የአማሌቃዉያን ጂሃድ በአርሲ | መሀመዳውያን በነጌሌ ከተማ የሚገኘውን መስቀል ማየት የለብንም ብለው አነሱት
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 5, 2020
መምህር ዘመድኩን በቀለ እንዳካፈለን፦
• ነገ የአንገት ማዕተብህን ካልበጠስክ የሚልህ አራጅ መምጣቱን ምልክቱ ይኸው።
ወሀቢዮቹ የአርሲ ነገሌ ምእመናንን በመጨረሻም በሕግ ሽፋን መስቀላቸው እንዲነሣ ተደርጓል። ህዝቡም በአባቶች ምክርና ተረጋግቶ መስቀሉ በእንባና በጸሎት ተነቅሎ ተነሥቷል።
በአርሲ ነጌሌ ከተማ የሚገኘውና ለረጅም ዓመታት በኦርቶዶክሳውያን የመስቀልና የጥምቀት ማክበሪያ ሜዳ ላይ ተተክሎ ይገኝ የነበረውን መስቀለ ክርስቶስ በወሀየቢያ አክራሪ ሙስሊም ባለስልጣናት መስቀሉን ማየት የለብንም በማለት አስቀድሞ በጉልበት ነቅለው ቢወስዱትም የነገሌ ህዝብ ነቅሎ ወጥቶ መስቀሉን ባለ ሥልጣናቱ ከደበቁበት ሥፍራ አስመልሶ ከተነቀለበት ሥፍራ መልሶ ተክሎት የነበረ ቢሆንም
ወሀቢዮቹ ባለሥልጣናት በጉልበት እንደማይችሉ ሲያውቁ በሕግ ሰበብ ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ በተሰጠ ትዕዛዝ የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲወስን ተደርጎ መስቀሉን ኦርቶዶክሳውያን እንዲያነሱት ለሀገረ ስብከቱ እንዲደርስ ተደርጓል። ይህ ዛሬ የተፈጸመው ግፍ በእስላሞች ላይ ቢሆን ብላችሁ አስቡት። የሚጠራው ሰልፍ ብዛቱ፣ የሚወጣው ሰይፍም ብዛቱ፣ ዛቻና ፉከራው መግለጫው ራሱ ብዛቱ ለጉድ ነበር።
አባቶቻችንም ይሄን አስታክከው ወሀቢዮቹ የጅምላ እልቂት ሊፈጽሙ እንደሚችሉ በማሰብ ህዝብ በኦሮሚያ ወታደር እንዳይረሸን ሲሉ በዛሬው ዕለት የከተማና የገጠሩ የተዋሕዶ ልጆች በተገኙበት በታላቅ ጸሎትና በታላቅ ልቅሶ የጥምቀት በዓል ማክበሪያ የመስቀል ምልክታችን እንዲህ በሚያሳዝን መልኩ በለቅሶ እና በእንባ ታጀቦ ከነበረበት የመስቀል አደባባይ ወደ ደብረ ልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን በክብር ታጅቦ ወደ ደብሩ ከሄደ በኋላ በተዘጋጀለት ስፍራ በዚህ መልኩ በክብር ተተክሏል።
ይሄ ምልክት ነው። ትግራይ አክሱም ያለህ፣ ጎንደር ጎጃም ወለጋ ጅማ ባሌ ያለህ፣ ሆሣዕና ወላይታ ጋሙጎፋ ያለህ የተዋሕዶ ተከታይ ይሄ ምልክት ነው። አዲስ አበባ ለአርሲ ነገሌ ቅርብ የሆነ ከተማ ነው። የሚገርመው በአርሲ ነገሌ የሚሾሞ ከንቲባዎች የመመረጫ ዋናው መስፈርታቸው የነበረው “ በመስቀል አደባዩ ላይ የተተከለውን መስቀል የሚያስነሳ” መሆን ነበረበት። እናም አሁን በስንትና ስንት ሙከራ አቶ ሽመልስ ገብተውበት የአሁኑ ከንቲባ ተሳክቶለታል።
“ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን። ”ፊልጵ 3፣ 18-20
በሉ ደኅና ዋሉ። ኦርቶዶክሳውያን ኮረንቲና ፖለቲካ በሩቁ ነው ስትሉ ከርመን አሁን ኮሬንቲው ብንሸሸውም ጠብሶ እየጣለን ነው። ያውም እያንጨረጨረ። ፖለቲካና ኮሬንቲ በሩቁ ነው ይልልሃል ኦርቶዶክስ ሆነህ ተሳትፎ ልታደርግ ስትል። እነሱ ግን እስላሞቹና ፕሮቴስታንቶቹ ኮረንቲውን ከነ ባልቦላው ጠቅልለው ወስደው አሁን ደም እምባ ያስለቅሱሃል።
የእኔ ምክር !! አልረፈደምና የተኛህ ኦርቶዶክሳዊ ንቃ !! ተነስ !! መብትህን አስከብር። ዝም አልክም አላልክም፣ ተናገርክም ዘንዶው እንደሆነ አንተን መዋጡን አልተወም። የራሴ የምትለውን የፖለቲካ ፓርቲ አቋቁመህ በጨዋታው ሜዳ ላይ ግጠም። በእርግጠኝነት የምነግርህ ታሸንፋለህ። በሉ ደህና ዋሉ። አርሲ ነገሌዎች አይዟችሁ ዛሬ አልቅሳችሁ መስቀሉን ነቅላችሁ እንዳነሣችሁ፣ በቅርቡ በታላቅ ክብርና አጀብ በስፍራው ትመልሱታላችሁ። ጊዜው ሩቅ አይደለም።
Leave a Reply