Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2020
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for January 13th, 2020

ዘመነ ዮሐንስ | ጥር ፬ / ፪፼፲፪ ዓ.ም ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 13, 2020

እንኳን ለወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ በአል አደረሰን

ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ

በዚህች ቀን ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ሞትን ሳይቀምስ የተሰወረበት ቀን ነው፤ ዮሐ ፳፩፥፳

ዮሐንስ ማለት የእግዚአብሔር ጸጋ ነዉ፤ ደስታ ማለት ነዉ፡፡ አባቱ ዘብዴዮስ ፤ እናቱ ማርያም ባዉፍልያ ትባላለች፡፡ቁጥሩ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የሆነ ያዕቆብ የተባለ ወንድም ነበረዉ፡፡ ማቴ ፬፥፳፩ ማር ፩፥፳ ፤ ማቴ ፳፥፳ ቅዱስ ዮሐንስ አስቀድሞ የዮሐንስ መጥምቅም ደቀ መዝሙር ነበር፡፡ ዮሐ ፩፥፴፭ ቅዱስ ዮሐንስ ከአባቱና ከወንድሙ ጋር ዓሣ በሚያጠምድበት በገሊላ ባህር ላይ መረቡን ሲያበጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያነት ጠራዉ፡፡ እሱም አባቱን ሌሎቹንና ታንኳን ትቶ ከወንድሙ ያዕቆብ ጋር ጌታን ተከተለዉ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ስሞች አሉት

  • 👉 ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ

  • 👉 ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ

  • 👉 ዮሐንስ ቁጽረ ገጽ

  • 👉 ዮሐንስ ታኦሎጎስ

  • 👉 ዮሐንስ አቡቀለምሲስ

  • 👉 ዮሐንስ ወንጌላዊ

  • 👉 ዮሐንስ ዘንስ

ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በህይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ ፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነዉ፡፡ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ “”ዮሐንስ እኔ እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ??”›ዮሐ ፳፩፥፳ ይህም እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነዉ፡፡በማቴ 1618 ላይ እዉነት….……ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ“”›ያለዉ ቃል ለቅዱስ ዮሐንስና መሰሎቹ የተነገረ ቃል ነዉ፡፡

ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ በሃይማኖታዊ ጉዳይ ላይ ምን ያህል ጠንቃቆች መሆን እንደሚገባን ሲናገር

ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት። ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።[ኛ ዮሐ፲፩]

በማለት አርቀን እንድናጥርና እንድንጠነቀቅ አስተምሮናል፡፡

የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በረከቱ ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡ ራዕዩ ይገለጥልን!

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: