Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2020
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    27282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 15th, 2020

ረቡዕ ፤ ምክረ አይሁድ ፥ የዕንባ ቀን ፥ የመልካም መዓዛ ቀን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 15, 2020

በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

👉 ኪርያላይሶን

ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «» በመሳሳባቸው በአማርኛ «»ን ፈጥረው ነው፡፡

👉 ናይናን

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡

👉 እብኖዲ

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው

👉 ታኦስ

የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡

👉 ማስያስ

የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው

👉 ትስቡጣ

«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው

👉 አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከአቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡

👉 አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ

የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው

👉 አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከየሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

_______________________

Posted in Ethiopia | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: