Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2020
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for January 16th, 2020

ኢትዮጵያን አትንኳት | በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 16, 2020

በሃገረ ኢትዮጵያ በተዋሕዶ ዜጎቿ ላይ እየተካሄደ ያለው የጥቃትና የግድያ ዘመቻ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በአሜሪካ፣ አውሮፓ እና አረብ ሃገራት አበረታችነት እንደሆነ እያየነው ነው። በጅማ፣ ጅጅጋ፣ ሐረርጌ፣ ናዝሬት፣ ከሚሴ፣ ነገሌ፣ ሆሣእና፣ ደምቢዶሎ ወዘተ እየተሠራ ያለው ግፍና በደል በእስማኤላውያኑ አረብ ሙስሊሞች እና በዔሳውያኑ/ኤዶማውያኑ ምዕራባውያን ፕሮቴስታንቶች የሚደገፍ ነው።

በእነዚህ የዲያብሎስ ልጆች ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳንወስድ ተኮላሽተናል፤ ነገር ግን የበቀል አምላክ እግዚአብሔር ዝም አይልም፤ እነዚህ ሃገራት አንድ በአንድ በእሳት እንደሚጠረጉ አብረን እንታዘባለን።

ከዚህ በፊት ይህን ቪዲዮ አቅርበን ነበር

፲፪ / / ፲፪ ቅዱስ ሚካኤል ዕለት በአሜሪካዋ ቪርጂኒያ ግዛት የተከሰተው ተዓምር ነው። በዋሽንግተን ዲ.ሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በየአብያተክርስቲያናቱ ቅዱስ ሚካኤልን ሲያወድሱና ሲማጸኑ በአቅራቢያቸው በሚገኝ አንድ መንገድ ላይ የተተከለው ግዙፍ የኢሬቻ ዛፍ መኪና ላይ ወድቆ ተጓዦቹ ለአርባ አምስት ደቂቃ ያህል ከመኪናቸው መውጣት አልቻሉም ነበር። እንደሚታወቀው ጂኒ ጃዋር በዚሁ መንገድ በኩል አድርጎ ነበር ቤተዘዳ ወደተባለው መንደር የሚያመራው። ይህ ዛፍ ለጂኒ ጃዋር ተዘጋጅቶለት ይሆን?

በእነዚሁ ቀናት እስክንድር ነጋ ወደ ዋሽንግተን እና ቪርጂኒያ ተጉዞ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ኢትዮጵያውያን የድንግል ማርያም መቀነት ቀለማት ያረፉበትን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ የጂኒ ጃዋርን እባባዊ እንቅስቃሴ ተከታትለውት ነበር። ጂኒ ጃዋር በመጀመሪያ ዋሽንግተን በሚገኝ አንድ የፊልጲናውያን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከቄሮ አጋንንት አጋሮቹ ጋር መሰባሰብ አቅዶ ነበር፤ ነገር ግን በኢትዮጵያውያኑ ተጽዕኖ ይህ አልተሳካለትም። ቤተ ሳይዳ የሚገኝ አንድ የጴንጤ መናፍቃን ቸርች ግን በሩን ጂኒው ለመክፈት ፈቃደኛ ስለነበር ወደዚያ አመራ። ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አንድ ላይ ይበራሉ!

ይህ ሁሉ የሆነው አሜሪካ ዋንኛ የሃገሪቱ ክብረ በዓል የሆነውን “የምስጋና ዕለት” / “Thanksgiving“ ለማክበር በምትዘጋጅበት ዋዜማ ነው። ይህ በዓል የኛዎቹ ጣዖተኞች የሚያከብሩት ዓይነት ኢሬቻ ነው፤ ይህ በዓል በአሜሪካም ሆነ በኢትዮጵያ በጭራሽ መከበር የለበትም። ምክኒያቱም በአሜሪካ ከአውሮፓ የመጡት ነጮች “አሜሪካን ህንዶች” ተብለው የሚታወቁትን ቀደምት የአሜሪካ ነዋሪዎችን በመጨፍጨፍ መሬታቸውን በመውረሳቸው አምላካቸውን የሚያመሰግኑበት በዓል ስለሆነ ነው። በኢትዮጵያም “ኦሮሞ” የተባሉት መጤዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ከታንዛኒያ አካባቢ በመፍለስ ሃያ የሚጠጉ ቀደምት የኢትዮጵያን ነገዶችን በመጨፍጨፍ ምድራቸውን በመውረሳቸው ለዋቄዮአላህ “ዋቄኒ” እያሉ ምስጋናቸውን የሚሰጡበት እርኩስ በዓል ስለሆነ ነው። …”

አሁን በዚሁ የቨርጂኒያ ግዛት፡ ሰኞ በጥምቀት ዕለት፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጇል። በዚሁ ዕለት፡ ልክ እንደ ደምቢዶሎው “የታጠቁ ሚሊሻዎች/ሽፍቶች የቨርጂኒያ ካፒቶልን ለማጥቃት አቅደዋል ተብሏል።

የቨርጂኒያ ግዛት መሪዎች ስጋት ስላደረባቸው ስለሽፍቶች ማንነት ትክክለኛ ዝርዝር ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆኑም ፣ ነገር ግን ከክልሉ ውጭ የሚመጡና ትጥቅ ለመፍታት ፈቃደኞች ይልሆኑ ቡድኖች የቨርጂኒያ ግዛት መስተዳደር ካፒቶልን በጉልበት ለማጥቃት እንዳቀዱ ተናግረዋል። በሚቀጥለው ሰኞ ትጥቅ የማስፈታት ሕግን ለመደገፍ የሚሰበሰቡትን ቡድኖች በመቃወም ሚሊሻዎቹ / ሽፍቶቹ አመፅ እያቀዱ ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል።

በየዋህና ንጹሐኑ በኢትዮጵያ ህፃናት፣ አረጋውያን፣ ሴቶችና ተማሪዎች ላይ በሚያስቆጣ መልክ ግፍና ወንጀል ሲፈጽሙባቸው የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር ለዘላለም ዝምታውን የሚቀጥል ይመስለናል? አይቀጥልም፤ ፈጠነም ዘገይም የእግዚአብሔር ፍርድና ቁጣ በእነዚህ አመጸኞች ላይ ይሆናል።

በደንቢዶሎ የታገቱት እህቶቻችን ጥምቀትን ጫካ ውስጥ ከአውሬ ጋር ነው የሚያሳልፉት? ታዝበናል፡ ከስም ዝርዝሩ ኦሮሞ እንደሌለ ግልጽ ነው፡ ምናልባት ኦሮሞ ያልሆነ እስላም ሊኖር ይችላል ብላችሁ ለምታሰቡ ከመካከላቸው አንድም የታገት እስላም የለም። እስኪ እራሳችንን እንጠይቅ ከእህቶቻችን ጋር አብረው የሚማሩት ኦሮሞዎቹና ሙስሊሞቹ ተማሪ ጓደኞቻቸውትምህርታቸውን ያለእነሱ በሰላም ቀጥለዋል። በአንድ ጤናማ ዓለም ሁሉም ተማሪዎች ወይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመሄድ ይቆጠቡ ነበር፤ ወይም ለታገቱት ተማሪዎች የድጋፍ ድምጻቸውን ያሰሙ ነበር። ግን ይህ አይሆኑም ምክኒያቱም ኦሮሚያ በሃገረ ኢትዮጵያ የሲዖል ተምሳሊት ለመሆን የበቃ እርኩስ ምድር ነውና።

ላለፉት ሁለት ዓመታት ይህ ሁሉ ግፍ ሲሰራ ቤተክርስቲያንና ምዕመናኗ ምንም አለማድረጋቸውን ያየውና በዚህም የደፋፈረው አውሬው አብዮት አህመድ ሥልጣን ላይ ገና ሁለት ዓመት ሳይሞላው እንደ ፈርዖን እራሱን እንደ አምላክ ማድረግ ጀምሯል(እየታየ ነው)፤ ምናልባት አሁን ለበዓል እኔ አስፈታኋቸው፤ ስለዚህ ስሜን ጥሩ፣ አጨብጭቡልኝ፣ ውደዱኝ፣ ምረጡኝ፣ አንግሡኝሊለን አቅዶ ይሆናል ተማሪዎቹን ያሳገታቸው።

ጦርነቱን በእግዚአብሔር አምላክ ላይ በመስቀሉ ላይ ቀስበቀስም በሰባቱ ምስጢረ ቤተክርስቲያን ላይ መሆኑን እየተከታተልነው ነው። ጥምቀት ከእግዚአብሔር ዳግም የምንወለድበት ምሥጢር ስለሆነ አሁን በጥምቀት ላይ ጦርነት ከፍተዋል። ቀጥሎም በቍርባን እና ተክሊል ላይ ይሆናል።

ለማንኛውም፤ የጥምቀት በዓልን በ666ቱ ተቋም ዩኔስኮ ከመዘገቡ በኋላ ሆን ተብሎ በዓሉ በደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል በነፃነት እንዳይከበር በአሜሪካና አረቢያ ግን እንዲከበር በማድረግ ያው በሃገራቸው አልቻሉም!” እያሉ ይሳለቁብናል። ግን፡ ቀስ በቀስ ሃገራችንን ብቻ ሳይሆን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንንም ለመንጠቅ ከፍተኛ ሤራ መጠንሰሱን እያየን ነውን? አገራችንና ሃይማኖታችንን በምስር ወጥ ለመለወጥ ዝግኙና ፈቃደኞች ነንን? እንግዲያውማ እባቡ አብዮት አህመድብልጽግናብሎ መጥቶላችኋል። ከማን ጋር ነን? ከእግዚአብሔር ጋር ወይስ ከቄሳር ጋር?

የሚከተለውን ጽሑፍ ያቀበለን መምህር ዘመድኩን በቀለ ነው

የበዓለ ጥምቀት አከባበር ዝግጅት በኢትዮጵያና በአሜሪካ ልብ ብላችሁ ተመልከቱልኝማ።

ሀ፥ በኢትዮጵያ ፦

በደቡብ ኢትዮጵያ በሆሣዕና ከተማ የጥምቀት በዓል የማክበሪያ ስፍራውን ፕሮቴስታንቱ ወርሰውታል። የገበያ ሥፍራ፣ የቆሻሻ መጣያና የአውቶቡስ መነሃሪያ አድርገው የከተራ ሥፍራውን ከልክለዋል። ምን አባህ ታመጣለህ ተብለናል። የሚመጣውን አብሮ ማየት ነው። የከተማው አስተዳዳር ጴንጤዎቹ የምን ዩኔስኮ ነው፣ የምን ጥምቀት ነው ብለው ለአህያ ማቆሚያ ፓርኪንግ 5 ሺ ካሬ መሬት ፈቅደዋል። ለኦርቶዶክሳውያን ይሄም አይገባችሁም ተብለዋል። ዮናታን አክሊሉ መቶ ሺ ካሬ፣ ፓስተር እስራኤል ዳንሳም እንዲሁ በነፃ ተሰጥቷቸዋል። ኦርቶዶክስ ግን የራሷን ያላትን መሬት ዐይኗ እያየ ነጥቀዋታል።

በዚያው በደቡብ ኢትዮጵያ በመሎለሃ ከተማ የበዓለ ጥመቀቱን ማክበሪያ ሥፍራውን አሁንም የጌታ ልጆች ፕሮቴስታንቱ ባለሥልጣናት ጊዜ ሰጠን ብለው ወታደር አሰማርተው በቀን ብርሃን በአደባባይ መሬቷን ነጥቀው ወርሰዋል። ካህናቱን ደብድበው፣ ምዕማናንን ቀጥቅጠው ከወኅኒ ወርውረዋል። ዚስ ኢዝ ኢትዮጵያ አለ ኢዩ ጩፋ።

በአርሲ ነገሌም በቅርቡ የሆነውንም በዓይናችን አይተናል። መስቀሉን ነቅለው እንዲነሳ ሲያደርጉ አይተናል። አሁን በባሌ ለበዓለ ጥምቀቱ ምንጣፍ ማንጠፍ፣ አዲስ አበባ ጫፍ በሱሉልታ፣ በዝዋይ፣ በናዝሬትና በአጠቃላይ በኦሮሚያ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መያዝና መስቀል ማውለብለብም ባልተጻፈ ዐዋጅና ባልተነገረ ሕግ በይፋ ተከልክሏል። ሞተን ነው ቆመን ነው እያሉ ነው። ፕሮቴስታንት ኦሮሞ ቄሮዎችና የወሃቢያ እስላም ቄሮዎች።

ቀውሲ በላይና አህመዲን ጀበል በሊቀመንበራቸው በጃዋር ትእዛዝ ኦሮሚያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ከታየ ሞተን ነው ቆመን እያሉ እየፎከሩ ነው። ኦርቶዶክሳውያኑ ኦሮሞዎችና ዐማራ፣ ትግሬ፣ ደቡብ ሁሉ እስቲ የሚሆነው ጊዜው ይድረስ እያሉ ነው። ሀረር ለጥር ሥላሴ ባንዲራው ሲዘረጋ፣ ሱልታ ልጥር ሥላሴ ከሐረር ተፈናቅለው ሱሉልታ እንዲሰፍሩ የተደረጉ እስላም ቄሮዎች ደብሩን አስፈራርተው ሰንደቅ ዓላማው እንዳይውለበለብ እንዳይሰቀልም አድርገዋል። [ የዘንድሮ ጥመቀት በተለይ በኦሮሚያ ከበድ የሚል ይመስላል። ]

ሁ ፥ በአማሪካ ፦

ይህን ሁሉ ዓይተው፣ በዓለ ጥምቀት በትውልድ ሃገሩ በኢትዮጵያ በገዛ ልጆቹ እንዲህ ፍዳውን ሲያይ አይተው፣ ተመልክተውም ከዚያ ራቅ ባለ ሥፍራ፣ በሰዶምና ገሞራ ምድር፣ በአህዛብ ምድር፣ በኢአማንያን ሀገር ደግሞ ሞተረኛ ተመድቦለት፣ በሰረገላ በሊሞዚን በፈረሰኛ ታጅቦ፣ ዐውራ ጎዳናዎች ተዘግተው፣ የየሀገሩ የየከተማዎቹ ከንቲባዎች በተገኙበት፣ የነጮቹ፣ የዐረቦቹ፣ የሩቅ ምስራቅና የጥቁሮቹ የመገናኛ ብዙሃን በተገኙበት በታልቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓትና ድምቀት ሲከበር ስታይ በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ትደመማለህ።

ይሄን ማስታወቂያ ሳየው ገረመኝ። በሀገረ አሜሪካ እንዲህ በይፋ በዓለ ጥምቀትን እንዴት ኢትዮጵያውያኑ እንደሚያከብሩትና ከወዲሁ ዕቅድ አውጥተው በይፋ እንዴት እንደሚያውጁ ተመልከተሉኝማ። ቄሮ የለ ቀሬ፣ ወሃቢይ የለ ሰለፊ፣ ነፃነት ብቻ። ሰንደቅ ዓላማው ከፍ፣ ዝማሬው፣ ወዳሴው፣ ሥርዓተ አምልኮውና ሥርዓተ ቅዳሴው ከፍከፍ ይላል።

በዋሽንግተንና አካባቢው በሜሪ ላንድ ( ሀገረ ማርያም) የምትኖሩ ምዕመናን ፏ ብላችሁ፣ እንቁጣጣሽ መስላችሁ፣ ጅንስና ሚኒስከርታችሁን ወዲያ ጥላችሁ፣ በሀገር ባህል ልብሱ፣ በጃኖ፣ በኩታው፣ በእጀጠባቡ ጀነን ኮራ ብላችሁ አማሪካን የትራንፕን ከተማ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ፣ በዝማሬው፣ በከበሮ፣ በእልልታ አናውጧት። ማዕጠንቱ ይታጠን፣ መስቀሉ ይወጣ አጋንንቱን ይቀጥቅጥ፣ ይቀደስ፣ ወረቡ፣ ዝማሜው፣ ሽብሸባው ይታይ ይፈጸም።

በኢትዮጵያ ደግሞ በተቃራኒው ነው። በዓለ ጥምቀትን እንዴት እንደምታከብር፣ እንዴት እንደምትዘምር፣ ምን መልበስ፣ ምን መያዝ እንዳለብህ ቄሮ የተባለ የወሃቢያ እስላም ሠራዊት ሊያዝህና ሊያስፈራራህ ይሞክራል። አዲስ አበባ መርካቶ ተክለሃይማኖቶች ገራሚ ዝግጅት እያደረጉ ነው። አንዳንድ አድባራትም እንዲሁ። የተከልሃይማኖት ልጆች የሚሠሩትን ለማስቆም የወሃቢይ እስላሞቹ ሆያ ሆዬ ቢዘፍኑም የተክልዬ ልጆች ግን መስሚያችን ጥጥ ነው ብለው ዝግጅታቸውን ቀጥለዋል። አብነት አደባባዩ በሰንደቅ ዓላማው አሸብርቋል። ደምቋልም።

______________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅድስት ሥላሴ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ይባርኩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 16, 2020

እንኳን ለአግዓዚተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰንየአብርሃሙ ሥላሴ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን። ሕዝባችንንም በሰላም በፍቅር በአንድነት ያኑርልን

ወደ መጨረሻ ላይ ያለውን መልዕክት እናዳምጥና እራሳችንን እንጠይቅ፤ “እንደው በዚህች ዓለም ላይ እንደ ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትሮ የሚሄድ፣ በጾምና በጸሎት የሚተገባ ሕዝብ ይኖራልን? እኔ መመስከር እችላለሁ፤ የለም! የትም ሃገር የለም። ሃጢአተኞች ሁላችንም ሃጢአተኞች ነን፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያን እየተቃጠለ ያለው እኛ ከዓለም ሁሉ የከፋ ሃጢአት ሰርተን ሳይሆን ክርስቲያን ወገናችንን እና ቤተክርስቲያናቱን ለመከላከል ዝግጁ ባለመሆናቻን፣ የእኛና የአምላካችን ጠላት ከሆኑት አህዛብ ጋር በመደባለቃችን፣ የሃገር ጠላት ከሆነው መንግስት ጋር በመደመራችን ብሎም እንደ ቀደሙት አባቶቻችን መንግስትን በቁጣ ለመገሰጽና ለማስጠንቀቅ ባለመድፈራችንና በራድ ወይ ትኩስ ስላልሆንን ነው። ስለዚህ መንግስትን ለመቃወም “ሰልፍ አትውጡ፡ እኛ እንደራደራለን!” ቅብርጥሴ የሚለው መልዕክት የትም አያደርሰንም። እንዲያውም የተዋሕዶ አርበኞች በቁጣ ወደ አራት ኪሎ ቤተመንግስት አምርተው ባለሥልጣናቱ ሁሉ እንዲወገዱ መጮኽና አጥሩን መነቅነቅ ይኖርባቸዋል። ለሁሉም ጊዜ አለው፤

ከወዳጆችህ ጋር ብቻ ሳይሆን ከጠላቶችህም ጋር እንኳ ሳይቀር በሰላም ኑር፤ ነገር ግን እንዲህ የምልህ ካንተ ከግል ጠላቶችህ ጋር እንጂ ከእግዚአብሔርና ከቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ጋር አይደለም፡፡አንድ ገዳማዊ አባት

ሰውን ከእግዚአብሔር ከሚለየው አጉል ሰላም ይልቅ ከእግዚአብሔር የማይለየው ጦርነት ይሻላል፤ ስሜታዊ ከሆነና ለቤተ ክርስቲያን ዘለቄታዊ ጉዳት ከሚኖረው ስምምነትና አንድነት ይልቅ ስለ ሐይማኖት መጠበቅ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ የሚኖረውና ለዚህ ሲባል የሚሆን አለመስማማት ይሻላል፡፡ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

በዚህ የጥምቀት በዓል ከአባቶች የምጠብቀው መልዕክት፦

ሴት ልጆቼ በደምቢዶሎ ጫካ ውስጥ የጥምቀት በዓልን እንዲያሳልፉ አልሻም፤ ስለዚህ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በቃህ፡ ስልጣኑን አስረክብና በሥላሴ ስም ተጠመቅ!”

የሚለውን መልዕክት ነው።

እስኪ እናስበው፤ አቡነ ማትያስ ይህን ቢናገሩ፤ ምንም ጥርጥር የለኝም ብዙ እንቅስቃሴ ሊታይ ይችል ነበር።

የቤተክርስቲያን አገልጋዮች፡ በቃን! ስሜታዊ አትሁኑ!” እያላችሁ ሰውን አታስተኙት፤ ወኔውን አትንጠቁት! እንዲያውም “ምርጫ” የተባለው ነገር የሚካሄድ ከሆነ በመጭዎቹ ሳምንታት ምእመናኑን ለእነ አብዮት አህመድ፣ ለእነ ብርሃኑና ስብሐት ነጋ፣ እንዲሁም ለሌሎቹ አቋምየለሽ ልክስክስ ፓርቲዎች በጭራሽ ድምጽ እንዳይሰጡ ማስጠንቀቅ፤ በተቃራኒው ደግሞ ለእስክንድር ነጋ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ግልጽ የሆነ ቅስቀሳ ማካሄድ አለባቸው።

ሜዲያው ሁሉ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ አሉታዊ በሆነ መልክ 24 ሰዓት ቅስቀሳ በሚያደርጉባት ሃገራችን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በጣም አመች የሆነው የቅስቀሳ እና የትምህርት መድረክ በቤተክርስቲያን ነው የሚገኘው።

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: