ይህ በጣም አስደናቂ ትዕይንት ነው፤ ከዚህ በፊት በዚህ መልክ አይቼው አላውቅም። እውነታዊ ድራማ!
እንግዲህ መረጃው የተገኘው ሙስሊሞች ቅዱሳት ከሚሏቸው መጻሕፍት፡ ከቁርአን እና ከሃዲት ነው። ለመስማት እንኳን የሚቀፉትን ቃላት የተናገሩትም አላህ እና መሀመድ ናቸው።
እዚህ ላይ የሚገርመው እነዚህ አጸያፊ የሆኑ ቃላት በቁርአናቸው እንዳሉ የማያውቁት ሙስሊሞች ይህን ሲሰሙ በድንጋጤና ግራ በመጋባት የስካር ዓይነት ሁኔታ ላይ ወድቀው ይታያሉ፤ በጽሑፉ ላይ ዕውቀቱ ያላቸው ሙስሊሞች ደግሞ በቁጣና በንዴት እንደ እብድ ወዲያና ወዲህ እያሉ ለማጭበርበር ይወራጫሉ፤ ሃቁ እንዲታወቅባቸውና ሌላው እንዲሰማባቸው አይሹምና። (ምስጢሩ እንዳይታወቅባቸው በአረብኛ ቋንቋ ካባ ሸፍነውት ነበር)
አዎ! እውነት መራራ ናት! በአንድ በኩል በጣም ያሳዝናሉ፤ በሌላ በኩል ግን እነርሱን ለማንቃት፡ በተለይ በአሁኑ ዘመን፡ እንዲያውም ይህ በጣም ቀላሉና ጎጂ ያልሆነው መንገድ ነው፤ ከራሳቸው በተገኘው መረጃ (እባብ ሲነድፈን መድኃኒቱን የምናገኘው ከራሱ ከእባቡ መርዝ ነውና፟)።
ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ፤ “አይዟችሁ! እያለ የሚያባብለን ወይም እንደገና የሚሰቀልልን ይመስለናልን? በጭራሽ! ጌታችን ለሁለተኛ ጊዜ ሲመጣ “ዳግም ምጽአት”፡ ቪዲዮው ላይ በለንደኑ መናፈሻ እንደሚታየው ዓይነት ዕድል አይኖርም፤ እንዲያውም በጣም ኃይለኛና አስፈሪ የሆነ ፍርድ ይሰጣል እንጂ፤ ክርስቶስ ለመንግሥቱ የማይፈልጋቸውን ሁሉ መንጥሮ ይጥላላ፤ ይህ ጊዜ ሰማያት የሚንዋወጡበትና የሚያልፉበት ቀድሞ የነበረው ፍጥረት ሁሉ በእሳት ነበልባል የሚቀልጥባት፤ ምድርና በእሷ ላይ ያለው ፍጥረት ሁሉ የሚቃጠልባት ጌዜ ይሆናል።