“የዲያቆን ቢንያም ፍሬው አሰቃቂ እና አሳዛኝ ታሪክ” ከሚለው የተወሰደ(ሙሉውን በቅርቡ እናቀርበዋለን)
ኢትዮጵያ ለዚህ ውርደት እና ጥልቅ ዝቅጠት መብቃቷ በጣም አስከፊ የሆነ መቅሰፍት እየመጣ እንደሆነ ይጠቁመናል።
የሲዖል ልዑካን ኢየሱስ ክርስቶስንም በተወለደባት ሃገር፣ በፈጠራት ምድር ሰቅለውታል። እናንተን አያድርገኝ፤ አቤት የሚጠብቃችሁ የእሳት ወለፈን!
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2020
“የዲያቆን ቢንያም ፍሬው አሰቃቂ እና አሳዛኝ ታሪክ” ከሚለው የተወሰደ(ሙሉውን በቅርቡ እናቀርበዋለን)
ኢትዮጵያ ለዚህ ውርደት እና ጥልቅ ዝቅጠት መብቃቷ በጣም አስከፊ የሆነ መቅሰፍት እየመጣ እንደሆነ ይጠቁመናል።
የሲዖል ልዑካን ኢየሱስ ክርስቶስንም በተወለደባት ሃገር፣ በፈጠራት ምድር ሰቅለውታል። እናንተን አያድርገኝ፤ አቤት የሚጠብቃችሁ የእሳት ወለፈን!
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: መሀመዳውያን, ስደት, ኢትዮጵያ, ክርስትና, ክትትል, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ዲያቆን ቢንያም ፍሬው, ግፍ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2020
የቢል ጌትስ ባለቤት መሊንዳ ጌትስ፤ ስለ በሽታና ሞት እያወራች ትስቃለች፤ እንዲህም ትላለች፦
ክትባት፣ ክትባት፣ ክትባት ሌላ መፍትሔ የለም!!!“አፍሪቃውያንን” እኛ መርፌ ካልወጋናቸው ተስፋ የላቸውም። ልክ እንደ ኤኩዋዶር በቅርቡ በአፍሪካም ሬሳዎች በመንገድ ላይ እንደ ቆሻሻ ይወረወራሉ። የአፍሪቃ ወላጆች ጭንቀት እንቅልፍ ይነሳኛል።
“ማማ አፍሪቃ” መሆኗ ነው። ባሏ ቢል ከማይክሮሶፍት ኃላፊነቱ የተሰናበተው ያለ ምክኒያት አልነበረም። ተመልከቱ፤ በአፍሪቃ 54 አገራት አሉ፤ እነዚህ አገራት በመልክ ዓምድር፣ በአየር ጸባይ፣ በታሪክ፣ በባሕል፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በምጣኔ ሃብት እጅግ በጣም የተለያዩ አገራት ናቸው፤ ነገር ግን ሁሉም እንደ አንድ ሃገር “አፍሪቃ” እያሉ መጥራቱን ይመርጣሉ፤ እንደነርሱ፤ አፍሪቃ አህጉር ሳትሆን አንድ አገር ናት።
የሚገርመው ግን አፍሪቃ በኮሮና እምብዛም ያልተጠቃችው ብቸኛዋ አህጉር መሆኗ ነው። ይህ ደግሞ በጣም ያንገፈግፋቸዋል። ሁሉም የሚጠይቁት “ኮሮና በአፍሪቃ የኛን ያህል ለምን አልተስፋፋም?” የሚለውን ቅናትና ጥላቻ የተሞላበትን ጥያቄ ነው። እግዚአብሔር የአፍሪቃ ሃገራትን ይጠብቃቸው እንጂ ከዚህ በፊትም እንዳወሳሁት በአፍሪቃ ኮሮናን የመሰለ ወረርሽኝ ከተቀሰቀስ(ማድረጋቸውም አይቀርም) እነዚህ አረመኔዎች ለጉብኝትና አደን የሚቋምጡላቸውን የዱር አራዊቱን አስቀርተው መላውን አህጉር ከመጨፍጨፍ እንደማያመነቱ እርግጠኛ መሆን ይቻላል። ሰሞኑን በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ የተቀሰቀሰው የጥቃት ዘመቻ ይህንን ነው የሚጠቁመን።
Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia, Health | Tagged: ሉሲፈር, መሊንዳ ጌትስ, መንግስት, ማይክሮሶፍት, ቢል ጌትስ, አፍሪቃ, ክትባት, ኮሮና ቫይረስ, ዘር ማጥፋት, የህዝብ ቁጥር ቅነሳ, የክርስቶስ ተቃዋሚ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2020
ባለፈው ሳምንት ሐምራዊቷን የፋሲካ ጨረቃ አይተናታል…አሁን ደግሞ እየመጣ ያለውን እንከታተል…”ምስጋና ለኮሮና ፥ አንበጣ ይምጣ!” የምንልበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ከጠላቶቻችን ውድቀት ይልቅ የፍትሕ አምላክ እግዚአብሔር የሚሰጠው መልስ በይበልጥ ያስደስታል።
ፋሲካን ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመሩት የእስራኤል ልጆች ናቸው ። በዓሉንም ማክበር የጀመሩት ከግብጽ ነው።
ኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ ፲፪
እግዚአብሔር በግብጻዊን ምክንያት በእስራኤላዊያን ላይ ሲደርሱ የነበሩ በርካታ ችግሮችን :- ጡብ መስራት ግርፋት መጨረሻ ላይም የእስራኤል ሴቶች የሚወልዷቸው ህጻናት ወንዶች ከሆኑ እንዲገደሉ ልምድ አዋላጆችን አሰልጥኖ ማሰማራት…ይህ ሁሉ ግፍ ሲደርስባቸው እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮሁ እግዚአብሔርም ጩኸታቸውን ሰምቶ ሙሴንና አሮንን “ያመልከኝ ዘንድ ህዝቤን ልቀቅ” የሚል መልዕክት አስይዞ ወደ ንጉሥ ፈርኦን ላካቸው። ፈርኦን ግን ልቡ ደንዳና ስለነበረ እግዚአብሔር ማነው? ህዝቡንም አልለቅቅም አለ ይልቁንስ በእስራኤል ላይ የባሰ ጫና መፍጠር ጀመረ :-ትናንት ጡብ እንዲሰሩ ገለባ ይሰጣቸው ነበር አሁን ግን ገለባውን ራሳቸው ከየትም እንዲያመጡ የጡቡ ቁጥር ግን ከትናንቱ እንዳያንስ ተወሰነባቸው ። ከዚህም የተነሳ እስራኤል አሁንም ይጮሃሉ ።
በዚህም ምክኒያት እግዚአብሔር በግብጽ ላይ መቅሰፍት ማውረድ ጀመረ።
መቅሰፍቶችም:-
ይህ ሁሉ ሲሆን ፈርኦን እስራኤልን አልለቅቅም አለ። ስለዚህ አሁን የቀረውና የመጨረሻው የፋሲካን በዓል ማክበር ነው።
ላይ እንደተጠቀሰው የእስራኤል ልጆች ፋሲካን የጀመሩት በግብጽ ሳሉ ነው።
በእነሱ የዘመን አቆጣጠር በመጀመሪያ ወር ወሩም በገባ በ10ኛ ቀን ጸሐይ ስትጠልቅ በግ ወይም ፍየል እንዲያርዱ የሚታረደው በግ ወይም ፍየል ምንም አይነት ነውር የሌለበት ሆኖ ከታረደ በኋላ ደሙ ከስጋው የሚበሉትን ሰዎች ቤት ጉበኑንና መቃኑን እንዲቀቡት ከዚያም የበጉ ወይም የፍየሉ ስጋ ተጠብሶ በዚያች ሌሊት ከመራራ ቅጠልና ካልቦካ ቂጣ ጋር እንዲበሉት ሲበሉም በአጭር ታጥቀው ጫማቸውን አድርገው በትራቸውን ይዘው በጥድፊያ እንዲበሉ ምክኒያቱም አሁን በግብጽ ላይ የሚመጣው መቅሰፍት እጅግ ከባድ (የበጉ ወይም የፍየሉ ደም በቤታቸው ጉበንና መቃን ላይ የቀቡ እስራእል ብቻ ስለሆኑ ቢያች ሌሊት እግዚአብሔር በከተማ ውስጥ እያለፈ ደሙን በጉበኑና በመቃኑ ላይ ያልተቀባ ቤት ሲያገኝ በእያንዳንዱ ቤት ከሰው እስከ እንስሳ በኩር የተባለውን በሙሉ ስለሚገድል) ግብጾች በራሳቸው ጊዜ ወጡልን ስለሚሏቸው ነው ።
ከዚህ በኋላ ለእስራኤል ፋሲካን ማክበር የዘላለም ስርዓት እንዲሆን ተደነገገ። በመጀመሪያ እርሾ የተባለ ከቤታቸው ያወጣሉ ለሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ይበላሉ።
ሰሞኑን በመላው ዓለም እርሾ ከገበያ መጥፋቱን ልብ ብለናል?! ለምን እርሾ?
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: መቅሰፍት, መንጋ, ምስራቅ አፍሪቃ, ሰብል, አብይ አህመድ, አንበጣ, ኢትዮጵያ, እህል, እስራኤላውያን, ኦሮሚያ, የታገቱት ተማሪዎች, የእግዚአብሔር መልስ, የግብጽ መቅሰፍቶች, ፈርዖን, ፋሲካ, ፍርድ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2020
በእኛ ላይም የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ላከ፤ የቅድስት ቢተ ክርስቲያንህንም ደጆች በምሕረትና በሃይማኖት እንዲከፈቱ አድርግልን። እስከ መጨረሻዪቱ ሕቅታም ድረስ ልዩ ሦስትነትህን ማመንን ፈጽምልን።
የቤተክርስቲያን ሸምጋይ እና አስታራቂ ሆኖ የመጣው ልወደድ–ባይ የአውሬው መንግስት ኮሮናን ተገን አድርጎ ሕዝበ ክርስቲያኑን ከቤተ ክርስቲያን ለማራቅ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ እንደሆነ እያየነው ነው። የክርስቶስ ተቃዋሚው የቤተ ክርስቲያንን ቦታ ለመውረስ ተወዳጅነት እያጡ የመጡትን ቴሌቪዥን እና ኢንተርኔት ጣቢያዎች (ኢቢሲ፣ ፋና)የሰሙነ ሕማማት ሥርዓተ ጸሎት በቀጥታ በማስተላለፍ ላይ ይገኛል። የቤተ ክርስቲያንን እና ሜዲያዎቿን ኃላፊነት በመንጠቅ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፎች ይመታል ማለት ነው።
ሲጀመር ዲያብሎስ አስታራቂ ሆኖ እንዲገባብን መደረግ አልነበረበትም፤ ካሜራዎቹንም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲያስገባ መፈቀድ አልነበረበትም። መንግስትና ሜዲያዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየሠሩት ያሉት ወንጀል ለይቅርታ፣ ለዕርቅና ለንስሐ የሚያበቃ አይደለምና።
በደመራ ዕለት መስቀል አደባባይ አጥር ላይ የተላተመችውን የኢቢሲ ድሮን ካሜራ እናስታውሳለን? በሬውንስ? እነዚህ ነገሮች ያለምክኒያት አልተከሰቱም! ዛሬ ግራኝ አህመድ በክቡር መስቀሉ የተሰየመውን አደባባይ እና የጃን ሜዳን ጥምቀተ ባሕር ለመውረስና ያለመውንም አንጋፋ መስጊድ በቅርቡ ለመሥራት በመንቀሳቀስ ላይ ነው። በኮሮና ድራማ ተጠምደን ጸጥ ብለናል፤ አይደል! አዎ! የበሬውን አንጀት ለሞኙ ኢትዮጵያዊ ሰጥቶ አፉን ይዘጋና ሰንጋውን ለራሱ በማግበስበስ ላይ ነው። ትንሽ ከፊት ሲሆን ሀገር ያሳንሳል!
“….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው…የሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸው… ከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ… ብለህ ተርትባቸው” ብሎን የለ ተሳላቂው አብዮት። በመስቀል አደባባይ ደመራ ዕለት በሬው የተላከውም በቤተ ክርስቲያን እና ክቡር መስቀሉ ላይ ለመሳለቅ ታስቦ ነበር። አንርሳው!
ወገኖቼ መታለሉ ይብቃ! ይብቃ! ይብቃ! ንቁ! እንንቃ! ነፍሱ እንዳይታወክበት የሚሻ የተዋሕዶ ልጅ ይህን የቀጥታ ስርጭት በዚህ ሰሙነ ሕማማት ከመከታተል መቆጠብ ይኖርበታል።
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ማክሰኞ, ሰሙነ ሕማማት, ትምህርት, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጥያቄ, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith, Holy Week, Jesus Christ, Passion Week | Leave a Comment »