[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፯፥፮|
“በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።”
ውሀችን / ጸበላችን ከመካ እና ውሀን ከተሞች የፈለሰውን የኮሮና ጋኔን ያርቅልናል!
እስኪ ይታየን፤ ከግብጽ እና አረቦች ጠላቶቻችንን ጎን በመሰለፍ የህዳሴው ግድብ እንዳይገነባ ፊርማዋን ያስቀመጠችው ጂቡቲ ንጹህ ውሀ ከኢትዮጵያ በነፃ ተሰጥቷታል። ኢትዮጵያን ለመውረር ያቀዱትን የኤዶማውያን እና እስማኤላውያን የጦር ሠራዊቶች በግዛቷ የምታስተናግደዋ ጂቡቲ ኢትዮጵያውያን የማይጠጡትን ንጹሕ ውሀ በነፃ ትጠጣለች።
ጥንታውያን ግሪካውያን ረጅም እድሜ የሚያስገኘው የመጠጥ ውሃ የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው በማለት ይናገሩ ነበር። ታዲያ ይህን ምስጢር ጠላቶቻችን ስለሚያውቁ ኢትዮጵያውያን ይህን እግዚአብሔር የሰጣቸውን ፀጋ አውጥተው እንዳይጠቀሙና ወደፊት እንገነባታለን ለሚሏት አዲሷ ዓለም ውሃው እንዳይነካባቸው ኢትዮጵያውያኑ ከሽንት ቤት ተጠራቅሞ የተጣራውን ውሃ ብቻ እንዲጠጡ ማድረግ አለብን ስላሉ ያው እነ ቆቃ ተገንብተዋል። እነዚህም የውሃ ማጠራቀሚያዎች ከላይም ከታችም እንደማይበከሉ የሚታወቅ ነገር የለም። የጣናው እንቦጭም ከአውሮፕላን ላይ ተረጭቶ የተተከለ የአትክልት አውሬ ነው።
በእሳቱ ለመጠረግ ችቦው ውስጥ በመግባት ላይ ያሉት የሃገራችን ጠላቶች በውሀው፣ በአየሩና በምድሩ ላይ ነው ጥቃት እየፈጸሙ ያሉት። ከሁሉም አቅጣጫ!
ለዘመናት ለኢትዮጵያውያኑ መንፈሳዊ እና ስጋዊ በጎነት፣ ጤንነትና ብልጽግና ብቸኛውን ሚና የምትጫወተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነች በየቦታው እየፈለቁላት ያሉት ጠበላት ምስክሮች ናቸው። ይህ ቀላል ነገር አይደለም፤ ይህን በተለይ በያዝነው ዘመን በጣም ክቡር የሆነውን የጸበል ውሃ ነው ጠላቶቻችን ሊነጥቁን የሚሹትና። አሁን ለተጀመረው የፀረ–ቤተ ክርስቲያን ዘመቻ አንዱ ምክኒያትም ይህ ነው። ኢትዮጵያዊው ጤናማ እንዲሆን፣ የታመመውም እንዲፈወስ አይፈልጉም። “በዓለማችን በጣም ውድ የሆነው ነገር ለእኛ ብቻ የተቀደሱት ተራራዎች ውስጥ ተቀብሮ ይቆይልን” ይላሉ ፤ ውሀ ኬኛ!
በአንድ ወቅት ከግብጽ የመጡ የኮፕት ቤተ ክርስቲያን አባቶች ከእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ጠበል ወደ ሰላሳ በርሚል የፀበል ውሃ በጭነት መኪና አስጭነው ወደ ግብጽ ሲወስዱ እና በሌላ በኩል ብዙ የእኛ ሰው ይህን በእጁ የያዘውን ወርቅ ለመጠቀም አለመፍቀዱን ሳይ በጣም ነበር ያዘንኩት። የሚጠመቁ መሀመዳውያንን እንኳን ደስ እያለኝ በየጊዜው አይቻለሁ፤ ግን አንዳንዶቹ ከተፈወሱና ከዳኑ በኋላ የፈወሰቻቸውን ቤተ ክርስቲያን ያጠቋት ዘንድ የዲያብሎስ አባታቸውን ፍላጎት ለመፈጸም ተመልሰው ይመጣሉ።
ይህ ዘመን ሃገራችን ያጠባቻቸውን ጡቷን ሊነክሱባት የሚሹ ከሃዲዎች የበዙበት ዘመን ነው።
በቤተ ክርስቲያን ላይ ጦርነቱ ተጧጥፏል፣ ጠላቶቻችን እግዚአብሔር በሰጠን ጤናማ ውሃችን ላይ ዓይናቸውን አሳርፈዋል፣ ጥምቀተ ባሕር መውረስ ጀምረዋል፣ በጠበላቱ አቅራቢያ የኬሚካል ፋብሪካዎችንና ጋራጆችን ይሠራሉ (አያት፣ ነፋስ ስልክ፣ ፉሪ፣ ለጋሃር፣ ቃሊቲ ወዘተ) ሰው አምላኩ ከሰጠው ንጹህ ምንጩ ሳይሆን “ሃይላንድ” በተሰኘው ላስቲክ ምናምኑን ቀምመው ያዘጋጁለትን ውሃ ካልቻለ በኬሚካል የተበከለውንና የደፈረሰውን ውሃ ብቻ እንዲጠጣ አማራጩን ሰጥተውታል።
ታዲያ ይህ ትልቅ፤ እጅግ በጣም ትልቅ ወንጀል አይደለምን?! በደንብ እንጅ! አዎ! አባታችን አባ ዘ–ወንጌል “ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ ናቸው!” ሲሉ 100% ትክክል ናቸው።
_________________________________
Like this:
Like Loading...