Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • February 2019
  M T W T F S S
   123
  45678910
  11121314151617
  18192021222324
  25262728  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

ጂሃድ በ ለገጣፎ | ቤተክርስቲያን ያፈረሰችው ሙስሊሟ ከንቲባ፡ “ታቦት የሚሉት እስቲ ኃይል ካለው ለምን አያድናቸውም?!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 24, 2019

ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ከሚፈርስ የኔ ቤት ለምን አልፈረሰም ብዬ አልቅሻለሁ

የለገጣፎ ጉዳዩ ከዓመት በፊት ነበር የጀመረው

መጀመሪያ ቤተክርስቲያናቸውን (መንፈሳዊ ሕይወታቸውን) ከዚያ መኖሪያ ቤቶቻቸውን (ሥጋዊ ሕይወታቸውን) ማወክ፣ መዋጋትና ማጥፋት

ይህ ለአንድ ሺህ አራት መቶ ዓመታት ያህል በመላው ዓለም የሚታይ የእስልምና ጂሃዳዊ አካሄድ ነው። በዘመነ ግራኝ አህመድ ተከስቷል፤ በዳግማዊ ግራኝ አህመድ ዘመንም በመከስተ ላይ ይገኛል።

ከሁለት ዓመት በፊት፡ ሰኔ ፴/ ፪ሺ፱ ዓ.በአንዲት እርኩስ ሙስሊም ከንቲባ የሚመራ ጂሃዳዊ ሠራዊት አላህ ወአክበር እያለገጣፎ የሚገኘውን የመጥምቀ መለኰት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ አፈራረሰው።

ሙስሊሟ ከንቲባ ጫልቱ ሰይና አህመድ ራሷ ቆማ ነበር ያስፈረሰችው። በቦታው የነበሩ ታዛቢዎች የከንቲባዋ ደስታ ወደር እንዳልነበረው ገልጸዋል።

በትክክለኞቹ የቁርአን ሙስሊሞች ዘንድ ቤተክርስቲያን ማፍረስና ክርስቲያኖችን መግደል እንደ ጂሃዳዊ ግዴታ ብቻ ሳይሆን፤ ትልቅ ሽልማት የሚያስገኝና “ጀነት” የሚያስገባ ተግባርም ነው።

ሰኔ ፳፱/፪ሺ፱ ዓም ፦ በማግስቱ ዓርብ ሰኔ ፴ ለሚከበረው የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ክብረ በዓል ካህናቱ የዋዜማውን ጸሎት አድርሰው በዓውደምህረቱም ላይ የሰርክ ጉባኤው በሚያምር መልኩ ተካሂዶ ካህናቱም ጥቂት አረፍ ብለው ለማኅሌቱ አገልግሎት ለመዘጋጀት ፣ ምእመናንም ለበዓሉ ዝግጅት ወደየማረፊያቸው ይሄዳሉ ።

ከምሽቱ ፪ ሰዓት ሲሆን ግን አስደንጋጭ ነገር በስፍራው ተከሰተ። በሙስሊሟ ከንቲባ የሚመራና ከሰንዳፋ ከተማ የመጡ ናቸው የተባሉ የወታደር ቁመና ያላቸውና በሲቢል እንዲንቀሳቀሱ የተደረጉ ማንታቸው የማይታወቅ ጎሮምሶች በወታደር ታጅበው ከስፍራው ይደርሳሉ። በቤተክርስቲያኑም ውስጥ ያገኙት የቤተክርስቲያኒቱን አስተዳዳሪና ቀሳውስቱን በመያዝ ወደ ዘብጥያ ያወርዷቸውና አፍራሽ ግብረ ኃይል የተባሉት መጤዎችና ፀጉረ ልውጦች አሏህ ወአክበር እያሉ እስከ ምሽቱ ፬ ሰዓት ድረስ ቤተክርስቲያኒቱን ማፍራሳቸው ነው የተነገረው ። የከንቲባዋ ደስታ ግን ይህ ነው ተብሎ አይገለፅምም ተብሏል ።

ከዚያ በመቀጠል ሰኔ ፴ የመጥምቁን በዓል ለማክበር የሚመጣው ህዝብ በአካባቢው ድርሽ እንዳይል ከጎዳናው ጀምሮ የፌደራልና የኦሮሚያ አርማን ያጠለቀ የወታደር ዓይነትና የመከላከያ ሠራዊቱም አንድ ላይ በመሆን በባጃጅ ፣ በእግር ሀገር ሰላም ብለው ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄዱትን በሙሉ እየቀጠቀጡ መልሰዋል ተብሏል።

ሐምሌ ፬ /፪ሺ፱ ዓም ከቀኑ ፬ ሰዓት ሲሆን ደግሞ የለገጣፎዋ ከተማ ከንቲባ የሆነችውና ይኽችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችን ክፉኛ ትጠላለች የምትባለው አክራሪ ሙስሊም ከንቲባ ወይዘሮ ጫሉት አህመድ በእርሷ የሚመራ የከተማውን አስተዳደር ሠራተኞች አስከትላ በመምጣት ለምልክት እንዳይገኝ አድርጋ በድጋሚ በግሬደር አስፈርሳዋለች።

የሚገርመው ነገር ቤተክርስቲያኑ ለማስተር ፕላኑ ውበት በማይሰጥ ቦታ ነው ያለው በሚል ተልካሻ ምክንያት የለገጣፎ መዘጋጃ ቤት ሠራተኞችን እና የዚያው ከተማ አፍራሽ ግብረ ኃይሎችን ይዛ በመምጣት ለማፍረስ ባደረገችው ሙከራ በሁኔታው ግራ የተጋቡት የመዘጋጃ ቤቱ ሠራተኞችና አፍራሽግብረ ኃይሎቹ ፤ የከንቲባዋን ድርጊት በመቃወም እኛ በፍፁም እንዲህ አይነት ተልካሻ ድርጊት ላይ አንሳተፍም በማለት አልታዘዝ ቢሏትም ከንቲባዋ በኃይልና በቁጣ በማስፈራራትና በዛቻ ለማስገደድ ብትሞክርም ሰሚ ታጣለች ። በሁኔታው የተናደደችው ወጠጤዋ ከንቲባዋ ስልኳን በማውጣት አለቃዋ ለሆነና ትእዛዝ እየሰጣት ነው ለሚባል አካል በተደጋጋሚ ትደውላለች ። በመጨረሻም የአካባቢው ወጣቶች በማፍረሱ ሥራ ላይ አልተባበር ማለታቸው ሲረጋገጥ ወደ ሰንዳፋ በመሄድ ማንነታቸው ያልታወቀና ሲቪል ልብስ እንዲለብሱ የተደረጉ ወታደሮችን በማምጣት ቤተክርስቲያኒቱን አፍርሳለች ።

አስቀድሞ የጦር ሠራዊቱ አነጣጣሪ ተኳሽ ይዞ በስፍራው እንዲፈስ በመደረጉ ምክንያት ህዝቡ ወደ ቤተክርስቲያኑ ለማለፍ አልቻለም ነበር። በሁኔታው የተናደዱ የሚመስሉ ወታደሮች ከንቲባዋን በመለመን ካግባቧት በኋላ ካህናት መጥተው ታቦቱን ይዘው ወደ መዘጋጃ ቤት እንዲወስዱት አስደርገው ነበር። ሌሎች ንዋያተ ቅዱሳቶችም በአፍራሽ ግብረ ኃይሉ እንዲወድሙ ከተደረገ በኋላ ንዋያተ ቅዱሳቱም ልክ እንደ ታቦተ ህጉ ወደ መዘጋጃ ቤቱ ተወስደዋል።

ቤተክርስቲያኑ ሙሉ በሙሉ እንዲወድም የተደረገ ሲሆን ፤ አገልጋይ ካህናቱ ከእነ የህግ ባለሙያቸው በሙሉ ወደ ዘብጥያ ወርደዋል። ታቦተ ህጉ በመዘጋጃ ቤቱ በሚገኝ ኮንቴነር ውስጥ እንዲቀመጥ የተደረገ ሲሆን ንዋያተ ቅዱሳቱም በመዘጋጃ ቤቱ መጸዳጃ ቤት አጠገብ ዝናብና በረዶ ፣ ፀሐይና ነፋስ እየተፈራረቁባቸው እንዲቀመጡ ተደርገው እጅግ በሚያስለቅስ ሁኔታ እንዲቀመጥ ተደርገዋል ተብሏል ። ከሁሉም በላይ ሕዝበ ክርስቲያኑን እያስለቀሰና በቁጭት እያንገበገበ የሚገኘው የከንቲባዋ ታቦት የሚሉት እስቲ ኃይል ካለው ለምን አያድናቸውም?!” የሚለው መርዛማ ንግግሯ ነበር

[መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፭፥ ፩፡፲፪]

ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ወሰዱ፤ ከአቤንኤዘርም ወደ አዛጦን ይዘውት መጡ።

ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ወስደው ወደ ዳጎን ቤት አገቡት፥ በዳጎንም አጠገብ አኖሩት።

በነጋውም የአዛጦን ሰዎች ማለዱ፥ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር፤ ዳጎንንም አንሥተው ወደ ስፍራው መለሱት።

በነጋውም ማለዱ፥ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር፤ የዳጎንም ራስ እጆቹም ተቈርጠው በመድረኩ ላይ ወድቀው ነበር፤ የዳጎንም ደረት ብቻውን ቀርቶ ነበር።

ስለዚህም የዳጎን ካህናት ወደ ዳጎንም ቤት የሚገቡት ሁሉ በአዛጦን ያለውን የዳጎንን መድረክ እስከ ዛሬ ድረስ አይረግጡም።

የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፥ አጠፋቸውም፥ አዛጦንንና ድንበራቸውንም በእባጭ መታቸው።

የአዛጦንም ሰዎች እንዲህ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ። እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክራለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አይቀመጥ አሉ።

ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ወደ እነርሱ ሰበሰቡና። በእስራኤል አምላክ ታቦት ምን እናድርግ? አሉ፤ እነርሱም። የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ ጌት ይዙር ብለው መለሱ። የእስራኤልንም አምላክ ታቦት ወደዚያ ተሸከሙት።

ከተሸከሙትም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በታላቅ ድንጋጤ በከተማይቱ ላይ ሆነች፤ ከታናሹም እስከ ታላቁ ድረስ የከተማይቱን ሰዎች መታ፥ እባጭም መጣባቸው።

የእግዚአብሔርንም ታቦት ወደ አስቀሎና ሰደዱት። የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አስቀሎና በመጣ ጊዜ አስቀሎናውያን። እኛንና ሕዝባችንን ሊገድሉ የእስራኤልን አምላክ ታቦት አመጡብን ብለው ጮኹ።

በከተማይቱ ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበርና፥ የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ እጅግ ከብዳ ነበረችና ልከው የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው። የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱ፥ እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል ወደ ስፍራው ይመለስ አሉ።

ያልሞቱትም ሰዎች በእባጭ ተመቱ፤ የከተማይቱም ዋይታ እስከ ሰማይ ወጣ

_________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: