Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • October 2021
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for October 17th, 2021

ይድረስ ለትግራይ መከላከያ ሰራዊት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 17, 2021

👉 ምስጋና ለ፤ አድማስ

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Earthquake in Ethiopia 6-7? | የመሬት መንቀጥቀጥ በኢትዮጵያ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 17, 2021

✞✞✞[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፮፲፰]✞✞✞

መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፥ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ከሁሉ በለጠ። ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፥ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች። ደሴቶችም ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም።”

🔥 4.5 / 4.3 አማካይ መጠን የመሬት መንቀጥቀጥ

ዓርብ፣ ጥቅምት ፭/፳፻፲፬ ዓ.ም(አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ)

እሑድ፣ ጥቅምት ፯/ ፳፻፲፬ ዓ.ም (ሥላሴ)

‘አድዋ’ በተባለው እሳተ ገሞራ አካባቢ

(ሶማሌ + ኦሮሚያ በተሰኙት ፀረ-ኢትዮጵያ ክልሎች)

🔥 6 እስከ 7 ከፍተኛ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ

በመጭው ማክሰኞ ጥቅምት ፱/ ፳፻፲፬ ዓ.ም (ጨርቆስ)

‘አድዋ’ በተባለው እሳተ ገሞራ አካባቢ

(ሶማሌ + ኦሮሚያ በተሰኙት ፀረ-ኢትዮጵያ ክልሎች)

ይህ ከአክሱም/አድዋ ጋር የተያያዘ ነው፤✞

በትግራይ በጽዮናውያን ላይ ከተከፈተው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ጋር የተያያዘ ነውን? አዎ! የሚገርም ነው በሶማሊያ እና ኦሮሚያ ህገወጥ ክልሎች መከሰቱ ለዚያውም “አድዋ” የተሰኘው የተኛ እሳተ ገሞራ ነቃ ነቃ በሚልበት አቅራቢያ። ዋው!

በተጨማሪ ከዚሁ ጋር በተያያዘ፤ እርቀት የማይወስነው መለኮታዊ ኃይል በአትላንቲክ ውቂያኖስ አፍሪቃ ጠረፍ በምትገኘውና የስፔይን ግዛት በሆነችው የላስ ፓልማስ ደሴት ኃይለኛ የእሳተ ገሞራን ቀስቅሷል። ይህ በጣም የሚፈራው እሳተ ገሞራ የሚፈጥረው የመሬት መንሸራተትና፣ የሱናሚ ጎርፍ አውሮፓን እና ምስራቅ አሜሪካን አውድሞ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሊገድል ይችላል። ይህ ለብዙ ዓመታት ሲጠብቅ የነበረ አስፈሪ ትንቢት ነው። የቱሪስቶች መናኸሪያ ከሆኑት ከካናሪ ደሴቶች መካከል በሆነችው ላስ ፓልማስ ልክ ከወር በፊት እሳተ ገሞራው ፈንድቶ የላቫ ፍሰቱ እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ ቀጥሏል። ከደሴቲቷ ሰማኒያ አምስት ሺህ ነዋሪዎች መካከል አሥር ሺህ የሚሆኑት ተፈናቅለዋል።

አንዳንድ ታዋቂ ሳይንቲስቶች እርግጠኞች ሆነው እንደሚናገሩት ከዚህች ደሴት የሚቀሰቀሰው ከፍተኛ የእሳተ ገሞራ በሰሜን አሜሪካ ምስራቃዊ ዳርቻ (ኒው ዮርክ) እና የሜዲትራንያን ባሕር አዋሳኝ በሆኑ የአውሮፓ ሃግራት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሊገድል ይችላል፤ ይህ እስኪሆን ድረስ የጊዜ ጉዳይ ብቻ እንደሆነ ያስጠነቅቃሉ።

____________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቆሻሻው ግራኝ አብዮት አህመድ የጨለቖት ሥላሴ ቅርስን መንካት አልነበረበትም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 17, 2021

እንግዲህ ይህን ‘ምናልባት ለንግስናው ሊጭነው‘ አቅዶት የነበረውን ዘውድ እንዲመለስ የፈቀደውም ለተንኮል፣ ለዲያብሎሳዊ ዓላማው፣ ምኞቱ እና ስልቱ መሆኑ ግልጽ ነው። አዎ! አታክልቶችን፣ ሰብሉን፣ እህሉን፣ ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታሎችን በማውደም ከቦምብና ጥይት ጭፍጨፋ የተረፉትን ጽዮናውያን በስጋ ማዳከም ብቻ ሳይሆን ዓላማው ፥ ዓብያተ ክርስቲያናቱን፣ ገዳማቱንና ቅርሶቿን በትግራይ የቀሩትን ዛፎችን (ልብ እንበል፤ በተለይ ለኮሮና ወረረሽኝ ብቸኛ የመድኃኒት ምንጭ የሆኑትን የእጣን ዛፎችን ሁሉ በማውደም ትግራይን ልክ እንደ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ልክ ‘እንደ በሻሻ‘ የመንፈሳዊ ምድረበዳ የማድረግም ፍላጎትና ሕልምም ስላለው ነው።

በውጭ ሃገር ያሉትን የተዋሕዶ ክርስትና ቅርሶች ሁሉ በማስገባት ማውደም፤ ልክ በሱዳን ስደት ላይ የሚገኙትን ጽዮናውያንን ወደ ትግራይ መልሶ እና ወደ ሱዳን ተሰደድው ለመውጣት የሚሹትን ሁሉ ድንበሩን ዘግቶና አፍኖ ለመጨፍጨፍ እንዳቀደው። ልክ አቡነ መርቆርዮስን ከአሜሪካ አስመጥቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የዋቄዮ–አላህ ባሪያው ኢሬቻ በላይ መፈንጫ እንድትሆን እንዳደረገው።

😈 አረመኔው ግራኝ ከ ጨለቖት ሥላሴ የተዘረፈውን ዘውድ ለምን ለማምጣት ፈለገ? አምባሳደሩስ ለምን ከዱት?

ለማንኛውም ይህ በዛሬው በሥሉስ ቅዱስ ዓርብ ዕለት የምናነበው ተዓምር የግራኝ አብዮት አህመድን እና ጭፍሮቹን ማንነት እና እጣ ፈንታቸውን በከፊል ይገልጥልናል።

ቀደም ሲል ጄነራል ጻድቃን አዲስ አበባ እያሉ ለፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ መሪ ለግራኝ አብዮት አህመድ ትግራይን እንዳይተናኮል እና በሕዝቡም ላይ ጦርነት እንዳይከፍት፣ ሕዝቡን ፈጽሞ ማንበርከክ እንደማይቻል መክረውት እንደነበር ሰምተናል። ግራኝ ግን የመለሰላቸው፤ “በገንዘብ እና በጦር ኃይል የማንበረከክ ሕዝብ የለም!” በማለት ነበር መልስ የሰጣቸው።

ጄነራል ጻድቃን እና ባልደረቦቻቸው አሁን ወደ ማንነታቸው ተመልሰዋል ለሥላሴ ይሰግዳሉ፣ ጽዮን ማርያምን ይማጸናሉ የሚል ተስፋ አለኝ። ከዚህ ሁሉ ዕልቂትና ጥፋት በኋላ ዛሬም ይህን ካላደረጉ ግን የትግራይን ሕዝብ ሊመሩት አይችሉምና እነርሱ ለንስሐ የሚያበቃቸውን ገድል ፈጽመው ከአመራርነት በክብር እንዲሰናበቱ ይደረጋሉ፤ ከዚያም የከንቱ ምድራዊ ርዕዮተ ዓለም ባሪያ ያልሆነና ለሕዝቡ የቆመ ጽዮናዊ የሆነ መሪ ይነሳ ዘንድ ግድ ይሆናል።

አንጐት = ጨለቖት

የተረፈው አስተዋዩ፣ ታማኙ ነጋዴ = በቅድስት ሥላሴ ፍቅር የተጠመደ ጽዮናዊ መሪ

😈 በገንዘብ ፍቅር ተታለው ነፋሱ ጠራርጎ ያጠፋቸው ከሃዲዎቹ ነጋዴዎች = ግራኝ አሊ ባባ እና የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮቹ

❖❖❖የሥላሴ ተአምር❖❖❖

. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው በወዳጃቸው…….ላይ ይደርና

የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተአምራታቸው ይህ ነው።

. አንጐት በሚባል አገር ብዙ ነጋዴዎች ነበሩ።

. እኒህ ነጋዴዎች ኢየሩሳሌም ወርደው በሥላሴ ሥዕል እነሆ እንዲህ ሲሉ ተማፀኑ።

. ከሄድንበት ሀገር ከጥልቅ ባሕር መሰጠምና መርዘኛ ከሆነው ከአዞ መበላት ወይም መነከስ ድነን

በሰላም ወደ ቤታችን ብንመለስ።

. እነሆ ከአተረፍነው ትርፍ ወርቅና ብሩን ግማሽ በግማሽ ለሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንሰጣለን ተባባሉ።

. ይህንም ካሉ በኋላ ለንግድ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ወረዱ።

. ወደ መርከብ በገቡ ጊዜ የባሕሩ ማዕበል ፀጥ አለላቸውና የሰላም ጉዞ ሆኖላቸው ተጓዙ።

. በዚህ ጊዜ ከሀገሩ ሰዎች አንዱ እንዲህ አላቸው።

. ይህ ጥልቅ ባሕር ሳያሰጥማችሁ እንደምን ተሻገራችሁ ሰውን የሚውጠው አዞስ እንዴት ሳያገኛችሁ ቀረ አላቸው።እኒህ ነጋዴዎችም በእምነታችን መሠረት በብዙ ወርቅ የሥላሴን መርከብ ተከራየን (ለሥላሴ ብፅዓት አደረግን)

፲፩. ወደ ሀገራችንም በሰላምና በደህንነት ብንመለስ ከገንዘባችን ሁሉ እኩሌታውን ለሥላሴ ቤተ ክርስቲያን

ብፅዓት አድርገን እንሰጣለን ብለናል አሉት።

፲፪. ከጥቂት ቀን በኋላም እኒህ ነጋዴዎች ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በተነሡ ጊዜ ከመካከላቸው አንዱ ነጋዴ

ወንድሞቼ ሆይ ባሕሩን ተሻግረን እዚህ ለመድረስ አስቀድመን የተናገርነውን አንርሳ በማናውቀውም ሀገር

ብዙ ወርቅና ብር አትርፈናልና ብፅዓታችንን ወይም ስእለታችንን እንዳንተው ሲል አሳሰባቸው።

፲፫. አሁንም ወንድምቼ ሆይ በእውነት የምነግራችሁን ስሙኝ እንደ ሥእለታችን ከገንዘባችን ካልሰጠን

ዳግመኛ ለንግድ በምንሄድበት ጊዜ እሊህ ሦስቱ ሥላሴ ገንዘባችንን ሁሉ ያጠፉብናል አላቸው።

፲፬. እነሱ ግን እኛ አንድ ብር እንኳ አንሰጥም አንተ ግን ከፈለግህ ስጥ ለራስህም አንተ ራስህ እወቅ።

፲፭. እኛስ ነገርህን አንሰማም እንደ አንተ ያለም መካሪ አንሻም በሥላሴ ስም ከቶ አልተማፀንምና አሉት።

፲፮. ይህም ነጋዴ ወንድሞቼ ሆይ የተናገራችሁትን ቃል እንዴት ታጥፋላችሁ ወይም እኮ ሰይጣን

ኃላፊና ጠፊ በሚሆን በገንዘብ ፍቅር አታለላችሁ ይሆን አላቸው።

፲፯. ይህ በቅድስት ሥላሴ ፍቅር የተጠመደ ነጋዴም ይህን ተናግሮ ዝም አለ።

፲፰. ከዚህ በኋላ ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ በመርከብ ተሳፈሩ።

፲፱. በዚህ ጊዜ ከነፋሱ ኃይል የተነሣ መርከቡ ተነዋወጠ ሊያሰጥማቸውም ተቃረበ።

. በዚህ ጊዜ መርከቡ ተሠበረና ሰዎቹ በባሕር ውስጥ ሰጠሙ።

፳፩. ይህን ታማኝ ነጋዴ ግን ሥላሴ ከባሕር አውጥተው በባሕር ዳርቻ አስቀመጡት።

፳፪. ከጣፈጠ አነጋገርህ የተነሣ ታማኝ አገልጋይ አደረግንህ አሉት።

፳፫. እንግዲህ የአንተን ገንዘብ አንፈልግም እምነትህ ይበቃናል።

፳፬. እነዚህ ከሐዲዎች ጓደኞችህ ግን በጥልቅ ባሕር ውስጥ እንደሰጠሙ ተመልከት አስተውል አሉት።

፳፭. እንግዲህ አንተ ወደ ምድረ አንጐት ውረድና የሆነውን ነገር ሁሉ ለዘመዶቻቸውና ለቤተ ሰባቸው ሁሉ

ንገር አሉት።

፳፮. ነጋዴውም እናንት የሀገር ታላላቅ አባቶች ሆይ እናንተ እነማን ናችሁ ስማችሁስ ማን ይባላል አላቸው።

፳፯. እነሱም እኛ ዓለሙን ሁሉ የፈጠርን ሥላሴ እንባላለን አሉት።

፳፰. ይህንንም ቃል ከአብና ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ አንደበት በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደስ አለው።

፳፱. የደረሰበትን ነገር ሁሉ ነጋዴዎቹም በከንቱ እንደጠፉና እሱ ግን ሥላሴን በማመን እንደዳነ ለአንጐት ሰዎች

ነገራቸው።

. ይህን የሰሙ ሰዎች ሁሉ ስለ ነጋዴዎቹ የተደረገው ነገር ሁሉ እጅግ አስደናቂ ነው በማለት አደነቁ።

፴፩. በዚህ ጊዜ ይህ ነጋዴ ብሩንና ወርቁን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች በሥላሴ ስም መፀወተ።

፴፪. ኃላፊና ጠፊ ከሚሆን ከዚህ ዓለም ድካም እስከ ዐረፈ ድረስ በየወሩ በ፯ ቀን ይልቁንም በጥርና በሐምሌ ወር

የበዓላቸውን መታሰቢያ አብዝቶ ያደርግ ጀመር።

፴፫. ይቅርታቸውና ሀብተገ ረድኤታቸው ከወዳጃቸው ከ…….ጋር ለዘለዓለሙ ይኑር አሜን።

💭 ቅዳሜ / ጥቅምት ፰/8 ፪ሺ፲፪ / 2012 ዓ.ም ላይ እባቡ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ በትግራይ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻውን ሊጀምር ፩ ዓመት ሲቀረው የጨለቖት ቅድስት ሥላሴ ዘውድ ወደ ትግራይ እንዲመለስ ፈቀደ። እዚያ ክቡር ዘውድ ላይ እጁ ሲያርፍ ሳየው እጅግ በጣም ነበር ያንቀጠቀጠኝና ያስቆጣኝ!

👉 ያኔ የወጣው መረጃ የሚከተለው ነበር፤

/20 ዓመታት በላይ በኔዘርላንድ የቆየው የዘውድ ቅርስ ትግራይ ክልል ለሚገኘው የጨለቆት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተመለሰ

ከመቐለ ፲፮/16 ኪሎ ሜትር በደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኘውና ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረው የሥላሴ ጨለቆት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በርካታ ንዋየ ቅድሳት እንዳሉ ይነገራል። በተለይም ራስ ወልደሥላሴ ለቤተ ክርስትያኑ እልፍ ንዋየ ቅዱሳን ማበርከታቸውን ቤተ ክርስትያኑ ግቢ ውስጥ ለዓመታት የኖሩ አባቶች ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።

ለአሥራ ስድስት ዓመታት መንነው በቤተ ክርስቲያኗ የሚኖሩት የ፹፪/82 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ አባ ገብረሥላሴ፤ ሦስት ዘውዶችን ራስ ወልደሥላሴ ለቤተ ክርስቲያኗ መስጠታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ፲፯፻፵፭–፲፰፻፷፭/1745-1865 በወቅቱ የእንደርታ ዙሪያ የሚባለውን ሰፊ ግዛት ያስተዳደሩት ራስ ወልደሥላሴ በአራት ቦታዎች ማለትም በጨለቆት፣ በሕንጣሎ፣ በፈለግዳዕሮና በመቐለ ቤተ መንግሥቶችን ገንብተው ነበር። በአንድ ወቅትም ጨለቆትን ዋና ከተማቸው አድርገዋታል።

ራስ ወልደሥላሴ ካበረከቷቸው ዘውዶች መካከል አሁን በኔዘርላንድ የተገኘው ዘውድ አንዱ ሲሆን፤ ከ፳/24 ዓመታት በፊት መሰረቁንና ከዚያም መሰወሩን ተናግረዋል።

ከኢትዮጵያ ተሰርቆ የተወሰደው ዘውድ ኔዘርላንድ ውስጥ መገኘቱንና በዛሬው ዕለት ወደ አገሩ መመለሱን ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሳውቀዋል።

ይህ ዘውድ ንብረትነቱ የጨለቆት ሥላሴ መሆኑ የማያጠራጥር በመሆኑ ወደቦታው ተወስዶ በክብር ሊቀመጥ ይገባዋል።”

💭 በቪዲዮው፤

👉 ማክሰኞ/ የካቲት ፳፬/24 ፪ሺ፲፪ / 2012 .

የዘውዱ ሥርዓት አቀባበል በትግራይ

👉 ነሐሴ ፪ሺ፲፫ / 2013 .

በኔዘርላንድስ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሚሊዮን ሳሙኤል አረመኔውን ግራኝ አብዮት አህመድ አሊን ከድተው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ።

👉 በዚሁ ወር ላይ ከሃዲዋ ኦሮሞ ሲልፋን ሃሳን ለኔዘርላንዶች ሦስት ሜዳሊያ ሠረቀችላቸው።

💭 ቀደም ሲል የቀረበ፤

❖❖❖ ጨለቖት ሥላሴ ❖❖❖

😈 በአውሬው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የሚመራው የኦሮማራ አህዛብ ሠአራዊት ለዝርፊያ ከተሰማራባቸው ታሪካዊ ዓብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት አንዱ የደብረ ምሕረት ጨለቖት (ሀገረ ማርያም)ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ነው። ወረድ ብለን እንደምናነበው በረከታቸው ይደርብንና የሃገር ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ከማረፋቸው በፊት በቦታው ላይ ያሉትን በርካታ የታሪክ ቅርሶች የዝመነ መሳፍንት ታሪክና ቅርስ ዝክር እና በዚያ ዘመን ቤተ ክርስቲያን የነበራትን ሕይወት ማስታዋሻ የሆኑ ሐብቶች መጠበቂያ የሚሆን ቤተ መዘክር የማሠራት እቅድ እንደነበራቸውና ይኽውም ከፍተኛ ድጋፍና ማበረታቻ እነሚያስፈልግ ገልጸው በአካል ተለይተውናል። ዛሬ ይዞታው ምን ላይ ይሆን? ታሪካዊ ቅርሶቹስ? የኦሮሞራ ቃኤላውያኑ እነዚህን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ቅርሶች ለመዝረፍ የብዙ ዓመታትና ዘመናት ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ዛሬ በፍሬዎቻቸው አውቀናቸዋል፤ ለዚህ የዘረፋ ተግባር ከኤዶማውያኑ የተማሩትን ስልት እና ጥበብ ተጠቅመዋል፤ የትግርኛን ቋንቋ ማጥናት ችለዋል። ከግራኝ እስከ ጉማሬው ብርሃኑ ነጋ ለፖለቲካው ድራማም ለሌብነቱና ለጭፍጨፋው ያመቻቸው ዘንድ የትግራይ ኢትዮጵያውያን ስነ ልቦና፣ ባሕል፣ ህልም ብሎም የትግርኛን ቋንቋ ሳይቀር በሚገባ አጥንተዋል።

_______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ምስጉን ነው። ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 17, 2021

✝✝✝[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፲፩]✝✝✝

፩ ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ምስጉን ነው።

፪ ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል፤ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።

፫ ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።

፬ ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፤ መሓሪና ይቅር ባይ ጻድቅም ነው።

፭ ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥ በፍርድም ነገሩን ይፈጽማል።

፮ ለዘላለም አይናወጥም፤ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል።

፯ ከክፉ ነገር አይፈራም፤ በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው።

፰ በጠላቶቹ ላይ እስኪያይ ድረስ ልቡ ጽኑ ነው፥ አይፈራም።

፱ በተነ ለችግረኞችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘላለም ዓለም ይኖራል፤ ቀንዱ በክብር ከፍ ከፍ ይላል።

፲ ኃጢአተኛም አይቶ ይቈጣል፥ ጥርሱንም ያፋጫል፥ ይቀልጣልም፤ የኃጢአተኞችም ምኞት ትጠፋለች።

❖ ❖ ❖ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ፤ ሥሉስ ቅዱስ ሆይ በስማችሁ ብዙ ተአምራትን ያደረገና ‘ኮከብ ክብር’ የተባለ የሰማዕታት አለቃ በሚሆን በኃያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ለመፍረድ በልዳ ሀገር የተሰበሰቡትን ፯ (ሰብዓ) ነገሥታትን ደምስሰው እንዳጠፏቸው፡ የተነሱብንን የጽዮንን ተቃዋሚዎች፣ የኔንም/የኛንም ጠላቶች ሁሉ ይደመስሱልን ዘንድ እማፀናለሁ።

የጽዮን ጠላቶች የሆኑትና በጽዮን ልጆች ላይ በጣም ብዙ ግፍ ያደረሱት የዋቄዮአላህ ጭፍሮች እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ተከታይ መንጋው 😈 ሁሉ በመለኮታዊ ሰይፍ ይጨፍጨፉ፣ ነበልባላዊ በሚሆን ቃላችሁ ሥልጣናችሁ ይንደዱ ይቃጠሉ፣ በሲዖል የጨለማ አዝቀት ውስጥ ይዝቀጡ ወይም ይስጠሙ፣ ኅዘን ከላያቸው አይራቅ፣ ትካዜም ከልባቸው አይጥፋ።

የጽዮን ጠላቶች የሆኑትና በጽዮን ልጆች ላይ በጣም ብዙ ግፍ ያደረሱት የዋቄዮአላህ ጭፍሮች እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ተከታይ መንጋው 😈 ሁሉ የአክሱም ጽዮን ኢትዮጵያውያን ከምድረ ገጽ ላይ እንዲጠፉ የሚፈልጉ ናቸውና እነሱን ራሳቸውን እንደቃየልና ይሁዳ በዱርና በበረሃ በታትኗቸውና ሲቅበዘበዙ ይኑሩ።

ያለምንም ጉድለት በሥላሴ ስም ይህን ሦስትነት አምናለሁ፤ ወዳጅ መስለው ጽዮናውያንን በመጠጋት፣ እያታለሉና በየዋሕ እንግዳ ተመስለው አክሱም ጽዮንን ያጠቋትን የጽዮን ጠላቶች የሆኑትና በጽዮን ልጆች ላይ በጣም ብዙ ግፍ ያደረሱት የዋቄዮ-አላህ-አቴቴ ጭፍሮች እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ተከታይ አህዛብ፣ እባብ ገንዳ መንጋው 😈 ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል መቅ ያውርዳቸው፣ በተሣለ የመለኮት ሠይፍ አንገታቸውን ይረደው። አሜን! አሜን! አሜን!❖ ❖ ❖

❖❖❖

ጥንታዊው የደብረ ምሕረት ጨለቖት (ሀገረ ማርያም) ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ፣ ከባቢ መቐለ

፲፯፻፹፭/ 1785 .ም ተመሠረተ ❖❖❖

በ ፲፰/18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተመሰረተው የተለያዩ ነዋያ ቅዱሳትን የያዘው የጨለቖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን

ጨለቖት ትግራይ ክፍለ ሀገር በእንደርታ አውራጃ የሚገኝ ታሪካዊ ቦታ ነው። ይህ ቦታ ከመቀሌ በስተደቡብ ከሕንጣሎ ከተማ በስተሰሜን የሚገን ሲሆን እንደ ሰንሰለት በተያያዙ ተራራዎች የተከበበ ነው። የቦታው አቀማመጥ ወይና ደጋ ስለሆነ የአካባቢው አየር እንደየወቅቱ ይለዋወጣል። በክረምት ቀዝቃዛ ሲሆን በበጋ ወራት ደግሞ በጣም ይሞቃል።

በሰሜንና በደቡብ ጨለቖትን እየከፈለ ከምስራቅ ወይም ምዕራብ የሚፈስ ወንዝ አለ። ወንዙ በክረምት ወራት ይሞላል። በበጋ ግን መጠኑ የቀነሰ ውሃ የሚወርድበት ሲሆን ከሁለት ቦታ እየተነፈሰ ለመስኖ ተግባር ትልቅ አገልግሎት ይሰጣል።

የጨለቖት ነዋሪ ህዝብ ወንዙን ገድቦ የሚዘራቸው የእህል ዓይነቶች በቆሎ፣ ገብስ፣ ጢፍ፣ ስንዴ…የመሳሰሉት ሲሆን ከአትክልትና ፍራ ፍሬ ዓይነትም ጌሾ፣ ሽንኩርት፣ በርበሬ፣ ሎሚና ብርቱካን ወዘተ ተክሎ እያሳደገ ይጠቀማል።

ሀገረ ማርያም ❖

ጨለቖት መጀመሪያ “ሀገረ ማርያም” ይባል ነበር። ሀገረ ማርያም የተባለበት ምክኒያትም በ፲፫/13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩት አፄ ዐምደ ጽዮን ከጨለቖት በላይ ወደ ምስራቅ ባለ በሁለት ዳገት የተከበበ ጉድጓድ ቦታ ቤተ ክርስቲያን ሰርተው ታቦተ ማርያምን አስገብተው ሲያበቁ በዙርያዋ ያለውን መሬት በመስቀልና በዕጣን አስከልለው ያም ማለት መስቀልና ማዕጠነት ተይዞ የተሰጠው ርስት እየተዞረ ለታቦቲቱ አገልጋዮች ካህናት ማደሪያ ሰጥተው ሌሎች ባላባቶቹ ርስታችን ነው ብለው እንዳይካፈሉ በአዋጅና በውግዘት ይህች “ሀገረ ማርያም” ናት ብለው ስለሰየሟት “ሀገረ ማርያም” ተብላለች። ዳግመኛም ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን ይዘው ሲመጡ ጨለቖት ውስጥ ስላደሩ መስቀሉ ያረፈበት ቦታ እስካሁን ድረስ ቤተ መስቀል ይባላል።

ታላቅ ራእይ የተገለጸበት ሱባኤ ❖

መምህር ገብረ ሥላሴ ማዶ ጭኽ በሚባል የቅዱሳን መጸለያ ቦታ ሱባኤ ገብተው ሲጸልዩ ከሰማይ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን እስከሚሠራበት ቦታ ቀስተ ደመና ተተክሎ ሦስት ጌቶች ቅዱሳን መላእክትን አስከትለው ሲወርዱና ቀስተ ደመናው በቆመበት ቦታ ሲያርፍ በራዕይ አዶ እርሳቸውም በሱባኤያቸው ወጥተው ያዩትን አምላካዊ ራእይ ለደጃዝማች ወልደ ሥላሴ ለብቻቸው ነገሯዋቸው። ደጃዝማችም በነገሩ እየተደሰቱ ከመምህር ጋር ሆነው ከሕንጣሎ ከተማ ወደ ሰሜን አቅጣጫ አፍጎል ወደ ሚባለው ቦታ መጥተው ከአደጉበት ጀመሮ እስከ ባሕርያቱ ድረስ በጥድና፣ በወይራ፣ በዋንዛም… የተሸነፈ ታላቅ ወንዝ አገኙ። መምህሩ እየመሩ በጫካው ውስጥ ለውስጥ አብረው ሲጓዙ ወለል ያለ መልክ ባዩ ጊዜ “ዝየ ይትሐነጽ ቤተ እግዚአብሔር”…ማለት የእግዚአብሔር ማመስገኛ ቤተ መቅደስ ከዚህ ይሠራል፤ በዚህ መልክ መካከል ያለው ቆት የሚባለው ትልቅ ዛፍም በጠቅላላ ለቤተ ክርስቲያኑ መዝጊያና መስኮት ይበቃል ብለው ነገርዋቸው።

ያን ጊዜ ቆት በሚባለው ትልቁ ዛፍ ስርም ሁለት አንበሶች ተኝተውበት ነበርና ደጃዝማች ወልደ ሥላሴ ደንግጠው ጦር ወርውረው ሁለቱን ገደሉዋቸው። በዱሩ ውስጥ ተሰውሮ ሲጸልይ የነበረው ባሕታዊ ወጥቶ መላእክት ገደልህ እንጂ እናብስት አልገደልህም ንስሐ ግባ ብሏቸው ተሰወረ። እርሳቸውም መምህራን በወሰኑላቸው ቀኖና መሠረት ኃጢአታቸውን ለማስተሰረይ ንስሐ ገብተናል ከዚህ በኋላ በአዋጅ በተሰበሰበው ሕዝብ ጫካው ተመንጥሮ ቆት የሚባው ትልቁ ዛፍ ተቆረጠ። ቤተ ክርስቲያኑ የሚሠራበት ቦታ ተስተካክሎ ተደለደለ።

የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ መመሥረት ❖

በዘመነ ማቴዎስ ሰኞ መስከረም ፱/9 ቀን 1785 .ም በጠቢባኑ መሪነት ከሦስት ክፍል ተከፍሎና ተለክቶ መሠረቱ ተቆፈረ የመሠረቱ ጥልቀት አስር ሜትር ሆኖ በጥቁር ድንጋይ ከተነጠፈ በኋላ በላይ ላይ አሞሌ ጨው እንደ ብሎኬት ተደርድሮ በንጣፍነት ተሠራ። እንዲህ የተደረገበት ምክንያትም ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራባቸው ዕንጨት ነክ የሆኑ እቃዎችና ዐምደ ወርቆች በምስጥ እንዳይበሉ ለመከላከል ነው። የቤተ ክርስቲያኑ መቅንና መድረክ ገብን መዝጊያ እንዲሁ በልዩ ልዩ ጌጥ የተሠሩ አአማድ የተዘጋጁት ከተቆረጠው ትልቁ የቆት ዛፍ ስለሆነ አናጢዎቹና ሠራተኞቹ ሕዝቡም ሁሉ ዛፍን ጨለቖት እያሉ በትግርና ቋንቋ አደነቁት “ጨለቖት” ማለት በአማርኛ ቋንቋ መልካም ቆት ማለት ነው፤ በብዙ ቀን በኋላም ቃሉን መሠረት በማድረግ ያገሩ ስም ጨለቖት ተብሎ ተጠራ።

የቤተ ክርስቲያኑ ውስጣዊና አፍአዊ ቅርጽ ❖

የቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ክብ ሆኖ በሦስት ክፍል የተከፈለ ነው። ውስጣዊ ክፍል ቤተ መቅደስ መካከለኛው ቅድስት ሦስተኛው ደግሞ ቅኔ ማኅሌት ይባላል። ቤተ መቅደሱ ጸሎተ ቅዳሴ የሚደርስበት ቅዱስ ቁርባንና መስዋዕት የሚቀርብበት ነው። ከቀዳስያን በቀር ሌላ ሰው አይገባበትም። ሁለተኛው ክፍል ቅድስትም ቀሳውስትና ዲያቆናት ሰዓታትና ስብሐተ ፍቁር የሚያደርሱበት ምዕመናንም የኅሊና ጸሎት የሚጸልዩበት ነው። ቅኔ ማህሌቱም ሊቃውንትና መዘመራን ያሬዳዊ ማኅሌት የሚያደርሱበት ምዕመናንም የሚጸልዩበት ነው። በጉልላት ላይም ታላቅ መስቀል አለበት።

ቤተ ክርስቲያኑ ሊሠራ ሲል ወልደ ሥላሴ ታመው ስለነበር ፍጻሜውን ሳያዩ እንዳይሞቱ ከመስጋታቸው የተነሳ ሥራው በተጀመረበት ዓመት እንዲያልቅ ስለወሰኑ ወደ ላይ ያለው ከፍታ ከስፋቱ ጋር የተመዛዘነ አይደለም። ስለዚህ የተፈለገውን ያህል ወደ ላይ ሳይረዝም ባጭሩ ጥራው አልቆ ማክሰኞ ሐምሌ ፬/4 ቀን 1785 .ም ታቦቱ ገባ። የቅዳሴ ቤቱ በዓልም በታላቅ ክብር ከተከበረ በኋላ የቤተ ክርስቲያኑ ስመ ማዕረግ “ደብረ ተድላ” ተብሎ ተሰየመ።

የቤተ መቅደሱ የግድግዳ ላይ ሥዕል ❖

የቤተ ክርስቲያኑ ስዕል የተሳለው ሠዓሊ አለቃ ኃይሉ በተባሉ ባለሙያ ነው። የተሳለውም ከሌላው ቦታ በተለየ መልኩ የመቅደሱና የቅድስቱ የውጭ ግድግዳ በሙሉ ሲሆን በቅድስቱ የውጭ ግድግዳ ዙሪያ የተሳለው አቡቀለምሲስ ዮሐንስ ያየው ራእይ ሁሉ ነው። በተለይም ከመቅደሱ ፊት ለፊት የምስለ ፍቁር ወልዳ ሥዕል ዕፁብ ድንቅ በሆነ ህብረ ቀለም የተሳለ ሲሆን በተለያዩ ጊዜ በመሰሉና ረዘም ያለ ጊዜ በመውሰዱ የራስ ወልደ ሥላሴ ስም አንዳንድ ጊዜ ደጃዝማች አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ራስ እየተባለ ተጽፎአል። በግድግዳው ላይ ብቻ ሳይሆን በየበሮቹ ላይ ያሉት ስዕሎች ሁሉ ሳይቀሩ ለተመልካች እጅግ የሚያስደንቁ ሆኖ ይታያል፡፤ የቤተክርስቲያኑ ሥ ዕልና በመስከረም ወር ፲፱፻፸፮/1976 .ም ተጀመሮ በ፯/7 ዓመታት ተፈጽሟል ይባላል።

የቤተ ክርስቲያኑ ንዋያተ ቅድሳት ❖

ከእንግሊዝ ንጉሥ ጊዮርጊስ ሣልሳዊ በስጦታ የተላኩት የሚከተሉት ናቸው፦

የወይን ዘለላ የተቀረፀበት ባለ መክደኛ ድምፅ

ትልቅ ቋሚ መስቀልና መዝሙረ ዳዊት

የቅዱስ ጊዮርጊስ ምስል ከነፈረሱ

መንገር ታቦት ዘውድና አክሊል

ልዮ ልዩ የዜማ ስልት የሚያሰማ ባለምት ኦርጋኖን

ልብሰ መንግስትና ሌሎችም በወርቅ ያጌጡ ብዙ አልባሳት

ብዙ መስቀሎችና ከዕረፈ መስቀሎቻቸው ጋር

ከእነዚህም አልባሳቱ በወርቅ ያጌጡ እቃዎቹም ከወርቅ የተሠሩ ናቸው። ራስ ወልደ ሥላሴም እነዚህን ስጦታዎች ሁሉ በምስጋና ተቀብለው በፊርማቸው ተረክበዋቸዋል። ከውጭ በመጡ አቡስትሊ በተባሉ ግብፃዊ ጠቢብ የተሠሩ ንዋያተ ቅድሳትም የሚከተሉት ናቸው፦

ክወርቅና ከብር የተሠሩ ዘውዶች

መስቀሎች፣ ፃህልና ጽዋዕ

ከበሮ፣ መቋሚያና ጸናጽል

ልዩ ልዩ ያጌጡ አልባሳትና መነሳነስ

የወይን ማጣሪያ ወንፊት

የወርቅ ዙፋንና ወንበር፣ የሐር ምንጣፎች

ጠቢባኑ እነዚህን ሁሉ ሠርተው ለራስ ወልደ ሥላሴ አስረክበዋቸዋል። እርሳቸውም አይተው እጅግ ደስ ስላላቸው በሚልዮን የሚቆጠር ወርቅ ሸልመዋቸዋል ይባላል።

በቤተ ክርስቲያኑ ቤተ መጻሕፍትም ብዙ መጻሕፍት ይገኛሉ። በተለይም ከመጻሕፍቱ መካከል ሽፋኑ ወይም ገሉ በወርቅ የተለበሰ ወርቅ ወንጌልና የሦስት መቶ ዐስራ ስምንት ሊቃውንት ሥዕል ያለበት ሃይማኖት አበው ይገኙበታል።

መደምደሚያ ❖

የጨለቖት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተሠራው በተደረገው ተአምራትና በተለገጸው ራዕይ መሠረት ነው። በተደረገው ተአምራት መባሉ መምህር ገብረ ሥላሴ የሁለት ቀን ሬማ ጸልየው ካስነሱ በኋላ ደጃዝማች ወልደ ሥላሴን ከእንግዲህ ወደዚህ አይምጡ በከተማዋ የሥላሴን ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ከዚያ ይጸልዩ ብለው ስለመከርዋቸው ነው።

በአሁን ጊዜ የሃገር ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ በቦታው ላይ ያሉትን በርካታ የታሪክ ቅርሶች የዝመነ መሳፍንት ታሪክና ቅርስ ዝክር እና በዚያ ዝመን ቤተ ክርስቲያን የነበራትን ሕይወት ማስታዋሻ የሆኑ ሐብቶች መጠበቂያ የሚሆን ቤተ መዘክር የማሠራት እቅድ ያላቸው ሲሆን ይኽውም ከፍተኛ ድጋፍና ማበረታቻ የሚያስፈልገው ነው። (በረከታቸው ይደርብንና ብፁዕ አባታችን ከማረፋቸው በፊት የተጻፈ ነው)

በተገለጸው ራእይ መባሉም መምህር ገብረ ሥላሴ የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሚሠራበት ቦታ እንዲገለጽላቸው ሱባኤ በገቡ ጊዜ በቀስተ ደመና ምልክት ቦታው ስለታያቸው ነው። (የሉሲፈርን ባለ ሁለት ቀለማት ብቻ እና ባለ አምስት ፈርጥ ኮከብ ያረፈባቸውን ባንዲራ የምትይዙ ትግራዋይን ልብ በሉ! ዋ!)በተአምራትና በራእይ እየተመሩ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ ጥረት ያደረጉ ሁለቱ ሰዎች ራስ ወልደ ሥላሴና መምህር ገብረ ሥላሴ በዘርፍና ባለቤት ሙያ በስመ ሥላሴ መጠራታቸው ቤተ ክርስቲያኑን ለማሠራት መመረጣቸውን ስለሚያመለክት እጅግ ያስደንቃል። ስምን መልአክ ያወጣዋል እንዳሉ (ሉቃ. ፩፥፴፩) ብለው መምህር ያሬድ የታርክ ሐተታቸውን አጠቃሏል።

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: