Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2020
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for March 28th, 2020

በኢትዮጵያ ያገለገሉ የመጀመሪያው የካቶሊክ ኤጲስ-ቆጶስ በኮሮና ሞቱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 28, 2020

ጣልያናዊው ኢጴስቆጶስ “አቡነ አንጄሎ ሞረሺ” ይባሉ ነበር። በደቡብ ኢትዮጵያ በዲላ እና ጋምቤላ ያገለገሉ ሲሆን ወደ ጣልያን ከተመለሱ በኋላ ነበር በኮሮና ቫይረስ የተያዙት። ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

የሚያሳዝን ነው፤ እስከ አሁን በአጠቃላይ ፷/ 60 የካቶሊክ ቀሳውስት በኮሮና ሞተዋል፤ ግን ለምን ጣልያን? ለምን ካቶሊኮች፣ ለምን ፕሮቴስታንትና ሙስሊም በሆኑት ሃገራት? እንግዲህ እስከ አሁን በይብለጥ እየተጠቁ ያሉት እንደ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዊዲ አረቢያና ቱርክ የመሳሰሉት ሙስሊም ሃገራት፣ እንደ ጣልያን፣ ስፔይን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ብሪታኒያ እና ዩ.ኤስ አሜሪካ የመሳሰሉት የካቶሊክ እና ፕሮቴስታንት ሃገራት ናቸው።

ግብዝነት እንዳሆንብን እና በይበልጥ እንዳይፈታተነን መጠንቀቅ ቢኖርብንም፤ አሁን ባለው መጠይቅ ያለብን በአውሮፓ እንኳን ለምን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በሆኑት ግሪክ፣ ቆጵሮስ ሩሲያ፣ ጆርጅያ፣ አርሜኒያ፣ ቡልጋርያ፣ ሩማኒያ ወይም ሰርቢያ እስካሁን የኮሮና ሰለባ የሆነ ሰው የለም። ለምን? እንዴት?

ለወገኔ እንደ ማጽናኛ የምለው በተቀደሱት የኢትዮጵያ ተራራዎች እንደ አዲስ አበባ ከባሕር ከሁለት ሺህ ሜትር በላይ ከፍታ ባላቸው ቦታዎች ኮሮና ቫይረስ ድርሽ የማለት አቅም ያለው አይመስለኝም። በተጨማሪ በእነዚህ ቦታዎች ወባ አለመኖሩ የሚጠቁመን ነገር አለ።

_______________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Health, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዲያብሎስ ኮሮናን የፈጠረው ክርስቲያኖች ከቤተ ክርስቲያን እንዲርቁ ለማድረግ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 28, 2020

የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እድገታቸው በ “ተሽከርካሪ” ላይ መሠረት እንደማድረጋቸው ፣ የፍልስፍናዊ፣ ርዕዮት ዓለማዊ ፣ ማሕበረሰባዊ፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎቻቸው ሁሉ በፈላስፋው ጆርጅ ሄጌል ጽንሰሃሳብ ላይ፤ ሁሉም ነገር፦

ችግር – እርምጃ – መፍትሔ

ላይ የተመሠረተ ነው።

ወረርሽኙን በአየር ላይ ይበትናሉ ፤(ከአውሮፕላን፣ ሳተላይት፣ ማይክሮዌቭ የሞባይል አንቴናዎች (3G, 4G,5G) “! ኡ! !” ተራራቁ፣ አትሰባሰቡ፣ ዝጉ” የሚሉ መግለጫዎችን በየቀኑ ይሰጣሉ ፤ ከዚያም “በቃ መድኃኒት ተግኝቷል ይህን ኪኒን ውሰዱ፣ ይህን መርፌ ተወጉ” ይላሉ።

ወረርሽኙ ገና ባልገባባት ኢትዮጵያ ደግሞ የሉሲፈራውያን አሽከሮች በተጋላቢጦሽ “መፍትሔ – እርምኛ – ችግር” የሚለውን ሃሳብ ተከትላለች። ገና አንድም ሰው ሳይሞት “መድኃኒት ተገኝቷል” ተብሎ እንዲታወጀ ተደርጓል። እንግዲህ እንደ “ሀኪም አበበች” የተባለችውን ሴትዮ ዛሬ ቀድመው ብቅ በማለት“መፍትሔውን” እንዲያቀርቡ ላለፉት ዓመታት ሥራችን ብለው በሜዲያ ሲያስተዋውቋቸው ነበር። ይህ ሁሉ እንግዲህ ሰው መፍትሔውን ከቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ፣ ፀበላትና ማዕጠንት እንዳያገኝ፣ ቤተ ክርስቲያንን እንዲሸሽ ለማድረግ ነው። የእነ “ሀኪም አበበች” መድኃኒት ውጢታማ ካልሆነ ሰው አሁን ከቤተ ክርስቲያን ያሉ መፍትሔዎችን ለመቀበል ተለማምዷልና እነርሱ ላዘጋጁለት የ666 ክትባት ክንዱን እንዲያዘጋጅ ሰው ይገደዳል ማለት ነው።

እስኪ ተመልከቱ፦ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን በየቦታው ሲታረዱ፣ ወጣት ሴት ተማሪዎች እልም ብለው ሲጠፉ፣ የተጨነቁ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየበርሃው፣ ባሕራቱና ባዕድ አገራቱ ኮንቴነር ውስጥ ታፍነው ሲሞቱ አንዴም የሃዘን መግለጫ ለመስጠት ብቅ ብሎ የማያውቀው ግራኝ አብዮት አህመድ አሁን ፕሬዜደንት ትራምፕን በመኮረጅ የሚወዳት ካሜራ ፊት ዱቅ ማለቱን መርጧል። ሰውየውን ላየውና ልሰማው አልሻም፤ በጣም ነው የሚያቅለሸልሽኝ፤ ግን ለመሆኑ መግለጫውን ለብቻው እየወጣ ነው የሚሰጠው ወይስ እንደ ትራምፕ ማብራሪያዎችን የሚሰጡ ባለሙያዎች አብረውት አሉ?

አብዮት አህመድ “ቤተ ክርስቲያናትን እናዘጋለን!” አለ፤ ተብሏል። ለብልግና ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳዎችን ለማካሄድ የሚሰበስብ ሰው፣ ብር ለማሰበሰብ ሺህ ሰዎችን በአዳራሽ ውስጥ የሚያጉር አስመሳይ ሰው አሁን ለምዕመናን ደህነነት አስቦ? ፣ “አማራና ትግሬ” የተባሉት ኢትዮጵያውያን እርስበርስ እንዲተላለቁ ሌት ተቀን የሚያውጠነጥን መሰሪ ግለሰብ የኢትዮጵያውያን ሕይወት አሳስቦት? ጨምላቃ ሌባ፣ የዲያብሎስ ልጅ! እንደ ግብረሰዶማዊው ግብረአበሩ ኢማኑኤል ማክሮን በፈረንሳይ በየሳምንቱ ሲካሄዱ የነበሩት ዓይነት ተቃውሞዎች ከማየትና ከመስማት አረፍ ይላል። አሁን ፖሊሶችን ወደ ቤተ ክርስቲያን በመላክ ምዕመናን በመግደል ቤተ ክርስቲያንን ማደናገጥና ማሸማቀቅ አያስፈልገውም፤ “ህገ መንግስቱ ቤተ ክርስቲያን እንድናዘጋ ያዘናል” ማለት ይደፍራልና። “እናንተን ብቻ አይደለም፣ ያው መስጊድንም አዘግቻለሁ” ይለናል። መስጊድ? እስልምና ኢአማኒያዊ የክርስቶስ ተቃዋሚ አምልኮ ነው፤ ክርስትና እስከተወገደለት ድረስ ሌላው ነገር ሁሉ ግድ የለውም፤ ሌላ ምንም የሚያጣው ነገር የለም።

የክርስቶስ ተቃዋሚው ጥልቅ የምድር ውስጥ ዋሻዎቹ ውስጥ በሚገኙት የምርምር ላብራቶሪዎች ውስጥ እንደ ኮሮና የመሳሰሉትን አጋንንት ማምረት ጀምሯል። ቪዲዮው ላይ የተጠቀሰው ፊልም አሁን የምንገኝበትን ዘመነ ወረርሽኝ በደንብ አድሮ ይገልጸዋል። ፊልሙን ገና አሁን ማየቴ ነው፤ ይገርማል፡ የዓለም የጤና ድርጅት ተወካይ ሆኖ እንዲተዋናይ የተደረገው ጥቁሩ ተዋናይ “Joseph Anthony Foronda” ነው፤ ገና ከዘጠኝ ዓመት በፊት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ማስተዋወቃቸው ነበር ማለት ነው።

ለማንኛውም ይህን ቫይረስ የፈጠሩ ሉሲፈራውያን ተቀዳሚ ዒላማቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት። በየትኛውም የዓለማችን ሃገር እንደ ኢትዮጵያ ዜጎች ለእምነታቸው በብዛት የሚሰባሰቡባት ሃገር የለችም። በየቤተ ክርስቲያኑ በየገዳማቱ ለቅዳሴ፣ ጸበል ለመጠመቅና በዓላትን ለማክበር እንደ ኢትዮጵያ በዝተው የሚሰባሰቡባት የዓለማችን ክፍለ ሃገር የለችም። ምዕመናን በየቤተ ክርስቲያናቱ ሲሰባሰቡ የሚፈነጥቀውን ኃይል (Vibration) በቴክኖሎጂያቸው ሆነ በሌላ መልክ ደርሰውበታል፣ ከገዳማቱ የሚወጣውን ከፍተኛ ኃይል በትሪሊየን ፒክሰል/ ነጠብጣቦች ቁልጭ አድርገው የማንሳት ብቃት ባላቸው ሳተላይቶቻቸውና ቴሌስኮፖቻቸው ለማየት በቅተዋል።

ስለዚህ ሉሲፈራዊውን የአንድ ዓለም መንግስት ለመመስረት እንቅፋት የሆነችባቸውን ጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማጥፋት እንደሚኖርባቸው አምነዋል። ዋናው ዓላማቸው ክርስቲያኑ ከቤተ ክርስቲያን እንዲርቅና ተሰባስቦ እንዳይጸልይ፣ እንዳይባረክ፣ በጸበል እንዳይድን ነው። “የክርስቶስ ተቃዋሚው ቀጣዩ ሥራ ሕዝበ ክርስቲያኑ ምስጢረ ጥምቀት፣ ምስጢረ ንስሐን እና ምስጢረ ቁርባንን እንዳንካፈል ማድረግ ነው።” በማለት ላለፉት ዓመታት ስጽፍ ነበር። ያው! አሁን ጊዜው ደረሰ!

አሁን እንደ ዱሮው ፋብሪካዎችን፣ ሱቆችና መጠጥ ቤቶችን አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት አቅራቢያ ሄደው መስራት አያስፈልጋቸውም ፤ ወረርሽኙን ተደብቀው አየር ላይ መርጨት የሚችሉበት ጊዜ ነው።

የፈለጉትን ቢያቅዱና ቢያደርጉም ከቤተ ክርስቲያን በፍጹም መቅረት የለብንም!

_____________________________________

Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: