ወገኖቼ፡ በእነዚህ የፈተና ቀናት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሂዱና ልክ ቪዲዮው ላይ እነድሚታየው (ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን) ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስገዱለት፣ ግቢዋን ሙሏት ፥ የተገረፈልንን፣ የተሰቀለልንና የሞተልንን አምላካችንን እናስደስተው፣ ዓለምን አናሳፍሯት፤ የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ግቢዎች ለዚህ ዘመን የተዘጋጁ አመቺና የተቀደሱ ናቸው፣ የምን ወረርሽኝ! የምን ኮሮና! ሁሉም ነገራቸው ከዲያብሎስ የመጣ ቅጥፈት ነው፤ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ የማታለያ ድራማ ነው፤ የምን እገዳ! የእገዳ ትዕዛዝ ደግሞ ከእግዚአብሔር ብቻ ካልሆነ ጠላታችሁ ከሆነው መንግስት ተብየው ከመጣ አትቀበሉት፣ እምቢ በሏቸው! አምጹ! አላያችሁም ትናንትና በሺ የሚቆጠሩትን ወገኖችን ከሳውዲ አረቢያ ወደ አዲስ አበባ በአውሮፕላን ከዚያም በአውቶብሶች እንደ ከብት ጭነው ወደ ባሕር ዳር ሲልኳቸው?! አያችሁ አይደል! ኮሮና የሚባል ወረርሽኝ በኢትዮጵያ የለም! ካለም፤ ወሮበላው መንግስት ከቻይና እና አረቢያ በበርሚል ጭኖ ያስገባው ብቻ ነው። ወገኖቼ፤ እግዚአብሔርን እንጅ የእግዚአብሔር ያለሆነውን መንግስት መፍራትና መታዘዝ የለባችሁም። ስለዚህ አሁን እግዚአብሔር አምላክ ሁልጊዜ ወደ ቤተ መቅደሱ እንድትመጡለት መሻቱን አውቃችሁ፤ በተለይ በዚህ የሕማማት ሣምንት ቤተ ክርስቲያንን ሙሏት። እግዚአብሔር እረኛችን፣ ብርኃናችንና መድኃኒታችን ስለሆነ የሚያስፈራን የለም!
[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፫]
፩ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
፪ በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
፫ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
፬ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።