Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2021
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for February 23rd, 2021

የስደተኞቹን የአክሱም ጽዮን እናት እና ልጇን ምስል ሳይ እግዚእትነ እና እግዚእነ ነበር የታዩኝ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 23, 2021

በስተግራ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ሩሲያውያኑ የሳሉት የወላዲተ አምላክ እና ልጇ ስዕል፥ በስተቀኝ ከሁለት ወራት በፊት የተነሳው የስደተኞቹ የአክሱም ጽዮን እናት እና ልጅ።

ኦርቶዶክስ ሩሲያውያን የሚታያቸው ይህ ነው፤ ጥቁር(ኢትዮጵያዊ)እግዚእትነ & እግዚእነ። ከ፲፮ኛው ምዕተ ዓመት ጀምሮ ሩሲያንና ሩሲያውያኑን ከብዙ ችግሮችና ረሃቦች ያተረፈቻቸው፣ በታላላቅ ጦርነቶች ላይ (በአህዛብ ቱርኮች ላይ፣ በፖላንዶች፣ በናፖሊዮኗ ፈረንሳይና ጃፓን ኢምፔሪያሊስቶች ላይ፣ በናዚ ጀርመን ላይ)ድል እንዲቀዳጁ የረዳቻቸው ይህችው ትክክለኛዎቹን ኢትዮጵያውያን የምትመስለውን የ”ካዛን ወላዲተ አምላክ” / Our Lady of Kazan እንደሆነች ኦርቶዶክስ ሩሲያውያኑ ይመስከራሉ።

በሁለተኛው ዓለም ጦርነት፤ ናዚ ጀርመን ሶቪየት ህብረትን በወረረችበት ወቅት፤ ኢ-አማንያን የነበሩት እነ ጆሴፍ ስታሊን ተደናግጠውና ተስፋ ቆርጠው ወደ ከዳነ ምሕረት ለመመለስ በኮሙኒስቱ ከሃዲ ቭላዲሚር ሌኒን ተዘግተው የነበሩ ሃያ ሺህ ዓብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ ተደረጉ፤ እ.አ.አ በ1942 ለመጀመሪያ ጊዜ በዘመነ ኮሙኒዝም የትንሣኤ በዓል እንዲከበር ተፈቀደ። በኪዳነ ምሕረትም እርዳታ ሶቪየት ሩሲያ በናዚ ጀርመን ላይ ድል ተቀዳጀች። በተራቸው በዚህ የተደናገጡት ናዚዎች ታዋቂውን የወላዲተ አምላክን ስዕል(ቅጂውን) ከሩሲያ ወደ ጀርመን ወስደውት ገና ከ ፲፪/12 ዓመታት በፊት በ2009 ዓ.ም ነበር ለሩሲያ የተመለሰላት

ይህን የስደተኞቹን የአክሱም ጽዮን እናት ልጅ ምስል ካየሁበት ዕለት አንስቶ ላለፉት ሁለት ወራት ያለማቋረጥ እራሴን “የት ነው ያየኋቸው?” በማለት እየጠየቅኩ ነበር። ፎቶውንስ ማን ነው አንስቶት ለዓለም አቀፉ የዜና አውታሮች ያሰራጨው? እንዴት? በጣም ይገርማል! ፊልሙን ፈልጌ ማግኘት አቃተኝ እንጅ ልክ ይህንን የአክሱም ጽዮን ሕፃን የሚመስል ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚታይበት ፊልም ይታወሰኛል። አዎ! ዛሬም ኪዳነ ምሕረት እናታችን እግዚእትነ እና ጌታችን እግዚእነ ከየትኛውም ቦታ ይልቅ በትግራይ ከማንኛውም ሕዝብ ይልቅ ከአክሱም ጽዮን ልጆች ጋር ናቸው። ፻/100%.

አክሱምን ከ ወራሪዎቹ አረመኔ የአህዛብ (ሰ)አራዊቶች ነፃ የምታወጣው ጽዮን ማርያም ብቻ ነች!!!

አዎ!

እናት አለኝ የምታብስ እንባ

አያታለሁ ስወጣ ስገባ

ክዳነ ምህረት

ኪዳነ ምህረት

ኪዳነ ምህረት

አንባ መጠጊያ ናት

____________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: