Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2020
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    27282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 17th, 2020

እግዚአብሔር መልስ አለው! | የኢትዮጵያ ሰማይ በማርያም መቀነት ተከበበ | ድንቅ ነው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 17, 2020

ጌታችን ሲሰቀል ፀሐይ ጨለመች፣ ጨረቃ ደም ኾነች፤ ክዋክብትም ረገፉ ፥ ዛሬ ከ፪ሺ፲፪ ዓመታት በኋላ በዕለተ ስቅለት ዝናብ እና ደመና በሌለበት የቅድስት እናቱን መቀነት አሳየን። ታዲያ ይህ ድንቅ ተዓምር አይደለምን?! ነው እንጂ!

አዎ! አውሬው በእመቤታችን የአሥራት ሃገር ሊነግሥና የልጇን ደምና ስጋ ለመከልከል ሲቃጣና ሲደፍር ይታያል። ኢትዮጵያውያንን አግቶ ሲሳለቅ፣ ኢትዮጵያውያንን ከእስማኤላውያን ሃገራት አምጥቶ እንደ ከብት አውቶብስ ውስጥ እየጫነ በንቀት ከአዲስ አበባ ሲጠርፍ ፣ ለሁለት ወር ሲጾሙና ሲሰግዱ የቆዩትን ኢትዮጵያውያንን በፋሲካ ዋዜማ ከስራቸው ሲያባርር እና እናቶችን ቤትአልባ አድርጎ ወደ መንገድ ሲጥላቸው፤ እግዚአብሔር አምላክ መልሱን በሰማይ ሰጠ። ዋ! ለዲያብሎስ የግብር ልጆች! !

ትክክለኛዋና ብቸኛዋ የእግዚአብሔር ሃይማኖት በተዓምር፣ በማርያም መቀነት / በቀስተ ደመና የታጀበች እምዬ ኦርቶዶክስ ፥ አድዋ ዘምታ ጊዮርጊስ ድል ያደረገላት፣ መከላከያ ሚንስትሯ ጊዮርጊስ የሆነ፣ ጳጳሳቷ ለአገር የሞቱ፣ አንድነት የምትሰብክ፣ የድኾች መጠጊያ፣ ፀበሏ የሚፈውስ፣ እምነቷ የሚፈውስ፣ ደመራዋ የሚያምር፣ ጥምቀቷ የሚያምር፣ አፅዋማቷ የሚያምሩ፣ ሥርዓቷ፣ መጻሕፍቷ፣ ገዳማቷ፣ ውቅር ዓብያተክርስቲያናቷ፣ የካህናቱ ዝማሬው፣ ቅኔው፣ ማሕሌቱ፣ ቅዳሴው፣ አለባበሳችን ፥ ሁሉ ነገራችን እንደ ኦርቶዶክሶች የሚያምርና የሚያስገርም የለም። አውሬው ግን በዚህ ይቀናል፣ ይበሳጫል ፥ ስለዚህ በተፈቀደለት በዚህ አጭር ዘመን ይህን የእግዚአብሔር ስጦታ ለመንጠቅ ሌት ተቀን በመወራጨት ላይ ይገኛል። አንድ የዝሆን እርምጃ ወደፊት ሲራመድ እግዚአብሔር ማስጠንቀቂያውን ይሰጠዋል።

ይህ የማርያም መቀነት ኃይለኛ ምልክት ነው! ተመሳሳይ የማስጠንቀቂያ ምልክት ለቅሌታሙ የግብረሰዶማውያን ልዑክ ለባራክ ሁሴን ኦባማም ከአምስት ዓመታት በፊት ልክ የኢትዮጵያን ምድር ሲረግጥ ተሰጥቶት ነበር።

አገር ቤት ያላችሁ የተዋሕዶ ልጆች የማርያም መቀነትን አይታችሁታል፤ ኮሮኖ የሚባል ቫይረስ በኢትዮጵያ የለም! እግዚአብሔርን እንጅ ሌላ ማንንም/ምንንንም አትፍሩ! ባካችሁ የማንንም ፈቃድ ሳትጠይቁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሂዱ! መላው ዓለም “ኢትዮጵያውያኖች ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዱን?” ብሎ በመጠየቅ ላይ ነው። ባለፈው ሳምንትም ተናግሬው ነበር፤ ይህ ሌላ ጊዜ ተመልሶ የማይመጣ ልዩ አጋጣሚ ነው! በዚህ ጊዜ ከተሰቀለላችሁ አምላካችሁ ጋር ካልሆናቻሁ መቼ?! ለብርሃነ ትንሣኤ ቤተ ክርስቲያንን አጥለቅልቋት!

+____________________________________+

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 17, 2020

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡

👉 ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል

  • . ፀሐይ ጨለመ፤
  • . ጨረቃ ደም ኾነ፤
  • . ከዋክብት ረገፉ፤
  • . የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤
  • . አለቶች ተፈረካከሱ፤
  • . መቃብራት ተከፈቱ፤
  • . ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩፶፬)

👉 ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል

  • . “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)”
  • . “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ
  • . “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው
  • . እመቤታችንን ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ ደቀ መዝሙሩንም እናትህ እነኋትበማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤
  • . አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ
  • . ተጠማሁ
  • . ዅሉ ተፈጸመ (ማቴ. ፳፯፥፵፭፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲)፡፡

+_______________________________+

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: