Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2020
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    27282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 18th, 2020

ተዓምረ ቀዳሚት ሥዑር በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ | የማያቃጥለው ቅዱስ እሳት በጌታ መካነ መቃብር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 18, 2020

በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በቀራንዮ ጎልጎታ የጌታ መካነ መቃብር በሚገኝበት ቅዱስ ቤተክርስትያን ውስጥ እያንዳንዱ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በዛሬው የቀዳሚት ሥዑር / ቅዱስ ቅዳሜ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኢየሱስ መቃብር ዙሪያ በተዓምር የሚወርደውን“ነበልባል” ለመመልከት ይሰበሰባሉ፡፡

የእግዚአብሔር እጅግ አስደናቂ ከሆኑት ተዓምራት ውስጥ አንዱ ይህ በቀዳሚት ሥዑር በኢየሩሳሌም በጌታችን መካነ መቃብር ላይ የሚወርደው የተባረከ/ቅዱስ እሳት ነው።

የምስራቅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ይህ የትንሳኤ ጉልህ ምልክት ነው ብለው ያምናሉ።

ይህ ዋና ከሆኑት የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተዓምራት መካከል አንዱ ነው። ይህ ተዓምር ላለፉት 1,200 ዓመታት በየዓመቱ እየተከሰተ እንደሆነ ይታመናል።

ሥነ ሥርዓቱ የሚጀምረው በግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ (ወይም በሌላ የኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ) በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ወደ ክርስቶስ ባዶ መካነ መቃብር ወርዶ ልዩ ጸሎቶችን በማንበብ ነው። ኦርቶዶክስ ያልሆነ ክርስቲያን ደግሞ ፓትርያርኩ ሻማዎቹን ለማብራት የሚጠቀሙባቸው የነዳጅ ዘይት መብራቶች በውስጣቸው እንዳይቃጠሉ ለማድረግ መቃብር (አነስተኛ መቃብር ዙሪያ ያለውን ትንሽ መዋቅር) እንደሚመረምሩ ተገልጻል ፡፡

ከመቃብሩ በላይ እና በዙሪያው በተከበበች ቤተክርስቲያን ውስጥ ፣ ምዕመናን በአንድ ድምፅ “ኪራላይሶን”(እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ!)ያሰማሉ፡፡ ቆይታው ረጅም ወይም አጭር ሊሆን ይችላል ግን ውሎ አድሮ ፓትርያርኩ ለብቻቸው በሚጸልዩበት መቃብር ላይ እንደሚታዩ ይነገራል ፡፡ ከዛም ፓትርያርኩ ከዚህ ተዓምራዊ ነበልባል ሻማዎቹን በማቀጣጠል ደወሎችን እየደወሉ በምዕመናኑ መካከል ተገኝተው እሳቱን ወደ ሌሎች ቀሳውስት ያስተላልፋሉ፡፡ በዚህ ወቅት ጨለማ የነበረው የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ በተዓምራዊው የተባረክ/ ቅዱስ እሳት ያበራል፡፡

ለመጀመሪያዎቹ በርካታ ደቂቃዎች እሳቱ ይቀጣጠላል ነገር ግን አይባላም ፡፡ በዚህን ጊዜ ፣ ብዙ ምዕመናን ፊታቸውን እና እጆቻቸውን ሳይቃጠሉና ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በእሳቱ ነበልባል ውስጥ ይታጠባሉ፡፡ እሳቱ ከሻማ ወደ ሻማ ከተላለፈ በኋላ በሩቅ በሰፊው እንዲሰራጭ በመብራት ሳጥን ውስጥ ይቀመጣል፡፡

________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አውሬው ቤተክርስቲያንን ለጌታ ቍርባን ዘግቶ በ666 የተከተቡትን ዶሮዎች እንድትገዙ ገበያዎችን ፈቀደ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 18, 2020

እርግብ እና በግ ታሥረዋልን?!

ከሁለት ሣምንታት በፊት ታዋቂው የአሜሪካ የዜና ድሕረ ገጽ “Breitbart News“ „Devout Ethiopians Defy Coronavirus Ban on Large Gatherings, Religious leaders have failed to cancel congregational meetings in Ethiopia, despite government orders to limit large gatherings amid the Chinese coronavirus outbreak in the country“ብርቱ ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት የወጣውን የትላልቅ ስብሰባዎችን እገዳን በመቃወም ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሄዱ ነው ፤ የሃገሪቱ መሪዎች በሀገሪቱ ውስጥ በተከሰተው የቻይና ኮሮኔቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ትላልቅ ስብሰባዎችን እንዲገድቡ ትእዛዝ ቢሰጥም የሃይማኖት መሪዎች ግን በኢትዮጵያ ውስጥ የጉባኤ ስብሰባዎችን ይሰርዙ ዘንድ አልተሳካም፡፡” የሚለውን መረጃ አውጥቶ ነበር። በማግስቱ ነበር ከቤተ ክህነት በኩል ክልከላው የጸደቀው። ይህ ሜዲያ ኢትዮጵያን የተመለከተ መረጃዎችን አዘውትሮ አያቀርብም፤ ይህን ዜና ግን ለማውጣት ግን ቸኩሎ ነበር።

የቤተ ክርስቲያናችንን እንቅስቃሴ በደንብ ነው የሚከታተሉት፤ በዕለተ ስቅለት የተነሳው ይህ ቪዲዮ ላይ የሚታየውን ዓይነት ብርቱ የሆነ የእምነት ፍቅርና ጽናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ ብቻ እንደሚታይ የአውሬው ዓለም እያየው ነው። እናት፣ አባት፣ ህፃናት ከጥዋት እስከ ማታ ለጌታቸው ሲሰግዱ፣ ካህናትና ቀሳውስትም ሌሊቱን ሙሉ ቆመው የሚቀጥለውንም ቀን ያለማቋረጥ በሥርዓተ ጸሎትና ቅዳሴ ሲያሳልፉ የሚታዩባት ብቸኛ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብቻ ናት። ለመሆኑ በፕሮቴስታንቶች በተለይም በእስላሞች ዘንድ ሕፃናት ወደ አምልኮ ቦታዎች ሲሄዱ አይታችሁ ታውቃላችሁን? እኔ አልገጠመኝም።

አውሬው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በጣም ይቀናል! ለዚህም ነው ልክ ፪ሺ፲፪/ 2012 ዓመተ ምሕረትን ጠብቆ፣ ልክ የሑዳዴ ጾም ሲገባ የኮሮና ቫይረስን ዓየር ላይ የለቀቀው። የአውሬው አምላኪዎች የሆኑት መሀመድውያንም ልክ ፋሲካ ሲገባደድ ረመዳናቸውን መጀመራችውም አውሬው ይህችን ዓመተ ምሕረት በጉጉት ሲጠብቅት እንደነበር ይጠቁመናል።

የአውሬው ተቀዳሚ ዓላማው ሕዝበ ክርስቲያኑን ከክርስቶስ ደም እና ስጋ እንዲሁም ከጥምቀት ማራቅ ነው። ይህንም በግልጽ እያየነው ነው። የተዋሕዶ ልጆች ስጋና ደሙን “በነጻ” እንዳይቀበሉ ቤተ ክርስቲያንን በሠራዊቱ አሳጠረ ፤ ፋሲካ ሲቃረብ ገበያዎቹን ከፍቶና የ”አበሻ” ዶሮዎችንና እንቁላሎችን አጥፍቶ በአውሬው መንፈስ የተበከሉትን የአላሙዲን ኤልፎራ ዶሮዎች ክርስቲያኑ ሺህ ብር እየከፈለ እንዲገዛና ለአውሬው የደም መስዋዕት እንዲያደርግለት ፣ እግረ መንገዱንም የዶሮውን ስጋና እንቁላል ተመግቦ በአጋንንት እንዲታሠር ያደርጋል። ይህ ግልጽ የሆነ የዲያብሎስ አካሄድ አይደለምን? በደንብ እንጅ!

የሚከትሉትን ቀናት በጥሞና እንከታተል፤ ፋሲካ ካለፈ በኋላ የአውሬው መንግስት መስጊዶችን ለስግደት ቢፈቅድ አይግረመን!

አሁን ግን አገር ቤት ያላችሁ የተዋሕዶ ልጆች ትናንትና የማርያም መቀነትን አይታችሁታልና ወደ ቤተ ክርስቲያን ተሰባስባችሁ አምሩ። የማርይም መቀነቱ “ወደኔ ኑ! ምንም አትሆኑም!” የሚለውኝ ምልክት ነው ያሳያችሁ! በዚህ በትንሣኤ ወቅት ኮሮኖ የተባለው ቫይረስ ቤተ ክርስቲያን ድርሽ አይልም! እግዚአብሔርን እንጅ ሌላ ማንንም/ምንንንም አትፍሩ! አባታችንን አብርሃምንና ይስሐቅን አስታውሱ! አሁን ትንሽ ሰዓት ነው የቀረውና ባካችሁ የማንንም ፈቃድ ሳትጠይቁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሂዱ! መላው ዓለም “ኢትዮጵያውያኖች ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዱን?” ብሎ በመጠየቅ ላይ ነው። ባለፈው ሳምንትም ተናግሬው ነበር፤ ይህ ሌላ ጊዜ ተመልሶ የማይመጣ ልዩ አጋጣሚ ነው! በዚህ ጊዜ ከተሰቀለላችሁ አምላካችሁ ጋር ካልሆናቻሁ መቼ?! ለብርሃነ ትንሣኤ ቤተ ክርስቲያንን አጥለቅልቋት!

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: