን ተከትሎ ግራኝ አህመድ በህዳሴው ግድብ ግንባታ ጉዳይ በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ሦስተኛ ወገን ቢገባ ምንም ችግር እንደሌለው በመግለጽ በሚቀጥለው የህዳር ወር የድርድሩን መድረክ ወደ አሜሪካ እንዲዘዋወር በማድረግ ሩሲያን ለማግለል በቅቷል።

ሰሞኑን ከድርድሩ ለመራቅ እየተሞከረ እንደሆነ የተሰማው ዜና ከድራማና ጊዜ ከምገግዛት ውጭ ምንም ፋይዳና ትርጉም የለውም። ግራኝ አህመድ “እስኪመረጥና ህጋዊ እስኪሆን”፣ የታጠቁት ኦሮሞ ወንድሞቹ የህዳሴው ግድብ የሚገኝበትን “ቤኒ ሻንጉል” ተብሎ ልክ ለዚህ ዘመን የተፈጠረውን ክልል ለአረቦች ሲሉ ሙሉ በሙሉ እስከ ተቆጣጠሩ ድረስ እንጂ ኢትዮጵያውያን በደማቸው፣ በላባቸውና በገንዘባቸው የገነቡትን የህዳሲውን ግድብ ለግብጽ ሸጦታል። ይህ በስቅላት የሚያስገድል የክህደት ወንጀል እንደሆነ ከወዲሁ ይወቀው!

የድራማው ቅደም ተከተል፦

👉 ክፍል ፩

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የሞስኮና መላው ሩስያ ፓትርያርክ ክሪል ባደረጉላቸው ግብዣ መሠረት፣ ከ ግንቦት 7/ / 2010 / ፪ሺ፲ ዓ.ም፡ የአምስት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ። የኢትዮጵያና የሩሲያ ኦርቶዶክስ ዓብያተክርስቲያናት ፓትርያርካት ንግግር በአብዛኛው ያተኮረው ሙስሊሞች በአፍሪቃና እስያ ክርስቲያኖች ላይ እያካሄዱት ስላለው ጭፍጨፋ ነበር፤ በዚህም ሶማሊያን፣ ናይጀሪያንና ሰሜን አፍሪቃን በምሳሌነት ጠቅሰዋል። በሊቢያ ሰለተሰዉት ኢትዮጵያውያን ሰመዓታትም አውስተው ነበር።

👉 ክፍል ፪

ማክሰኞ ታህሣሥ ፱ /9 / ፪ሺ ፲፩/2011.ም – አቡነ ማትያስ በስድስት ወር ወስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞስኮ በረሩ። የፓትሪያሪኩ በረራ የመንግሥት አካላትን አበሳጫቸው። ለማ መገርሳ፤ “ፖለቲከኛ የሃይማኖት አባት” ብሎ ሰደባቸው። አቡነ ማትይስ ከአውሮፕላን ሳይወርዱ ከሞስኮ ወዲያው እንዲመለሱ ተደረጉ።

በወቅቱ የወጣ መረጃ፦

በቅርቡ የሃይማኖት አባቶች ከአቶ ለማ መገርሳ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት አቶ ለማ መገርሳ አንዳንድ ፖለቲከኛ የሃይማኖት አባቶችም አሉ በማለት የተናገሩት እኔን ነው። አቶ ለማ በቀጥታ ሰድቦኛል ብለው እንዳኮረፉ የሚነገርላቸው ቅዱስ ፓትሪያርኩ አባ ማትያስ የእነ አቶ ለማ መገርሳን ፊት አላይም፣ ከእንግዲህም ከእነሱ ጋር በአንድ መድረክ አብሬ አልቆምም በማለት ዛሬ ሥርዓተ ቀብራቸው በሚፈጸመው በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት በመቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ላለመገኘት ሲሉ ፓትሪያርኩ ወደ ሩሲያ በረራ ከጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ወደ ሩሲያ ሄደዋል ተብሎ ነበር። በወቅቱ በደረሰን መረጃ ደግሞ የፓትሪያሪኩ ድርጊት ያበሳጫቸው የመንግሥት አካላት በግልፅ ዛቻ በማሰማታቸው ፓትሪያርኩ በፕሬዘዳንቱ ቀብር ላይ ለመገኘት ፈጥነው መመለሳቸው ተሰምቷል። ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ ይሉሃል ይሄ ነው። በአውሮፕላን ሄደው ከአውሮፕላን ሳይወርዱ ተመለሱ ማለት ነው። ለአረጋዊ ሽማግሌ አባት ከአዲስ አበባ ሞስኮ፣ ከሞስኮ አዲስ አበባ ለረጅም ሰዓት ዓየር ላይ መቆየት ብዙም አይመከርም። ለጤናቸውም ጥሩ አይደለም የሚሉም አሉ።”

👉 ክፍል ፫

ታህሣሥ ፮ /6/፪ሺ፲፩ /2011 .ም – የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ (94)አረፉ።

የሞት ምክንያት በይፋ አልተገለፀም። ሥርዓተ ቀብሩም በ ረቡዕ ታኅሣሥ ፲/10 ቀን ተካሄደ።

👉 ክፍል ፬

ብልጭታ – ፰ ዓመታት ወደ ኋላ እንጓዝ – መጋቢት ፬ /፪ሺ፬ /4/ 2004 .ም ፕሬዚደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ አረፉ(88) ተብሎ እንዲወራ ተደረግ። የፕረዚዳንት ግርማ ሞት የወያኔን ባለስልጣናት አስደንግጧቸዋል የሚል ወሬ ተሰማ።

ግን ፕሬዚደንት ግርማ አልሞቱም ነበር፤ – ግን የታሰበው ለጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ነበር፤ አቶ መለስ

ነሐሴ ፲፬/፳ሺ፬/4/2004 .ም መሞታቸው ይፋ ሆነ።

በዚህም ግድያ ከባራክ ሁሴን ኦባማ፣ ከግብጹ ፕሬዚደንት ሙርሲ፣ ከሸህ አላሙዲን እና ደመቀ መኮንን እጆች ጎን የአብዮት አህመድ እጅ ይኖርበታልን?

______________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሳጥናኤል መንገዱን ከፍተው እኛ ላይ እንዲዘመትብን ያደረጉት “ኢትዮጵያ ሃገር ናት” ያሉን መሪዎቻችን ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 4, 2020

ያልተነገሩት የ24 ቀበሌ ኦርቶዶክሳውያን ጉዳቶች” በሚል ርዕስ በግሩም መልክ በተዋሕዶ ቴሌቪዥን የተቀነባበረና የቀረበ ቪዲዮ ነው። ወይዘሮ የሽን በጥሞና እናዳምጣቸው፤ ዓይኖቻቸውን ተመልከቱ የኔ እናት

ቤተ ክህነት ገዳዩን መንግስትንና ህገ-ወጡን የአዲስ አበባ መስተዳደርን ማክበር፣ መለመንና መማጸን ማቆም አለባት…. ደም የፈሰሰበትን ቦታ ወደዱም ጠሉም ለቤተ ክርስቲያን እንደሚሰጧት አትጠራጠሩግን እንዲከበሩ፣ እንዲመሰገኑ፣ እንዲወደዱና እንዲመረጡ ገና የክርስቲያኑን ልብ ማንጠልጠል አለባቸውአባቶችና ህፃናት አሁንም ተመርዘው እየታመሙ ነው፣ የተዋሕዶ ልጆች በሃገራቸው እንደ ሁለተኛና ሦስተኛ ዜጋ እንዲኖሩ እየተደረጉ ነው፤ ወጣት ሴት ተማሪዎች እየታገቱ፣ እየተደፈሩና እየተገደሉ ነውስለዚህ እነዚህን ገዳዮች ካባ ለማልበስ እንደቸኮላችሁት አህንም በስሜት ቀድማችሁ ለማመስገን እንዳትቸኩሉይቅርታ የማይደረግለት ከፍተኛ ሃጢዓትና ወንጀል ሠርተዋልና፣ ለመስራትም በመዘጋጀት ላይ ናቸውና!

ቀደም ሲል ሉሲፈራውያኑ እንዲ ብለው ነበር፦

“ኢትዮጵያውያን “ዶክተር” የተባለውን ማዕረግ ያክብሩታል ፤ ኢትዮጵያን ከፍ እያደረገ የሚያወራውንና የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ የሚጠራውን ወሬኛም ያደንቁታል ስለዚህ አንድ ተዋሕዶ ያልሆነና የማይታወቅ ቆለኛ “ኦሮሞ” ስልጣን ላይ እናውጣ እና እዚህ በእኛ እጅ የገቡትን የቀድሞውን ፓትርያርክና አዲስ አበባ የሚገኙትን ፓትርያርክ “እንዲያስታርቅ” የመጀመሪያው ሥራው እንዲሆን አድርገን እንስጠው፣ እመኑን ሙሴ ተመልሶ መጣ ብለው ካባ ያለብሱታል

_______________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: