Drones Raining From The Sky in China | በቻይና ድሮኖች እንደ በረዶ ዘነቡ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 5, 2021
ሳተላይቱን፣ የጠፈር ጣቢያውን ወይንም ድሮኑን ከሰማይ ማወርድ፣ ኢንተርኔቱን መዝጋት የሚችሉ ጽዮናውያን አባቶች አሉን! በትናንትናው የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለት በውል ባልታወቀ ምክኒያት በጣም ብዙ ድሮኖች በቻይናዋ ዜንግዙ ከተማ ላይ ከሰማይ እንደ ዝንብ አንድ በአንድ መርገፋቸው ተነግሯል። 😬 ዋ! ይህን ባለ ሉሲፈር ኮከብ ባንዲራ የምትይዙ ተጋሩ! ዋ! ብለናል። ኢ-አማኒዋ የሉሲፈራውያኑ ፋብሪካ ቻይና እኮ ልክ እንደ ሁሉም ከድታናለች! እኛን የማይከዱን የእግዚአብሔር ቅዱሳን ብቻ ናቸው! እንግዲህ አንዳንዶቹ ዛሬም እንኳን ለጽዮን እናታችን ምስጋና ሲያደርሱ አይታዩም አይሰሙም።
በዚሁ በትናንትናው ዕለት የሉሲፈራዊው ‘ማርክ ሱከርበርግ ‘ ተቋም “ፌስቡክ” ከ እነ ‘ኢንስታግራም‘ እና ‘ዋትስአፕ‘ ልጆቹ ጋር ከአገልግሎት ተወግዶ ነበር። አቡነ ተክለ ሐይማኖት? ይህ ገና ጅማሮው ነው። በመጪው የፈረንጆች ኖቬምበር 4 (በአክሱም ጽዮን ላይ በግራኝ የተከፈተው ጂሃድ ዓመት ይሞላዋል፤ የተክለ ሐይማኖት ዕለት ነበር) እንዲህ የሚል ድብቅ መረጃ ወጥቷል፤
“እ.ኤ.አ ኖቬምበር 4 2021 የኢሉሚናቲ ወንጀለኞች በስድስት ዋና ዋና ከተሞች ዋሽንግተን ፣ ካሊፎርኒያ ፣ ለንደን ፣ ኒው ዮርክ ፣ ሮም እና ፓሪስ የኑክሌር ቦምቦችን የጫኑ የጭነት አውሮፕላኖችን ሊያበላሹ ነው። በእነዚያ ከተሞች ውስጥ እንደ ሳን ፍራን ሲስኮው‘ወርቃማው በር ድልድይ‘ ፣ ለንደን ቢግ ቤን ፣ ኒው ዮርክ የነፃነት ሐውልት ፣ ሮም ኮሎሲየም ፣ ቫቲካን እና የፓሪሱ አይፈል ማማ ያሉ ዋና ዋና ምልክቶች ይጠፋሉ። በኒው ዮርክ ሁኔታ ፣ ኑክሌር በምሥራቅ የባሕር ዳርቻ ላይ ይፈነዳል ፣ እናም ሱናሚ ከተማዋን ያጥለቀለቃታል!
ይህ ዓለም ከዚህ በፊት አይቶ የማያውቀው የግዙፍ የውሸት ባንዲራ ክስተት ይሆናል። አይሲስ ሃላፊነቱን ይወስዳል ግን ትልቅ ውሸት ይሆናል። ይህ ሴራ የአዲሱ የዓለም ሥርዓት(NWO) አጀንዳ አረማጆቹ ሊሲፈራውያኑ ዘንድ ቢያንስ ለ 50 ዓመታት ቆይቷል። ይህ የአዲሱን ዓለም ሥርዓት ለማንገስ ሲባል የሚከሰት ክስተት ይሆናል።”
“On November 4 2021, Illuminati criminals are going to crash cargo planes loaded with nuclear bombs in six major cities: Washington, California, London, New York, Rome and Paris. The major landmarks in those cities like, the Golden Gate bridge, Big Ben, the Statue of Liberty, the Colosseum, the Vatican, and the Eiffel tower will be destroyed. In the case of New York, a nuke will be detonated in the east coast, and it will cause a tsunami to overwhelm the city !
This will be a mega false flag event like the world has never seen before. ISIS will take responsibility but it will be a huge LIE. This plot has been on the NWO agenda for at least 50 years. This will be THE event that will give rise to the NWO.”
እንግዲህ በዚህ ዕለት እንኳን ባይከሰት፤ ፈጠነም ዘገየም ተመሳሳይ ዲያብሎሳዊ ተግባር መፈጸማቸው አይቀርም፤ አንድ በአንድ፣ ቀስ በቀስ እየፈጸሙትም እኮ ነው። የእኛው አውሬ ግራኝ አብዮት አህመድ እንኳን እነርሱ በሰጡት ፍኖተ ካርታ መሠረት በአክሱም ጽዮን ላይ የዘር ማጥፋት ጂሃዱን በማካሄድ ላይ ይገኛል። ባለፈው የመጥመቁ ቅዱስ ዮሐንስ ዕለት ያገኘሁት አንድ መጥመቁ ዮሐንስን የሚመስል አየርላንዳዊ (ከሚስቱ እና ሴት ልጁ ጋር) እኔ ከአስራ ሦስት ዓመታት በፊት በጦማሬ ካወሳኋቸው ክስስተቶች ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጣመሩ መረጃዎችን አካፍሎኝ ነበር። ባቡር ጣቢያ ነበር አቅጣጫ ሲጠይቀኝ በድንገት የተገናኘነው። ኢትዮጵያዊ መሆኔን ስነግረው፤ እንዲህ አለኝ፤ “የእኔ አባት ከተባበሩት መንግስታት መስራቾች መካከል አንዱ ነበር፤ ዛሬ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት የወንድማማቾች ጦርነት ነው፤ ክርስቲያን በክርስቲያን ላይ እንዲነሳ የተባበሩት መንግስታት መሥራቾች ዕቅድ ነበር፤ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ አዋሳኝ ቦታ አካባቢ እጅግ በጣም ጥልቅና ረጅም ዋሻ አለ፤ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሕፃናት ለዘመናት እየተጠለፉና እዚህ ዋሻ ውስጥ እየገቡ ለሉሲፈራውያኑ እንዲላኩ ይደረጋሉ.…” አለኝ። ሌላ ብዙ ጉድ አለ። ምንም ሳልለው በሚገባ ካዳመጥቁት በኋላ ስልክ ቁጥሩን ተቀብዬ ተሰናበትኩት። ወዲያው ብልጭ ብለው የታዩኝ ግን በልጅነቴ ወደ ሰሜን አቅጣጫ የሐመር መኪናን በመሰለ የመጓጓዣ ነገር ወደ ሰሜኑ በጣም እየበረሩ በካራቫን ሲጓዙ የነበሩትን “ቆማጣ መሰለ ድንክየዎች/ Reptilians’ የሚመስሉት ፍጥረታት ነበር የታዩኝ። ታሪኩ እዚህ ይገኛል።
ለማንኛውም በትግራይ እየተካሄደና እየተሠራ ያለውን ከፍተኛ ግፍ ለይስሙላ እንደተቆረቀሩ ድምጽ ከማሰማትና ቃላት ከመደጋገም ሌላ ምንም ሊያደርጉበት የማይፈልጉት የዚህ ሁሉ አሳዛኝ ሤራ ጠንሳሾች እነርሱ እራሳቸው ስለሆኑ ነው። በምኒልክ በኩል የአደዋው ጦርነት በትግራይ እንዲካሄድ አደረጉ፣ በአፄ ኃይለ ሥላሴ በኩል የብሪታኒያ ተዋጊ አውሮፕላኖች ጭፍጨፋዎች በመቀሌ አካባቢ አካሄዱ፣ ቀስ ብለውም “የቃኛው ጣቢያ” የተሰኘውን “የአላስካውን ሃርፕ/ HAARP” (ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት ሉሲፈራውያኑ ግዙፉን የአላስካ ግዛትን በ7.2 ሚሊየን ዶላር ብቻ ነበር ዛሬ ኡ! ኡ! በሚያሰኝ መልክ ከኦሮቶዶክስ ሩሲያ ገዝተው ከአሜሪካ ጋር የቀላቀሏት) የመሰለ ምስጢራዊ የሲ.አይ.ኤ የሙከራ ጣቢያ ተከሉ፤ ከዚያም በትግራይና ወሎ ረሃብ ፈጥረው በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ሕይወት ቀጠፉና ለእርዳታ በሚል ሰበብ የኔቶ ወታደሮችን በሰሜን ወሎና በትግራይ አሰፈሩ። በደርግ ጊዜም ተመሳሳይ ሁኔታዎችን ፈጥረው በሰሜን ኢትዮጵያ (ትግራይ እና ኤርትራ) ተመሳሳይ ተግባር ፈጸሙ። ከባድሜው ጦርነት በኋላም የተባበሩት መንግስታት “ሰላም አስከባሪ” በሚል በትግራይ እና ኤርትራ ድንበር መከከል “ወታደሮቻቸውን” አስፍረው ብዙ ዲያብሎሳዊ ሥራዎችን በዚህ ምስጢራዊ የኢትዮጵያ ክፍል ሲሰሩ ነበር። ዛሬም አስፈላጊ ነው የሚሉትን ጥንታዊውን ክርስቲያናዊ ሕዝብ በሁሉም አካላት ረዳትነት ከጨረሱ በኋላና በረሃብ የተጎዱትን ወግኖቻችንን ምስሎችም ለመላው ዓለም ካሰራጩ በኋላ ወራሪ ሰራዊቶቻቸውን በዚሁ ምስጢራዊና የተቀደሰ ቦታ በማስፈር ከኑክሌር ሆለካውስት/እልቂት እንዲተርፍ የሚሹትን ዘራቸውን አምጥተው ይተክላሉ።
ለዚህ ሉሲፈራዊ ዕቅዳቸው በተለይ በአሜሪካ እና በእንግሊዝ ይኖሩ የነበሩ “ኢትዮጵያውያን” ተባባሪ ወኪሎቻቸውን በመጠቀም ላይ ይገኛሉ። አንዷ “እኅተ ማርያም” እያለች እራሷን የምትጠራዋ “እኅተ አቴቴ” ናት። ከሁለት ዓመታት በፊት፤ “የትግራይ ሕዝብ እሳት ሊወርድብህ ነው አገርህን ለቅቀህ ውጣ” በማለት ያስተላለፈችውን መል ዕክት እናስታውሳለን? አዎ! በወቅቱ በከፊልም ቢሆን እኔንም ሳይቀር ለማታለል በቅታ ነበር። ግራኝ አብዮትንም ስትዘልፈው የነበረችው ለስልት ነበር፤ ፈቅዶላት ነበር፤ ያው ዛሬ ከአስር ሺህ የሚበልጡ የምዕራብ ትግራይን ተጋሩዎች ባሰቃቂ እየጨፈጨፉቸውና አካላቸውንም ወደ ተከዜ ወንዝ በመጣል፤ (ዋይ! ዋይ! ዋይ! 😠😠😠 😢😢😢)ሑመራ እና አካባቢዋን ከክርስቲያን ተጋሩዎች ካጸዷቸው በኋላ፤ ያው አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የዲያብሎስ ልጅ ለ “እኅተ አቴቴ” ሁለት መቶ ሄክታር መሬት በሑመራ ለግሷታል። ጉድ ነው! ተጋሩ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን ከምዕራብ ትግራይ ለማስወገድና ጽዮናውያን መነኮሳትን፣ ቀሳውስትን፣ እናቶቻችንን፣ እኅቶቻችንን፣ ሕጻናቱን ለመጨፍጨፍ እቅድ እንደነበረ ከሁለት ዓመታት በፊት በግልጽ ነግራን ነበር ማለት ነው። ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን በአሰቃቂ መልክ ጨፍጭፈው እና አፈናቅለው መሬታቸውን ለእኅተ አቴቴ ሰጧት! እርሷም በደስታ ተቀብላ በአባቶቼና እናቶቼ ደም ሰሊጥና ኑግ ለመዝራት ትራክተሯን በመጋለብ ላይ ናት። ኡ! ኡ! ኡ!፤ ጽዮናውያንን ለመግደል ወደ ትግራይ እዘምታለሁ እያለ ለእነ ቢቢሲ ሰሞኑን ሲቀባጥር የነበረው “መነኩሴ” የእኅተ አቴቴ ችግኝ ቢሆን አይግረመን፤ ሉሲፈራውያኑ ወኪሎቻቸውን ሁሉ ወደ የገዳማቱ ልከዋቸዋል፤ እግዚኦ! እግዚኦ! እግዚኦ! አንድም ለጽዮን፣ ለቤተ ክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ የቆመ ወገን የጠፋበት ዘመን ላይ ነን፤ ሁሉም እራሳቸውን እያሳዩ መጋለጣቸው ጥሩ ነገር ቢሆንም፤ እየተደረገ ባለው ግን ሁሉም ነገር ህልም መስሎ ነው የሚታየኝ። አምላኬ ሆይ፤ ባክህ ፍርድህን አታዘግይ!
ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ ስግደትህ በማዕረገ መላእክት ደረጃ ነውና አከናውነህ የሠራሃት ጸሎትህ ባለ ዘመናችን ሁሉ ከጦርነትና ከጽኑ መከራ ሁሉ ጠባቂ ትሁነን።
ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ መሥዋዕትን የምታሣርግ ታላቅ ካህን የእግዚአብሔር ባለሟል ነህና ቀንዶቹ ዓሥር ከሆኑ ከእባብ መተናኮልና አንደበቱ ሁለት ከሆነ ሰው ፀብ በክንፈ ረድኤትህ ሠውረህ አድነኝ።
ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ ልጆችህ በዚህ ዓለም ብዙ መከራ ቢያገኛቸውም በአንተ ዘንድ ፍጹም ሰላምና እረፍትን እንደሚያገኙ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ።
ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ ከሐዲዎችን የምትበቀል ቄርሎስ የተባልክ አንተ ተክለ ሐይማኖት ነህ እኮን።
____________________________________
Leave a Reply