እግዚአብሔር መልስ አለው! | የኢትዮጵያ ሰማይ በማርያም መቀነት ተከበበ | ድንቅ ነው!
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 17, 2020
ጌታችን ሲሰቀል ፀሐይ ጨለመች፣ ጨረቃ ደም ኾነች፤ ክዋክብትም ረገፉ ፥ ዛሬ ከ፪ሺ፲፪ ዓመታት በኋላ በዕለተ ስቅለት ዝናብ እና ደመና በሌለበት የቅድስት እናቱን መቀነት አሳየን። ታዲያ ይህ ድንቅ ተዓምር አይደለምን?! ነው እንጂ!
አዎ! አውሬው በእመቤታችን የአሥራት ሃገር ሊነግሥና የልጇን ደምና ስጋ ለመከልከል ሲቃጣና ሲደፍር ይታያል። ኢትዮጵያውያንን አግቶ ሲሳለቅ፣ ኢትዮጵያውያንን ከእስማኤላውያን ሃገራት አምጥቶ እንደ ከብት አውቶብስ ውስጥ እየጫነ በንቀት ከአዲስ አበባ ሲጠርፍ ፣ ለሁለት ወር ሲጾሙና ሲሰግዱ የቆዩትን ኢትዮጵያውያንን በፋሲካ ዋዜማ ከስራቸው ሲያባርር እና እናቶችን ቤት–አልባ አድርጎ ወደ መንገድ ሲጥላቸው፤ እግዚአብሔር አምላክ መልሱን በሰማይ ሰጠ። ዋ! ለዲያብሎስ የግብር ልጆች! ዋ!
ትክክለኛዋና ብቸኛዋ የእግዚአብሔር ሃይማኖት በተዓምር፣ በማርያም መቀነት / በቀስተ ደመና የታጀበች እምዬ ኦርቶዶክስ ፥ አድዋ ዘምታ ጊዮርጊስ ድል ያደረገላት፣ መከላከያ ሚንስትሯ ጊዮርጊስ የሆነ፣ ጳጳሳቷ ለአገር የሞቱ፣ አንድነት የምትሰብክ፣ የድኾች መጠጊያ፣ ፀበሏ የሚፈውስ፣ እምነቷ የሚፈውስ፣ ደመራዋ የሚያምር፣ ጥምቀቷ የሚያምር፣ አፅዋማቷ የሚያምሩ፣ ሥርዓቷ፣ መጻሕፍቷ፣ ገዳማቷ፣ ውቅር ዓብያተክርስቲያናቷ፣ የካህናቱ ዝማሬው፣ ቅኔው፣ ማሕሌቱ፣ ቅዳሴው፣ አለባበሳችን ፥ ሁሉ ነገራችን እንደ ኦርቶዶክሶች የሚያምርና የሚያስገርም የለም። አውሬው ግን በዚህ ይቀናል፣ ይበሳጫል ፥ ስለዚህ በተፈቀደለት በዚህ አጭር ዘመን ይህን የእግዚአብሔር ስጦታ ለመንጠቅ ሌት ተቀን በመወራጨት ላይ ይገኛል። አንድ የዝሆን እርምጃ ወደፊት ሲራመድ እግዚአብሔር ማስጠንቀቂያውን ይሰጠዋል።
ይህ የማርያም መቀነት ኃይለኛ ምልክት ነው! ተመሳሳይ የማስጠንቀቂያ ምልክት ለቅሌታሙ የግብረ–ሰዶማውያን ልዑክ ለባራክ ሁሴን ኦባማም ከአምስት ዓመታት በፊት ልክ የኢትዮጵያን ምድር ሲረግጥ ተሰጥቶት ነበር።
አገር ቤት ያላችሁ የተዋሕዶ ልጆች የማርያም መቀነትን አይታችሁታል፤ ኮሮኖ የሚባል ቫይረስ በኢትዮጵያ የለም! እግዚአብሔርን እንጅ ሌላ ማንንም/ምንንንም አትፍሩ! ባካችሁ የማንንም ፈቃድ ሳትጠይቁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሂዱ! መላው ዓለም “ኢትዮጵያውያኖች ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዱን?” ብሎ በመጠየቅ ላይ ነው። ባለፈው ሳምንትም ተናግሬው ነበር፤ ይህ ሌላ ጊዜ ተመልሶ የማይመጣ ልዩ አጋጣሚ ነው! በዚህ ጊዜ ከተሰቀለላችሁ አምላካችሁ ጋር ካልሆናቻሁ መቼ?! ለብርሃነ ትንሣኤ ቤተ ክርስቲያንን አጥለቅልቋት!
Leave a Reply