President of Rwanda Paul Kagame | Immediate Action Must be taken to Help Tigrayans
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 4, 2021
የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ካጋሜ | ትግራዮችን ለማገዝ አፋጣኝ እርምጃ መወሰድ አለበት
የሩዋንዳው ፕሬዚደንት በትግራይ እየታየ ያለው ሁኔታና በመገደል ላይ ያሉት ንጹሐን ቁጥር በጣም ከፍ ማለቱን፤ “ከሩዋንዳ ልምድ በመነሳት ከሁለት ዓመት በኋላ የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ሲታወቅ በጣም አስደንጋጭና አስቆጭ ይሆናል” ብለዋል። ፕሬዚደንት ካጋሜ ስለ ሁኔታ አሳሳቢነት እና ሕዝቡን ለመርዳት አፋጣኝ እርምጃ መወሰድ እንደሚኖርበት ሲናገሩ አዲስ አበባ ካሉ ፖለቲከኞችና “ኢትዮጵያውያን ነን” ባይ ከንቱዎች በተሻለ መልክ ነው። በተለይ ስልክና ኢንተርኔት አለመኖሩ፣ ጋዜጠኞችና ገለልተኛው ወገኖች እንዲገቡ አለመፈቀዱ ትክክል እንዳልሆነ በመገረም አውስተዋል። አዎ! እንዲህ ያለ ክስተት የሚታይባት ብቸኛዋ የዓለማችን አገር ኢትዮጵያ ብቻ መሆኗን መላው ዓለም በጣም እየተገረመበት ነው። በ21ኛው ክፍለዘመን! ሰሜን ኮርያ እንኳን እንዲህ ዓይነት ጥብቅ ቁጥጥር እና ጭካኔ አይታይም። እነ ግራኝ እያሳዩት ያሉት ዓይነት ጭካኔ ሂትለር፣ ሙስሊሊኒ እና ስታሊን እንኳን አላሳዩትም።
ወንጀለኛው የግራኝ አገዛዝ ዛሬ ለተባበሩት መንግስታት “40% የሚሆነውን የትግራይን ግዛት እኛ አንቆጣጠረውም! አማራዎችና ኤርትራውያን ናቸው የሚቆጣጠሩት!” ማለቱ እኮ “እኛ በማንቆጣጠራቸው ቦታዎች ትግራዋይን ቢሞቱና ቢራቡ እኛ ከደሙ ንጹህ ነን፤ ሴማውያኑ የሰሜን ሰዎች ናቸው እርስበርስ እየተጨራረሱ ያሉት እኛ ደቡባውያን ኦሮሞ ኩሾች አንጠየቅበትም” ለማለት ነው። ልክ ወስላታው ዘመድኩን በቀለ “የኤርትራ ትግሬ የትግራይን ትግሬ ጧ! አደረገልኝ፤ ኢትዮጵያን የነካ ይፈረፈራል!” እያለ በትግራዋይን ስቃይ እና ሰቆቃ ላይ እንደተሳለቀው፤ የዳንኤል ክብረት አማካሪ አይደል!
በገሃነም እሳት ይቃጠሉ፤ እነዚህ ቆሻሾች የዲያብሎስ የግብር ልጆች!
_______________________________
Leave a Reply