Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 5, 2020
ከመደበኛ ወደ ኮንትራት በረራ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኒው ኦርሊንስ መደበኛ በረራ የለውም። ዛሬ ግን አራት አውሮፕላኖች የከተማዋን አየር ማረፊያ ሞልተውት ታይተዋል። አየር መንገዱ ከመደበኛ በረራ ወደ ቻርተር/ኮንትራት በረራ ተሸጋግሯል ማለት ነው።
በደቡቡ ዩ.ኤስ.አሜሪካ ሉዊዚያና ግዛት የምትገኘዋ ኒው ኦርሊንስ በፈረንሳዮች የተቆረቆረች ሲሆን በአፍሪቃውያን የባርነት ንግድ ዘመን ከፍተኛ ሚና የተጫወተች ከተማ ናት። ከተማዋ መጀመሪያ የምትታወቀው በጃዝ ሙዚቃ ነበር፤ ቀስበቀስ ግን የስካር፣ የሽርሙጥና፣ የዕጽ ተገዢዎችና የግብረ–ሰዶማውያን መናኸሪያ ለመሆን በቅታለች። ለዚህም ይመስላል እ.አ.አ በ2005 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ተራሮች የተነሳው ምስጢራዊ ነፋስ “ካትሪና” የተባለውን ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ሠርቶ ኒው ኦርሊንስ ክፉኛ የመታት። 1400 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በ90ቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረትም ወድሞ ነበር። ካትሪና – ኮሮና
በዛሬው ዕለት እንደታወቀው ኒው ኦርሊንስ በኮሮና ወረርሽ ከኒው ዮርክ ቀጥላ እየተጠቃች ያለች ከተማ ለመሆን በቅታለች።
ሆን ተብሎ ይመስላል፤ አየር መንገዳችንም ኮሮናን ተክትሎ መብረሩን ቀጥሏል። ይህ ለገንዘብ ብቻ ተብሎ የሚደረግ ነገር አይደለም፤ ከበስተጀርባው እጅግ በጣም ከፍተኛ ተንኮል አለ።
____________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Health | Tagged: ሀሪኬን ካትሪና, ሉሲፈር, ባዮ-መሳሪያ, ኒው ኦርሊንስ, አሜሪካ, አሜሪካውያን, ኢትዮጵያ, ኮሮናቫይረስ, ወረርሽኝ, የሳጥናኤል ሴራ, የኢትዮጵያ አየር መንገድ, የኮንትራት በረራ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 5, 2020
[፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ ፭፥፰]
“ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።”
ብዙዎች በሃይማኖት ከሚመሳሰሏቸው ጋር በማበርና አንድ ከመሆን ይልቅ ለጠላቶቻቸው ሲቆሙና ድጋፍ ሲሰጡ ይታያሉ። ይህ ትልቅ ስህተት ነው! የተዋሕዶ ልጅ ከሌሎች ማስቀደም ያለበት እንደርሱ ተዋሕዶ የሆኑትን ወገኖቹን ብሎም በተለየ መልክ መልካም አያያዝ ሊያደርግ የሚገባው ለመድኃኔ ዓለም ልጆች መሆን አለበት ፤ በተለይ በዚህ ከማይመስሉን ሁሉ መራቅ በሚገባን ዘመን። ማንነታቸውን ባለማወቅ ወይም እራሳቸውን በመጥላት፣ ወይም በምዕራቡ ለብ ለብ ለዘብተኝነት ስልተወሰዱና መሃል–ስፋሪያዊ ማንነት በመያዛቸው “ሁሉን አቃፊ” ለመሆን ሲወራጩ ይታያሉ። “ገለልተኝነት”፣ “ሚዛናዊነት” እና “ሁሉን አቃፊነት” ከላይ ቆንጆ የሚመስሉ ነገር ግን ውስጣቸው ከንቱ የሆኑና በዓላማ–የለሽኝነት ላይ የተመረኮዙና በስንፍና ቅመም የተከለሱ የለዘብተኛነት መገለጫ ከኮሮና የከፉ በሽታዎች ናቸው። አንድ ዜጋ ወይ ኢትዮጵያዊ ነው ወይም አይደለም ፥ ወይ ከተዋሕዶ ነው ወይም አይደለም ፥ ወይ ጥሩ ወይም መጥፎ ፥ ወይ በስትግራ ፣ ወይም በስተቀኝ ፥ ወይ በራድ ወይም ትኩስ ፣ ወይ ከእውነት ጋር ወይም ከሐስት ጋር ፥ ወይ ከበጉ ጋር ወይም ከፍየሎች ጋር ፥ ወይ ከመድኃኔ ዓለም ጋር ወይም ከዋቄዮ–አላህ/አዱኛ ፈይሳ ጋር።
አህዛብ የዋቄዮ–አላህ ልጆች ምንም እንኳን ፍቅረ–ቢሶችና ብቻቸውንም ሲቀሩ እርስበርስ የሚነካከሱ ግብዞች ቢሆኑም ቅሉ ለጋራ ግባቸው ሲሉ ግን እርስበርስ ሲተባበሩ ይታያሉ፤ ነገራቸው ሁሉ በጥላቻ ላይ የተመረኮዘ ቢሆንም ግን ለዓላማቸው ሲሉ በአንድነት ይቆማሉ። ዓላማቸው ኢትዮጵያን፣ ተዋሕዶ ባሕሏን፣ ቁንቋዋን እና ሃይማኖቷን ለማጥፋት ስለሆነ ኢትዮጵያና አምላኳ እስካሉ ድረስ ከዚህ ዓላማቸው ፎቀቅ አይሉም። ልክ እንደ ነቀርሳ፤ የሚመገበው ጤናማ ሕዋሳት እስካሉ ድረስ እነርሱን እይተመገበ ይስፋፋል፤ ጤናማው ህዋሳት ሲያልቅ ነቀርሳው እራሱን በልቶ ይጠፋል።
የዘመናችን ተዋሕዷውያን ተገቢ በሆነ መልክ እርስበርስ እንዳይተባበሩና የራሳቸው የሆነውን ነገር ሁሉ እንዳያስቀድሙ እንቅፋት የሆኑባቸው ነገሮች፦ ማንነታቸውን በሚገባ አለመገንዘባቸው፣ መድኃኔ ዓለም የሰጣቸውን ፀጋና በረከት ዋጋ ባለማወቃቸው፣ ሃገራቸውና ሃይማኖታቸው ያሰቀመጧቸውን ተልዕኮዎችና ዓላማዎች ባለመከተላቸው እንዲሁም የአምላካቸውንና የራሳቸውን ጠላት በብልጠት እንዲያውቁ ባለመፍቀዳቸው ብሎም ለመዋጋት ቁርጠኝነት ባለማሳየታቸው ነው።
እስኪ እናስበው፤ የዋቄዮ–አላህ ልጆች ፍቅር–አልባ በሆነ የጥላቻ መንፈስ ተነሳስተው ዲያብሎሳዊ አላማዎቻቸውን ሁሉ ለጊዜውም ቢሆን አንድ ባንድ በማሳካት ላይ ናቸው ፥ በሌላ በኩል፡ በፍቅር የተሞሉት የመድኃኔ ዓለም ልጆች ኃያሉን አምላካቸውን አጥብቀው በመያዝና ቅዱሳን ሠራዊቱንም ከጎናቸው በማሰለፍ እርስበርስ እየተሳሰቡና እየተደጋገፉ በአንድ ዓላማ ቢኖሩ ምን ያህል መሬት አንቀጥቅጥ ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ። እስኪ እናስበው! አዎ! የመድኃኔ ዓለም ጠላት የሆኑት የዋቄዮ–አላህ ልጆች 150 ዓመት አይደለም አንድ ቀን እንኳን አይቆዩም ነበር።
___________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሃይማኖት, መድሐኔ ዓለም, ቤተክርስቲያን, ቦሌ መድኃኔ ዓለም, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ወንድማማችነት, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ፪ሺ፲፪, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »