War in Ethiopia: Holy City Axum Staged Massacre | Guerra na Etiópia Cidade Sagrada Foi Palco de Massacre
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 15, 2021
💭 የብራዚል ሜዲያ፤
በኢትዮጵያ በትግራይ ላይ በሚካሄደው ጦርነት እጅግ አስከፊ ከሆኑት ጭፍጨፋዎች መካከል አንዱ በተቀደሰ መሬት ላይ የተከናወነ ሲሆን ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው አሠርቱ ትእዛዛትን የየዘው ጽላተ ሙሴ ይገኛል ብለው በሚያምኑባት አክሱም ከተማ ውስጥ ነው።
በጣም እሩቅ የሆኑትና እንደ ጃፓን እና ብራዚል የመሳሰሉት ሃገራት ሳይቀሩ በትግራይ እየተካሄደ ስላለው ጭፍጨፋ፣ በአክሱም ስለተፈጸመው ግፍ፣ ስለ አክሱም ጽዮን እና ስለ ሙሴ እንዲህ ያወሳሉ ፥ “ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ክርስቲያን ነኝ” የሚለው ወገን ግን “አለማጣ እርስቴን ካላስመለስኩ፣ ከአረብ እና ቱርክ አህዛብ ጋር አብሬ ተዋሕዶ ትግራዋይን ካልጨፈጨፍኳቸው፣ በረሃብ ካልጨረስኳቸው!” ይላል። ያለማቋረጥ ለዘጠኝ ወር ያህል!
💭 ይገርማል፤ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ባቀረብኩት ቪዲዮ ‘ሙሴን’ እንዲህ በማለት ጠቅሼው ነበር፤
“ሙሴ እግዚአብሔር ላለው ፈጣሪና ገዥ ሕግ የሠራው የ “መገናኛ” ድንኳንም የሚናገረው ስለሁለቱ ፈጣሪና ገዥ የሕግ አካላት ነው። በዚህም የመገናኛ ድንኳን ውስጥ የተገለጠው የረቀቀውና የመጠቀው አንዱና ዋናው መለኮታዊ ምስጢር ደግሞ የሰውን ልጅም ይሁን ዓለማትን(ሥነ–ፍጥረታትን) በመልካቸውና በምሳሌያቸው ለስማቸውና ለክብራቸው የፈጠሩ ሁለት ሕጎች መኖራቸው ነው። በፊተኛይቱም ድንኳን (እስራኤል ዘ–ስጋ/ሐጋር/እስማኤል)መልክ በምሳሌ የተለጠው እጅግ አስፈሪውና አስደንጋጩ እውነት ደግሞ ሳጥናኤል የራሱ የሁኑትን ዓለማትን (ሥነ–ፍጥረታትን ሁሉ)የፈጠረበት ሕግ እና ሥርዓት መሆኑን ማወቅ አለብን።”
💭 One of the worst massacres of the civil war in Ethiopia took place on sacred ground: precisely in a city where Christians believe the ten commandments given by God to Moses are kept.
👉 Courtesy: Band Jornalismo
________________________________
Leave a Reply