Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • September 2023
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    252627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for September 27th, 2023

በበጎው ዘመን ፤’ጌታችን የተገኘበት’ የ፪ሺ፱ ዓ.ም መስቀል ደመራ በመስቀል ዓደባባይ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 27, 2023

እ.አ.አ ኖቬምበር 2016 ዓ.ም፤ ጎረቤቴ የሚገኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ የቆመው የኢየሱስ ክርስቶስ ኃውልት

ኖቬምበር 7, 2016 (መድኃኔ ዓለም) ጎረቤቴ ወደሚገኝው ቤተክርስቲያን ጎራ አልኩ። እዚያም፤ ውስጥ የተሰቀለውን ድንግል እመቤታችን እና የጌታችን ምስል ልብ ብዬ ሳይ፤ ሁለቱም ኢትዮጵያውያንን እንዲመስሉ ተደርገው ነው የተሳሉት፤ የእመቤታችን ልብስም ከእጇ ሥር አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት አሉት። ወቸው ጉድ አልኩና ዘወር ስል፤ የጌታችንን የእየሱስ ክርስቶስን ኃውልት ስመለከት፤ በመገርም ኩምሽሽ አልኩ፤ ወዲያው የታየኝ መስቀል አደባባይ በደመራ ዕለት የበራው ችቦ ላይ የታየውን የክርስቶስ ምስል በሚያስገርም መልክ ስለሚመስል ነው፤ ተንበርክኬ እምባ በእምባ ሆንኩ፤ ያው አሁን ስጽፍም የፈጣሪያችን ተዓምር እያስገረመኝ ያስለቅሰኛል ያለው።

የሁዳዴ ጾም ሊገባ አካባቢ አንድ ዘመዴ ጎረቤቷ እማማ ሐረገወይን በደመራ ዕለት ቤታቸው ችቦ ሲለኩሱ አንዷ ልጃቸው ያነሳችውን ፎቶ ላኩልኝ፤ ይህም እጅግ በጣም የሚያስገርም ነው፤ ስለ እኔ የእየሱስ ክርስቶስ ቪዲዮ የሚያውቁት ምንም ነገር የለም፤ አላሳየኋቸውም፣ እንዲልኩልኝ አልጠየኳቸውም። ፎቶው ላይ የእሳቱ ነበልባል አንዴ ፈረስ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቆሞ የሚሄድ ዝንጆሮ በደንብ ይታያል፤ ነገር ግን መልዕክቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ያው እስካሁን በደንብ አልተረዳሁትም፤ ሆኖም ትልቅ መልዕክት እንደሚኖረው አያጠራጥርም። ከቆሼ አደጋ ጋር ከ ለንደኑ የእሳት ቃጠሎ (ጁን 14 – ፲፬ በእኛ አቡነ አረጋዊ ነው) ጋር የሚያያዝ ነገር ይኖረው ይሆን?

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ደመራ በበጎው ዘመን፤ ምእመናን በመስቀሉ ስንዳሰስ ከልዩ ልዩ ደዌ እንፈወሳለን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 27, 2023

✞✞✞

ክብረ መስቀል በኢትዮጵያ

መስቀል ስንል ሦስት መሠረታዊ ቁም ነገሮችን መጥቀስ ይቻላል፤ የመጀመሪያው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከሞተ ነፍስ ለማዳን ሲል የተቀበለው መከራና የከፈለው መሥዋዕትነት መስቀል ይባላል፡፡ ሁለተኛው በክርስእንትና ውስጥ የሚያጋጥም ልዩ ልዩ ዓይነት መከራም መስቀል ነው፡፡ ጌታችን ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› /ማቴ.፲፮፥፳፬/ በማለት መናገሩም በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚደርሰውን ይህንኑ መከራ መታገሥ ተገቢ መኾኑን ሲያመለክተን ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ጌታችን የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ነው፡፡ በሦስቱም ቁም ነገሮች ነገረ መስቀል (የመስቀሉ ነገር) ከክርስትና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡ ስለ ክርስትና ሕይወት ሲነሣ ነገረ መስቀልም አብሮ ይታወሳል፡፡ ስለ ክርስትና ሲነገር ክርስቶስ የተቀበለው መከራ፣ የተሰቃየበትና ነፍሱን በፈቃዱ አሳልፎ የሰጠበት ዕፀ መስቀል፣ በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚከሠት ፈተና አብረው የሚነሡ ጉዳዮች ናቸው፡፡

ስለ መስቀል ሲነገር ክርስቶስ ሰውን ለማዳን ሲል በሥጋው የተቀበለው ስቃይ፤ ሰማዕታት በሃይማኖታቸው ምክንያት የሚደርስባቸው ስደት፣ መከራና ሞት፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዘመኑ በአረማውያንም በውስጥ ጠላቶችም የሚያጋጥማት የዘረፋና የቃጠሎ፣ እንደዚሁም የሰላም እጦትና የመልካም አስተዳደር እጥረት፤ በተጨማሪም በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚከሠቱ የኑሮ ውጣ ውረዶች መስቀልና ክርስትና የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ለመኾናቸው ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከዚሁ ኹሉ ጋርም መስቀል ሲባል ክርስቶስ መከራ የተቀበለበት፣ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው የለየበት፣ ድንቅ ተአምራትን ያደረገበት፣ ከኹሉም በላይ ለአዳምና ለልጆቹ ነጻነትን ያወጀበት ዕፀ መስቀልም አንዱ የክርስትናችን አካል ነው፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በጉልላቷና በሌሎችም ንዋያተ ቅድሳቷ መስቀልን እንደ ምልክት ትጠቀመዋለች፡፡ መሠረቷ፣ የልጆቿ መድኀኒት ክርስቶስ በመስቀል ላይ የከፈለው ዋጋ ነውና ሰንደቅ ዓላማዋ መስቀል ነው፡፡ አባቶች ካህናት ጸሎት ሲያደርጉ ‹‹ከመስቀሉ ዓላማ፣ ከወንጌሉ ከተማ አያውጣን›› እያሉ የሚመርቁትም ስለዚህ ነው፡፡ በእጃቸው ይዘውት የሚንቀሳቀሱት፣ እኛንም የሚባርኩትም በመስቀል ነው፡፡ መስቀል የጠላት ሰይጣን ተንኮል የከሸፈበት፣ የክርስቶስ ቤዛነት የተረጋገጠበት የድኅነት ኃይል ነውና፡፡ በየገዳማቱና በየአብነት ት/ቤቱ፤ እንደዚሁም በክርስቲያኖች መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በሚከናወኑ ተግባራት መስቀል ሰፊ ድርሻ አለው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ፣ በጠበል ቦታ፣ በጸሎት ጊዜያት፣ ወዘተ ቡራኬ የሚፈጸመው በመስቀል በማማተብ ነው፡፡ የመስቀሉን ምልክት ባዩ ጊዜ አጋንንት ይንቀጠቀጣሉ፤ ካደሩበት ሰው ላይም በፍጥነት ይወጣሉ፡፡ ምእመናን በመስቀሉ ስንዳሰስ ከልዩ ልዩ ደዌ እንፈወሳለን፡፡

ወደ አገራችን ክርስቲያዊ ባህል ስንመለስ በኢትዮጵያ የመድኀኒታችን የክርስቶስ መስቀል በብዙ ተግባራት ላይ በምልክትነት ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ ለምሳሌ በቡልኮ፣ ጋቢ፣ ነጠላ፣ ቀሚስ ወዘተ የመሳሰሉ የሸማ ልብሶች፤ እንደዚሁም በጆሮ፣ በአንገት፣ በእጅና ሌሎችም ጌጣጌጦች ላይ የመስቀል ምልክት አለ፡፡ ክርስቲያን ልጃገረዶች (በተለይ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል) በግንባራቸው፣ በጉንጫቸው፣ በአንገታቸው፣ በደረታቸውና በእጃቸው ላይ በመስቀል ቅርፅ እየተነቀሱ ያጌጡበታል፡፡ ክርስቲያኖች ከዚህ ዓለም በሞት ስንለይም በመቃብር ሣጥናችን ወይም በሐውልቶቻችን ላይ የመስቀል ምልክት ይቀመጣል፡፡ በቤት ውስጥም ስንተኛና ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፊታችንንና መላ ሰውነታችንን በትእምርተ መስቀል እናማትባለን፤ አባቶችና እናቶችም ውሃ ሲቀዱ፣ ሊጥ ሲያቦኩ፣ እንጀራ ሲጋግሩ፣ ምግብ ሲቈርሱ፣ ወዘተ በመስቀል አማትበው ነው፡፡ በአጠቃላይ መስቀል ብዙ ነገር ነው፤ መስቀል በክርስትና ሕይወት ውስጥ በሚደረጉ ተግባራት ኹሉ ያለው ድርሻ ጕልህ ነው፡፡ /ለተጨማሪ መረጃ ግሸን ደብረ ከርቤ የቃል ኪዳን አምባ፣ መስከረም ፲፱፻፺፮ ዓ.ም፤ ገጽ ፺፮-፻፪ ይመልከቱ/፡፡

በክርስቶስ ደም የተቀደሰው ይህ ክቡር መስቀል ለበርካታ ዓመታት በአይሁድ ምቀኝነት በጎልጎታ ተቀብሮ ከኖረ በኋላ በንግሥት ዕሌኒና በልጇ ቈስጠንጢኖስ ጥረት ከተቀበረበት ወጥቶ ከፀሐይ ብርሃን በላይ አብርቷል፤ ሙት በማስነሣት፣ ሕሙማንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን አሳይቷል፡፡ በመላው ዓለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ደመራ ተደምሮ በዓሉ የሚከበረውም ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ለማግኘት ከእግዚአብሔር መልአክ በተሰጣት አቅጣጫ መሠረት ያነደደችውን ዕጣንና የመስቀሉን መገኛ የጠቆማትን ጢስ ለማስታዎስ ነው፡፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይኹን! በንጉሥ ዳዊት በልጃቸው በዘርዐ ያዕቆብ አማካይነት ወደ አገራችን የመጣው የጌታችን መስቀል ቀኝ ክፍል በአገራችን ኢትዮጵያ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በግሸን ደብረ ከርቤ ይገኛል፡፡ ከቅዱስ መስቀሉና ከገዳሙ በረከት ለመሳተፍ ብዙ ምእመናን በየዓመቱ ቦታው ድረስ በመሔድ በዓለ መስቀልን ያከብራሉ፡፡

በዓለ መስቀል በቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይኾን በየመንደሩና በየቤቱም ምእመናን ደመራ በመደመር፣ ጸበል ጸሪቅ በማዘጋጀት በድምቀት ያከብሩታል፡፡ በተለይ በደቡቡ የአገራችን ክፍል በዓለ መስቀል በደማቅ ሥርዓት ይከበራል፡፡ ይህም የቀደሙ አባቶቻችን ስለ በዓለ መስቀል ይሰጡት የነበረው ትምህርት ቁም ነገር ላይ መዋሉን የሚያስረዳ መንፈሳዊ ትውፊት ነው፡፡ የአከባበሩ ባህል ከቦታ ቦታ ይለያይ እንጂ በዓለ መስቀል በየዓመቱ በመስከረም አጋማሽ በመላው ኢትዮጵያ በልዩ ድምቀትና በመንፈሳዊ ሥርዓት ይከበራል፡፡ በአገራችን መስቀልና ክርስትና እንዲህ ሳይነጣጠሉ ተሳስረው ይኖራሉ፡፡ እኛም አባቶቻችን እንዳስተማሩን ይህንን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን መስቀል በዘወትር ጸሎታችን ‹‹… መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንዕነ መስቀል ቤዛነ መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ አይሁድ ክህዱ ንሕነሰ አመነ ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ፤ … መስቀል ኀይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው፡፡ አይሁድ ይክዱታል፤ እኛ ግን እናምንበታለን፡፡ ያመነውም እኛ በመስቀሉ ኀይል እንድናለን፤ ድነናልም›› እያልን ለመስቀሉ ያለንን ክብር እንገልጻለን፤ በክርስቶስ መስቀል ኀይል መዳናችንንም ስንመሰክር እንኖራለን፡፡ ልዑል እግዚአብሔር በመስቀሉ ኃይል ኹላችንንም ከልዩ ልዩ ዓይነት መከራ ይጠብቀን፡፡

ምንጭ

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Celebration of The True Cross | “ጋላው በሬውን ጋኔን ሞልቶ ወደ መስቀል አደባባይ ላከው፤ የዲቃላው ምንሊክ አማራም ከጋላው ጋር አብሮ በአክሱም ጽዮን ላይ ዘመተ” የሚለውን ቪዲዮ ዲቃላዎቹ ተደናግጠው ከዩቲውብ አስነሱት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 27, 2023

UPDATE: ይህን ቪዲዮ ከዩቲውብ አሳግደውት ነበር

💭 ዲቃላዎቹ የዋቄዮ-አላህ-ባፎሜት-ሉሲፈር ባሪያዎች (ጋላ-ኦሮሞዎች + ኦሮማራዎች) ሕዝቤን ማሳደድ፣ መድፈር፣ ማስራብና መግደል አልበቃቸውም፤ በማሕበረሰባዊ ሜዲያም እውነትን እንደ ጦር ፈርተዋታልና እኵይ ተግባራቸውንም እንደ ትልቅ ነገር / እንደ ድል ቆጥረውታልና ይህን ያህል እንቅልፍ በማጣት ላይ ናቸው።

እንግዲህ ያው ከእነ ማስረጃው፤ እነዚህ ከሃዲዎች ተወዳጅነቱን እያጣ በመጣው በዩቲውብ ተቋም ውስጥ ተሰግስገው ሰለገቡ ለጀነሳይድ ጥሪ የሚያደርጉትን ሺህ ሜዲያዎች እንዴት ዝም እንደሚሏቸው እያየን ነው። እኛም እነርሱን እንዲህ ዓለማዊና ተልካሻ በሆነ መልክ አናሳድዳቸውም፣ ቻኔሎቻቸውን አናሳፍንባቸውም፣ አናዘጋባቸውም፤ ይታዩን። እነርሱ ግን የአባታቸውን ዲያብሎስን ፈለግ ተከትለው ፥ በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ የሠሩትንና እየሠሩት ያሉትን ዲያብሎሳዊ ተግባር ሁሉ በደንብ ያውቁታልና ፥ እንደተለመደው እንደ ቃኤል ተደናግጠውና ተቅበዝብዘው ቪዲዮውን ከቻኔሉ በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ እንዲነሳ አድርገውታል። ያውም በድጋሚ በመሰቀል ደመራ ዕለት፤ የሚገርም ነው! ከዚህ በፊት አንዱን ቻኔሌን ያዘጉትም ልክ በመስቀል ዕለት ሲሆን ብዙ ተከታይ የነበረውን ሌላውን ደግሞ በጌታችን የስቅለት ዕለት ነበር። እግዚአብሔር ይባርካቸውና ለእነርሱ በጣም አዝናለሁ! ለማንኛውም ለዚህ ያበቃንና ይህንም ማስረጃ ያሳያን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመተሰገነ ይሁን!

WHAT IS MESKEL (Maskal) ?

Meskel is an annual festival commemorating the finding of the true cross of Jesus Christ, observed primarily on September 27 or 28 of Leap Year as a religious and cultural celebration among Millions of people in Ethiopia.

Meskal also Means many things: It is a festival of Bone fire and flowers as the land of Ethiopia is decorated with a yellow flower at the Ethiopian New Year, but it is not only fire or flowers. It is a culture where people gather for a day of celebration and song, but it is not only a celebration or song. It is a day of solemn religious services and joyous secular celebrations. But it is all about the finding of the True Cross.

How Meskel is Celebrated

Though the story of Maskal Celebration reaches back into the pages of antiquity, its meaning is renewed each year. Maskal falls at the end of the long rainy season. It is marked by riotous flowering throughout the nation.

There are many well-known symbols of Maskal celebrations that are woven intimately into the lives of all Ethiopians. These symbols mark the day itself:

Demera Or Bone Fire

Demera, it is a massive pole set up on the eve of Maskal in every city, town, and village at the Eve of Mekel; Men and boys in the village gather and place long poles until an enormous pyramid is built. Later they Put Grasses and Maskal daisies or yellow flowers to make decorations. In the night elders come together and make a blessing. In a church, priests pray and chant around the pile with Cross and burn incense; Make a procession three times around the Demera. While twigs and branches are thrown into its base By the people; at dusk, they set fire to the poles or Demera; through the night they carry chibos( lighted torches), to the bonfire where they are hurled into the blaze; they will sing and chant and circling of the blaze, and, finally, the next day, on Maskal itself, the gathering of the charcoal of the burned wood which men and women take home to break into dust and used to anoint their foreheads with the Sign of the Cross.

On the twenty-seventh (28 on leap year) of September each year just at the end of the rainy season when flowers appear on the hill and plain in wonderful profusion, and the whole landscape goes yellow with “Maskal” daisies – the Ethiopian nation observes Maskal or the Festival of the Finding of the True Cross upon which was crucified our Lord and Savior Jesus Christ.

The Festival of the Cross is a great time for rejoicing. Like all other major church holidays, Maskal commands an enormous appeal in all parts of the country. It is observed with the appropriate church services, a national holiday, and, in Addis Ababa, an Imperial Luncheon.

The Story of the True Cross in Ethiopia

The festive of Meskel is a familiar symbol, known and shared by millions of Ethiopians and known, too, by many from other countries who have been moved by the profound Christianity and colorful symbolism of the feast. But there is another symbol of the day, less known in all the details of its history even to many Ethiopians. It is the fragment of the true Cross of Jesus Christ that lies high and remote in inaccessible mountains, far removed from the festivities, brooding over all other symbols of the day.

The fragment of the True Cross lies Lies in a Holly Sanctuary, High on a cross-shaped plateau, in a cross-shaped church at the monastery of Gishen Mariam.

Just at the end of the rainy season. The event commemorates the success of the pious queen Helena, mother of the emperor Constantine I of Rome, in finding the holly cross on which Christ was crucified. It is said in 326 Ad. through divine guidance, the true Cross was unearthed from the spot where the Jews had buried it at Golgotha.

Maskal has been observed in Ethiopia as a religious and secular festival ever since. However, the event received even greater Christian sanction and significance at the end of the fourteenth century — when by a miraculous chain of events a fragment of the original Cross was brought to Ethiopia, occasioning much rejoicing throughout this ancient Christian realm.

The following pages will attempt to describe – with as much coherence as closely interwoven Christian history, folklore, and legends will allow — the events leading to that historic episode, the personalities of the main characters involved, as well as the legends surrounding the monastery of Gishen, long-time Ethiopian home of the said fragment of the Holy Cross.

The LEGEND ABOUT THE TRUE CROS (MESKEL)

According to legend, Queen Helena (Eleni in Ethiopian scriptures), in her efforts to discover the Holy Cross, set up long poles and set them afire, and burned incense. Skyward rose the smoke and down it bent, touching the spot on the earth where the original Cross was found buried. After the unearthing of the Holy Cross, Queen Helena lit up torches heralding her success in the neighboring areas.

According to “The Ethiopian Synaxarium”( መጽሐፈ፡ ስንክሳር), the spot where the Cross Was unearthed was Golgotha, and the year was 326 after the birth of Christ and in the twentieth year of the reign of Queen Helena’s son, Emperor Constantine I, the first Christian King of Rome. The “Synaxarium,” the book of the saints of the Ethiopian Church and a vast storehouse of Christian traditions, legends, and folklore, has this to say about this important event:

“And the blessed woman Helena took a large sum of his money, and she said unto her Constantine, I wish to be blessed by God, and I will go the holy city of Jerusalem, and I will seek for and discover the wood of the life-giving Cross”. And Constantine rejoiced at these words, and he sent soldiers with her, and he gave her much money and apparel made of costly silks threaded with gold. When she arrived in the City of Jerusalem and had kneeled in prayer in certain of the holy places, she made inquiries about the Wood of the Honorable and life-giving Cross. And with much toil and tribulation, she found the Wood of the Cross, and she praised it with great praises, and she paid unto it very great reverence and honor. Then she commanded her men to build the altar of the sanctuary and (shrines at) Golgotha, and Bethlehem, and the cave wherein our Lord Jesus Christ was born, and the fortress of Lion, and the Gethsemane wherein was buried the body of our Lady the Holy Virgin Mary, and the Mount of Olives, and all the holy places; and she commanded (of the soldiers) to decorate them with pearl, and with gold, and with silver.”

At this point, “The Ethiopic Synaxarium” goes on, a certain bishop and holy man named Aba Macarius, from Jerusalem, counseled Queen Helena, saying:

“Do not thus, for after a few days (foreign) peoples will come and will rule over this country, and they will take possession of this place and will lay it waste, and will seize whatsoever is made of gold and silver and precious stones. But it is meet that you should build a good, strong building which can neither be overthrown nor torn up from the foundations. And the remainder of this money gives unto the poor and the needy.”’

The building was constructed according to bishop Macarius’ advice, Queen Helena’s son, Emperor Constantine, then sent messages to the Archbishops of Constantinople, Alexandria, and Antioch and commanded them to Jerusalem to consecrate the sanctuary and all the altars of the places which had been built by his mother.

“And they all assembled in the City of Jerusalem, and they tarried there until the seventeenth of the day of Maskaram (September 27) by which day they had consecrated the sanctuary and all the altars of the places (shrines) which had been built. On that day there was joy, the like of which had never before existed. a great light appeared, and many signs were wrought on that day, the sixteenth of Maskaram (the eve of + Maskal Festival).”

Ever since then, the fourth century after the birth of Christ, Ethiopians like all other Monophysite Christians, have been observing the Festival of the Cross in the firm and honest belief that “Maskal is our strength. Our might, the savior of our soul.”

♱ WHERE IS THEBTRUE CROSS (MESKEL) NOW ?

The Fragment of the True Cross is now found in Ethiopia at a forbidden mountain massifs of Ambasel in Wollo, north Ethiopia, inside of the historical monastery of Gishen Mariam. Kept in the innermost sanctuary of the church of Egziabherab. All this History has been recorded on a Manuscript called “Tefut” written by the order of Emperor Zar’ Yacob (1434-68). It describes the story of the True Cross and its way to Ethiopia in detail.

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »