እኛ እግዚአብሔር አምላካችንን እንዲህ ስለምነወድደው ከዚህ የተነሳ ሰይጣን በቅናት፣ በጥላቻ እና በእብደት ይሞላል። ዲያብሎስ ሁሉም እግዚአብሔርን የሚወዱትንና የሚያገለግሉትን ፍጥረታት መግደል እና ማጥፋት ይፈልጋል።
ያው እንግዲህ ዲያብሎስ በሸቀ፣ አበደ፣ ቅጥል አለ። ዲያብሎስ ሰይጣን ወደ እኛ የማለፍ ፈቃድ ካገኘ ይሰርቃል፣ ይገድላል እንዲሁም ያጠፋል። መስረቅ፣ መግደል እና ማጥፋት የእርሱ የደመ ነፍስ ስራዎች ናቸውና እግዚአብሔርን የሚወዱትን ለመግደል ወደ ሐረርና ድሬዳዋ አመራ።